Muktarovich Ousmanova


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Политика


Ethiopia forever

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Политика
Статистика
Фильтр публикаций


የቡድን ሰባት ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች ይታያሉ ያሏቸው፤ “የማያቋርጡ እና ኃይለኛ ውጥረቶች” እንደሚያሳስቧቸው ገለጹ። በኢንዱስትሪ የበለጸጉት ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ይፈጸማሉ የሚባሉ “የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እና በደሎች ሪፖርቶች”፣ “ብርቱ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ” እና “የምግብ ዋስትና እጦት መስፋፋት” እንዳሰጋቸውም አስታውቀዋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በኢትዮጵያ ጉዳይ ስጋታቸውን ያንጸባረቁት፤ በጣልያኗ ካፕሪ ደሴት ያካሄዱትን ስብሰባ ሲያጠናቅቁ ዛሬ አርብ ምሽት ባወጡት መግለጫ ነው። ሚኒስትሮቹ በዚሁ መግለጫቸው፤ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል በተፈረመው ግጭት የማቆም ስምምነት አተገባበር ረገድ የተወሰዱ እርምጃዎችን በበጎ እንደሚቀበሉ ገልጸዋል።

በሰብዓዊ መብቶች እና በሲቪል ሰዎች ጥበቃ፣ ውጥረቶችን ለመፍታት በሚደረግ ፖለቲካዊ ውይይት፣ በዕርቅ፣ በብሔራዊ ውይይት፣ የሽግግር ፍትህ እና በግጭት ወቅት ወንጀል የፈጸሙ ተጠያቂ ለማድረግ ተጨማሪ እና ዘላቂ እርምጃዎች ተግባራዊ እንዲደረጉ አበረታተዋል። በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በመካሄድ ላይ በሚገኙ ግጭቶች የሚሳተፉ ወገኖች፤ በንግግር ሰላም ለማውረድ ተመሳሳይ ቁርጠኝነት እንዲኖራቸው ጥሪ አቅርበዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)


የአንድ አመት ልጁን ከእነ ህይወቷ ለመቅበር የሞከረው ወላጅ አባት በቁጥጥር ስር ዋለ።
#FastMereja
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቤንች ሸኮ ዞን የሰሜን ቤንች ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፒክተር አለማየሁ አማረ ለክልሉ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን እንደገለፁት በወረዳው ኮሶል ቀጭን መንደር ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ላይ በባልና ሚስት መካከል በተፈጠረው ፀብ ምክንያት የወንጀል ድርጊቱን ለመፈፀም ሙከራ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡

አዛዡ አክለውም በባልና ሚስት መካከል በተፈጠረ ጊዜያዊ ፀብ እናት የአንድ ዓመት ሴት ህፃን ልጅ ጥላ በመጥፋቷ ወላጅ አባት ቲቲዮስ ኪያግላስ የተባለው ተጠርጣሪ የአንድ ዓመት ህፃን ልጁ እያለቀሰች ስታስቸግረዉ በሁኔታው ተበሳጭቶ የአንድ አመት ልጁን በህይወት ለመቅበር ጉድጓድ ሲያዘጋጅ የተመለከቱ የአከባቢው ነዋሪዎች ለፖሊስ ጥቆማ ይሰጣሉ፡፡

ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተጠርጣሪውን ጉድጓድ እየቆፈረ እያለ በቁጥጥር ስር እንዲውል በማድረግ ህፃኗን ጉዳት ሳይደርስባት መታደግ መቻሉንና በተጠርጣሪው ላይ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

ፖሊስ የህፃኗን ወላጅ እናቷን እያፈላለገ ሲሆን ህፃኗ በአሁን ሰዓት ሰሜን ቤንች ወረዳ ፖሊስ እንክብካቤ እያደረገላት እንደሚገኝ የገለፀት ፖሊስ አዛዡ በቤተሰብ መካካል አለመግባባቶች በሚፈጠሩበት ወቅት ችግሩን በመነጋገር መፍታት ይገባል ሲሉ ፖሊስ አዛዡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ሲል ፋስት መረጃ ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን መረጃ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።


📲 ስልክዎትን ለመቀየር ወይም አዲስ ለመግዛት አስበዋል 🤔?

አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል📱ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ

https://t.me/sellphone2777

📞 0929008292

📩 inbox @bina27

📍አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ

📨 ክፍለ ሀገር ላላቸሁ ደንበኞችቻችንም በ DHL መላክ ጀምረናል


ትናንት ማታ በኬንያ መርሳቤት አከባቢ በደረሰ የጄሎኮፍተር አደጋ የኬንያ የመከላከያ አዛዥ ፍራንሲስ ኦጎላን ጨምሮ በርካታ የወታደራዊ አዛዦች መሞታቸው ተገለፀ


በብራዚል በሞተ ሰው ስም ብድር ለመውሰድ አስክሬኑን በዊልቸር ላይ አድርጋ ወደ ባንክ የመጣችዉ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች

የ42 ዓመቷ ብራዚላዊት ሴት ህይወቱ ያለፈ ባለቤቷን ወደ ባንክ አምጥታ በስሙ ከባንክ ብድር ለማዉጣት ስትሞክር በቅርቡ በቁጥጥር ስር ውላለች።

ማክሰኞ ሚያዚያ 9 ቀን ኤሪካ ዴ ሱዛ ቪየራ ኑነስ የተባለችዉ ግለሰብ ህይወቱ ካለፈዉ የ68 ዓመቱ ፓውሎ ሮቤርቶ ብራጋ ስም 3,200 ዶላር የባንክ ብድር ለማዉጣት ወደ ባንጉ፣ ሪዮ ዴጄኔሮ ወደሚገኘው የኢታው ዩኒ ባንኮ ቅርንጫፍ መጥታለች። የአዛውንቱን በዊልቸር ላይ የነበሩ ሲሆን አጎቷ እንደሆኑ እና የመጀመሪያ ተንከባካቢ መሆኗን ተናግራለች። የባንኩ ሰራተኞች ብዙም ሳይቆይ በብራጋ ላይ ከባድ ችግር እንዳለ አስተውለዋል፡፡ምክንያቱም ይህችዉ ሴት የሟችን ጭንቅላት በእጇ ስትደግፍ ጥርጣሬ ፈጥሮባቸዋል። እናም ምንም አይነት በህይወት እንዳለ የሚያሳይ ምልክት አልታየበትም፣ ነገር ግን ቪየራ ኑነስ በተፈጥሮው ዝምተኛ እንደሆነ ለባንኩ ሰራተኞቹ እየነገራቻቸዉ ነበር ተብሏል።

ምንም እንኳን ለምትጠይቀዉ ጥያቄ መልስ የመስጠት አቅም እንደሌለው ግልጽ ቢሆንም አስክሬኑን ልታናግረው ስትሞክር ትታያለች፡፡“አጎቴ እየሰማህ ነው? መፈረም አለብህ። ካልፈረምክ ምንም መንገድ የለም ” እያለች ስትናገር እንደነበር ምስክሮች ኤሪካ ዴ ሱዛ ቪዬራ ኑነስ በዊልቸር ላይ ለተቀመጠዉ አስከሬን ስትናገር ሰምተዋል፡ "ላንተ መፈረም አልችልም፤ማድረግ የምችለውን አደርጋለሁ፤ ተጨማሪ ራስ ምታት እንዳትሰጠኝ ስምህን መዝግብ ስትል ትደመጣለች፡፡

ከባንኩ ሰራተኞች አንዱ "ደህና ነው ብዬ አላምንም" ሲል ይደመጣል፤ቪዬራ ኑኔስ ግን "አጎቷ" ደህና እንደሆነ ትናገራለች ፣ ትንሽ ዝምታ ስለሚያበዛ ነዉ በማለት ለማስተባበል ሞክራለች፡፡

ዳጉ ጆርናል


ቀሲስ በላይ መኮንን በተጠረጠሩበት በሀሰተኛ ሰነድ የዶላር ዝውውር ወንጀል ለምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደ‼️
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀሲስ በላይ መኮንን በተጠረጠሩበት በሀሰተኛ ሰነድ የዶላር ዝውውር ወንጀል ለምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ ፈቀደ፡፡

የፌደራል ፖሊስ መርማሪ ቀሲስ በላይ መኮንን ከትናንት በስቲያ በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ጊቢ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ በአካል ቀርበው ሀሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን በመያዝ ለ3 ግለሰቦች እና ለአንድ የግል ድርጅት ሒሳብ 6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ሊያዘዋውሩ ሲሉ በአፍሪካ ህብረት ሴኪዩሪቲዎች ተይዘው ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ተላልፈው መሰጠታቸውን ጠቅሶ የጥርጣሬ መነሻውን ለችሎቱ አቅርቧል።

በዚህ መነሻ መሰረትም መርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ ሥራ ለማከናወን የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።

ተጠርጣሪ ቀሲስ በላይ መኮንን ድርጊቱ መፈጸሙን አምነው፤ ይሁን እንጂ ወንጀል አለመፈጸማቸውን አስረድተዋል፡፡

ስለሆነም የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

የግራ ቀኝ ክርክሩን የተመለከተው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ተጠርጣሪው ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ በማለፍ ለፖሊስ የ7 ቀናት የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ፈቅዷል።
#FBC


" "የአማራ ታጣቂዎች" ያቋቋሟቸውን አስተዳደሮች ለማፍረስ ከፌደራል መንግስት ጋር ተስማምተናል ሲል የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ

ይህን ዜና በሰማን በማግስቱ ዛሬ የአማራ ክልል መንግስት ተወረርኩኝ መግለጫ አውጥቷል። የሚገርመው የፌዴራል መንግስት ይህን ወረራ ይከላከልልኝ ማለቱ ነው። ለአለማቀፍ ማህበረሰብም አቤቱታ አሰምቷል። ለአማራ ህዝብና ፋኖም እንደቀድሞው ሁሉ "ሀገርን ከመፍረስ" አብረን በመታገል፣ ከ"ሀዲውን ህወሓት አብረን እንታገል ብሏል


በከፋ ዞን በገጠመ የትራፊክ አደጋ አምስት ሰው ወዲያው ሲሞት፣ በርካቶች ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ገጥማቸዋል


የትህነግ ወታደሮች በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ትጥቅ መፍታት፣ Disarm ወታደሩ ወደየቤቱና ሞያው መበታተን Dimobilize እና መልሶ ወደ መደበኛ ህይወት መመለስ ነበረበት።
ይህ አልሆነም። እንደምታዩት ራያን ወረዋል። ምስሉ፣ አላማጣ ሲገቡ ነው። ወደ ሌላ ዙር ጦርነት የትግራይ ህዝብ ገብቷል።
በርግጥ የሚያሳምም ነው።
ነገም በወልቃይት የሚነሳ ነው ይህ ነገር። ያሳዝናል 😢


አለምነ ያስደነገጠው የኦርቶዶስ ቄስ የግድያ ሙከራ

ታዋቂው  የኤሲሪያን  (አሶራውያን) ኦርቶዶክስ ቄስ ብጹዕ አቡነ ማር ማርያም ኢማኑኤል (ቢሾፕ ማር ማሪ) ሲድኒ ውስጥ በዘውትራዊውና የተመለደው ቀጥታ የሚሰራጭ  የስብከት መርሃ ግብራቸው ላይ ሳሉ ማንም ባልገመተው ሁኔታ አንድ ሰው በፍጥነት ተጠግቶ በጩቤ ፊትና አንገታቸው አካባቢ ሲወጋጋቸው የሚያሳይ ምስል ተለቋል። እጅግ ይዘገንናል። የሰው ልጅ ጭካኔ ብሷል። ዓለሙ እያበደ ነው።   መስቀል የያዘ የሃይማኖት አባት በጩቤ እንዴት ይወጋል?...  ምዕመን መስሎ ገብቶ በአደባባይ ይህንን መፈጸም ግን እብደት እንጂ ምን ይባላል?
ተወግተው ተርፈዋል።
ጨርሶ ይማራቸው።
የአለም ጭካኔ ከብዷል።


የሕወሃት ኃይሎች በራያ አላማጣ አንዳንድ ቦታዎችን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ፤ የፕሪቶሪያዉ ስምምነት ጠላቶች ያደረጉት እንጂ በሕወሃት አልያም ጊዜያዊ መስተዳድሩ የተፈጸመ አለመሆኑን አቶ ጌታቸዉ ረዳ ተናገሩ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ፣ በደቡብ ትግራይና በሌሎች በኃይል የተያዙ የትግራይ ግዛቶች ባኹኑ ወቅት የተፈጠረው ክስተት በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ወይም በሕወሃት ወይንም በትግራይ እና በአማራ ክልሎች መካከል የተፈጠረ ግጭት አይደለም ሲሉ ትናንት እኩለ ሌሊት ላይ በኤክስ ትስስር ገጻቸው ላይ መለጠፋቸውን ተመልክተናል።

ጌታቸው፣ ክስተቱ ኹለቱ ወገኖች የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እያደረጉት ያለውን አወንታዊ ግንኙነት ለማደናቀፍ የፈለጉ የስምምነቱ ጠላት የኾኑ ኃይሎች የፈጠሩት ነው በማለት ከሰዋል።

ኹለቱ ወገኖች ችግሮችን ለመፍታትና የሚስማሙባቸውን ጉዳዮች ለማጎልበት አዲስ አበባ ውስጥ ስብሰባ ላይ እንደኾኑም ጌታቸው ጠቁመዋል።

ሕወሃት ጥቃት ከፍቶ ተቆጣጥሯቸዋል የተባሉት አካባቢዎችን በተመለከተም አብን ማምሻውን ጠንከር ያለ መግለጫ አሰራጭቷል።

አብን የሕወሃት ኃይሎች በድጋሚ በአማራ ሕዝብ ላይ "አራተኛ ዙር" ጥቃት ከፍተዋል ሲል ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ከሷል። የፌዴራሉ መንግሥትና የአማራ ክልላዊ መንግሥት ሕወሃት በአማራ ሕዝብ ላይ የከፈተውን ሌላ ዙር ጥቃት ባስቸኳይ እንዲያስቆሙ የጠየቀው አብን፣ የአማራ ሕዝብ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀናጀት የሕወሃትን ጥቃት እንዲመክትም ጥሪ አድርጓል።

አብን ይህን መግለጫ ያወጣው፣ የሕወሃት ኃይሎች በራያ አላማጣ አካባቢ አንዳንድ ቦታዎችን እየተቆጣጠሩ ስለመኾኑ በተሰማ ማግስት ነው።


ሀገሪቱ የጥቂቶች ሳይሆን በጣት ለሚቆጠሩት እንደሆነች ማሳያውን እዩት 👇

"ብሔራዊ ባንክ ሐሙስ ሚያዝያ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው የፋይናንስ ስታቢሊቲ ሪፖርት (Financial Stability Report) የባንክ ብድሮች በጥቂት ተበዳሪዎች እጅ ተከማችተው እንደሚገኙ ይጠቅሳል።

በአገሪቱ ያሉት ሁሉም ባንኮች እስካለፈው ዓመት ሰኔ መጨረሻ ድረስ በሥራ ላይ ካዋሉት አጠቃላይ 1.9 ትሪሊዮን ብር ብድር ውስጥ 23.5 በመቶውን ያበደሩት ለአሥር ተበዳሪዎች እንደሆነ በሪፖርቱ ተካቷል።

ከፍተኞቹ አሥር ተበዳሪዎች ከአጠቃላይ የባንክ ብድር መጠን ውስጥ በ2014 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ከነበረው 18.7 በመቶ ነው በ2015 ዓ.ም. መገባደጃ ላይ ወደ 23.5 ያደገ ነው ተብሏል።"

ደሀው ኑሮ እየከፋበት፣ ሀብታሙ እንዲህ በሚሆንበት ሀገር ሰላም ይኖራል ማለት ዘበት ነው


እስራኤል በኢራን ላይ ልትወስድ ባሰበችው የአጸፋ እርምጃ አሜሪካ እንደማትተባበር ገለጸች

ኢራን ሶሪያ በሚገኘው የቆንስላ ፅህፈት ቤቷ ላይ ለተቃጣባት ጥቃት ቅዳሜ ሌሊት እስራኤል ላይ 300 ሚሳኤሎችና ድሮን ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ እስራኤል ለምትወስደው የአጸፋ እርምጃ አሜሪካ እንደማትተባበር ገልጻለች።

አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን እሁድ ዕለት ለጋዜጠኞች በሰጠው ማብራሪያ ፕሬዝዳንት ጆው ባይደን እስራኤል ልትወስደው ያሰበችው የአጸፋ እርምጃን በጥንቃቄ እንድታጤነው ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ማሳሰባቸው ነው የተገለጸው።

ፕሬዝዳንት ባይደን እስራኤል ከኢራን የተቃጣባትን ጥቃት በአሸናፊነት መወጣቷን የጠቀሱ ሲሆን በዋናነት በአሜሪካና አጋሮቿ እገዛ 99 በመቶ የሚሆኑት ጥቃቶች በሚሳኤል መከላከያ መክሸፋቸውን በማሳያነት አቅርበዋል።

የአሜሪካ የብሔራዊ ጸጥታ ቃል አቀባዩ ጆን ኪርቢ በበኩላቸው አገራቸው በቀጣናው ግጭቱ እንዳይስፋፋ ለእስራኤል አቋሟን ግልፅ ስለማድረጓን ገልጸዋል።

አሜሪካ ለኢራንም በተዘዋዋሪ የዲፕሎማሲያዊ መረጀ ልውውጥ ተመሳሳይ መልዕክት እንዳስተላለፈች ነው የተነገረው።

የእስራኤል የጦር ካቢኔ በኢራን ላይ ሊወሰድ ስለሚገባው የአጸፋ እርምጃ ዙሪያ ተወያይቶ ከስምምነት ላይ ሳይደርስ መበተኑን ቢቢሲ ዘግቧል።
ይህ ውሳኔ አሜሪካ በቀጥታ ከገባች ራሺያና ቻይና ሊገቡ ስለሚችሉ ነው ተብሏል። ያኔ ሶስተኛው የአለም ጦርነት በይፋ ይጀመራል።


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
0921388158
ጊዮን ሆምስ የጊዮን ቢዝነስ ግሩፕ አካል በመሃል ከተማ ሌላ ከተማ እየገነባ ይገኛል።
➷ወሎ ሰፈር መስቀል ፍላወር አጠገብ
👉50%የባንክ ብድር የተመቻቸለት
90% የተገነባ መንደር አፓርትመንቶች
በ10 % ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤት ባለቤት
ይሁኑ
ባለ 1,መኝታ 96.5ካሬ
ባለ 2 መኝታ 168.9ካሬ
ባለ 3 መኝታ 205ካሬ
➷50 አመት በቢዝነሱ ዘርፍ ልምድ ያካበተው
በውስጡ ስምንት እህት ኩባንያዎችን የያዘ
ጊዮን ቢዝነስ ግሩፕ
@Modernhouseinethiopia?si=O1OgP4AI7Re2Yv5w' rel='nofollow'>https://youtube.com/@Modernhouseinethiopia?si=O1OgP4AI7Re2Yv5w


#መረጃ

ኦነግ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ስለ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ተጨማሪ መረጃዎችን አውጥቷል::

በቴን ካረፈበት ሆቴል ሲወስዱት የነበሩት የፀጥታ ሀይሎች ክፉኛ እየደበደቡት እንደነበር - ይህንን የተመለከቱ እና የአይን ምስክር የሆኑ የሆቴሉ ጥበቃዎች ታፍነው እንደጠፉ - እንዲሁም በመጨረሻ ዩኒፎርም የለበሱ የፀጥታ ሀይሎች በቴ ላይ ግድያ ሲፈፅሙ የተመለከቱ እና ይህንኑ የመሰከሩ የአካባቢው ነዋሪዎች በመንግስት ሀይሎች ደብዛቸው እንዲጠፋ መደረጉን አስታውቋል::


📲 ስልክዎትን ለመቀየር ወይም አዲስ ለመግዛት አስበዋል 🤔?

አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል📱ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ

https://t.me/sellphone2777

📞 0929008292

📩 inbox @bina27

📍አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ

📨 ክፍለ ሀገር ላላቸሁ ደንበኞችቻችንም በ DHL መላክ ጀምረናል


በተፈራው መሰረት ኢራን በእስራኤል ላይ ከፍተኛ የሆነ የሚሳኤልና የአጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች ጥቃት ከፍታለች ። ቀይ ባህርና ሜድትራኒያን ቀጠና ውጥረት ውስጥ ገብቷል ። በቀጥታ ስርጭቶች እየታየ እንዳለው እስራኤል እንዲሁም አጋሮቿ እንግሊዝና አሜሪካ የኢራንን ጥቃት ሙሉ በሙሉ ኢላማቸውን ከመምታት እንዲከሽፉ መከላከል እየተቻላቸው አይደለም ።

ጆ ባይደን ኢራን ላይ ያለንን ጦር መሳሪያ በሙሉ እንጠቀማለን ሲሉ የዛቱ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ ዓለም ለኒውክሌር ጦርነት ከምንግዜውም በላይ ቀርባለች ሲሉ ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች እየዘገቡ ይገኛሉ።


ሌላ ጦርነት ፈነዳ
በተፈራው መሰረት ኢራን በእስራኤል ላይ ከፍተኛ የሆነ የሚሳኤልና የአጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች ጥቃት ከፍታለች ። ቀይ ባህርና ሜድትራኒያን ቀጠና ውጥረት ውስጥ ገብቷል ። በቀጥታ ስርጭቶች እየታየ እንዳለው እስራኤል እንዲሁም አጋሮቿ እንግሊዝና አሜሪካ የኢራንን ጥቃት ሙሉ በሙሉ ኢላማቸውን ከመምታት እንዲከሽፉ መከላከል ይችላሉ ወይ የሚለው ጥያቄ ውስጥ ገብቷል።

ጆ ባይደን ኢራን ላይ ያለንን ጦር መሳሪያ በሙሉ እንጠቀማለን ሲሉ የዛቱ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ ዓለም ለኒውክሌር ጦርነት ከምንግዜውም በላይ ቀርባለች ሲሉ ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች እየዘገቡ ይገኛሉ።


የአውሮፓ ህብረት በፖለቲከኛ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ላይ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ መግለጫ አወጣ። በቴ ከሆቴል ለሊት አውጥተው በስድስት ጥይት እንደገደሉት ይታወሳል።


በአዲስ አበባ ፖሊስ ቦሌ አካባቢ ተታኩሶ የተገደለው ነሁሰናይ

Показано 20 последних публикаций.