Natnael Mekonnen


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Политика


በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Политика
Статистика
Фильтр публикаций


ምዕ/ሸዋ እና ደ/ምዕ/ሸዋ አዋሳኝ አካባቢ ሲንቀሳቀስ የነበረው የኦነግ/ሸኔ ታጣቂ በሰላም ከነ ትጥቁ ለመከላከያ ሰራዊት እጁን ሰጥቷል::

ሰላም ለኢትዮጵያ
ሰላም ለኦሮሚያ


የኢ ቢ ኤስ (EBS) ቴሌቪዥን “የአዲስ ምዕራፍ” ፕሮግራም ከስርጭት ታግዶ እንዲቆይ ተወሰነ!

በኢ ቢ ኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ የሚተላለፈውና “አዲስ ምዕራፍ” የተሰኘው ፕሮግራም በኤዲቶሪያል አሰራሩ ላይ አስፈላጊውን እርምት በመውሰድ ለባለሥልጣኑ እስኪያሳውቅና ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ፤ ከስርጭት ታግዶ እንዲቆይ የተወሰነ እና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን አስታውቋል።

ባለሥልጣኑ እሁድ መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ያሰራጨውን ፕሮግራም ከመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እና ከዘርፉ ሕጎች አንጻር በመገምገም አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን ነው የገለጸው፡፡

- የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የፕሮግራሙን መታገድ አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ ከላይ ተያይዟል።


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የቀነኒ አዱኛ እናት:- የኢትዮጵያ ህዝብ የልጄን ደም ሀቁን እንድታወጡልኝ

* ከውጪም ሆነ
* ከሀገር

ውስጥም ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ከጎኔ
እንድትቆሙልኝ እማፀናለሁ::


Good News : በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ቁጥራቸው ከሌላ ግዜው የሚበዛ የኦነግ/ሸኔ ታጣቂዎች ከነ መሳሪያቸው ለመከላከያ ሰራዊት እጃቸውን ሰጥተዋል::

ሰላም ለኢትዮጵያ
ሰላም ለኦሮሚያ


ዛሬ የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት የሚያሻሽለው አዋጅ ፀድቋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 22ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ የወጣ የማሻሻያ አዋጅን መርምሮ አጽድቋል።

አዋጁ እስከ አሁን በሥራ ላይ የነበረውን አዋጅ ቁጥር 359/ 1995 የሚያሻሽል ሲሆን፤ አዋጅ ቁጥር 1373/2017 ሆኖ በሁለት ድምጸ ተዐቅቦ በአብለጫ ድምፅ ጸድቋል፡፡

አዋጁ የክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን የቆይታ ጊዜ የማራዘም ስልጣን፤ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሚሰጥ ነው።

አዋጁ የፌደራል መንግስት በክልሎች የሚያቋቁመውን ጊዜያዊ አስተዳደር የስራ ዘመን ለሁለት ጊዜ የማራዘም ስልጣን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሚሰጥ ነው።

የአፈ ጉባኤው ውሳኔ በፌዴሬሽን ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ተቀባይነት ካላገኘ፤ ጊዜያዊ አስተዳደር በተቋቋመበት ክልል “ በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ምርጫ እንዲደረግ “ ያስገድዳል።

ይህ አዋጅ የፌዴራል መንግስት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ስርአት ለመደንገግ በ1995 ዓ.ም የወጣውን አዋጅ ያሻሻለ ነው።


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
900,000 ብር ምን መግዛት ይችላል?

መኪና? ቤት?

በዚህ ጊዜ 900,000 ብር ምንም መግዛት አይችልም ።

እኛ ጋር ግን በ900,000 ብር ሱቅ መግዛት ትችላላችሁ

ያውም እስከ 200,000 ብር መከራየት የሚችል ሱቅ።

ፒያሳ አድዋ ዜሮ ዜሮ አጠገብ 20 ካሬ ሱቅ አየሸጥን ነው።

ከግራውንድ እስከ 5ኛ ፎቅ።

ለሁለት ሳምንት ብቻ የሚቆይ ዋጋ ነው

ፈጥነው ይደውሉ!

ለበለጠ መረጃ (Direct/ Whatsapp) ፦ በ 0987170752 / 0987335552 ይደውሉ


Daily Express !

የእንግሊዙ ጋዜጣ Daily Express ስለ አዲስአበባችን እንዲህ ጽፏል።

Africa's huge mega-city that's one of the highest capitals in the world
The city's population in 2025 is estimated to be nearly six million, growing by over 4% year on year.

Africa is home to a number of fast-growing citiesthat are beginning to attract global attention. One of them also happens to be the continent’s highest capital city, sitting at around 2,355 metres above sea level. The city lies at the foot of Mount Entoto and is surrounded by hills and mountains. Its altitude also makes it the fourth highest capital city in the world.
Despite being close to the Equator, its elevation means it averages around 18C throughout the year. The city in question is Addis Ababa, the capital of Ethiopia and one of Africa’s largest metro areas. According to Macrotrends, the city’s population in 2025 is estimated to be nearly six million, growing by over 4% year on year. That makes it one of the fastest growing cities on the continent and, by many definitions, a mega-ci

https://www.express.co.uk/news/world/2033690/africa-mega-city-highest-capital-addis-ababa-ethiopia?fbclid=IwZXh0bgNhZW0CMTEAAR0g9ITyIrg1xT-1KfOWrTvAC9duWC3MDsZezy1zf5kcbdwkUfkq6noYorc_aem_M48T_QUk2DWQgdk3xbOtdg


ዩናይትድ ኪንግደም 40 ሀገራትን ያሳተፈ ሕገወጥ ስደት ላይ ያተኮረ ጉባኤ ልታዘጋጅ ነው

በለንደን ለሁለት ቀናት የሚቆየውን ህገ-ወጥ ስደትን ለመቅረፍ ያለመ ስብሰባውን ከተቀላቀሉት 40 ሀገራት መካከል የአሜሪካ፣ቻይና እና ፈረንሳይ ተወካዮች ይገኙበታል። የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር ሰር ኬር ስታርመር በተጎዱት ሀገራት መካከል ካለው የፖለቲካ ክፍፍል የሚመጡ ሰዎችን በማዘዋወር የሚሰራበት ንግድ እና የሚያገኙት ትርፍ "አስከፊ ንግድ" ነው ሲሉ አስጠነቃቀዋል። ዓለም አቀፉ ጉባኤው እንደ መጀመሪያ ሂደት የታየ ሲሆን የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት "የተጨባጭ ውጤቶችን" እንደሚያስገኙ ተስፋ አድርጓል።

ኢሚግሬሽን በፖለቲካዊ መልኩ የመንግስት ቁልፍ ጉዳይ ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን ሁለቱም ኮንሰርቫቲቭስ እና ሪፎርም ዩኬ ሌበር በጉዳዩ ላይ ቁጥጥር ማድረግ አልቻለም ሲሉ ከሰዋል።ከጉባኤው ቀደም ብሎ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ጽሕፈት ቤት የሰዎችን የህገወጥ ዝውውእ ለመግታት 33 ሚሊዮን ፓውንድ እንደሚውል አስታውቋል። የቬትናም፣ የአልባኒያ እና የኢራቅ ባለስልጣናት በጉባኤው  የሚገኙ ሲሆን የሶስቱ ሀገራት ስደተኞች ወደ እንግሊዝ በብዛት ይጓዛሉ። ከፈረንሳይ፣ ከቻይና እና ከአሜሪካ ተወካዮች ጋር በለንደን ላንካስተር ሀውስ በመሪዎች ስብሰባ ላይ ይገኛሉ።

በዓመት 10 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የወንጀል ንግድ እንዴት ማደናቀፍ እንደሚቻል በሚመክረው ጉባኤ ላፕ ከኩርዲሽ ክልላዊ መንግስት፣ ከኢንተርፖል እና ከማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች እንደ ፌስቡክ ወላጅ ኩባንያ ሜታ ፣ቲክቶክ እና ኤክስ የተውጣጡ ልዑካን ተሳታፊ ይሆናሉ።እ.ኤ.አ. በ2025 ዓመታ ብቻ እስካሁን ድረስ ከ6,000 በላይ ሰዎች ቻናሉን አቋርጠው ወደ እንግሊዝ የገቡ ሲሆን ይህም በአነስተኛ ጀልባዎች የተደረገ ሪከርድ የስደተኞች ጉዞ አድርጎታል። እንግሊዝ ከዚህ ቀደም እንደዚህ ያሉ ስደተኞችን ቁጥር ለመቅረፍ ከሌሎች ሀገራት ጋር ተከታታይ ስምምነቶችን ማድረጉን አስታውቃለች።


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
☎️ 09-01-97-86-97
📞 09-86-68-75-13

 
10% ቅድመ ክፍያ

ከ 65 ካሬ ጀምሮ ማግኘት ይችላሉ

ሪያሊቲ ሪል እስቴት ፤ ህልምዎን በማያወላውል ቁርጠኝነት እንገነባለን።

ሁሉም ቤቶቻችን ባለ 1፣ 2 እና 3 መኝታ ቤት ከአንድ ተጨማሪ ክፍል ጋር ናቸው። ሁሉም ቤቶቻችን ከሰፊ ኮሪደር ጋር ለበቂ የተፈጥሮ ብርሃን እንዲሁም ለንፁህ እና ነፋሻማ አየር ዲዛይን የተደረጉ ናቸው።

ዛሬዉኑ ይጎብኙን - ባለ ግርማ ቤትዎ እርስዎን ይጠብቃል።

Reality Real Estate: Building dreams with unwavering dedication.

With just 5 apartments per floor, each boasting 1,2&3 bedrooms plus an additional room, expansive corridors for ample natural light and ventilation.

Visit us today— Your Palace awaits.

ሪያሊቲ ሪል እስቴት

ሁሉም ባለ ግርማ ቤቶቻችን በመሃል ከተማ📍ቦሌ እና ሳር ቤት📍ብቻ!

REALITY REAL ESTATE
Your Gateway to Luxury Living!

Visit us!
📱 : +251
986687513
☎️ : +251
901978697

#Reality
#RralityRealEstate #Realestate #Bole#Sarbet #Addisababa #LuxuryLiving #Home #Fyp


ጌታቸው ረዳ በትግርኛ የለጠፈው ፅሁፍ፤


ባለፉት ሃያ ቀናት በትግራይ ተፈጥሮ ያለው ከፍተኛ የፖለቲካ ትርምስ ሀላቀሩ ቡድን ባለፉት ሁለት አመታት የስልጣን ወይም ሞት ሽረት ሴራው ወዲ መጨረሻ ምእራፍ እንዲደርስ አድርጎታል፣ ከዚህ በፊት ጥሩ ታሪክ የነበራቸው አንዳንድ ታዋቂ ግለሰቦችም ሳይቀሩ ስርዓቱ ወደ ማይገባ ተግባር አሰማርቶ ታሪካቸው እንዲጨቀይ አድርጎታል ።

የመንግስት መስሪያ ቤቶችን በሀይል ተቆጣጥሮ ማህተሞች የዘረፈው ሀይል እስካሁን ያከናወናቸው ሁለት ነገሮች አሉ።

መጀመሪያ በሀይል በተቆጣጠራቸእ ዋና ዋና ከተሞች መሬት ለደጋፊዎቼ ማከፋፍላልና መወረር፣ ለገቢ ምንጩ እንዲሆነው ብዙ መሬት ሽያጭ ማከናወን ናቸው::በተለይ በመቀሌ/ሀድነት፣ ሽሬ/ታች ቆራሮ፣ አክሱም/ላይ ማይጨው እና አዲግራት እና አካባቢው ዋና ትኩረቱ አድረጎ ወረራውን እያከናወነ ሲሆን ከምእራብ ትግራይ ውጪ በሌሎች ዞኖችም ይቀጥላል::

ያለውን መሬት ለመሸጥ እና ለመከፋፈል እንጂ ሌላ ምንም ህዝባዊ ፍላጎት ወይም ተነሳሽነት የሌለው ኃይል በመሆኑ ስለተፈናቃዮች መመለስ ስለ የትግራይ ግዛታዊ አንድነት መመለስ መፈክር ከማሰማት የዘለለ ምንም ተጨባጭ ተግባር ያከናወነው ነገር የለም::የትግራይ ወጣት መሬትህን ጠብቅ:: በወረሩት ማህተም የሚደረግ የመሬት ወረራ ህጋዊ ቅቡልነት ስለሌለው በመግዛት የተሰማራችሁ ባለሀብቶች ገንዘባችሁ አለባሌ ህገወጥ ተግባር ላይ ከማፍሰስ ልትቆጠቦ ይገባል::


የዚህ ኋላቀር ቡድን ሁለተኛ ፍላጎት ስልጣን ይገባኛል ብሎ ከአዲስ አበባ መቐለ እየተመላለሰ ስልጣን መለመንና: ስልጣኑ ይሰጠኝ እንጂ ፕሪቶርያ ስምምነት እፍፀምላሁ የተባልኩትን እፈፅማለሁ እያለ መኳተን ነው:: ፕሬዚዳንት መሾም ስልጣኑ እንዳልሆነ ስለሚያውቅ በየግዜው ሰዎች እየቀያየረ ለፕሬዚዳንት ሹሙልኝ እያለ እየለመነ እድሉ በመሞከር ላይ ይገኛል::

አሁንም ቢሆን ስለ ተፈናቃዮች መመለስ፣ ስለ ምዕራብ ትግራይ መሬት ተሳስቶም አያነሳም::አጀንዳውም አይደለም:: ምእራብ ትግራይ ሲባል ሰሊጥ የሚዘርፍበት መሬት እንጁ ተፈናቅሎ የሚሰቃይ ህዝብ አያሳስበውም::


ይህ ቡድን እና አሽከሮቹ በህልማቸውም ሆነ በእውናቸው ያልለቀቁዋቸው ሁለት አጀንዳዎች ካሉ መሬት መወረርና እና ስልጣን መያዝ ብቻ ናቸው፡ የመላ ህዝባችን ሰላም:የተፈናቃዮች ተስፋ: ለትግራይ ወጣት የነገ ተስፋውም ህልሙም ነጥቀው : ሊለቃቸው የማችል መጥፎ አመላቸው ለማስታገስ ወደ ተጨማሪ ትርምስ ለማስገባት እየታተሩ ይገኛሉ:: በቃ ብለን ልናስቆማቸው ይገባል::

ድል ​​የህዝባችን ነው!


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
900,000 ብር ምን መግዛት ይችላል?

መኪና? ቤት?

በዚህ ጊዜ 900,000 ብር ምንም መግዛት አይችልም ።

እኛ ጋር ግን በ900,000 ብር ሱቅ መግዛት ትችላላችሁ

ያውም እስከ 200,000 ብር መከራየት የሚችል ሱቅ።

ፒያሳ አድዋ ዜሮ ዜሮ አጠገብ 20 ካሬ ሱቅ አየሸጥን ነው።

ከግራውንድ እስከ 5ኛ ፎቅ።

ለሁለት ሳምንት ብቻ የሚቆይ ዋጋ ነው

ፈጥነው ይደውሉ!

ለበለጠ መረጃ (Direct/ Whatsapp) ፦ በ 0987170752 / 0987335552 ይደውሉ


ከሁሉ በፊት የረዳን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን!

ዛሬ በለነገዋ የሴቶች የተሃድሶ እና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ 2ኛ ዙር ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ 380 ሰልጣኞችን አስመርቀን ወደ ስራ አሰማርተናል።

ከአስከፊ ህይወት ወጥታችሁ ስልጠናችሁን በብቃት በማጠናቀቅ ለምርቃት የበቃችሁ እንዲሁም ወደ ስራ ለመሰማራት የተዘጋጃችሁ ልጆቻችን እና እህቶቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!

ለነገዋ የሴቶች የተሃድሶ እና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ለማህበራዊ፣ ለኢኮኖሚያዊ እና ለስነ ልቦና ስብራት የተጋለጡ ሴቶችን ካሉበት የህይወት ውጣ ውረድ እንዲወጡ በማድረግ፣ የስነ ልቦና ድጋፍ እና የሙያ ስልጠና በመስጠት ወደ ስራ በማሰማራት ላይ የሚገኝ ማዕከል ሲሆን በ2ኛው ዙርም በ17 የሞያ አይነቶች የብቃት ምዘና ያለፉ 380 ሰልጣኞችን አስመርቀን የስራ እድልም ተፈጥሮላቸዋል።

ለማዕከሉ ድጋፍ በማድረግ እና የስራ እድል በመፍጠር ላይ የምትገኙ ባለሀብቶች እንዲሁም ሰልጣኞቹ በማዕከሉ በነበራቸው ቆይታ እናትም አባትም ሆናችሁ ከስልጠና በላይ የሆነ እንክብካቤ እና ፍቅር በመስጠት ከልብ ያሰለጠናችሁ፣ የተንከባከባችሁ እና ወደ ስራ ያሰማራችሁ አመራሮች እና መምህራንን በሰልጣኞቹ እና በራሴ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ


የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አስመረቀ ።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ በክብር እንግድነት የተገኙት የመከላከያ ዘመቻ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል በላይ ስዩም ፣ ሃገር ታፍራና ተከብራ በነፃነት የምትቆመው የሃገርን ክብርና የነፃነትን ዋጋ የሚያውቅ ሃገር ወዳድ ሰራዊት ማፍራትና ማብቃት ስትችል ነው ብለዋል።

በመሆኑም ተቋማችን መከላከያ እንደተቋም በጠንካራ መሠረት ላይ ለመገንባት መጠነ ሰፊ የፕሮፌሽናል ሰራዊት ግንባታና ሪፎርም ስራዎችን እየሰራ ጎን ለጎንም ህዝብና መንግስት የሰጡትን ተልዕኮ በአኩሪ ተጋድሎ በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በተጨማሪም መከላከያ የውጭና የውስጥ ፅንፈኛ እና አሸባሪ ኃይሎችን በመዋጋት ህልማቸው እንዳይሳካ በማድረግ ሀገራችን እና ህዝባችንን በመታደግ ተግባር ላይ እንደሚገኝም አንስተዋል፡፡

ተመራቂዎች በስልጠና ቆይታችሁ በመሰረታዊ ውትድርና ስልጠና ያገኛችሁትን የወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ እንዲሁም እውቀት፣ ችሎታና ክህሎት በመጠቀም በምትመደቡበት የሰራዊታችን ክፍሎች የተልዕኮ አፈፃፀም ብቃት በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ኃላፊነት እንደሚጠበቅባችሁ አውቃችሁ በታላቅ ሀገራዊ ስሜት መንቀሳቀስ እና ከነባሩ ሠራዊት ጋር በመሆን ልምድና ተሞክሮን ቀስማችሁ ለሠላም መሥራት አለባችሁ ሲሉ አሳስበዋል።


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
900,000 ብር ምን መግዛት ይችላል?

መኪና? ቤት?

በዚህ ጊዜ 900,000 ብር ምንም መግዛት አይችልም ።

እኛ ጋር ግን በ900,000 ብር ሱቅ መግዛት ትችላላችሁ

ያውም እስከ 200,000 ብር መከራየት የሚችል ሱቅ።

ፒያሳ አድዋ ዜሮ ዜሮ አጠገብ 20 ካሬ ሱቅ አየሸጥን ነው።

ከግራውንድ እስከ 5ኛ ፎቅ።

ለሁለት ሳምንት ብቻ የሚቆይ ዋጋ ነው

ፈጥነው ይደውሉ!

ለበለጠ መረጃ (Direct/ Whatsapp) ፦ በ 0987170752 / 0987335552 ይደውሉ


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የ EBS ባለቤት ይቅርታ ጠይቀዋል:: እውነት ለመናገር #EBS በግሌ ከምወዳቸው ቴሌቭዥን ጣብያዎች አንዱ ነው:: ይህ ቴሌቭዥን ጣቢያ በተለይ ባለቤቶቹ በዚህ ደረጃ ህዝብን ሊያባላ የሚችል ፕሮግራም ሆን ብለው ያስተላልፋሉ ብዬ አልገምትም::

ለኢትዮጵያ ህዝብና ለቴሌቭዥኑ ተከታታዮች ይቅርታ መጠየቅ ትልቅነት ነው:: ይህን ስል ምናልባት በገንዘብ በብሔርተኝነት ተታለው ይህን ዝግጅት የሰሩ ያስተላለፉ የለም እያልኩኝ አይድለም:: ፓሊስ የያዘው ምርመራ ሲያልቅ አብረን የምናየው ይሆናል::

እንደ ሃገር ግን ሊደርስብን ከነበረው ትልቅ እልቂት ኢቢኤስም ቢሆን ተገቢውን ቅጣት ማግኘት አለበት ብዬ አምናለሁ:: አንዳንዶች ባለቤቶቹ ኤርትራዊ ናቸው ሻቢያ ናቸው የምትሉት ነገር ትክክል አይደለም:: ኢቢኤስ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በልማትም ተቋማትንን በመርዳትና በጎ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት ለብዙ አመታት የቆየ ተቋም ነውና ይህን የማይሆን አስተያየታችሁን እንድታቆሙ እጠይቃለሁ::

በተረፈ ኢቢኤስ ከዚህ በኃላ አሁን ከተፈጠረው ስህተት ትምህርት ተምሮ ብዙ ነገሮችን ያስተካክላል ብዬ እምናለሁ:: ሰራተኞቹን ጨምሮ:: የኢቢኤስ ትልቅ ስህተት ለሌሎችም ትምህርት ሊሆንም ይገባል::

Показано 15 последних публикаций.