Nuiman Edris Official


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана



Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: 𝑛𝑢𝑖𝑚𝑎𝑛
ኸሚስ ምሽት

'የሸህ ሁሴን ትንቢት እና የኑዕማን ትቢት'
(ኑዕማን ኢድሪስ)

ከእለታት በአንዱ ቀን አመለሰት ሙጬ ድል ባለ ሰርግ ተሞሸረች። ሃገር ጉድ ብሎ ተነጋገረ። 'ሰይፉን ትታ እንዴት ቴዲን አገባች?' ተብሎ ተወራ።

በዉጭ ሰዉ ወሬ የተነሳ አብይ አህመድ ማለቴ ቴዲ አፍሮ😜 በሰይፉ ላይ ቂም ያዘበት። የጦፈ ጸብ ዉስጥ ገቡ። ቴዲም ሚስቴን አድርጋሃታል፤ ማዕድኗን ዘርፈሃታል፤ ፍትሃዊ አልነበርክም፤ ስልጣኑን ለኔ መልቀቅ አለብህ፤ ሰሜን እዝን አጥቅታሃል  በሚል በሰይፉ ላይ ይዘምትበታል።

ሰይፉም የዋዛ ስላልነበር። ጠጉር አልባ ጭንቅላቱን በትክክል ባለማሰራቱ ከመደራደርና ከመወያየት ይልቅ ወደ ጦርነት ይገባሉ። ሁለቱም ሰራዊቶቻቸዉን አሰማርተዉ አመለሰት በተባለ ቦታ ላይ ይገጥማሉ።

ጦርነቱ ለአመታት ዘለቀ። ከሁለቱም ወገን ብዙ ወታደሮች አለቁ። በዚህ መሃል አክቲቪስቶች (ነገር ጎሳሚዎች) 'የሸህ ሁሴን ጅብሪል ትንቢት  ሰይፉ ወሎ ላይ ይሞታል' ቢሉም ሰይፉ ግን ያለዉን ሃይል ተጠቅሞ ደብረ ብርሃን ማለቴ አንሶላ እስከመጋፈፍ ደርሷል ይባላል😜

በስተመጨረሻም ድርድር አካሂደዉ ሰይፉ (ህወሃት) ትጥቁን ፈቶ ቴዲ ከአመለሰት ሶስት ልጆችን ወለደ።

እንግዲህ የዚች ሀገር ታሪክ ይህ ነዉ። ይቀጥላል...😂

የጁንታ መጥፊያዉ ወሎ ላይ ነዉ ሲሉ
ደ'ሞ ቀየር አርገዉ በራያ ሲምሉ
አብይን ደግፈዉ ሰሜኑን ሲያጥላሉ
እኚህ ዩቱዩበር፤
እኚህ አክቲቪስቶች፤
ይህን የዋህ ህዝብ ገንዘቡን ቀፈሉ😂

ቀፋይ ሁላ ..😂


Репост из: 𝑛𝑢𝑖𝑚𝑎𝑛
'ሽማግሌ ስሆን'
(ኑዕማን ኢድሪስ)

እቴ...
ላገባሽ አስቤ
ሽማግሌ ብለክ

እነዚያ አዛዉንቶች
ቆንጅናሽን አይተዉ
አሉብሽ ልክክ

ድሮም ሽማግሌ
ገንዘብም ስላላቸዉ
በስሜት የጋሉ

ወጣት ቆንጆ ሲያዩ
ቀና ያለች ሲያዩ
ምርኩዝ ያደርጋሉ

እኔ ሚስኪን ወጣት
ወይ ገንዘብ የለኝ

ሽማግሌ ስሆን
ፍሉሱን ስይዘዉ
ልምጣ መሰለኝ 😭


Репост из: 𝑛𝑢𝑖𝑚𝑎𝑛
ኸሚስ ምሽት 5
(ኑዕማን ኢድሪስ)

ሰዎቹ ይላሉ፤
በኸሚስ ምሽቱ
'ቡናሽ ጣዕም አለዉ'

ቄጤማዉ ጉዝጓዙ፤
እጣኑ አድሩስሽም
ለአፍንጫ ቀለብ ነዉ

እኔ ሚስኪን ኑዕማን
አንቺን የቀመስኩት
እንደምን ልሁነዉ?

ቴሌግራም ● telegram.me/Nuiman_9


Репост из: 𝑛𝑢𝑖𝑚𝑎𝑛
'መዉሊዱ'
ኸሚስ ምሽት 4
(ኑዕማን ኢድሪስ)


ለመዉሊዱ ደስታ ከቤት ስትወጪ
ባለሽ ነገር ሁሉ ፈኪበት አጊጪ

ግን...
በአረንጓዴዉ ሻልሽ
እንዳያይሽ ባልሽ

ምክንያቱም ዉዴ
የጨረቃን ዉበት፤ እጅጉን በልጠሻል
ከጧት ፀሐይ በላይ ይበልጥ ፈክተሻል

ቁንጅናሽን አይቶ መለየት ይሳሳል
እቅፉ ዉስጥ አ'ርጎሽ የልቡን ያደርሳል
ተያማ በኃላ... መዉሊዱ ይረሳል 😂
--
🙄 መዉሊድ ቢድዓ ነዉዴ 😜

👌 በቴሌግራም - telegram.me/Nuiman_9


Репост из: 𝑛𝑢𝑖𝑚𝑎𝑛
(4)

ሚስቴ በየቀኑ ለሥራ ከቤት ስወጣ የረሳሁትን ነገር ታስታዉሰኛለች። አንዳንዴ የመኪና ቁልፍ፣ ሌላ ጊዜ መነጽር፣ አንዳንዴም ሞባይል፣ እንዲሁም ሌላ ነገር መርሳት ልማዴ ነው።
"አሁንማ አረጀህ" እኮ አበቃህ ወይኔ ባሌ!" እያለች እየሳቀችብኝ ታቀብለኛለች የረሳሁትን።

ተረቧን ለማስቀረት የሆነ ዘዴ ዘየድኩ። የምረሳቸዉን ነገር በወረቀት ላይ መዝግቤ ያዝኩ። የሆነ ቀን ጠዋት ከመውጣቴ በፊት ወረቀቴን አውጥቼ ሁሉንም መያዜን አረጋገጥኩ።

ከዚያም በድል አድራጊነት ስሜት መኪናዬ ዉስጥ ገብቼ ሞተር አስነስቼ ግቢዬን ለቅቄ ወጣሁ።
ትንሽ እንደነዳሁ ደወለች። ባለቤቴ። ክው አልኩ፣ ዛሬ ደግሞ ምን ረሳሁ ብዬ ...
"ሄሎ" አልኳት።
" ዛሬ ደግሞ የት እየሄድክ ነው?" አለችኝ።
"ሥራ ነዋ"
" እሁድ እኮ ነው፣ የምን ሥራ!።"
ትንሽ ቆሜ ፈገግ እያልኩ ወደቤት ተመለስኩ።

የሰው ልጅ ጎዶሎ ነው የተሟላ አይደለም፣ ፍፁምነት ለአላህ ብቻ ነው።
ባልና ሚስት፣ ወንድና ሴት ... በሀሳብም በአካልም እንዲሞላሉ ተደርገው ነው ጀሊሉ የፈጠራቸው። አንዱ የጎደለው ሌላው አለው። አንዱ የማይችለዉን ሌላው ይችለዋል ፣ ለአንዱ የማይታየው ለሌላው ይታየዋል።

ለመናናቅ፣ ለመገፋፋትና ለመለካካት ሳይሆን ዱንያን አብረን እንድንኖር፣ ፈተናዎቿንም አብረን እያሸነፍን ወደ ጀነት እንድንጓዝ ነው አላህ ወደዚህች ምድር ያመጣን።

አራተኛው ህግ
አንዱ የሌላኛዉን ሀሳብ ጆሮ ሰጥቶ ያድምጥ፣ አይናናቅ፣ አያጣጥል።

👌 telegram.me/Nuiman_9


Репост из: 𝑛𝑢𝑖𝑚𝑎𝑛
'ዳዒም ተፈቀርኩ'
(ኑዕማን ኢድሪስ)

የኔ ነቢ፤ የኔ ራህመት
አደረሰኝ አመት ካ'መት

የኔ ረሱል፤ ሸፈዓዬ
ድርብ ሆነ ያ ደስታዬ

የኔ ሀቢቢ፤ ያ ሙስጠፋ
ሽርኩ ሁሉ ባንቱ ጠፋ

ባንቱ'ኮ ነዉ ሰዉ የሆንኩት
የኔን ጌታ አላህዬን ያመለኩት

ባንቱ'ኮ ነዉ ፤ ሴቱ ወንዱ
ለጀሊሉ ዳኢም መስገዱ

ያ ኻሊቅ...
የኔ አምላክ አላህ፤
ምንኛ ወዶኛል

የኑህን የሙሳን የሉጥን የኢሳን፤
የነሱን ጊዜ አልፎ ኡመቶ እንድሆን ከኃላሁ ፈጥሮኛል

ምንኛ እድለኛ ፤ ጀሊሉ አድርጎኛል
በወዱ ነቢ ልብ እኔን አስናፍቆኛል

ሀቢቢ...
እኛን ናፍቀሁ አንቱ፤ አፈር እንደጫርኩ
ይሄዉ በኔ ልብም፤ ዳኢም ተፈቀርኩ !

⭐️ በቴሌግራም - telegram.me/Nuiman_9




Репост из: 𝑛𝑢𝑖𝑚𝑎𝑛
ኸሚስ ምሽት 3

ዛሬ 3 ሰአት

Follow me @Nuiman_9


Репост из: 𝑛𝑢𝑖𝑚𝑎𝑛
ኸሚስ ምሽት 3
(ኑዕማን ኢድሪስ)

አንቺዬ...
ከቤትሽ ብመጣ
ምሽቱ አሸብርቋል
ቄጤማዉ ጉዝጓዙ
በጭሳጭስ ደምቋል

ከረከቦትሽ ስር
በሂጃብ ተዉበሽ
ዚክሩ ሶለዋቱ
በሃይባ ተከበሽ

ኸሚሱ አጅቦኛል
ዉበትሽ ማርኮኛል
ይዣለሁ ማብሰልሰል

ሰዉን መላዕክቱን
እንዲህ ያማለልሽዉ
ወሎዬ ነሽ መሰል

አጀብ አጀብ
👁 በቴሌግራም ፦ telegram.me/Nuiman_9


Репост из: 𝑛𝑢𝑖𝑚𝑎𝑛
አልሐምዱሊላህ

@Nuiman_9

Join


Репост из: 𝑛𝑢𝑖𝑚𝑎𝑛
የወሎዬ ዉበት
(ኑዕማን ኢድሪስ)

ቡና ልጠጣ ከተቀመጥኩበት በረንዳ ላይ የተሰባሰቡ ሰዎች በክርክር ተጠምደዋል። የክርክራቸዉ መነሻ ሁለት ሴቶች በመንገድ ሲያልፉ ተመልክተዋል። ጸጉራ ላይ ሻሽ ጣል ያደረገቸዉ ሴት ዉበቷ የሁሉንም ወንድ ልብ ፈትኗል። አብራት ያለችዉ ሴት ግን ጸጉሯን አንጨባራ፤ በሱሪ ተወጥራ፤ በመነጽር ለመጉላት ብትሞክርም አዲሱ የንግድ ባንክ ህንጻ ስር እንደሚገኝ ሳር ቤት ኩስስ ብላ ታየቻቸዉ።

ሁለቱም ወሎዬ ሆነዉ እንዴት በዉበት ይቺኛዋ በለጠች በማለት ሁሉም የየራሱን ሀሳብ ይሰነዝራል።

እንደኔ ራቅ ብለዉ ዉይይታቸዉን የሚያደምጡ አባት "በወሬያችሁ ገባሁ መሰል ብለዉ..." ንግግራቸዉን ቀጠሉ። ሁሉም ወደሳቸዉ ዙሪዉ ምን እንደሚሉ ለማዳመጥ ትኩረት ሰጧቸዉ። "... ወሎ የዉበት ምንጭ፤ የቆንጆ መፍለቂያ ሀገር ናት። አርጎባዉ፤ ኦሮሞዉ፤ ሶዶማዉ ተደማምሮ ወሎዬ ነዉ። ታዲያ ሴቶቻችን በሄዱበት ሀገር ሁሉ የወንድን ልብ ከፍተዉ እንዲገቡ ዉበትንና ገራገርነትን አብዝቶ አድሏቸዋል። ሴቶች በተሰበሰቡበት ቦታ ላይ ወሎዬዋ ከሁሉም ደምቃና አሸብርቃ ትታያለች። ምክንያቱም ወሎዬ ናታ..." አሉ። እኔን ጨምሮ በበዙሪያችን ያሉ ሰዎች በሽማግሌዉ ሰዉ ንግግር ተስበናል። ማሳረጊያቸዉ ምን ይሆን ብለን ጓጉተናል። "... እና ልጆቼ የወሎ ሴቶች ከሁሉም ይበልጥ ተዉበዉ የመታየታቸዉ ሚስጥር 'ሂጃባቸዉ' ነዉ።..." አሉ። ሁላችንም ተደነቅን። ያላስተዋልነዉ ነገር ነበር።

ዙሪያ ገባዉን ቃኝተዉ እየሰማናቸዉ እንደሆነ ሲያዉቁ ንግግራቸዉን ቀጠሉ "... ሂጃብ ዉበት ነዉ። ጸጉሯ ላይ ሻሿን ጣል ስታደርግ ፀሃዩ ላይ ጨለማን ጥሎበት አለምን በዉበት እንደምታስገርመዉ ጨረቃ ደምቃ ትታያለች። ሃያማኖቷ ደግሞ ክብሯን ይጨምርላታል፤ ቁጥብ ያደርጋታል። እና ልጆቼ የሴቶቻችን ዉበት ሚስጥር ሂጃባቸዉ ነዉ። ይሄን ደግሞ አሁን አብረዉ ካለፉት ሴቶች አረጋግጣችኃል።" ብለዉ ንግግራቸዉን ቋጩ።

Telegram.me/Nuiman_9

Photo - ከዚሁ መንደር


Репост из: 𝑛𝑢𝑖𝑚𝑎𝑛
ወሎየዋ
(ኑዕማን ኢድሪስ)

አላህዬ አላህዋ
ማርካኛለች ወሎየዋ

ስጠኝና አሳርፈኝ
ሸህዋዉ ነዉ በኢባዳ ያሰነፈኝ 😜


Репост из: 𝑛𝑢𝑖𝑚𝑎𝑛
ጀቢኝ
ኸሚስ ምሽት 2
(ኑዕማን ኢድሪስ)

በሂጃብ ተዉበሽ
ቡናዉን አፍልተሽ
ምሽቱን አድመቀሽ

ስትይ አወል ጀባ
እንደዉ ሆዴ ባባ

ከቡናዉ  በኃላ አንቺን ብጀቢኝ
ለጀሊሉ ሱጁድ አሁን ባረኩኝ

በይነል ፈኺዘይን ኒዕማዉን ይዘሽ
ሀላሌ አድርጌሽ ጀቢኝ እባክሽ

@Nuiman_9


Репост из: 𝑛𝑢𝑖𝑚𝑎𝑛
ኸሚስ ምሽት
- ተቀበይ
(ኑዕማን ኢድሪስ)

በሶለዋት ደምቆ
በዚክር አሸብርቆ

ቡናዉን አፍልተሽ
ነዱን አጫጭሰሽ
ስትይ አወል ጀባ

ቀና ብዬ ባይሽ
እስከ'ነ ሂጃብሽ
ከፊቴ ቁመሻል

ምርቃቱ ጠፋኝ
ጀሊሉ በቁድራዉ
ልቤን ጀብቶሻል

@Nuiman_9










Репост из: Nuiman View ኑዕማን
በጣም ተወዳጅ ነሽዳ 👉 ሊንኩን ተጭነዉ ይመልከቱ👉 https://youtu.be/7Uf8GVfBg8k



Показано 20 последних публикаций.

1 438

подписчиков
Статистика канала