ላንቺ ብቻ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ይሄ #Telegram channel የሚያገለግለው ለሴቶች ብቻ ነው
#ማንኛውንም ጉዳይ ይዳስሳል
#ይመክራል
#ያማክራል
#መረጃ ይሰጣል
#ለሴቶች አስፈላጊውን መረጃ ይሰጣል ተቀላቀሉን ይማሩበል
#ሀሳብ_አስተያየት ካለሽ
@onlygirlsb

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


በጣም በተደጋጋሚ በመልእክት የምጠነቀው ጥያቄ መጥፎ የአፍ ጠረን አለብኝ ምን ባደርግ ይሻለኛል የሚለውን ነው ይኸው ሙሉ መረጃ ይዤላችሁ መጥቻለው

መጥፎ የአፍ ጠረን የአለማችንን 25% የሚሆን ማህበረሰብ ያጠቃል። ለችግሩ ብዙ መነሻ ምክንያቶች ቢኖሩም አብዛኛውን ግዜ መነሻው ከአፋችን ነው።

ስለ መጥፎ የአፎ ጠረን (ሐሊቶሲስ/ halitosis) እውነታዎች

-መጥፎ የአፍ ጠረን ከ4 ሰዎች በአንዱ ላይ ይከሰታል
-አብዛኛው መነሻ ምክንያቱ የጥርስ እና የአፋችንን ንፅህና (oral hygiene) በደንብ ባለመጠበቅ የሚመጣ ነው።

-የበላነው ምግብ አፋችን ውስጥ ይቀእና ሰልፈር ወደሚባለው ንጥረ ነገር በባክቴሪያ ምክንያት ተከፋፍሎ መጥፍ የአፍ ጠረን ያመጣል
-ዋናው በቤት ውስጥ ማድረግ የምንችለው ህክምናም ጥርሳችንን ማፅዳት፣ ፍሎስ ማድረግ እና በቂ የሆነ ውሀ መጠጣት ናቸው።

መጥፎ የአፍ ጠረን (halitosis) ምንድን ነው?

መጥፎ የአፍ ጠረን በጣም የተለመደ እና በራስ መተማመንን የሚቀንስ በሽታ ነው። በጣም ብዙ መነሻ ምክንያቶች እና መፍትሄዎችም አሉት። ማንኛውም ሰው መጥፎ የአፍ ጠረን ሊያጋጥመው ይችላል። ከ4 አንድ ሰው ላይም ያጋጥማል። ወደ ጥርስ ሀኪም ከሚያስኬዱ መነሻ ምክንያቶችም 3ኛ ነው። ከጥርስ መቦርቦር እና ከድድ ችግር ቀጥሎ

አንዳንድ በቤት ውስጥ ልናደርጋቸው የምንችላቸው ነገሮች ለምሳሌ ጥርሳችንን እና አፋችንን ማፅዳት ፣ ሲጋራ ማጨስ እንዲሁም ጫት መቃም ማቆም ችግሩን እስከነአካቴው ያቆሙልናል ይህ ሳይሆን ከቀረ ግን ወደ ጥርስ ሀኪም መሄድ ያስፈልጋል።

ህክምናው

- ለመጥፎ የአፍ ጠረን ዋናው ህክምና ጥሩ የሆነ የጥርስ እና የአፍ ማፅዳት ልማድን (good oral hygiene) ማዳበር ነው። ተያይዞም ጥርሳችን እንዳይቦረቦር እና ድዳችን እንዳይጎዳ ይረዳናል።

- በአመት ቢቻል አንድ ግዜ የጥርስ ቼክ አፕ ማድረግ

- የጥርስ ሀኪምዎ ባክቴሪያን የሚቀንሱ መጉመጥመጫዎች ሊያዝሎት ይችላል እንዲሁም የጥርስ እጥበት እንዲያደርጉ ሊመክሮት ይችላል።

መነሻ ምክንያቶች

- ሲጋራ
- ምግብ ፦ የበላነው ምግብ ጥርሳችን ላይ ተጣብቆ መጥፎ የአፍ ጠረን ሊያመጣብን ይችላል። በተለይ ቀይ እና ነጭ ሽንኩርት ከተፈጨ በኋላ እንኳን በደም ስራችን አልፎ ወደ ሳንባችን ደርሶ ስንተነፍስ ሊሸት ይችላል።

- ደረቅ አፍ (dry mouth)፦ በተፈጥሮ ምራቃችን አፋችንን ያጥብልናል። አፋችንን ደረቅ ከሆነ ግን መጥፎ የአፍ ጠረን ይከሰታል።

- ጥርሳችንን እና አፋችንን የማፅዳት ልማድ፦ ጥርሳችንን በምንቦርሽበት እና ፍሎስ በምናደርግበት ግዜ አፋችን ውስጥ ያለው ምግብ ተፀድቶ ይወጣል ካልወጣ ግን በባክቴሪያዎች አማካኝነት ተከፋፍሎ ችግሩ እንዲከሰት ያደርጋል።

- የምግብ ሰዓትን ጠብቆ አለመብላት፦ መፆም እና ካርቦሀይድሬት ያነሳቸውን ምግቦችን መመገብ መጥፎ የአፍ ጠረን እንዲኖረን ያደርጋል ምክንያቱ ደግሞ ሰውነታችን ያጠራቀመውን ስብሰባብሮ ሲጠቀም ኬቶን (ketones) የሚባል ኬሚካል ያመነጫል ይህም ከፍተኛ ሽታ የመጣል።

- መድሀኒቶች፦ አንዳንድ መድሀኒቶች አፋችን እንዲደርቅ ያደርጋሉ ሌሎች ደግሞ ሲሰባበሩ የራሳቸው የሆነ ሽታ ይፈጥራሉ።

- የአፍ የአፍንጫና የጉሮሮ ችግር፦ አንዳንድ ግዜ ትንንሽ ባክቴሪያዎች ከቶንሲላችን ጀርባ እንደ ድንጋይ ተሰባስበው ይገኙና መጥፎ ጠረን ይፈጥራሉ። በተጨማሪም የአፍንጫ የጉሮሮ ወይም የሳይነስ ኢንፌክሽን እና መቆጣት የአፍ ጠረን ሊያመጣ ይችላል።

- የውስጥ በሽታ፦ አንዳንድ ካንሰር ፣ የጉበት ስራ ማቆም (liver failure) እና ሌሎች ከምግብ መፈጨት ጋር የተገናኙ በሽታዎች የአፍ ጠረን ሊያመጡ ይችላሉ ምክንያቱ ደግሞ የሚፈጥሩት ኬሚካሎች ናቸው። እንዲሁም የጨጓራ ህመም Gastroesophageal Reflux Disease (GERD) በሚለቀው የጨጓራ አሲድ ምክንያት መነሻ ሊሆን ይችላል።

ከስንት አንድ መነሻ ምክንያቶች

አብዛኛው መጥፎ የአፍ ጠረን መነሻ ምክንያት የአፋችንን ንፅህና በደንብ አለመጠበቅ ቢሆንም ሌሎች መነሻ ምክንያቶች ሊኖሩት ይችላሉ።

1- Ketoacidosis (ኬቶአሲዶሲስ)፦ አንድ ስኳር ህመም ያለበት ሰው ኢንሱሊኑ ዝቅ ሲል ሰውነታቸው ውስጥ ያለውን ስኳር መጠቀም ያቆምና የተጠራቀመውን ስብ ይጠቀማል። ስቡም ሲሰባበር ኬቶን (ketones) ይመረታል ይህም ሲበዛ መጥፎ የአፍ ጠረን ያመጣል እንዲሁም ለህይወት አስጊ የሆነ ጉዳይ ነው።

2- Bowl obstruction (የአንጀት መደፈን)፦ ትንፋሻቸው ሰገራ ሰገራ ሊል ይችላል በተለይ በተደጋጋሚ ማስመለስ ካለ እና የአንጀት መደፈን ካለ።

3- Bronchiectasis (ብሮንካይተስ)፦ የአየር ቧንቧችን ለረጅም ግዜ ኢንፌክሽን ካጋጠመው ሊሰፋና ሙከስ ተጠራቅሞ ለመጥፎ የአፍ ጠረን ሊዳርገን ይችላል።

ምልክቶች

×የአፍ ጠረን ሽታው እንደመነሻ ምክንያቱ ይለያያል። እርግጠኛ ለመሆኖ ጥሩ የሚሆነው ጓደኛችንን ወይም ቅርብ የምንለውን ሰው መጠየቅ ነው ምክንያቱም በራሳችን ለማወቅ እና እርግገኛ ለመሆን ከባድ ስለሆነ።

× ማንም ሰው አጠገባችን ከሌለ በእጃችን በደንብ ተንፍሰን ደረቅ እስኪል ጠብቀን ማሽተት ነው።

× አንዳንድ ሰዎች ግን ምንም አይነት መጥፎ የአፍ ጠረን ሳይኖርባቸው እንዳለባቸው ይሰማቸዋል ይህም halitophobia (ሀሊቶፎቢያ) ይባላል ይህም በከፍተኛ ሁኔታ ጥርሳቸውን የሚያፀዱ ሰዎች እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል።

እቤት ውስጥ ምን እናድርግ?

፩- ጥርሳችንን ማፅዳት፦ በቀን ቢያንስ 2 ግዜ ለ2 ደቂቃ ተገቢ በሆነ ሁኔታ ጥርሳችንን ማፅዳት

፪- ፍሎስ ማድረግ፦ ፍሎስ ማድረግ በጥርሶቻችን መሀከል የሚጠራቀመውን ምግብ እና ፕላክ ያወጣልናል። በብሩሽ ስናፀዳ የምናገኘው 60% የሚሆነውን የጥርሳችንን ክፍል ነው።

፫- ወጪ ገቢ ጥርስ ፣ አርቴፊሻል፣ ማውዝ ጋርድ፣ ሪቴነር ካለን በየእለቱ ማፅዳት

፬- የጥርስ ብሩሻችንን በየ3 ወሩ መቀየር

፭- ስስ(soft) የጥርስ ብሩሽ መጠቀም

፮- ምላሳችንን ማፅዳት፦ ምላሳችንን ሳሙና በሌለው ብሩሽ በአፍንጫችን እየተነፈስን ማፅዳት ለራሱም የተዘጋጀውን ማፅጃ ካገኘን መጠቀም በተለይ ደግሞ ሲጋራ የሚያጨሱ ፣ ጫት የሚቅሙ እና የአፍ መድረቅ ችግር ያለባቸው ሰዎች ምላስን በደንብ ማፅዳት ያስፈልጋል።

፯- አፋችን እንዳይደርቅ ማድረግ፦ ውሀ በተገቢው መንገድ በደንብ መጠጣት። የአልኮል መጠጥ ሲጋራ እና ጫት ማስወገድ ምክንያቱምየአፍ መድረቅ ስለሚያመጡ። ማስቲካ ማላመጥም ምራቅ እንዲመረት ስለሚረዳ ይመከራል ከተገኘ ስኳር የሌለው።

፰- አመጋገብ፦ ቀይ ሽንኩርት ነጭ ሽንኩርት እና ቅመም የበዛባቸውን ምግቦች ማስወገድ። ጣፋጭ ምግቦችም ከመጥፎ የአፍ ጠረን ጋር ይያያዛሉ። ቡና እና የአልኮል መጠጦችን መቀነስ። ቁርስ ላይ ጠንከር ያለ ምግብ መመገብ የምላሳችን ጀርባ እንዲያፀዳ ይረዳዋል።

ምርመራ

አብዛኛውን ግዜ መጥፎ የአፍ ጠረን አለብኝ ብሎ የመጣን ታካሚ በማሽተት እና ከምላስ ጀርባ ፍቆ በማሽተት ሊታወቅ ይችላል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ሌሎች የተወሳሰቡ ምርመራዎች አሉ።
የጥርስ ሐኪማችን የመጥፎ አፍ ጠረን መነሻ ምክንያቱን ያገኝልናል። መፍትሄም ይኖረዋል።

አብዛኛውን ግዜ መጥፎ የአፍ ጠረን ከተከሰተብን በኋላ ከላይ ያሉትን ነጥቦች ከተከተልን በቤት ውስጥ ጥንቃቄ ራሱ የሚጠፋ ይሆናል ይህ ካልሆነም የጥርስ ሐኪሞን ማማከር ያስፈልጋል።


አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዱቄት አንድ ማንኪያ የእኸሊ ቅጠል ከአንድ ስኒ ንጹሕ ማር ጋር ለውሶ በባዶ ሆድ መብላት፡፡

30ኛ. ለሽንት መታቀብ ችግር

ከእምብርት በታች ያለውን የሰውነት አካል በጥቁር አዝሙድ ቅባት ከመኝታ በፊት ማሸት፡፡ አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በአንድ ኩባያ ውኃ አፍልቶ በማር አጣፍጦ ከመኝታ በፊት በእለቱ መጠጣት፡፡

31ኛ. ፊት ላይ እንደ ቡጉር ክብ ሆኖ ለሚወጣ አተርን ያክል ጠጣር ነገር (WATER)

በሽታ በሽታው የሰፈረበትን አካባቢ በረጅላ (Purslane) ተክል በሚገባ ማሸት ከዚያም የጥቁር አዝሙድ ዘይት 15 ቀናት መቀባት በቀን ሦስት ጊዜ አንድ አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት መጠጣት፡፡

32ኛ. ለሚያስነጥስ

ከባሕር ዛፍ የተጨመቀ ዘይት 40% ከጥቁር አዝሙድ ዘይት ጋር ደባልቆ በሁለቱም አፍንጫ በቀን ሦስት አራት ጊዜ ጠብታ ማድረግ ነው፡፡


የጥቁር አዝሙድ : የጤና በረከቶች

1ኛ. ለእርጋታ

አንድ የሾርባ ማንኪያ ትክክለኛውን የጥቁር አዝሙድ ዘይት በባዶ ሆድ መውሰድ ቀኑን ሙሉ መረጋጋትና ንቃት ያጎናጽፋል፡፡ እንዲሁም ከራት በኋላ ወደ መኝታ ከማምራት በፊት አንድ የሾርባ ማንኪያ ትክክለኛውን የጥቁር አዝሙድ ዘይት መውሰድ ለሊቱን ሙሉ የተረጋጋና ደስ የሚያሰኝ እንቅልፍ ያስገኛል፡፡

አንድ ትልቅ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ሲኒ ቡና ውስጥ ጨምሮ መጠጣት፡፡ የአእምሮ ጭንቀትን አስወግዶ መረጋጋትን ያስገኛል፡፡

2ኛ. ለሳልና ለአስም

በዘይቱ ደረትንና ጀርባን ማሸት በቀን ሦስት የሾርባ ማንኪያ መጠጣት፣ ሁለት ማንኪያ በሙቅ ውኃ ውስጥ ጨምሮ እንፋሎቱን መሳብ ይረዳል፡፡

3ኛ. የመጫጫንና ስንፍናን ለማስወገድ

አንድ የሾርባ ማንኪያ ዘይት በአንድ ብርጭቆ ብርቱካን ጭማቂ ውስጥ ጨምሮ ጧት ጧት ለአሥር ተከታታይ ቀናት መውሰድ ልዩነቱን ያገኙታል፡፡

4ኛ. የማስታወስ ችሎታንና ፈጣን የግንዛቤ አቅምን ለማጎልበት

አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት፣ 100 ሚሊ ሊትር የፈላ ናእናእ (Nena) ተክል ጋር ተቀላቅሎ ለአሥር ተከታታይ ቀናት መውሰድ፡፡

5ኛ. ለኩላሊ ትጠጠር (የስኳር ሕመም ያለባቸው ማርን መተው ነው)

ሩብ ኪሎ ጥሬ ጥቁር አዝሙድ፣ ሩብ ኪሎ ንጹሕ ማር ማዘጋጀት፡፡ ጥቁር አዝሙድን በሚገባ መፍጨትና ከማር ጋር ቀይጦ በሚገባ ማዋሀድ፡፡ ከዚያም ሁለት ማንኪያ ከቅይጡ ቀንሶ በአንድ ብርጭቆ የሞቀ ውኃ ውስጥ ጨምሮ በጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ሻይ ማንኪያ በማከል በባዶ ሆድ መጠጣት፡፡

6ኛ. ለብሩሕ ገጽና ለውበት

አንድ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ማንኪያ የወይራ ዘይት ጋር አዋሕዶ ፊትን መቀባት አንድ ሰዓት ቆይቶ በውኃና በሳሙና መታጠብ ልዩነቱን በጉልህ ያገኙታል፡፡

7ኛ. ከበሽታ ሁሉ ለመጠበቅ

አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከአንድ ማንኪያ ማር ጋር አዋሕዶ ያለማቋረጥ ጧት ጧት መውሰድ በሕይወት ዘመንዎ ሙሉ ጤነኛና የሐኪም እርዳታ የማያሻው ሰው ይወጣዎታል፡፡

8ኛ. በጭንና ጭን መካከል የቆዳ መቆጣት ሲያጋጥም

በቅድሚያ አካባቢውን በውኃና በሳሙና በሚገባ ማጠብ፣ ቀጥሎ በሚገባ ማድረቅና በጥቁር አዝሙድ ዘይት ማታ ቀብቶ ማደርና ለሦስት ተከታታይ ቀናት ይህንኑ መፈጸም፡፡ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ውጤቱን ያዩታል፡፡

9ኛ. ለልብና ለደም ሥሮች ሕመም

የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከትኩስ መጠጥ ጋር በተከታታይ መውሰድ ስብን ለማሟሟትና የደም ሥሮችን ለማስፋት ይረዳል፡፡

10ኛ. ለለምጽና ለመሳሰሉት

ተጠቂውን የሰውነት ክፍል በቱፋሕ (ፖም) ወይም አፕል ኮምጣጤ ማሸት ከዚያም የጥቁር አዝሙድ ዘይት ለ15 ቀናት መቀባት፡፡

11ኛ. ለቁርጥማት ፣ ሮማቲዝምና የጀርባ ሕመም

የተወሰነ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በጥቂቱ በማሞቅ የታመመውን አካል አጥንትን ዘልቆ እስኪሰማ ድረስ በዘይቱ በደንብ መታሸት በቀን ሦስት ጊዜ አንድ የሾርባ ማንኪያ ዘይት መጠጣት፡፡

12ኛ. ለራስምታት

በጥቁር አዝሙድ ዘይት ግንባርንና በጆሮ አካባቢ ያለውን አካል ማሸት ለሦስት ተከታታይ ቀናት አንድ ሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በባዶ ሆድ መጠጣት፡፡

13ኛ. ለጨጓራና ለአሲድ

አንድ ኩባያ ወተት የአንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በቀን ሦስት ጊዜ መውሰድ፡፡ ከሦስት ቀናት በኋላ በሽታው ሙሉ በሙሉ ይወገዳል፡፡

14ኛ. ለራስ ማዞርና ለጆሮ ሕመም

አንድ ጠብታ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ጆሮ ውስጥ መጨመር በሻይ መልክ አዘጋጅቶ መጠጣት፡፡

15ኛ. ለቆዳ መቀረፍ

በዚህ አይነቱ ሕመም የተጠቃው የአካል ክፍል በጥቁር አዝሙድ ዘይት መቀባት ሕመሙ እስኪወገድ ድረስ ይህንኑ መቀጠል፡፡

16ኛ. ለቡግር

ጥቁር አዝሙድ አድቅቆ መፍጨት የሰሊጥ ዘይትና አንድ ማንኪያ የስንዴ ዱቄት ጨምሮ በአንድነት መለወስ ማታ ማታ ተቀብቶ ማደርና ጠዋት ለብ ባለ ውኃና በሳሙና መታጠብ፡፡

17ኛ. ለስብራት አፋጣኝ ጥገና

የምስርና የሽንኩርት ሾርባ፣ ቅቅል እንቁላል፣ አንድ ትልቅ ማንኪያ የደቀቀ ጥቁር አዝሙድ በአንድነት ቀላቅሎ ቢያንስ አንድ ቀን ወስዶ በቀጣዩ ቀን አርፎ እንደገና በሁለተኛው ቀን መውሰድ፤ ስብራቱ የዘመናዊ ሕክምና በጀሶ ከታሰረ በኋላ በአቅራቢያ ያለውን አካል በጥቁር አዝሙድ ዘይት ማሸት፤ እስሩ ከተፈታ በኋላ ደግሞ ለብ ባለ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በየቀኑ ማሸት ነው፡፡

18ኛ. ለጠባሳና ለመሳሰሉት

አንድ እፍኝ ጥቁር አዝሙድ በሚገባ ማፍላት የተጎዳውን አካል ማጠብና ለሩብ ሰዓት በተዘጋጀው ፍል ጥቁር አዝሙድ ውስጥ መንከር፡፡ አካሉን ማንቀሳቀስ፡፡ ሳይሸፈን አድካሚ እንቅስቃሴ ሳያደርጉ መቆየት፡፡ ከመኝታ በፊት በየቀኑ ይህን መደጋገም፡፡

19ኛ. ለደም ብዛት

ትኩስ መጠጥ ባሰኘው መጠን ጥቂት የጥቁር አዝሙድ ዘይት ጠብታዎችን ጨምሮ መጠጣት፡፡ በተጨማሪም ገላውን ጥቁር አዝሙድ በመቀባት ቢያንስ በየሳምንቱ አንድ ጊዜ የፀሐይ ሙቀት ቢወስዱ ምንኛ ጥሩ ነበር፡፡

20ኛ. ለኩላሊት ኢንፌክሽን

የጥቁር አዝሙድ ዱቄት በወይራ ዘይት ለውሶ ሕመም በሚሰማበት ቦታ መለጠፍ፤ በተጨማሪም አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ በየቀኑ በባዶ ሆድ ለአንድ ሳምንት ጥሬውን መቃም፣ ከዚያ በኋላ ኢንፌክሽኑ ይወገዳል፡፡

21ኛ. ለሐሞት ከረጢት

አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ፣ ሩብ ማንኪያ የተፈጨ ሬት፣ አንድ ኩባያ ማር ጋር መለወስና ጧትና ማታ መብላት፡፡ ፊትዎ ቅላት እስኪያሳይና ችግሩ እስኪወገድ ድረስ ይህንኑ መፈጸም፡፡ በየዕለቱ በባዶ ሆድ አንድ ሲኒ የወይራ ዘይት መጠጣት አይርሱ፡፡

22ኛ. ለልብና ለደም ዝውውር ችግር

የልብ ሕመምተኛ ሰው በማናቸውም ወቅት እንደ ምግብም፣ እንደመጠጥም እንደአስፈላጊነቱ መውሰድ ይኖርበታል፡፡

23ኛ. ለትውከት

ጥቁር አዝሙድ ከቅርንፉድ ጋር በደንብ ማፍላት ማጣፈጫዎች ሳይጨምሩ በቀን ሦስት ጊዜ መጠጣት፡፡ ሁለተኛ ዙር መጠጣት አያስፈልግም፡፡

24ኛ. ለቃርና ለመሳሰሉት

የተወሰኑ የጥቁር አዝሙድ ቅባት ጠብታዎች በአንድ ኩባያ ትኩስ ወተት ውስጥ ጨምሮ በማር አጣፍጦ መጠጣት፡፡ የቃር ስሜትዎ እንዳልነበር ሆኖ ይጠፋል፡፡ በእንግሊዘኛ (Lettuce) የተሰኘውን ተክል በብዛት መብላትንም አይዘንጉ፡፡

25ኛ. ለዓይን በሽታ

በጥቁር አዝሙድ ዘይት በዓይንና በጆሮ መካከል ያለውን የሰውነት አካል ከመኝታ በፊት ማሸት በማናቸውም ትኩስ መጠጥ ውስጥ አልያም የሥራ ሥር ጭማቂ እንደ ካሮት የመሳሰሉት ውስጥ ጥቂት ጠብታዎች ጨምሮ መጠጣት ነው፡፡

26ኛ. የምግብ ፍላጎትን ለማሳደግ

ከምግብ በፊት ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ አንድ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ቅመሙን በጥርሶችዎ ማድቀቅ፣ ከዚያም ጥቂት ኮምጣጤ ጠብታዎች የተቀላቀለበት አንድ ስኒ ቀዝቃዛ ውኃ ያወራርዱት፡፡

27ኛ. ለቅማልና ለቅጫም

ጥቁር አዝሙድ አድቅቆ መፍጨት በኮምጣጤ ለውሶ ለመታሻ በሚያገለግል መልኩ ማዘጋጀት ፀጉርን ተላጭቶ መቀባት አሊያም ቆዳው ድረስ ዘልቆ እንዲገባ ማድረግና ለሩብ ሰዓት ለፀሐይ ማጋለጥ፡፡ ከአምስት ሰዓታት በኋላ መታጠብ፡፡ ለአንድ ሳምንት ያህል ይህንኑ ደጋግሞ መፈጸም፡፡

28ኛ. ለጥርስ፣ለቶንስልና ለጉሮሮ ሕመም

የጥቁር አዝሙድ አፍልቶ መጉመጥመጥና ለጉሮሮ ችግር እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ አንድ ማንኪያ አዘጋጅቶ ለብ ባለ ውኃ ውስጥ ጨምሮ መጠጣትና በዘይቱም የጉሮሮን ውጫዊ አካል መቀባት በውስጥ ደግሞ መንጋጋን መቀባት፡፡

29ኛ. ከደም ላይ ኮሊስትሮን (ስብን) ለማስወገድ


#አቢጊያ_ነኝ

በመጪው የ#በጋ ወቅት መረሳት የሌለባቸው ነገሮች 🤗🤗🤗

1. ሁሌም #ውሃ መጠጣት አለብን ይሄ ቆዳ ደረቅ አንዳይሆን ይረዳዋል::ከዛም በተጨማሪ ሰውነታችንን ቶሎ ቶሎ ሎሽን መቀባት ቆዳ እንዳይደርቅ እና ነጭ እንዳይሆን ይረዳዋል እኔ እና መሰሎቼ  ምንጠቀመውን በጣም ቆንጆ  #hydrating mask እና ሎሽን  ልጠቁማችሁ
👉#perfect cosmetics peel-off mask
👉#glysolid body lotion
👉#hand cream alovera+ avocado- for your hands

2. ቆዳችን ላይ ያሉትን #dead skin ለሱ ተብለው በተዘጋጁ #scrubs ወይም ቤታችን ውስጥ በቀላሉ በሚዘጋጁ የፊት #mask  ቶሎ ቶሎ ማስወጣት/ማስወገድ ያስፈልጋል::

3.ሁልጊዜ የፀሀይ መከላከያ(#sun  screen) መጠቀም የቆዳችንን በፀሀይ የመጎዳት አቅም ይቀንሰዋል:: ለሁሉም የቆዳ አይነት የሚስማማ እኔ ለራሴ ምጠቀመውን ላጋራቹ ትወዱታላቹ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ
👉#skin aqua sunscreen, light textured and non greasy, for normal to oily skin

4. ስለ ቆዳ ብቻ እያወራን ከንፈራችንን  ረሳነሳው 🙊🙊🙊🙊,,, #ከንፈራችንን ቢያንስ በየ ሁለት ሰዓቱ ሚያለሰልስ ቻፒስቲክ መቀባት ቆንጆ ነው
ጥቆማ 😊😊😊
👉# Nivea sun protect chapstick
👉# carmex moisturizing lip balm

5. በቫይታሚን እና omega-3 የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር የሰውነት ፀሃይን የመከላከል አቅም ያሳድጋል

በመጨረሻማ እንደ ኮፍያ እና መነፅር የመሳሰሉ ነገሮችን መጠቀም ለቆዳችን ተጨማሪ ሽፋን ይሰጥልናል::

Join

Share

@onlyfemaleb


ይሄ #Telegram channel የሚያገለግለው ለሴቶች ብቻ ነው
#ማንኛውንም ጉዳይ ይዳስሳል
#ይመክራል
#ያማክራል
#መረጃ ይሰጣል
#ለሴቶች አስፈላጊውን መረጃ ይሰጣል ተቀላቀሉን ይማሩበል

#ሀሳብ_አስተያየት ካለሽ

@onlygirlsb


#አቢጊያ_ነኝ

#ፍቅረኝነት
#ጋብቻ

🏯በፅኑ መሠረት ላይ ያልተመሰረት ህንፃ በብርቱ ንፋስ እንደሚዋድቅ፤ ጋብቻም እንዲሁ በጽኑ  #መርሆዎች ላይ ያልተመሰረተ ከሆነ የህይወት ተግዳሮቶች በገጠሙት ጊዜ መቋቋም መቻሉ የሚያጠራጥር ነው።

እስኪ ደስተኛና ስኬታማ ጋብቻ  የሚመሰረትባቸውን #አስር የመርህ አለቶች እንይ!

1. ❤️ #ፍቅር
2. ✅ #እውነት
3. 👍 #መተማመን
4. 💞 #መስጠት
5. 💚 #መከባበር
6. 💝 #መታዘዝ
7. 🤴 #እውቀት
8. 💑 #ታማኝነት
9. 💗 #ትዕግስት
10. 💵 #አስተማማኝ_ኢኮኖሚ

#ሴቶች_ብቻ_ተቀላቀሉ
#share
#Join

@onlyfemaleb


ስለ እኛ ብቻ ለማውራት አሁን ዝግጁ ነኝ


ሰላም ሴቶችዬ




#ግለ_ወሲብ_ሊያስከትለው_ስለሚችለው_የጤና_ጠንቅ_ማወቅ_ትፈልጋለህ_ትፈልጊያለሽ ? እንግድያውስ አንብበህ ሸር አድርገው።

• ግለ_ወሲብ ወይም እራስን በራስ ማርካት የሚባለው ነገር ጠቀሚታ አለው ችግር አያመጣም ሲባል ሰምተው ይሆናል። ይሄ ግን ፈፅሞ ውሸት ነው። ጠቀሜታ ቢኖረውም የበለጠ ጉዳት ደግሞ ያስከትላል።
#ግለወሲብ በጤና ላይ የሚያስከትላቸው የጤና ጠንቆች የሚከተሉት ናቸው።

#1 ብልት እንድቆስል በማድረግ ለሽንት ቱቦ እና ለዘር ቱቦ ኢንፌክሽን ሊያጋልጥ ይችላል። ግለ ወሲብ ሲደጋገም የብልት አካል ላይ ቁጣና መቁሰል ስለሚፈጠር ፈሳሽ በውስጡ ስለሚፈጠር እብጠት የሚባል በሽታ ይከስታል።

#2 የዘር ህዋስ ወይም የዘር ፈሳሽ መጠን እንድቀንስ ያደርጋል።

#3 ድሀት የሚባል የጤና ቀውስ እንድፈጠር ሊያደርግ ይችላል። ድሀት ከሽንት ጋር የዘር ፈሳሽ ተቀላቅሎ መውጣት ነው። በመጨረሻም ብልት እንዳይቆም ወይም ቀድሞ የዘር ፈሳሽ ቀድሞ እንድፈስ ምክንያት ይሆናል።

#5 ሽፍታ እና መቅላት በብልት ላይ በተደጋጋሚ እንድፈጠር ያደርጋል። የብልት ቆዳ በመድረቁ ምክንያት ወይም ኢንፌክሽን ሊኖር ስለሚችል ይህ ችግር የተለመደ ይሆናል።

#6 ብቸኝነትን እንድመርጡ ያደርጋል። እንደ ስነ-አዕምሮ ባለሙያዎች እይታ በዚህ ባህሪ የተጠቁ ሰዎች ወደ ውጭ ወጥተው ከሰዎች ጋር ከመቀላቀል ይልቅ በቤት ውስጥ ወይም በግል ክፍላቸው ለብቻቸው ማሳለፍን ይመርጣሉ።

#7 በግለ-ወሲብ ሱስ ውስጥ ያሉ ሰዎች እያደረጉ ባሉት ነገር ምክንያት በድብርት እና ጭንቀት በእጅጉ ተጠቂ ናቸው። በራስ መተማመናቸውን ያጣሉ። በሰዎች ፊትም ቁጡና ነጭናጫ የመሆን እድል አላቸው። ይሄ ደግሞ ለራሳቸው ያላቸውን ክብር እንኳ ሊያሳንስባቸው ይችላል።

#በተጨማሪም
🔹 በሰውነት ውስጥ ያለውን ፕሮቲንና ካልሲየም እንዲቀንስ በማድረግ አቅምን ያዳክማል
🔹 የብልት መነሳት ችግርን ያስከትላል
🔹 ሱስ በመሆን ህይወታቸው ይቆጣጠራል
🔹 ድብርት ውሰጥ እንድንገባ ያደርገናል
🔹 ፈጥኖ መርጨት (premature ejaculation) እንዲከሰት በማድረግ በራስም ሆነ በፍቅር አጋር ላይ አለመርካትን ያስከትላል
🔹 የወንድ የዘር ፈሳሽ እንዲቀንስ በማድረግ እርግዝናን አዳጋች ያደርጋል
🔹 የማስታወስና የማሰብ አቅምን ያዳክማል
🔹 የጸፀት ስሜት መሰማት
🔹 ከፍቅር አጋራችን ጋር ወሲብ ለማድረግ ያለንን ፍላጎት ቀስ በቀስ ይቀንሳል

#መፍትሔ
1. ራስን በስራ ማድከም
2. ብቻ ላለመሆን መሞከር
3. በነገሩ ጉዳት እየደረሰብህ መሆኑን ማመን
4. ሰውነትህን ማክበር እንዳለብህ ማወቅ
5. እቅድ ማውጣት
6. እራስን እንደ ህሙማን ቆጥሮ ለመዳን ጥረት ማድረግ
7. ሴክስ ፊልም አለማየት
8. በሀይማኖት መፅናት
9. ሲተኙ ጠበቅ ያለና ረጅም ልብስ መልበስ። ከተቻለ መደረብ እና ከሌላ ሰው ጋር በማደር ግለ ወሲብን ላለማድረግ መጣር
10. ሊረዳህ የሚችል ባለሙያ በቅርብና ቶሎ ቶሎ ማግኘት እና የመሳሰሉት ናቸው።


መንገድህን ቀጥል!!!

1.  የምትኖርበት ቤት ማንነትህን አይወክልም!

አሁን ያለህበት ቤት ወደፊት የምትኖርበትን ስፍራ እስክታዘጋጅ መቆያህ ነው እንጂ ከማንነትህ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ስለዚህ የምትኖርበት ቤት ማንነትህን እንዲተረጉመው ባለመፍቀድ መንገድህን ቀጥል፡፡ 

2.  የምትሰራበት ስፍራ ማንነትህን አይወክልም!

አሁን የምትሰራው ስራ ጨዋና የስራ ሰው የመሆንህ ማሳያና ለወደፊት ማዳበር ለምትፈልገው ነገር መሸጋገሪያ ድልድይ ነው እንጂ ከማንነትህ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ስለዚህ የምትሰራው ስራህ የማንነትህ መለኪያ እንዲሆን ባለመፍቀድ መንገድህን ቀጥል፡፡

3.  የምታገኘው ደሞዝ ማንነትህን አይወክልም!

አሁን የምታገኘው የገቢ መጠን ራእህን በመከታተል ላይ ሳለህ ለጊዜው ያለህን ፍላጎት ማሟያና ቀዳዳ መድፈኛ ነው እንጂ ከማንነትህ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ስለዚህ ደሞዝህ የማንነትህን ደረጃ እንዲመድብ ባለመፍቀድ መንገድህን ቀጥል፡፡

4.  የትምህርት ደረጃህ ማንነትህን አይወክልም!

አሁን በጭንቅላትህ ውስጥ ያለው እውቀት ወደፊት ማወቅ ለምትፈልገው ነገር መነሻ፣ እንዲሁም ጥበብን ጨምረህበት የወቅቱን ሁኔታህን መግፊያ ነው እንጂ ከማንነትህ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ስለዚህ የትምህርት ደረጃህ ሰው የመሆንህን ዋጋ እንዲጨምረውና እንዲቀንሰው ባለመፍቀድ መንገድህን ቀጥል፡፡

5.  ሰዎች ስለአንተ የሚያስቡት ነገር ማንነትህን አይወክልም!

ሰዎች ስለአንተ የሚያስቡት ሃሳብ በመላ ምት ላይ የተመሰረተ፣ ከራሳቸው ምልከታ፣ ውስንነትና ልምምዳቸው ጋር የተዛመደ፣ ማመን የሚፈልጉትን ነገር እንደምክንያት የሚጠቀሙበት ሁኔታ ነው እንጂ ከማንነትህ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ስለዚህ ሰዎች ማንነትህን እንዲተረጉሙት ባለመፍቀድ መንገድህን ቀጥል፡፡

ከላይ የዘረዘርኳቸውን እውነታዎች በሚገባ ስትገነዘብ በዙሪያህ ካሉ ሁኔታዎች ባሻገር ዘልቀህ የመሄድ አቅም ይሰጥሃል፡፡ ይህንን ሃሳብ በመታጠቅ ቀና ብለህ ራእይን ተመልከት፣ እቅድን አውጣ፣ ባለህ አቅም የመጀመሪያዋን እርምጃ ተራመድ፣ ግራና ቀኝ ሳትል በርትተህ መንገድህን ቀጥል . . . ትደርሳለህ !!!


የወንዶች የወሲብ ያለማድረግ ችግሮች

የግብረ ስጋ ግንኙነት በሰዉነታችን ዉስጥ አራት ዋና የስርአት ቅንብር ዉጤት ነዉ። የደም ስር ፣ የነርቭ ስርአት፣ የሆርሞኖችና የአእምሮ ዉህድ ዉጤት ነዉ።

ከነዚህ የአንዱ ወይም ከአንድ በላይ ችግሮች የተለያዬ የወሲብ ችግሮችን ያመጣሉ።

የብልት መቆምና እንደቆመ ለግንኙነት ለሚያስፈልግበት ጌዜ መቆየት በዋናነት ወደብልት በሚሄድ የደም ስር በደም መወጠር የሚከሰት ሲሆን የነርቭ መልእክቶችና የሆርሞኖች መልእክቶች በየአእምሮ መልእክቱን የመተንተን ዉጤት ይወሰናል። ስለሆነም የግብረስጋ ግኑኙነት በዋናነት የሚደረገዉና የሚቆጣጠረዉ በእምሮችን ክፍል ነዉ ።

በወንዶች ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ የወሲብ ችግሮች ሶስት አይነት ናቸዉ።

1-የብልት የግብረስጋ ግንኙነት በሚፈለገዉ ግዜ ያለመቆም (erectile dysfunction)
በወነዶች ላይ ከሚከሰቱ ችግሮች ዋንኛዉ ሲሆን እድሚያቸው ከ20-75 አመት በሆኑት ላይ ከ6ሰዎች በአንዱ ላይ ይከሰታል(16%)

ችግሮቹ የሚከሰቱበት ምክንያቶ፦
ዉፍረት ፣ ሲጋራ ማጨስ፣ የልብ የደም ስር ችግሮች ፣ የተወሰኑ መድሀኒቶች (ለድባቴ የሚወሰዱ: ለደም ግፊት የፈንገስ መድሀኒቶች)

የስነአእምሮ ሁኔታ ፦የድባቴ ፣ የዉጥረት፣ የፍራቻ ችግሮች

የነርቩ ችግሮች፦ ስትሮክ ፣የጀርባ ጉዳቶች ፣ የህብለሰረሰር ችግሮች

የሆርሞን መዛባት ፦የስኳር በሽታ ፣ የወንድ ሆርሞን (ቴስቴስትሮን) እጥረት

2- የፍላጎት መቀነስ ወይ አለመኖር (diminished libido) በተለይ እድሜ እየጨመረ በሚመጣበት ወቅት የመከሰት ሁኔታ ይጨምራል።

3-የመርጨት ችግሮች (በፍጥነት መርጨት: በመዘግየት ወይ ያለመርጨት ችግሮች ሊሆኑ ይችላሉ) - abnormal ejaculation
በፍጥነት መርጨት (premature ejaculation ) ከሶስት ወንዶች በአንዱ ላይ ሊከሰት ይችላል። በሴቷ ብልት ዉስጥ በተለይ ከ60ሰከንድ በታች ከተረጨ ችግር እንዳለ ያመለክታል።

ይህ ችግር በወንዶች ላይ ከፍተኛ ዉጥረትና የተስፋ መቁረጥ ችግሮች በማምጣት ወንዶችን ከግብረስጋ ግንኙነት መራቅን ብሎም ከትዳር መፋታትን ያስከትላል።

የችግሮችን መንስኤ በማወቅ በህክምና ባለሙያዎች ሊረዱ ስለሚችሉ ያማክሩ ።

ዶ/ር ዘለቀ ከበደ ፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ና የህብረተሠብ ጤና አጠባበቅ ባለሙያ (MD, MPH, gyn-obs specialist)


#ላንቺ_ብቻ

በእጮኝነት ጊዜያችሁ እጮኛችሁን #ለማቆየት ብላችሁ ያልሆናችሁትን ነኝ ብሎ ከመናገር ተቆጠቡ።


👅 #እውነትን_ተናገሩ።

Join us here 👉 @onlyfemaleb


Репост из: ላንቺ ብቻ
#ላንቺ_ብቻ

በእጮኝነት ጊዜያችሁ እጮኛችሁን #ለማቆየት ብላችሁ ያልሆናችሁትን ነኝ ብሎ ከመናገር ተቆጠቡ።


👅 #እውነትን_ተናገሩ።

Join us here 👉 @onlyfemaleb


Репост из: ላንቺ ብቻ


ተመልሻለው ውዶቼ በራሴ ምክኒያት ጠፍቼ ነበር sorry


♡ #ሴት ልጅ 3 ነገር ያለውን
ወንድ ትወዳለች ...
① ያለሷ የማያይ አይን ያለው
② ክህደት የማያውቅ ልብ ያለው እና
③ ሁሌም የሚያሞግሳት ...


Lulit Sileshi:
Free delivery to mexico, bisrate gebriel, bole, saris and megenagna, jemo

Order us anything from Shein.com
https://t.me/acos_metics


​​❤️ፍቅር 😍እና ቅናት

1💓#የፍቅር ትክክለኛ ጥልቀቱን የምትረዱት ያች የመጨረሻዋ #የመለያያ ሰዐት ስትደርስ ነው፡፡

2❤️#የሰው ነፍሱ በሚኖርበት #ሳይሆን ባፈቀረበት ነው፡፡

3❤️#በዓለም ላይ #ራስህን ከማንም ጋር አታወዳድር ያን ካደረክ ራስህን እየሰደብክ ነው::

4❤️#እንደማንኛውም ሰው ከሚያያችሁን ሰውጋ #በፍቅር አትውደቁ፡፡

5❤️#ፍቅር አይደለም ዕውር፤ ዕውርስ #ቅናት ነው፡፡

6❤️#ቀናተኛ አፍቃሪ ላለመሆን ሞክር፤ በግልፅነት ቅናትን ለማስወገድ ሞክር፤ አለበለዚያ በመጨረሻም #ደስታንም ፍቅርንም እራስህንም ታጣለህ፡፡

7❤️#ቅናት ከፍቅር #ይበልጥ ለራስ ወዳድነት ቅድሚያ ይሰጣል፡፡

8❤️ቅናት የፍቅር #መቃብር ነው፡፡

9❤️ቅናት እና ፍቅር እህትማማች #ናቸው፡፡

10💕እንባ ልብ ሊገልጻቸው የማይቻለው #ቃላቶች ናቸው፡፡

Share and join ❤️
@Onlyfemaleb


💕💕Valentine Day Special Gift Packages💕💕
የፍቅረኞችን ቀን ምክንያት በማረግ የወንዶች, የሴቶች እና የጥንዶችየተለያዩ የስጦታ ጥቅሎችን አዘጋጅተናል
🎁 ከነፃ ስጦታ መያዣ ጋር
❤️ በነፃ ያሉበት እናመጣለን
❤️ ሁሉንም በአንድ ያግኙ
Contact @be_liye 0941573710
ለስጦታ ሚሆኑ ቦርሳዎች ሰዐቶች ዋሌቶች ጫማዎች ሽቶዎች ለማግኘት Telegram Channel ይቀላቀሉ
https://t.me/simplysellerstore
https://t.me/simplysellerstore

Показано 20 последних публикаций.

1 863

подписчиков
Статистика канала