Natinael Mekonnen


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Шок-контент


ይህ ቻናል ቴሌግራሜ hacked በተደረገበት ሳት ለግዝያዊነት የከፈትኩት ቻናል ነው ለችግር ጊዜ ይጠቅማል ተቀላቀሉ
በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ከፈለጉ @NatnaelMekonnen7 በማለት መረጃዎችን ይላኩልን
I blog about marketing and sales
Buy ads: https://telega.io/c/NatinaelMekonnen21

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Шок-контент
Статистика
Фильтр публикаций


“ዘለንስኪ ትሁትና ውጤታማ ኮሜዲያን ነው” ትራንፕ 😂

“ዜለንስኪ ጥሩ የነበረበት ብቸኛው ነገር ባይደንን ማታለል ብቻ ነው” ብለዋል ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን “ትሁትና ውጤታማ ኮሜዲያን ነው” ሲሉ ወርፈዋል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትሩዝ በተባለው የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን “ያለ ምርጫ የተቀመጠ አምባገነን ነው” ብለዋል።

ትራምፕ “ትሁቱና ውጤታማ ኮሜዲያን ዘለንስኪ አሜሪካን 350 ቢሊየን ዶላር በማስውጣት መጀመር ያልነበረባቸው እና የማያሸንፉት ጦርነት ውስጥ ገብተዋል” ብለዋል።

“ዩክሬን ጦርነቱን ያለ አሜሪካ እና ትራምፕ በፍፁም መቋቋም አትችልም” ሲሉም ገልጸዋል።

ዜለንስኪ ከላክንለት ገንዘብ ግማሹ “የጠፋ” መሆኑን አምኗል ያሉት ትራምፕ “ምርጫ ለማድረግ ፈቃደኛ አይደለም፣ በዩክሬን የሕዝብ ዘንድ ያለው ተቀባይነት በጣም ዝቅተኛ ነው” ብለዋል።

“ዜለንስኪ ጥሩ የነበረበት ብቸኛው ነገር ባይደንን ማታለል ብቻ ነበር” ሲሉም ገልጸዋል።

“ያለ ምርጫ የተቀመጠ አምባገነን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በፍጥነት መንቀሳቀስ ይኖርበታል፤ ካልሆነ ግን የሚያተርፈው ሀገር አይኖርም” ብለዋል ትራምፕ።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አክውም “ዩክሬንን እወዳለሁ፣ ነገር ግን ዘለንስኪ አስከፊ ስራ ሰርቷል፣ ሚሊዮኖችም ያለምክንያት ሞተዋል እየሞቱም ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪ “ዶናልድ ትራምፕ የሀሰት መረጃ ውስጥ እየኖሩ ወይንም በሀሰት መረጃ እየተነዱ ነው” ብለዋል።


የመሳይ መኮንን (ቦምብነሽ) ቦምቦች 😄

መሳይ መኮንን (ቦምብነሽ) አዲስ አበባ ላይ “አራት ቦምብ ፈነዳ” ብሎ ዘግቧል።😄 እንደዘገባው ከሆነ የነመሳይ ምናባዊ ቦምቦች የፈነዱት አንዱ አራት ኪሎ አካባቢ ነው። ሌላው ደግሞ ፒያሳ የከንቲባዋ office አካባቢ ነው 😄 አንዱ ደግሞ ፌደራል ፖሊስ ሲሆን የመጨረሻው ደግሞ ቦሌ ኤርፖርት መግቢያ በሩ ጋር ነው 😄 (የነመሳይ ቦምቦች የፈነዱት የኮሪደር ልማቱን ተከትለው ይመስላል 😄)

የነመሳይ ቦምቦች ከአለም ለየት የሚያደርጋቸው አራቱንም ቦምብ መሀል ከተማ ውስጥ ሲያፈነዱ የአዲስ አበባ ሠው ምንም አለመስማቱ ነው 😄 በርግጥ ከውስጥ አዋቂ ምንጮች እንደሰማነው ቦምቡን ያፈነዱት በሳቅ ነው ተብሏል 😄

ቦምቡ ፍቅርሽ ሲፈነዳ
ላንቺ ብዬ ገባሁ ዕዳ 😂

አይ ቦምብነሽ


ወይዘሮ ኬሪያ ኤብራሂም ‹‹የታክሲ ሰልፍ ጠብቄ እየሄድኩ ነው›› በማለት ተናገሩ፡፡ የቀድሞው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ የሆኑት ወይዘሮ ኬሪያ በአሁኑ ወቅት ከቤተሰባቸው ጋር በአዲስ አበባ እንደሚኖሩ ገልፀው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ውስጥ እየሰሩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ከቪኦኤ ትግርኛ ቋንቋ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ‹‹እኔ ስልጣን ላይ በነበርኩበት ጊዜ አጃቢና ሹፌሮች ነበሩኝ፡፡ አሁን ግን የታክሲ ሰልፍ ጠብቄ እየሄድኩ እገኛለሁ፡፡ ምንም ችግር የለውም፡፡ ህይወት ይቀጥላል›› ብለዋል፡፡

ስልጣን መልቀቅ የህይወት መጨረሻና ሞት ማለት እንዳልሆነም አስረድተዋል፡፡ ‹‹በረሀ ወርደን መስዋእትነት የከፈልነው ለስልጣን ነበር ወይ?›› የሚል ጥያቄ ያነሱት ወይዘሮ ኬርያ ስልጣን መያዝ የመጨረሻ ግብ መሆን እንደሌለበት አሳስበው እሳቸው ግን እንደማንኛውም ሰው በህዝብ ጋር እየኖሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ወይዘሮ ኬርያ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤነታቸው በፈቃዳቸው ከለቀቁ በኋላ በጦርነቱ ወቅት ታስረው የነበረ ሲሆን ከእስር ከተፈቱ በኋላ ከህወሀት መባረራቸው ይታወሳል፡፡


Good Morning #Ethiopiaዬ : ኢትዮጵያ እና ሱማሊያ አንካራ ውስጥ ያካሄዱትን የመጀመሪያ ዙር የቴክኒክ ድርድር ትናንት አጠናቀዋል።

ኹለቱ ወገኖች፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይና ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሐመድ በአንካራው ስምምነት ያስቀመጡትን ራዕይ ወደ ተግባር ለመለወጥ ቁርጠኛ መኾናቸውንና ኹለቱን አገራት ተጠቃሚ ለሚያደርግ ዘላቂ ልማት መሠረት መጣላቸውን በጋራ ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል።

ኹለቱ ወገኖች ለኹለተኛው ዙር የቴክኒክ ድርድር በመጋቢት ወር ለመገናኘት ከስምምነት ላይ መድረሳቸውንም ጠቅሰዋል።

በቴክኒክ ድርድሩ የኢትዮጵያን ልዑካን ቡድን የመሩት ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ሲኾኑ፣ የሱማሊያን ልዑካን ቡድን የመሩት ደሞ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደኤታ ዓሊ ኦማር ናቸው።


የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሥራ ዘመን ለአንድ አመት ተራዘመ።

ኮሚሽኑ ዛሬ የሦስት አመታት ሪፓርቱን ለፓርላማ ያቀረበ ሲሆን፣ የፓርላማ አባላት በሪፓርቱ ላይ የተለዩዩ ጥያቄዎችንና አስተየቶችን ሰጥተዋል።

በመጨረሻም ሦስት አመቱን የካቲት 14 ቀን በመድፈን የሥራ ዘመኑ ይጠናቀቅ የነበረው ኮሚሽኑ፣ በፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ የአንድ አመት ተጨማሪ ጊዜ ተሰጥቶታል።

በቋሚ ኮሚቴው የተሰጠው የአንድ አመት ተጨማሪ ጊዜ ውሳኔው የቀረበበት ሦስት የተቃውሞ ድምፅ ብቻ ነው።

በተለይ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ስላለው ሁኔታ የፓርላማ አባላት ያነሷቸውን ነጥቦችና የተሰጡ ምላሾችን በተመለከተ ተጨማሪ ይኖረናል።


ልዩ ዜና ትግራይ

“ በሃይማኖት አባቶች የተጀመረው የሽምግል እና የእርቅ እንዲሁም የካቲት 11 በጋራ የማክበር እንቅስቃሴ አልተሳካም አሉ “ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ።

ፕሬዜዳንቱ ለእርቅ እና ሽምግልና አለመሳካት “ ቡድን “ ሲሉ የጠሩትን አካል ተጠያቂ አድርገዋል።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ባወጡት መግለጫ “ መንግስት የማያውቀው ርችት በመተኮስ የሚያጋጥም ችግር ካለ ተጠያቂው ቡድኑ ነው “ ብለዋል።

አላስፈላጊ የአመፅ እንቅስቃሴዎች እየታዩ መሆናቸው የገለፁት ፕሬዜዳንቱ ፤ ህዝቡ አከባቢውን በልዩ ሁኔታ በመጠበቅ በዓሉ እንዲያከብር አሳስበዋል። 

ከቀናት በፊት ለእርቅና ሽምግልና ፍቃደኛ መሆናቸው በትግራይ የሃይማኖት አባቶች መግለጫ የተሰጠባቸው ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳና የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በትናንቱ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እጅ ለእጅ ሲጨባበጡ የሚያሳይ ፎቶ መለቀቁ ብዙዎች አስደስቶ ነበር።


ካይሮ በማለት የሚያንቆለጳጵሰው ሃይማኖት አፈወርቅ ከነታጣቂው ተደምስሷል!

እራሱን የአማራ ፋኖ በጎጃም በማለት የሚጠራዉን የጃውሳ ክንፍ ከሚመሩት ታጣቂዎች መካከል አንዱ የነበረው ሃይማኖት በተወሰደበት እርምጃ ተደምስሷል። ሃይማኖት ብቻ ሳይሆን ሲመራው የነበረ ታጣቂ በሙሉ ሙት እና ቁስለኛ መሆኑን የደረሱኝ መረጃዎች ጠቁመዋል። ሃገርን የማፍረስ እድቅ ይዞ የተነሳው ጽንፈኛው ቡድን የሚገባውን እያገኘ ያለ ሲሆን አሁን አሁን ቡድኑ የሰራዊቱን ክንድ መቋቋም እያቃተው እንደሆነም ከየቦታው የሚደርሱኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ።


ኢትዮጵያ በዚህ አመት የማዳበሪያ ግዢ የፈፀመችው ሙሉ በሙሉ ከራሺያ ሲሆን የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚ በትናንትናው እለት የጭነት እና የማውረድ ሂደትን ለማሳየት የአርካይቭ ፎቶ መጠቀማቸውን እንደ ማሳያ በማቅረብ ከቅርብ ግዜ ወዲህ የወረደ የፌስቡክ “ትግል” እያደረገ የሚገኘው ጃዋር መሀመድ ግዜው ያለፈበት ማዳበሪያ ለአርሶ አደር ሊከፋፈል ነው የሚል የተዛባ መረጃ ሲያሰራጭ አምሽቷል::

እራሱን የፓለቲካ ስትራቴጂስት አድርጎ የሚያቀርበው እና በብዙዎች እንደ ጥልቅ አሰላሳይ እና የመረጃ ሰው የሚታየው ጀዋር ኢትዮጵያ በዚህ አመት ስላስገባችው ማዳበሪያ ኢ/ር ታከለ በስህተት የለጠፋትን የቆየ ምስል ብቻ እንደ ማስረጃ በማቅረብ ብዙ ትንታኔ እና ከ 6 በላይ ፖስቶችን አጋርቷል::

“ስትራቴጂስቱ “ ጃዋር እውነት ግዜው ያለፈበት ማዳበሪያ ገብቶ ከሆነ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ምርመራ በማድረግ እና ማስረጃዎችን በማቅረብ መንግስትን ቢሞግት ተገቢ ይሆን ነበር:: ለማንኛውም ግዜው ያለፈበት ማዳበሪያም የለም የተፈጠረው በተራ ስህተት ምክንያት ብቻ የተፈጠረ ውዥንብር ነው::


በቋራ ወረዳ ነብስ ገበያ ቁጥር 1 እና በመተማ ወረዳ ቱመት መንዶካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ ለመንግስት እጃቸውን ሰጡ።

ሻለቃ መሪ ይታያል ውዱ ተገኘ በማለት ራሱን እየገራ በመተማ ወረዳ በቱመት-መንዶካ ፣ እና በቋራ ወረዳ ቀጥር 1 እና ነብስ ገበያ 22 ራሱን ሆኖ ሲንቀሳቀስ የነበረ ታጣቂ በሽንፋ ለሚገኘው ጥምር የጸጥታ በሰላም እጃቸውን ሰጥተዋል።

ታጣቂው ሃይሉ 15 ባለመሳሪያ እና 7 ጀሌ ሆነው ለመንግስት በሰላማዊ መንገድ እጅ ሰጥተዋል።

ታጣቂ ሀይሉ የሰላምን መንገድ የመረጥነው የማያዋጣ እና አላማ የሌለው ትግል በመሆኑ ማህበረሰባችን ጋር ተቀላቅለን እንዲሁም ከመንግስት ጎን ሆነን ለአገራችን ሰላምና ልማት የበኩላችን ለመወጣት ነው ብለዋል።

የመተማ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ሞገስ በቦታው ተገኝተው እነደተናገሩት ለህዝብ በማሰብ የሰላምን መንገድ መርጣችሁ በሰላም ወደ ማህበረሰባችሁ ሰለተቀላቀላችሁ ስልጡንነታችሁን ያሳያል።

በመንግስት በኩል የተለያዩ የተሃድሶ ስልጠና ወስዳችሁ ከህዝባችሁ እና ከመንግስት ጎን ሆናችሁ የበኩላችሁን እንድትወጡ ያደርጋል ብለዋል።

ዘገባው የመተማ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ነው።


የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ የጎንደር ከተማን የኮሪደር ልማት በምሽት ጎበኙ።

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ፣የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ዴኤታዎች፣ የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር ፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን የሥራ ኀላፊዎች፣ የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ጋሻው አወቀ ፣ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው ፣ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አወቀ አስፈሬን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች የጎንደር ከተማን የኮሪደር ልማት በምሽት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል



Показано 11 последних публикаций.