እነዚህን ሁለት ህፃናት እናሳክማቸው‼
==========================
✍ ከታች በፎቶው ላይ ከእናቶቻቸው ጋር የምትመለከቷቸው ሁለት ታዳጊዎች፤ ህፃን ፋጡማ አሕመድ እና ህፃን ሰዓዳ ካሳዉ ይባላሉ። ፋጡማ የ13 አመት ታዳጊ ስትሆን ሰዓዳህ የ14 አመት ታዳጊ ናት። ሁለቱም አላህ በወሰነባቸው በልብ ቧንቧ ክፍተትና የሳንባ ጥበት በሽታ እየተሠቃዩ ይገኛሉ። በአስቸኳይ አድስ አበባ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሂደዉ ሰርጀሪ ካልተሠሩ አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን ክትትል ሲያደርግላቸዉ በነበረ ዶክተር ተነግሯቸዋል። አንዷ እህታችን ከክፍለ ሃገር እዚህ ጥቁር አንበሳ መጥታ በሕክምና ላይ ስትሆን ሕክምናውን ማስሄጃ ገንዘብ ተቸግራለች።
አንዷ በገንዘቡ ብዛት ተስፋ ቆርጣ ካለችበት አካባቢም አልተንቀሳቀሰችም። ለሕክምና አገልግሎት ብቻ ለእያንዳንዳቸው ከ600 ሺህ ብር በላይ ያስፈልጋቸዋል።
የቤተሰቦቻቸዉን ሁኔታ በተመለከተ፦ ህፃን ሰዓዳ ለእናቷ ያለቻት ልጅ እርሷ ብቻ ናት። በዛ ላይ እናቷ የመስማት ችግር አለባቸው፤ አባቷ ወደ አኺራህ ሄዷል፤ የቲም ነች። በተጨማሪም መጠለያ ጣቢያ ላይ በመንግስት እርዳታና በቅን አሳቢዎች ድጋፍ ነዉ የምትኖረው። እንኳን ይህን ያክል ብር አግኝታ ልታሳክም፤ ለዕለት ኑሮዋም ከአላህ እዝነት ቀጥኮ በሌሎች ድጋፍ ነው።
የህፃን ፋጡማ ቤተሰቦችም ከ2 አመት በፊት ከወለጋ በተፈጠረዉ የሰላም ችግር ከቤታቸውና ሀብት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዉ በመምጣት አውራ ጎዳና መጠለያ ጣቢያ ላይ ሆነው በእርዳታ እየኖሩ ያሉና የከፋ ችግር ውስጥ ሆነው የልጅቱ በሽታ እየባሰ መምጣቱ ደግሞ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሁኖባቸዋል። እናትየዋ ጧት ማታ ለቅሶ ላይና ናቸው።
እናማ ውዶች፤ ከታች በተቀመጡት ጥምር አካውንቶች እንደተለመደው በመሰደቅ የእናቶቻችንና የእህቶቻችንን እምባ እናብስ!
√ የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር: 1000672888666
√ አቢሲኒያ ባንክ: 216629407
√ የአካውንት ስም፦ ሰርኬ ዓሊ ለጋስ እና ሉባባ ሰይድ ሙሄ
መልዕክቱን ሼር በማድረግ፣ አላህ ከሰጣችሁ ላይ በመሰደቅና በመልካም ዱዓችሁ አግዟቸው።
የምትሰድቁበትን ደረሰኝ በውስጥ
@Murad_Tadesse ላኩልኝ።
ቡሪክቱም!
||
t.me/MuradTadesse