New Life Ministry


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


በክርስቶስ አዲስ ሕይወት አገኘን!

እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።
ወደ ሮሜ ሰዎች 6 : 4

@newlifeministrybot
2013 የከፍታ ዓመታችን ነው!!
@NEW_LIFE_MINISTRY
@AMBASSADORLIFE

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: Jc youth
ከ 10,000 ሺህ በላይ ተከታይ ባለዉ ዩቱዩብ ቻናላችን ላይ መዝሙራችሁን እንዲሁም የተለያየ ዝግጅቶችን በነፃ ማቅረብ ለምትፈልጉ ከታች በምታገኙት አድራሻ አናግሩን ።
👇👇👇👇👇👇

@Elyas_jc


" ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች።"
(የዮሐንስ ወንጌል 9:4)






አስቀድመን በትውልድ አሕዛብ የነበርን በአካል ላይ በሰው እጅ ከተደረገው የተነሣ ራሳቸውን ''ተገርዘናል'' በሚሉት ''ያልተገረዙ'' የተባልን እኛ፡ በዚያን ዘመን ከክርስቶስ ተለይተን፣ ከእስራኤል ወገንነት ርቀን፣ ለኪዳኑም ተስፋ ባዕዳን ሆነን፣ በዓለም ላይ ያለ ተስፋና ያለ እግዚአብሔር ነበርን።

ነገር ግን የአብርሃም ዘር የሆነ ከአብርሃም የሚቀድም፣ የዳዊት ልጅ የሆነ ግን ዳዊት ጌታ ጌታዬ የሚለው ንጉሥ፣ ከዘላለም ዘላለም በፊት የነበረ፣ የሚታየውና የማይታየው ሁሉ የእርሱ እጅ ሥራ የሆኑለት የዓለማት ፈጣሪ፣ ሁሉም ለእርሱና በእርሱ ከእርሱ የተፈጠሩለት አምላክ፣ ሁሉንም በስልጣኑ ቃል ደግፎ የያዘ ያህዌ፡ ለተቀበልነው ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች እንድንሆን ሥልጣንን ሊሰጠን ከድቅድቁ ጨለማ ወደ አስደናቂው ብርሃኑ ሊጠራን፣ የንጉሥ ካህናት፣ ቅዱስ ሕዝብ ሊያውም እግዚአብሔር ለራሱ የለየው የተመረጠ ትውልዱ ደግሞም የመንግሥቱ ወራሾች ሊያደርገን ያህዌ ተወለደ

ባባሕርዩ አምላክ ሆኖ ሳለ ኃይሉን እንደመቀማት ያልቆጠረ፣ ከድንግል ማርያም በግርግም ተወልዶ የባሪያን መልክ የያዘ በሰውም አምሳል ተገኝቶ ራሱን ባዶ ያደረገ፣ እንዲያገለግሉት ሳይሆን ለማገልገል፣ ለንግሥና ሳይሆን እንደ በግ ታርዶ ሰውን ከእግዚአብሔር የለየውን ኅጥያት ሊያስወግድ የተወለደ የይሁዳ አንበሳ የነገሥታት ንጉሥ ተወለደ።

ዛሬም በስሙ የምያምኑትን ከኅጥያት ከኩነኔ ሊያድናቸውና የዘላለምን ሕይወት ሊሰጣቸው ይችላል። ኢየሱስ ይወዳችኋል!!

@new_life_ministry
@new_life_ministry




ወደ ቆላስይስ 2
16፤ እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለ ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ።


Colossians 2
16 Let no man therefore judge you in meat, or in drink, or in respect of an holyday, or of the new moon, or of the sabbath days:


በዓላችን ኢየሱስ ነው::


Репост из: Kingdom Muzic Ethio💚💛❤️
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
Prepare your self for the coming of the lord. His coming back again!!!😇😇

@kingdommuzicethio🎧
@kingdommuzicethio🎧


ኢየሱስ ይመጣል


ኦሪት ዘጸአት 39
30፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው፥ ከጥሩ ወርቅ የተቀደሰውን የአክሊል ምልክት ሠሩ፤ በእርሱም እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገው፦ #ቅድስና_ለእግዚአብሔር_የሚል_ጻፉበት።






ቅድስና ለእግዚአብሔር




በክርስቶስ በማመን የእግዚአብሔር ልጅ መሆን ለምትፈልጉ የተደረገ ፀሎት ሁላቹም አብራችሁን ፀልዩ🙏

ለሁሉም ሰው ሼር ያድርጉ ቢያንስ ለ 20 ሰው 😊

Contact👉 @barackkkk
@new_life_ministry
@new_life_ministry


ወንጌልን እና እኛ አማኞች

ወደ ሮሜ 1
16፤ በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና።

በወንጌል ድነናል
ወንጌል እመሰክራለን
በወንጌል እንቆማለን
ለወንጌል እንኖራለን

በመንፈስ ቅዱስ ሃይል እመስክር ከክርስቶስ የተቀበልነው አደራ ነው::

የማቴዎስ ወንጌል 28
19-20፤ እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።

ወንጌል መስበክ ግዴታችን ነው::

1ኛ ቆሮንቶስ 9
16፤ ወንጌልን ብሰብክ እንኳ የምመካበት የለኝም፤ ግድ ደርሶብኝ ነውና፤ ወንጌልንም ባልሰብክ ወዮልኝ።

@new_life_ministry
@new_life_ministry


መለኮታዊ ስጦታችሁን አግኙ


ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ አምስት መክልት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ሌላ አገር ወዲያው ሄደ።ማቴ 25፥15

በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ስጦታ ወይም መክሊት የሚባል የተቀመጠ ነገር አለ እግዚአብሔር እያንዳንዱ ሰው በምድር ስፍራውን እንዲይዝ አንድ ነገር ሰጥቶታል።

አንዳንዶቹ አምስት ሁለት ወይም አንድ ብቻ አላቸው ነገር ግን ሁሉም ሰው አንድ የተሰጠው ነገር አለው።

በውስጣችሁ ያለውን መለኮታዊ ስጦታ ማወቅ ዓላማችሁን ማግኛ ታላቅ መንገድ ነው።

ነገር ግን አንድ ቀን የመክልቱ ባለቤት ይመለስና ምን እንደ ሰራችሁበት ይጠይቃል:: ያተረፈውን ብርቱ ሥራተኛ ይሾማል:: ያልሰራውን ሰው ግን ወደ ውጭ ይጥላል::

ማቴዎስ ወንጌል 25:16-30

16 አምስት መክሊትም የተቀበለው ሄዶ ነገደበት ሌላም አምስት አተረፈ፤
17 እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ።
18 አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቈፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ።
19 ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቆጣጠራቸው።
20 አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ። ጌታ ሆይ፥ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት አለ።
21 ጌታውም። መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው።
22 ሁለት መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት አለ።
23 ጌታውም። መልካም፥ አንተ በጎ፥ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፥ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው።
24 አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤
25 ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ አለ።
26 ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው። አንተ ክፉና ሃኬተኛ ባሪያ፥ ካልዘራሁባት እንዳጭድ ካልበተንሁባትም እንድሰበስብ ታውቃለህን?
27 ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር፥ እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር።
28 ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት አሥር መክሊትም ላለው ስጡት፤
29 ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።
30 የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።

@new_life_ministry
@new_life_ministry


ኢየሱስ ❤️

Показано 20 последних публикаций.