ሰማያዊ ፓርቲ ‼️
ሰማያዊ ፓርቲ ከኢዴፓ፣ አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ እና ከቀድሞው አንድነት ፓርቲዎች ጋር ለመዋሃድ መስማማቱ ተገለፀ።
ሰማያዊ ፓርቲ በዛሬው ዕለት ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ከሶስቱ ፓርቲዎች ጋር ለመዋሃድ በሙሉ ድምፅ መወሰኑን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ የሽዋስ አሰፋ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
"ትልቅ አገራዊ ፓርቲ ለኢትዮጵያ አንድነት" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ የኢህአዴግ፣ አርበኞች ግንቦት ሰባት፣ ኢዴፓ፣ መድረክ፣ አረና፣ የቀድሞው አንድነት እና ሌሎች ፓርቲዎች ተወካዮች በክብር እንግድነት መታደማቸው ተገልጿል።
ፓርቲው በጠቅላላ ጉባኤው ከሶስቱ ፓርቲዎች ጋር ብቻ ሳይሆን ከሌሎች በአላማ ከሚመሳሰሉ ፓርቲዎች ጋር ተዋህዶ ትልቅ አገራዊ ፓርቲ ለመመስረት መወሰኑን ሊቀመንበሩ ተናግረዋል።
በቀጣይም ሰማያዊ፣ ኢዴፓ፣ አርበኞች ግንቦት ሰባት እና የቀድሞው አንድነት ከወረዳ ጀምሮ መዋሃድ የሚጀምሩ መሆኑ ነው የተገለፀው።
የአራቱ ፓርቲዎች ጥምር አገራዊ ፓርቲም በአዲስ ስያሜ እስከ መጋቢት 30 ይፋ የሚደረግ መሆኑን ጠቁመዋል።
ሰማያዊ ፓርቲ በጠቅላላ ጉባኤው ባሳለፈው ውሳኔ እና በቀጣይ ስራዎቹ ዙሪያ ነገ መግለጫ የሚሠጥ መሆኑን አቶ የሽዋስ ተናግረዋል።
ምንጭ:- ፋና
@News_24Hour