ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ዲያቆን ፍፁም ከበደ
ሀሳብ ካሎዎት @Fisumkeb
+ ግሩፕ ለመቀላቀል +
https://t.me/NablisNablis
+ facebook Link...
https://www.facebook.com/deaconezemarefitsume.kebede
TikTok
https://www.tiktok.com/@zdfitsumkebede1?_t=8pguEgtdsVq&_r=1

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


የፊልም አፍቃሪ ነህ እንግዳውስ ይሄን የፊልም ቻናል Join በል  ሁሉንም አዳዲስ የሚወጡና ቆየት ያሉ ተከታታይና ሲንግል ፊልሞችን የሚለቅ ምርጥ ቻናል ነው👇👇
https://t.me/addlist/rxO9b4uRwV02OTFk
https://t.me/addlist/rxO9b4uRwV02OTFk




+ የተሰበረ ጽዋዕ +

እዚኽ ፎቶ ውስጥ በአካል የማውቀው ዘማርያምን ብቻ ነው፡፡ ሌሎች ግን በማኅበራዊው ሚዲያ መልስ ሲሰጡና ሲጠይቁ አያቸዋለሁ እንጂ ፊት ለፊት ተገናኝተን አናውቅም፡፡በወንድሞቻችን ፊት ፕሮቴስታንት ሰባክያን ምላሳቸውን ሲተሳሰር ብዙ ጊዜ አይቻለኹ፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ "ከኦርቶዶክስ ወንድሞች ጋር እንዳትከራከሩ" የሚል አዋጅ ሲያውጁ ሰምቻለኹ ጰንጤዎቹ፡፡
በአጭሩ፥ እኒኽ ወንድሞቻችን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱሳን መላእክትና ሰዎችን ታመልካለች የሚለውን ፕሮቴስታንታዊ የድር ምሽግ ሲበጣጥሱ ተመልክቻለኹ፡፡ ከዐይን ያውጣችኹ አልላችኹም፡፡ ዐይንም ጆሮም ውስጥ ናችኹና፡፡
ጽንዑ ወኀይሉ፡፡ ለማለት ነው አመጣጤ፡፡
ከእኒኽ ወንድሞች መኻል አንዱ ወይም ኹሉም ሊሳሳቱ የሚችሉ ናቸው፡፡ የቀለም ሠረገላ የማያሰናክለው የለምና፡፡
ደግሞም እኔ እንኳ የሰማኋቸው የሚታረሙ ስሕተቶች አሉ፡፡ የሚታረም ነገር ተገኘ ማለት ግን፥ ሙሉ እርሻው አረም ነውና አያስፈልግም የሚል ቧልት መናገር ቅንነትና ወንድማዊ ፍቅር ይጎድለዋል፡፡

በአንድ ወቅት፦
አንድ እጅግ የተከበሩ ሊቅ ከአንዲት ሴት ጋር ድቀት አገኛቸው፡፡ እኒኽን ሊቅ ብዙ ሰው ያውቃቸዋል፡፡ በዚኽኛው ታሪክ ግን ሰፊው ሕዝብ ስለማያውቃቸው ስማቸውን ልለፈው፡፡
ይኽን ድቀታቸውን የሰማ ደብተራ አንድ ቀን ማሕሌት ውስጥ አገኛቸው ሊቁን፡፡"ደግሞ አንተ እዚኽ ምን ልታደርግ ገባኽ?"
ሲል በፍና ተሣልቆ አፌዘባቸው፡፡ እርሳቸውም "እኔኮ የተሰበርኩ ጽዋዕ ነኝ" ብለው አንጀት የሚበላ መልስ ሰጡት፡፡
የተሰበረ ጽዋዕ ሰባራ ስለኾነ አይጣልም፡፡ንዋይ ቅዱስ ነውና በክብር ከዕቃ ቤት ይቀመጣል እንጂ፡፡

እንደዚያ ደብተራ ለቤተክርስቲያን የቀናን እየመሰለን ጥቂት ሸራፋ ያገኘንባቸው ጽዋወችን ኹሉ አውጥተን እንጣል ማለት እጅግ የከፋ በደል ነው፡፡ክርስቶሳዊውን መንገድ የረሳ ነውና፡፡ "ድኅረ ተሰብረ አጽንዖ ለሰብእናነ ልሕኵት፥ ለብሓዊ ክርስቶስ በማየ ሐዲስ ጥምቀት" የምትል ድንቅ የንጉሥ ጉባኤ ቃና አለች፡፡ ግርድፍ ትርጉሟ፦ ገላ'ችን ከተሰበረ በኋላ ሸክላ ሠሪው ክርስቶስ በአዲስ የውኀ ጥምቀት እንደገና ሠራው፡፡ ማለት ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ከጌታዋ የተማረችው የተሰበረን መጠገን ነው፡፡
ችግሩ፥ መጠገን እንደመስበር ቀላል አይደለም፡፡ ለመጠገን ዕውቀትና ቅንነት ያስፈልጋል፡፡ ለመስበር ግን ኦርቶዶክሳዊ የዘብነት ቀለም የተቀባች ምላስ በቂ ናት፡፡
ወንድሞች በጎ ሲሠሩ እናበርታ፡፡ሲስቱ እንክርዳድ ከስንዴ እየለየን በፍቅር እናርም፡፡አልታረምም የሚል ካለ ደግሞ የቤክርስቲያን ቱንቢ ያርመዋል፡፡እንደ ግለሰብእ እኔ ነኝ ቱንቢው ማለት ግን የስሕተት ስሕተት ነው፡፡

በየሚዲያው ሌሎች ጥሩ ወንድሞችም አሉ፡፡ ነገር ግን በልዩ ልዩ የቤተክርስቲያን አገልግሎት የተገለጡ ናቸውና ተውኳቸው ፡፡

( ሊቀ ሊቃውንት ስሙር አላምረው )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ




ሰላም እንዴት ዋላችሁ ውድ ቤተሰቦቻችን ለ 2 ባለ እድለኞች ቀድሞ ለተሳተፈ ልዩ የ50 ብር ሞባይል ካርድ ሽልማት ። ከታች በተቀመጠው የቴሌግራም ሊንክ 30 ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞችን አድ ካደረጋችሁ በኃላ ኮመንት መስጫው ላይ አለን ይለው ።

የግሩፑ ሊንክ
👇👇👇👇
https://t.me/edomiyass21

https://t.me/edomiyass21

https://t.me/edomiyass21


Репост из: አሞኒ
በየእለቱ የአባቶችን ዜና ሕይወት (ስንክሳር ) ማግኘት እና ማንበብ ይፈልጋሉ እንግዲያውስ በየእለቱ የአባቶችን ዜና ሕይወት ሚለቀቅበት አዲስ chanal ላስተዋውቃችሁ
እሱም

@መዝገበ ቅዱሳን ይሰኛል #

ከታች ያለውን link በመንካት join ይበሉ

@mezigebekidusan


እንኳን አደረሳችሁ የሚባልለት ሞት።

ማንም ሰው እናትኽ ለሞተችበት ቀን እንኳን አደረሰኽ ቢሉት ሐዘን እንጂ ደስታ አይሰማውም።

የቅዱሳን ሞት ግን ነቢዩ ዳዊት እንደነገረን"በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረ ነው" የቅዱሳኑ ሞት እንዲኽ ክቡር ከኾነ
አምላክ ሰው የኾነባት የድንግል ማርያም ሞት ከሌሎች እንዴት የከበረ ይኾን?
ክቡር ስለኾነ ክብር እናገኝበታለን::
ለዚኽ ክቡር ሞት ነው እንኳን አደረሳችሁ የምንባባለው።

( ሊቀ ሊቃውንት ስሙር አላምረው )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ




ጥር 18 የተዘጋጀ መንፈሳዊ ጉባኤ


ብዙ ሰው ሰርጉ እንዲያምር እንጂ ትዳሩ እንዲያምር የማይዘጋጅ መሆኑ ግርም ይላል።

(ገብረ እግዚአብሔር ኪደ )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ




በአዳማ ከተማ ዙሪያ ላላችሁ የተዘጋጀ 🥰


ከሥራ የተለየ እምነትና ገዳሚዊ ኅብረት የለም !

የምናኔ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን ገዳም እስከ ገባ ድረስ እንደ አንድ ተራ መናኒ ከመታየት በቀር የኋላ የመደብ ጀርባው የተለየ ክብር ሊያሰጠው አይችልም ። የተሰጠውን ትእዛዝና የሥራ ክፍፍል ሁሉ ተቀብሎ ይፈጽማል ። ገዳም የዓለሙ ኑሮ የቸከው ሰው የሚደበቅበት የማረፍያ ዋሻ አይደለም ። ለተልእኮ የሚፍጠኑ ትጉሃን ገዳማውያን ፣ ድውያንና አረጋውያንን የሚራዱ ርኅሩኃን ሕመማቸውን በአኮቴት የሚቀበሉ መናንያን ያላቸው ጉልበትና እውቀት ሁሉ አዋጥተው በራሳቸው ላብ በአንድ ማኅበር የሚያድሩበትና ለሌሎችም የሚተርፍበት ኅብረታዊ ክርስቲያናዊ ኑሮ ነው ። ከሥራ የተለየ እምነትና ገዳማዊ ኅበረት የለም ። ( መዋዕያን በአማን ነጸረ ገጽ-63)

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


+ ንስሐ ግቡ +

የጌታቻን የኢየሱስ ክርስቶስ መጠመቅ አሰቀድሞ በዮሐንስ ለሀጥያት ስርየት ማጥመቅ መንገድ ጠራጊነት የተጀመረ ነው እርሱም እኔስ ለጠጅ ፡ ቢረሌን ፡ ለልብስ ፡ ገላን ፡ እንዲያጥቡለት ፡ ለሱ ፡ ጥምቀት በሚያበቃ ጥምቀት አጠምቃቹሀለው ይል ነበር እንዲሁም እርሱ የሚያጠምቀው ጥምቀት ክርስቶስ ከሚያጠምቀው ጥምቀት ልዩ መሆኑን ሲገልፅ "በመንፈስ : ቅዱስ : እሳትነት" ክፍውን : ሕሊና : ከበጎው : ሕሊና የሚለይበት ስልጣነ ክህነት ገንዘቡ የሚሆንለት በማለት ይገልፃል ። ዮሐንስ ትንቢት የተነገረለት ያለነቀፌታ ይኖሩ ከነበሩ በእግዚአብሔር ፈት ጻድቃን ከነበሩ ከካህኑ ዘካርያስ እና ከኤልሳቤጥ የተወለደ ነው ። በሉቃ 8-11"

***
በእግዚአብሔር ፈት በቤተ መቅደስ ገብቶ የማጠን ተራ በመዓት አንድ ጊዜ የደረሰበት ካህኑ ዘካርያስ በመሰዊያው ቀኝ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦለት ታየው ። ይህም በዓመት አንዴ ሳይሆን አንድ ጊዜ በፈሰሰ ደሙ አለምን የሚያድን አምላክ ሊወለድ መሆኑን ሲነግረው ነው አንድም ካለመታዘዝ ወደ መታዘዝ የሚመልስ ከጣኦት አምላኪነት ወደ እግዚአብሔር አምላኪነት የሚመልስ ልጅ ትወልዳለህ ሲለው ነው በተጨመሪም በቀኝ እጁ አምላክን የሚያጠምቅ ልጅ ትወልዳለህ እያለ መንገሩ ነው ("ጸያሔ ፍኖት" ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ ) ።

ለዚህም ነበር በሰፈው ፈት ፃድቃን መስለው ይታዩ ለነበሩት በእግዚአብሔር ፈት ፅድቃቸው ከተመሰከረላቸው ቤተሰብ የተገኘው ዮሐንስ እርሱ በጌታ ፈት ታላቅ የሆነ ሉቃ 1፡15 በህሊና የተሰወረውን ክፍ ግብራቸውን ሳይፈራ እግዚአብሔር ገልጦለት ይገስፃቸው ነበር ፈሪሳውያንን "መልካም ፍሬ የማያፈራ ይጣላል " ማቴ 3-10 እያለ የነብያት ልጆች መሆናቸው ብቻ ንስሃ ካለመግባታቸው የሚመጣባቸውን ቅጣት እንደማያስመልጣቸው ክቡዳነ አእምሮ ለሆኑት ለእነርሱ "ንስሀ ግቡ" እያለ ያስተምራቸው ነበር ። ምንመካባቸው ብዙ የተከማቹ ሀብት ይዘን ሊሆን ይቻላል በዘመንድ ብዛት የእከሌ ዘመድ የእከሌ ዘር እያልን ምንመፃደቅባቸው በሰው ፈት ከሁሉ የተሻልን ለመምሰል የምናቀርባቸው ቁሶች ከመቃብር አይሻገሩም ያለን ግዙፍ ቤት በሁሉ ፈት ለመመካት ይዘነው አንዞርም አንድ ቦታ እንደተተከለ ይቀራል የሰማይ መንግስት እንወርስ ዘንድ ዮሐንስ ዛሬም "እንግዲህ ለንስሐ የሚያበቃቹሁን በጎ ስራ ስሩ" ይለናል " ማቴ 3-8 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይለናል " ጸጋስ ይሉሃል የኃጥያት ስርያት ማግኘት "

እንኳን አደረሳቹሁ ። !!!

(ዲያቆን ፍፁም ከበደ)

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


ብታነቡት አንድ ሥርዓት ትፈጽማላችሁ ታቃላችሁ 👍

ጾመ ገሃድ

ገሃድ ምንድን ነው?

ገሃድ የቃሉ ትርጉም መገለጥ፣ መታየት ነው፡፡ በጥምቀት መገለጥ መባሉ ሰው የሆነው አምላክ በዓለም ሲኖር እስከ 30 ዓመት እድሜው ድረስ ሰዎችን ለማዳን የመጣ መሲህ ሰው የሆነበት፣ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ እሱ መሆኑን ሳያውቁ ከኖሩ በኃላ በ 30 ዓመት እድሜው በባሕረ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ እጅ ሲጠመቅ አብ በደመና ሆኖ ‹‹የምወደው ልጄ ይህ ነው›› በማለቱ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በራሱ ላይ ሲያርፍ በመታየቱ ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ይሰቀላል ይሞታል ይነሳል ብለው የተናገሩለት መሲሕ እርሱ መሆኑ ተገልጦአልና እንዲሁም ሦስቱ አካላት በአንድ ጊዜ ታይተዋልና ምስጢረ ሥላሴ የተገለጠለት በመሆኑ ገሃድ ይባላል፡፡(ማቴ 3፡13-17)

ይህን በማሰብ የምንጾመው ጾም “የገሃድ ጾም” ይባላል፡፡

በዚህ መሠረት የአሁን የገሃድ ጾም የራሱ አዋጅ አለው

ስንክሳር ዘጥር ፲ እንዲህ ብሎ ያዛል

ወለእመ ፡ ኮነ ፡ ዕለተ ፡ በይረሙን ፡ ዘውእቱ ፡ አስተርእዮ ፡ በዕለተ እሁድ አው፡በዕለተ፡ ሰንበተ አይሁድ፡ይጹሙ፡በእለተ ፡ ዓርብ ፡እምቅድሜሁ፡እስከ፡ምሴት፡በከመ ተናገርነ፡ ቅድመ ዳዕሙ ይትዓቀቡ፡እምነ፡በሊዕ፡ጥሉላተ።

ጥምቀት እሁድ ስለዋለ አስቀድመን አርብ እስከ 12 ሰአት ይጾማል። በዋዜማው ደሞ ቅዳሜ ከቅዳሴ በኃላ ምግብ መመገብ ይቻላል። ግን ጥሉላት አይበሉም።
ለምሳሌ  ሥጋ ፣ ወተትና የወተት ተዋጽኦ......

በረከት የምናገኝበት ጾም ያድርግልን!!!
@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera


የጥምቀት መዝሙር ጥናት ተጀምሯል

ሊንኩን በመጫን ቮይስ ቻት ግቡ 🥰🙏




በቤተ ክርስቲያናችንም የስም ፍቅርና የሚፈጥረው ችግር ፣ የማእረግ ስሞችን የኩራታቸውና የገቢያቸው ምንጭ ለማድረግ እንጂ በሚጠሩበት ስም ልክ ሥራ ለመሥራት ዐላማ ያላቸው ሰዎች በጣም ጥቂቶች መስለው ነው የሚታዩኝ፡፡ ለዚያ ነው እኮ ያልነበረ የክህነት ደረጃ ጨምረን 'በዕደ ገብሩ ካህን' የሚለውን 'በዕደ ገብሩ ቆሞስ' ወደማለት ሁላ ያመራነው፡፡ አንድም ቀን ተጠቅሜበት አላውቅም፣ አብረውኝ የቀደሱ ቆሞሳት እንደማይደሰቱ ግን ይገባኛል፡፡


( Arega Abate )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


ዘንድሮ ከተራ ቅዳሜ ነው የሚውለው ፤ ጥምቀት ደሞ ገሀድ ጾም አለው

ጥያቄ ዘንድሮ እንዴት ነው ገሀድ ሚጾመው?

መልሳችሁን በ coment section ላይ ይላኩ ዋና ምላሹን በኋላ ይዘን እንመጣለን
@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera


ማቃጠሩን ትተን...
--
ተረት እናስቀድም:-
እማሆይ የአብነት ተማሪዎች ጎጆ በእንግድነት አድረው ሌሊት መቁጠሪያቸውን እየቆጠሩ “አምላክ ሆይ እንደነዚህ ሰነፍ ተማሪዎች ስላላደረከኝ አመሰግንሀለሁ” ሲሉ አንዱ ተማሪ ተነስቶ “እማሆይ ማቃጠሩን ትተው ስለራስዎ ይጸልዩ” አላቸው፡፡
--
ጉዳያችን:-
የእግዚአብሔር መጋቢነት ኃጥእ ጻድቅ አይልም። መጋቢነቱን በዚህ ምድር በሚያጋጥሙን ፈተናዎችና ዕድሎች ለመለካት መሞከር መዳረሻው የብልፅግና ወንጌል እንዳይሆን ያሰጋል። ለቅጣት መቅሠፍት ቢያመጣ እንኳ ለየትኛው ጥፋት እንደሆነ አናውቅም። ምንና ለምን ሠራህ የሚለው የለም።
--
ደግሞስ የማያበራ ጦርነት፣ ረኀብና ርዕደ መሬት ላይ ያለ ሕዝብ የሌላውን መከራ የኃጢአት ውጤት አስመስሎ ጣት ለመቀሰር፣ የሎስ አንጀለስን በደል ለመዘርዘር ምን አንደበት አለው?!
--
ማቃጠሩን ትተን ለራሳችን እንጸልይ!


(በአማን ነጸረ )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

Показано 20 последних публикаций.