Фильтр публикаций


ቶማሳዊነት
ቅዱስ ቶማስ ከ፲፪ቱ ሐዋርያት አንዱ ነው።
ጠያቂ እና ተረጂ ደቀ መዝሙር ነው።
አርቆ አሳቢ ነው።
ማረጋገጥ የሚወድ ደቀ መዝሙር ነው።
ፍጹም ወንጌላዊ ነው።


Репост из: ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
ዋናው ጉዳይ ለሰሞኑ ሲኖዶስ የተያዘውን አጀንዳ ለመፈጸም ማደንዘዣና ማስቀየሻ መንገድ ነው።
ማንኛውም ሰው ዓይኑን ተክሎ ማየት ያለበት ጉዳይ ቀጥሎ የሚሆነውን ነው።


Репост из: ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
ጳጳስ የሚወገዘው ምን ሲያደርግ ነው?


ጳጳስ አይከሰስ፣ አይወቀስ፣ አይወገዝ የኾነባት ቤተክርስቲያን ነው ያለችን። ሊቃውንቱ የዚኽ ሁሉ ሚዛን አስጠባቂ ነበሩ። ይሁን እንጂ የኑሮ እጣ ፈንታቸው በጳጳስ እጅ ኾነና በዝምታና በኀዘን ይተባበሯቸዋል። ትክክል አይደለም የሚል የለም። 

ልጅ ወልደው አያት ሲኾኑ ጥፋታቸው በደብዳቤ ለዓለም ተገልጦ ሳለ የሚጠይቃቸው የለም። የገንዘብ ዘረፋ ዐይን አፍጥጦ ወጥቶ ሳለ ጠያቂ ያለባቸውም። 

ረዥም ዓመት ባለኾነ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ :- “የጻፉት መጽሐፍ እንደ ካቶሊክ ኹለት ባሕርይ የሚል ነው” ብለው ብፁዕ አቡነ ገብርኤልን (የቀድሞው) “አባ ኢያሱ” ብለው ሲኖዶስ አውግዟቸው ነበር። ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስም ጋር ይከራከሩ ይጋጩ ስለ ነበር በኋላም ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋርም ተጣልተው ስለነበር ነገር ሠርተው አወገዟቸው። 

ብፁዕነታቸው ይኽንን ክስተት ሲገልጹ :- “አቡነ ጎርጎርዮስ ግሪክም ሀገር ኾነዉ ስምተዉ ነበርና በተገናኘን ጊዜ በጣም ተከራከርን፡፡ የክርክራችን ማዕከልም ሞኖፌስት (Monophysis) የሚለዉ የግሪክ ቃል ትርጉሙ እና ሃይማኖታዊ ዳራዉ ነበር፡፡ ሞኖፌስት የእኛን ሃይማኖት ይገልጣል አይገልጥም በሚል እጅግ ተከራከርን፡፡ ይህም ክርክራችን ሰፍቶ እሰከ መጣላት አድርሶን ነበር፡፡ ….

ከዚያም በተለያዩ ጊዜያት ተገናኝተን እንወያይ ነበር:: በቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ በዶክትሪን፣ በአገላላጽ እንከራከር ነበር፡፡

በወቅቱ ከብፁዕ ወቅዱስ ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋራ በአጋጣሚ ተጣልቼ ስለነበር በጻፍኩት መጽሐፍ ምክንያት ተከሰስኩኝ፡፡ “ይህቺ መጽሐፍ ውስጧ ኹለት ባሕርይ ነች፤ ስለዚህ አቡነ ገብርኤል ኹለት ባሕርይ የሚሉ ካቶሊክ ናቸው” በማለት፡፡

 ከቤተ ክህነት ግቢ አስወጥተውኝ ስለነበረ ለጊዜው እቴጌ ጣይቱ ሆቴል ሳለሁ ግንቦት ወርእኔ በሌለሁበት መጽሐፏ ተኮነነች፡፡ “ይሄ ኦርቶዶክሳዊ አይደለም፤ ይሄ የቤተ ክርስቲያን አባባል አይደለም ይሄም የሁለት ባሕርይ ነው” እያሉ እያስጠኑ አሳመኗቸው፡፡ “እንዲህ ከኾነ መልስ ይስጥበት፤ አንድ ሰው ሲሳሳት ይጠራል፣ ይጠየቃል እምቢ ካለ ይወገዛል” ተባለና ወደእኔ አንዳንድ አባቶች መጥተው “ተዘጋጅተው ይምጡ” አሉኝ፡፡ ተዘጋጅቼ ስጠብቅ የእኔን መምጣት አከሸፉት፡፡ ብጥብጥ ይፈጠራል፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ናቸውና ሰዎች ይከተሏቸዋል በማለት ቅዱስነታቸውን አሳሳቷቸው፡፡ በሌለሁበት ውግዘት ተፈጸመብኝ፡፡ 

የ“እኛን አክሊል (ቆብ) እንዳያደርግ፣ ከምእመናን ጋራ እንዳይገናኝ ሳይጠየቅ ሳይናገር እንዳይባርክ፣ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገኝ˝ ብለው ውግዘት አስተላለፉ፡፡ ውሳኔያቸው ደረሰኝ፡፡ ተናደድኩ “ይህ ከኾነ ዘንድ እናንተ (Monophsis) ሞኖፌስቶች ናችሁ ከእናንተ ከአውጣኪያን ጋራ ግንኙነት የለኝም፧ ብዬ አወገዝኩኝ፡፡ የእልህ ውግዘት እብደት ማለት ነው፤ አወገዙኝ አወገዝኳቸው፡፡” በማለት በወቅቱ የነበረውን ክስተት ገልጸውታል። (የማውቀውን እናገራለሁ ገጽ 63-64)

የጠቡ ዋና ጉዳይ ቃል (Terminology) ነው እንጂ የይዘት አልነበረም። 

በስተ መጨረሻ ግን በብዙ ውይይትና ንግግር በኋላ መንግሥቱ ኃይለ ማርያምም ጣልቃ ገብተው ጉዳዩ በውይይት ታየ፣  ብፁዕ አቡነ ገብርኤልም ይቅርታ ደብዳቤ አስገብተው ውግዘቱ ተነሣ አለቀ። (ዝኒ ከማሁ ገጽ 65)

ዛሬ በነገረ መለኮት ዙሪያ ቁጭ ብለው የሚወያይ ጳጳስ የለም። ተሰብስቦ ቁርጥ የሚበላ የሚያድም፣ በጎጥ ዩሚቧደን ብቻ ነው። ይኽንን የምለው ለማቃለል እንዳልሆነ ልቤን ያውቃል። ችግሩን በትክክል አይተን ለተጋድሎ እንድንዘጋጅ ነው። ቤተ ክርስቲያንን ከጳጳሳት ነጻ ለማውጣት እንጂ። 

በቀኖና ቤተ ክርስቲያን በመማለጃ በጉልበት በተንኮል የተሾመ መማለጃ ተቀብሎ የሾመው ይሻር ይላል።   "ኤጲስቆጶስነትን ፡ በማማለጃ ፡ በጉልበት ፡ በተንኰል ፡ ስለ ፡ ተሾመው ፡ ወይም ፡ማማለጃ ፡ ተቀብሎ ፡ ስለሾመው ፡ ነው።” ፍት. ነገ.5:173

ከዓለማዊ ሥራ አንዳቸውን የሚሠራ ኤጲስ ቆጶስ ቢኖር ይሻር” ፍት.ነገ.5:198

የሃይማኖት ሕጸጽ የሚገኝበት ጳጳስ ቤተክርስቲያን ታወግዘዋለች። ለምእመኑ አርዓያ የማይሆን ጳጳስ ይሻራል። 
በቀኖና ቢመዘን የሚተርፍ ጳጳስ የለም። 

ዛሬ አይነኬ ሆነው ፓለቲከኞች የማይኾኑትን እየኾኑ። አመጻቸውንና ግፋቸውን በቀሚስና በቆብ ሸፍነው መጽሐፍ ቅዱስን የወንጀላቸው መሸፈኛ አድርገው ይኖራሉ። 

አባ ሳህለ ማርያም “አቡነ” ገብርኤል የሚጠይቃቸው ሲኖዶስ የለም፣ “አባ ወልደ ትንሣኤን “ አቡነ” በርናባስን የሚጠይቅ የለም። አቡነ ሳዊሮስንና አቡነ ኤዎስጣቴዎስን፣ አቡነ ዜና ማርቆስንማ ቀና ብሎ የሚያይ የለም። ክቡራን ጠራርጎ ከማስወጣት ውጭ ምርጫ የለም። ቤተክርስቲያንን ለሉቃውንቱ ማስረከብ ላይ መሥራት ብቻ ነው። 

ንዋይ ካሳሁን(ከፍኖተ አበው ገጽ)


Репост из: ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
ጥንታዊው ገዳም ደብረ ድማኅ በዚህ መልኩ እየተደበደበ ነው።
ኦርቶዶክሳዊነት በውስጣዊ የዕቅድ አዋጅ መከራ እየተቀበለች ነው።
ገዳማውያኑ በስቅለት ላይ ሌላ ስቅለት በሕማማት ሌላ ሕማማት ሰንብተዋል።
የማን ያለሽይባላል?


አሰግዚአብሔር ቃልያዳነው ከዚህ ሁሉ መከራ ነው።


ኖላዊ ሆይ ! ባይጠብቁ አያስክዱ !?!?
➠ እመቤታችን ቤዛ አትባልም እንዲሉ ያስገደደዎት ምንድን ነው ? አውቀው ነው ? ወይስ ሳያውቁ ነው ?
ለማደናገር ነው ? ለማስካድ ነው ? ለማሰናከል ነው ?

➠ እመቤታችን ቤዛ እንዳይደለች ያነበቡት መጽሐፍ አለ?
ወይስ የጠየቁት  መምህር አለ ? ነው የተገለጠልዎት መገለጥ አለ ? ወይስ ያዩት ራዕይ አለ? ነው የነገረዎት መልአክ አለ ? ይህንንስ ተናግረው የሚመልሱት መናፍቅ በትምህርትዎት የሚያጸኑት ምዕመን አለ ? ነው የሚያስጨብጡት መሠረታዊ ዕውቀት አለ ከሌለ ይህን እንዲናገሩና እንዲያስተምሩ ምን አስገደደዎት ?

➠ በእርግጥ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ጵጵስና ? ካገኙ የማያጧት ከገቡ የማይወጡባት ከወረሷት የማትነጠቅ መንግሥተ ሰማያት
ከሆነ ውሎ አድሯል ። አንድ ሰው የጵጵስና ቆብ ከጫነ በኋላ የፈለገውን የሚናገርበት ያሰበውን የሚተነፍስበት ዓውደምህረት ይፈጥራል ከዚያ በኋላ ለተናገረው ስሑት ነገር ቀኖና ሳይገባ ወይ ተድበስብሶ ይታለፋል ያለዚያም በይቅርታ ይተዋል ግን ለምን ይሆን ?

➠ ቤዛ ማለት ምንድን ማለት ነው ?
ይህ ኃሳብ በእርግጥ የጳሱ ሳይሆን የፕሮቴስታንት ኃሳብ ነው ፕሮቴስታንት ቤዛ መድኃኒት መባል ለጌታ ብቻ እንጅ ለሌላ አይገባም ቤዛነትን ለሌላ አካል መስጠት የጌታን አዳኝነት መካድና ሌሎቹን ከጌታ ጋራ ማስተካከል ነው ይላሉ ስለዚህ ብፁዕነትዎ እንዲህ እንዲሉ ከጀርባዎት ማን ነው ያለ ?

⏩ ቤዛነት በቤተክርስቲያን አስተምህሮ ምንድን ማለት
  ነው ?  ቤዛ ማለት ሁለት ትርጕሞችን የያዘ ነው
፩ , ተቤዘወ አዳነ ካለው የወጣ  የግዕዝ ግሳዊ ቃል ሲሆን ትርጕሙ መድኃኒት አዳኝ ማለት ነው ።
ዮም ተወልደ ቤዛ ኵሉ ዓለም  ፦ ዛሬ የዓለም ሁሉ መድኃኒት ተወለደ እን ቅ ያሬ
፪, ስለ፣ ፈንታ ማለት ነው ዐይን ቤዛ ዐይን ወስን ቤዛ ስን ስለዐይ ፈንታ ዐይን ይጥፋ ስለ ጥርስ ፈንታ ጥርስ ይርገፍ እን ዘጸ ማቴ ፭ ÷  ስለዚህ እመቤታችንን ቤዛ ሲላት ምን ማለት ነው ኅፀፅስ አለው ወይ ?

⏩  ስለእመቤታችን ቤዛነት ከመናገሬ በፊት ትንሽ ነገር ልናገር  እወዳለሁ ለአንድ ግስ ሦሰት ነገሮች አሉት
፩, ንባብ
፪, ትርጕም
፫, ምሥጢር ፦ እነዚህን ጠንቅቆ አለመረዳት ፍጹም ወደሆነ የስህተት ጕድጓድ መውደቅ ነው ።
ማንኛውም ነገር በንባብ ይገናኛል በትርጕምም ይገናኛል በምሥጢር ግን ይለያያል ።

⏩ ይህም ማለት እግዚአብሔር ቅዱስ ይባላል መላዕክት ቅዱሳን ይባላሉ ሰዎችም ቅዱሳን ይባላሉ ፍጥረታትም ቅዱሳን ይባላሉ ።
ቅዱስ ማለት ልዩ ንጹህ ክቡር ማለት ነው ስለዚህ እግዚአብሔርን ቅዱስ ስንለው የባህርዩ ነው መላእክትን ቅዱሳን ስንላቸው የጸጋ ነው አንድ ጊዜ ተሰጥቷቸዋል እያደጉ ይሄዳሉ እንጂ መመለስ መውደቅ የሌለበት ነው (ከዲያብሎስ ውጭ) ሰዎችን ቅዱሳን ስንላቸው በተፈጥሮ ይሰጣየዋል በልጅነት ይታደላየዋል ኋላ በኃጢአት ነሳቸዋል በምግባር በትሩፋት በንስሃ ይመለስላቸዋል ፍጥረታትን ቅዱሳን ስንላቸው የተፈጥሮ ነው ማለት እግዚአብሔር ሲፈጥር አንድ ጊዜ ንፁህ አድርጎ ፈጥሯቸዋልና ፤
ስለዚህ ቅዱስ ባለው ንባብ ይገናኛሉ ልዩ ባለው ትርጕምም ይገናኛሉ በምሥጢር ይለያሉ ማለት የእግዚአብሔር ቅድስና ከመላዕክት የመላዕክት ቅድስና ከሰዎች የሰዎች ቅድስና ከሥነፍጥረት ቅድስና ፈጽሞ የተለየ ነው

⏩ እግዚአብሔር ረቂቅ ነው መላዕክትም ረቂቃን ናቸው
ነፋስም ረቂቅ ነው ውሃ በእጅ የማይጨበጥ በዓይን የማይታይ በእቃ የሚያዝ ረቃቅ ነው እሳት በዓይን የሚታይ በእጅ የማይጨበጥ ረቂቅ ነው ሰይጣን ረቂቅ ነው እሊህ ሁሉ ግን ንባብ ትርጕም ቢያገናኛቸው የርቀት ምሥጢር ይለያየዋልና የአንዱ ርቀት ከአንዱ ርቀት ፈጽሞ የተለነ ነው

🕎 መጽሐፍ እመቤታችንን ቤዛ ሲላት ከጌታ ቤዛነት ጋራ
ንባብና ትርጕም አገናኛት እንጅ ምሥጢር አያጋናኛትም
የእርሷ ቤዛነት ( ፈንታነት ) ስለሔዋን ነው ይህ ማለት ሔዋን ትዕዛዘ እግዚአብሔርን እንቢ በማለት ሞትን አመጣች ቤዛ ሔዋን እመቤታችን እንደቃለህ ይሁንለኝ ብላ ትዕዛዘ እግዚአብሔርን በመቀበል ሕይወትን አመጣች ።

🕎 ሔዋን ባለመታመን በጥርጥር በዓለም ላይ የሞት አዋጅን አሳወጀች ቤዛ ሔዋን እመቤታችን በፍጹም እምነት በፍጹም አለመጠራጠር በዓለም ላይ የሕይወት አዋጅን አሳወጀች ሔዋን ቃለ ሰይጣንን ሰምታ ሰምታ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስን አመጣችብን ቤዛ ሔዋን እመቤታችን ቃለ መልአክን ሰምታ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስን አመጣችልን ቤዛነት ማለት ይህ አይደለምን ?

🕎  ሔዋን ምክንያተ ሞት መሠረተ ሞት ቃኤልን ወለደች
ቤዛ ሔዋን እመቤታችን ምክንያተ ሕይወት መሠረተ ሕይወት ክርስቶስን ወለደች ።
ነገር ግን ሔዋንን ዲያብሎስ አሳታት የሞት ምንያት የሚሆን ቃኤልን ወለደች ማርያም ግን መልአክ በአበሠራት ጊዜ ሁሉን ወደዘለዓለም ሕይወት የሚመራ አካላዊ ቃልን በሥጋ ወለደች ሃይ አበ ፷፯ ÷ ፬

🕎  ገነት በሔዋን ምክንያት እነደተዘጋች በቤዛ ሔዋን በእመቤታችን ምክንያት ተከፍታለች ሔዋን ለዓለም ድቀት ምክንያት ከሆነች ቤዛ ሔዋን እሠቤታችን ለዓለም መነሳት ምክንያት ሆነች ቢባል ምንድን ነው ጥፋቱ ?

🕎 ክርስቶስ ግን ቤዛ ሲባል በመጥወተ ርዕስ (ራሱን ሠሥዋዕት አድርጎ) በመስጠት ሥጋውን በመቁረስ ደሙን በማፍሰስባህርያዊ መሥዋዕት በማቅረብ ነው ።
እርሱ የመሥዋዕት በግ ነው እርሱም መሥዋዕት አቅራቢ ሊቀ ካህናት ነው እርሱ ከባህርይ አባቱ ከአብ ከባህርይ ሕይወቱ ከመንፈስቅዱስ ጋራ መሥዋዕት ተቀባይ ነው
              ሃይ አበ  ፴፮ ÷ ፳፮
ስለዚህ ብፁዕነትዎ ቤተክርስቲያን እመቤታችንን ቤዛ ስትል የጌታን ቤዛነት ሰጥታ እመቤታችን ሥጋዋን ቆርሳ ደሟን አፍስሳ ቤዛ ሆነችን እያለች አደለም ።
ስንዱዋ እመቤት ቤተክርስቲያን ይህንን ያህል ዘመን እመቤታችንን ቤዛ ስትል በረቀቀ ዐይን ተመልክታ አየረ አየራትን ወጥታ እመቀ እመቃትን ወርዳ እንጅ በገዘፈ ዐይን እንዳይመስልዎት ?!?!
ስለዚህ ይህ ኃሳብ ለዘመናት ሲነገር የኖረ የፕሮቴስታንት ኃሳብ እንጅ የእርስዎት ኃሳብ አደለም ።
ወይ ተገልጠው ይምጡ ወይ አጥፍቻለሁ ብለው ቀኖና ገብተው ይመለሱ በጀርባዎት የሌላ ኃሳብ ተሸክመው አያወናብዱን !?!?
           ( ኖላዊ ሆይ! ባይጠብቁ አያስክዱ!?!?)


ቤዛዊተ ዓለም!

ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡ #ትርጉም፦ እንደ ልጅሽ ደም ጣሙ ድንቅ ለሆነው ስምሽ ሰላም እላለሁ፡፡ የሕይወት መሠረት የሆንሽ ከቀድሞ ጀምሮ የሆነ የመዳን መጀመሪያም የሆንሽ ማርያም ሆይ! አንችን ለዓለሙ ቤዛ በጎ አድርጎ የፈጠረ እግዚአብሔር ይባረክ፤ ስሙም ይመስገን፡፡ (ሥርዐተ ነግሥ)

እመቤታችን ቤዛ፣ ቤዛ ዓለም (ቤዛዊተ ዓለም)፣ መድኃኒት፣ የሕይወት መሠረት (መጀመሪያ)፣ የድኅነት ጥንት . . . በሚሉ ቃላት ትጠራለች፡፡ ምክንያቱ ብዙ ቢሆንም አንደኛው ምክንያት ክርስቶስ ለእኛ ቤዛ የሆነበት፣ እኛን ያዳነበት፣ ለእኛም ሕይወትን የሰጠበት ሥጋ ከእርሱ የነሣው በመሆኑ ነው፡፡

አባ ጊዮርጊስ ነገረ ድኅነትን ሲያብራራ "ዐቃቤ ሥራይ መጽአ እምሰማየ ሰማያት ወዕፀ ፈውስ ተረክበ በቤተ ዳዊት- ባለ መድኃኒት ከሰማይ መጣ፤ ከዳዊት ቤትም (ወገንም) የመድኃኒት ዕንጨት (ዛፍ) ተገኘ ይላል፡፡

ባለ መድኃኒት ደዌ ላለበት ሰው ከዕፅዋት መድኃኒቱን ቀምሞ ይፈውሰዋል፡፡ ደዌ ኀጢአተ አዳም፣ ባለ መድኃኒት መለኮት ሲሆን መድኃኒት ሥጋዌ፣ የመድኃኒቱ መገኛ ዕፅ (ዛፍ) እመቤታችን ናት፡፡ ለመድኃኒት የተፈጠሩ ዕፅዋት አሉ፡፡ ስለዚህ መድኃኒት ስለሚያስገኙ ዕፅዋቱ ሳይቀሩ መድኃኒት ተብለው ይጠራሉ፡፡ ባለ መድኃኒቱ መለኮት እመቤታችንን የሰውን ልጆች ሊያድንባት፣ (መድኃኒት የሆነውን ሥጋዌ ሊፈጽምባት) ነው የፈጠራት፡፡ መድኃኒት ሥጋዌን ቀመመባት፡፡ ይእቲኬ መድኃኒት እንተ ኀሠሥዋ ወዖድዋ ነቢያት - ነቢያት የሿት፣ የመረመሯት መድኃኒት ይላል፡፡ (1ጴጥ 1፥10) መድኃኒት የጌታ ሰው መሆን ነው፡፡

ስለዚህ ለእኛ ቤዛ ሊሆነበት የተዋሐደውን ሥጋ ከእመቤታችን የነሣው በመሆኑ ቤዛ ትባላለች፡፡ ለእኛ ሕይወት ሊሰጥበት የነሣው ከእርሷ በመሆኑ ሕይወት፣ የሕወይት አስገኝ፣ የሕይወት መሠረት፣ የመድኃኒት መገኛ ትባላለች፡፡


#እመቤታችን_ቤዛዊተ_ኩሉ_ዓለም_ናት!!!

በማኅበራዊ ሚድያ ሲዘዋወር አንድ አባት የተናገሩት ቢድዮ አየሁት፡፡ጥቂት ነገር ልበል፡፡
ቤዛ ምንድን ነው???
#ቤዛ፣ቤዛነት ማለት ስለ አንድ ነገር ምትክ መሆን ነው፡፡እመቤታችን ቤዛ ናት ማለት እግዚአብሔር ቃል ሰው እንዲሆን ከሰው ልጅ የሚጠበቅ ነገር አለ ይህም መርገመ አዳም ወሄዋን ያልወደቀበት ንጹሕ ዘርእ ነው፡፡
እመቤታችን ቤዛ የሆነችው ደቂቀ አዳም ይጠብቁት የነበረውን ንጽሕና ይዞ መገኘት ነው፡፡ስለዚህ እመቤታችን ቤዛ ናት ማለት የደቂቀ አዳምን ግብር ወክላ የተገኘች ስለደቂቀ አዳም ፋንታ በንጽሕና በቅድስና ቤዛ ሆነች ማለት ነው፡፡
#ቤዜነቷም፦
የንጽህና የቅድስና ቤዛነት
የድንግልና ቤዛነት
የመጽነስ ቤዛነት
የመውለድ ቤዛነት
የማሳደግ ቤዛነት
የመሰደድ ቤዛነት
የርሀብ የጽምእ ቤዛነት
የሕማም የመከራ ቤዛነት
የአቂበ ህግ ቤዛነት ከፍላለች፡፡
ቤዛ አበው ነቢያት
ቤዛ ጻድቃን ነገሥት
ቤዛ ንጹሃን ደናግል
ቤዛ ፍንዋን ሐዋርያት
ቤዛ ግፉዓን ጽድቃን
ቤዛ ከዓውያነ ደም ሰማዕት
ቤዛ ስዱዳን ባሕታውያን
ቤዛ ተላውያን ፸ አርድእት ናት፡፡
እኒህ ሁሉ አበው በእመቤታችን ቤዛነት የዳኑ ናቸው እንጂ በእነርሱ ሥራ አይደለም የእነርሱ መከራ ሰውነታቸውን እንደ ወርቅ ቢያጸራውም አምላክን ለመወሰን አለበቁም የእመቤታችን የንጽሕና ቤዛ ግን በማሕፀኑዋ እንድትወስነው አድርጉዋታል፡፡

"እውነት እላችኋለሁ፥ብዙዎች ነቢያትና ጻድቃን የምታዩትን ሊያዩ ተመኝተው አላዩም፥ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ተመኝተው አልሰሙም።
ማቴ13:17::
"ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል።
ትን.ኢሳ.64:6
ነቢያት ሁሉ የአዳም መርገም ወድቆባቸው ሥራቸው ሁሉ ለጽድቅ አላበቃቸው ብሎ ኑረዋል፡፡ እመቤታችን ግን የአበውን ሁሉ ጩኸት የፈጸመች የጩኸታቸው ቤዛ ሆነችላቸው ማለት ነው፡፡
እመቤታችን ቤዛዊተ ዓለም ማለት ከዓለም የሚያስፈልገውን ሥራ ይዞ መገኘት ነው፡፡
ይህን ቤዛነት አለመረዳት እጅግ አደጋ ነው፡፡

"ንትፌሣሕ ኩልነ በዝክረ ስምኪ ጥዑም ወበደመ ዮሐንስ መአድም ቅድስት ማርያም ቤዛዊተኩሉ ዓለም" ቅዱስ ያሬድ
"ኢትኅፈር ልደቶ እም ብእሲት እስመ ይእቲ ኮነተነ ምክንያተ ሕይወት አስተጋበአተነ ቅድስት ማርያም ዘይእቲ ንዋየ ድንግልና ዘአልቦ ሙስና ወይእቲ ዘዳግም አዳም ገነት እንተ መንፈስ ወይእቲ ጽምርተ ህላዌ ወይእቲ በዓለ መድኃኒት እንተ ተቤዘወነ ጽርኅ ንጽሕት እንተ ባቲ ተመርዐወ ቃል"
ተረ ቄር 18፡5
"ዮም ፍሥሓ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም እምሐና ወኢያቄም ከመ ተቤዙ ነቢያተ ወጸድቃነ አማን ተወልደት እመ ብርሃን"
ቅዱስ ያሬድ
"መጽአ ዐቃቤ ሥራይ እም ኀበ አብ እምጽርሐ አርያም መድኃኒት ተረክበት በሀገረ ዳዊት እንተ ስማ ጽዮን ወተፈጸመ ዘተብህለ መኑ ይሁብ መድኃኒተ እም ጽዮን"
መጽ ምሥ 20፡11:
#ቅዱስ ያሬድ፣አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፤ቅዱስ ቄርሎስ ቤዛዊተ ዓለም ካሏት እነዚህ አባት ቤዛዊተ ዓለም የማይሎት ከማን ወገን ሆነው ነው??
መልሱ ከንስጥሮስ ወገን መሆናቸው ነው፡፡

#እመቤታችን ለዓለም ሁሉ ብቸኛ ንጽሕት ዘርዕ ሆና ከጥፋት በመታደግ ለሁሉም ቤዛ ሆናለች፡፡
ጠቅለል ሲል እመቤታችን ንጹሕ አካሏን ለዓለም ቤዛ አድርጋ ለእግዚአብሔር አቅርባለች ነው፡፡
"የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር::
ትን. ኢሳ. 1:9::
#እሰግድ ለንጽሕናኪ ወአስተበርክ ለድንግልናኪ ማርያም ድንግል ቤዛዊተ ነፍስየ ዘኮንኪ!!!

❖እናመልከው ዘንድ ለፈጠረን እግዚአብሔር ምስጋና ይግባው እንላለን!!!
             ❖አ.ዘ.ያዕቆብ፡፡
©ጌዴዎን ዘለዓለም::


Репост из: ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


Репост из: ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


ማዕዶት

ከጌታ ትንሣኤ እሑድ እስከ ሳምንት እሑድ ድረስ ያሉት ዕለታት የየራሳቸው ስያሜና የመታሰቢያ በዓል አላቸው፡፡ ከእነዚህ ዕለታት መካከል የትንሣኤ ሁለተኛ ቀን የሆነው ሰኞ "ማዕዶት" በሚል ስያሜ ይጠራል፡፡

ማዕዶት ማለት ዐደወ ተሻገረ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን መሻገር፣ መሻገሪያ፣ ድልድይ፣ መሰላል ማለት ነው፡፡

የነፍሳት ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከገሃነም ወደ መንግሥተ ሰማይ፣ ከኀሳር ወደ ክብር፣ ከሞት ወደ ሕይወት መሻገር የሚታሰብበት ስያሜና በዓል ነው፡፡

በብሉይ ኪዳን ሁለት ዐቢይ የመሻገር ታሪኮች አሉ፡፡ ፩ኛ እስራኤል ከግብጽ ወጥተው ባሕረ ኤርትራን ከፍለው መሻገራቸው ነው፡፡ ፪ኛ ከባቢሎን ምርኮ ሲወጡ ሰባት ወንዞችን (ኢሳ 11፥15) በታወቁት ባብና እና ፋርፋ የሚባሉ ወንዞችን ተሻግረው ሀገራቸው ኢየሩሳሌም መግባታቸው ነው፡፡ በዚህም ዕብራውያን ተብለዋል፡፡ ዐዳውያነ ፈለግ- ወንዝ ተሻጋሪዎች ማለት ነው፡፡

እስራኤል የነፍሳት አምሳል ናቸው፡፡ ግብጽና ባቢሎን የሲኦል አምሳላት ናቸው፡፡ ከፍለው የተሻገሯቸው ባሕረ ኤርትራ፣ ሰባቱ ወንዞች (ባብና እና ፋርፋ) የሲኦል አምሳላት ይሆናሉ፡፡ የጥምቀት አምሳላትም ይሆናሉ፡፡ ነፍሳት በጥምቀት ከሲኦል ወደ ገነት መሻገራቸውን ያሳያል፡፡ ምድረ ርስት የገነት፣ የመንግሥተ ሰማይ ምሳሌ ናት፡፡

የትንሣኤ ማግስት ሰኞ ማዕዶት የተባለበት ምክንያት እስራኤል ምሳሌ የሆኑላቸው ነፍሳት ከሲኦል ጨለማ ወጥተው ወደ ገነት ብርሃን በግባታቸውን፣ ከዲያብሎስ አገዛዝ ነጻ ሆነው ወደ ነጻነት አምላክ ወደ ክርስቶስ መቅረባቸውን ለማዘከር ነው፡፡

ነፍሳት ከሲኦል የወጡት ጌታ ተሰቅሎ ዓለምን ባዳነበት ዕለተ ዓርብ ነው፡፡ ስድስት ሰዓት ሲሆን ተሰቀለ፡፡ ዘጠኝ ሰዓት በሆነ ጊዜ በገዛ ሥልጣኑ ነፍሱን ከሥጋው ለየ፡፡ መለኮቱ ከሥጋውም ከነፍሱም ሳይለይ በሥጋ ወደ መቃብር ሲወርድ በነፍስ ወደ ሲኦል ወረደ፡፡ ለነፍሳትም ወንጌል ሰበከላቸው፡፡ የተወጋ ጎኑን፣ የተቸነከረ እጅና እግሩን በአምላካዊ ሥልጣኑ አሳያቸው፡፡ አምነው ጥምቀትና ቁርባን ሆኗቸው ስብሐት ለእግዚአብሔር ዘአውረሰነ መንግሥቶ ሰማያዊተ እያሉ በ፲፩ ሰዓት ገነት ገብተዋል፡፡

አዳምና ሔዋን ከገነት የወጡት በዕለተ ዓርብ በሰርክ ስለ ነበር በወጡበት ዕለት በዕለተ ዓርብ፣ በወጡበት ሰዓት በሰርክ ተመልሰው እንዲገቡ አድርጓቸዋል፡፡ ይህም ቤዛነት ነው፡፡ ማዕዶት የሚባል ይህ ዕለተ ዓርብ ነበር፡፡ ሆኖም የሰው ልጆች መዳን የተገለጠው በትንሣኤው ስለ ሆነ የትንሣኤው ዕለት ማዕዶት ተብሏል፡፡ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ፋሲካ ብሂል ማዕዶት- ፋሲካ ማለት መሻገር ነው እንዳለ፡፡ ድኅነት የተፈጸመው ዓርብ ሲሆን ሐዋርያ ጽድቅ ጳውሎስ የትንሣኤውን ቀን "የመዳን ቀን ዛሬ ነው" እንዳለው፡፡ (2 ቆሮ 6፥2) ነቢዩ ሆሴዕም አስቀድሞ "ከሁለት ቀን በኋላ ያድነናል" እንዳለ፡፡ (ሆሴ 6፥2) ሁለት ቀን ዓርብና ቅዳሜ ናቸው፡፡ ያድነናል ሲል በትንሣኤው ማለቱ ነው፡፡ ትንሣኤው በራሱ መዳን ቢሆንም ዓርብ ድኅነት አልተፈጸመም እያለን ግን አይደለም፡፡ ነቢዩ ከዚህ ቀጥሎ "በሦስተኛውም ቀን ያስነሣናል" በማለት ትንሣኤያችን በጌታ ትንሣኤ መረጋገጡን ይነግረናል፡፡

የትንሣኤ የራሱ ቃለ እግዚአብሔር አለው፡፡ ስለዚህ በትንሣኤው ከሚደረብ ብቻውን እንዲታሰብ ለማድረግ አባቶቻችን ከእሑድ ነጥለው በማውጣት ሰኞን ማዕዶት ብለው ደለደሉት፡፡

ለዚህ (ለማዕዶት) ምክንያቷ እመቤታችን ናት፡፡ ሊቁ አባ ሕርያቆስ "ኦ ማዕዶት ዘበኀቤኪ ዐደዉ አበው ቀደምት - የቀደሙ አባቶች የተሻገሩብሽ ድልድይ (መሰላል) ሆይ! ይላታል፡፡ በዚህች ድልድይ (መሰላል) የወዲያው ወዲህ የወዲሁ ወዲያ ይሻገርባታል፤ የላዩ ወደ ታች የታቹም ወደ ላይ ይወጣባታል በእመቤታችን ምክንያትም ከኀሳር ወደ ክብር፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት ተሽጋግረንባታልና፡፡

ሌላው ቅዱስ መስቀሉንም እንዲሁ መሻገሪያ ይለዋል፡፡ ኀዳፌ ነፍስ- በመስቀል ትርክዛው እየቀዘፈ ባሕረ እሳትን የሚያሻግር እንዳለ፡፡ በጥቅሉ ማዕዶት ስንል በክርስቶስ አሻጋሪነት በእመቤታችንና በቅዱስ መስቀል የመሻገራችን ምክንያትነት ተሻገርን፡፡ ይህንንም ማዕዶት ብለን እናስበዋለን፡፡

ሰሎሞን ላመስግን


በዚያን ጊዜ ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል፡፡ ሞት ሆይ! መውጊያህ የት አለ?
ሲኦል ሆይ! ድል መንሣትህ የት አለ? (1ኛ ቆሮ 15፥55)


እስመ ከመ ንጉሥ ዘቦቱ ጸብዕ ምስለ ዘይቴሐቶ ወየአምር ከመ ጸላኢሁ ይትመዋዕ ወበተመውዖቱ ይማስና አህጉር እንተ የኀልፍ ወበጥበቡ ዝኩ ንጉሥ ዓቢይ ረሰየ ርዕሶ እስከ መሰሎ ለጸላኢሁ ከመ ዝንቱ ንጉሥ ዓቢይ ተመውዐ እምፍርሃቱ ወውእቱሰ ሶበ ርእየ ዘንተ አኅድዐ ኅሊናሁ ወተአመነ በርዕሱ ወእምዝ ተመይጠ ንጉሥ ዓቢይ ኀበ እማንቱ አህጉር ወአግብኦን ውስተ ዕዴሁ ወለውእቱኒ መስተቃርን አኀዞ ወበርበረ ኵሎ ንዋዮ ወአብጠለ ኵሎ ግብሮ ወከማሁ ኢፈርሀ እምነ ሞት አስመ ነገሮሙ ቀዲሙ ለአርዳኢሁ እንዘ ሀለዉ ምስሌሁ በፍኖት ወይቤሎሙ እስመ ወልደ እጓለ እመሕያው ይገብእ ውስተ ዕደ ኃጥአን ወይሰቀል ወይትቀተል ወይትነሳእ እሙታን በሳልስት ዕለት ሃይ አበ ዘኤጲ ፶፭ ÷ ፲፫~፲፮

ትርጕም
ከወሬኛ ጠላት ጋራ ጠብ እንዳለው ገናና ንጉሥ ያ ገናና ንጉሥ ጠላቱ ድል እንዲሆን ድል በመሆኑም የሚዘምትባቸው ሀገሮች እንዲጠፉ ያውቃል ነገረ ግን ያ ገናና ንጉሥ በጥበቡ ራሱ ድል እንደተነሳ አደረገ ለጠላቱ ያ ገናና ንጉሥ እርሱን ከመፍራት የተነሳ ድል የተነሳ እስኪ መስለው ድረስ ጠላቱም ይህንን ባየ ጊዜ ተዘለለ በኃይሉም ታመነ ከዚህም በኋላ ያ ገናና ንጉሥ ወደነዚያ ሀገሮች ተመለሰና እጅ አደረጋቸው ጠላቱንም ያዘው ገንዘቡንም በረበረው ስራውንም ሁሉ አጠፋ እንደዚህም ሁሉ ጌታችን ሞትን አልፈራም በቢታንያ ጎዳና ሳሉ አስቀድሞ ለደቀመዛሙርቱ ነግሯቸዋልና ወልደ እጓለ እመሕያው በኃጥአን ሰዎች እጅ ይያዛል ይሰቀላል ይሞታል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ይነሳል ።
ሃይ አበ ዘኤጲ 55 :13-16




የድርገት ዕጣን

በቅዳሴ ጊዜ ፲፫ ዕርገተ ዕጣን አለ፡፡ ከእነዚያ መካከል በድርገት ጊዜ ሁለት ቀሳውስት አንዱ ሥጋውን አንዱ ደሙን እያጠኑ ይወርዳሉ፡፡ አንድ ቄስ ቢሆንም ሁለቱን (ሥጋውንም ደሙንም) ዕያጠነ ይወርዳል፡፡

ምሥጢሩ፦ መዓዛ መለኮቱ እንዳልተለየው ለማጠየቅ ነው፡፡ "አንድም" ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ሽቱ እያረበረቡ ለመገነዛቸው ምሳሌ ነው፡፡ ዐሥራ ሦስቱ ዕርገተ ዕጣን ምዑዝ መለኮት በሥጋ ዐሥራ ሦስቱን ሕማማተ መስቀልን ለመቀበሉ አምሳል ነው፡፡ (ቅዳሴ ሐዋርያት ትርጓሜ ፪፥፫)

ይህችን ቤተ ክርስቲያን ክርቶስን አታውቅም ሲሏት እንደምን አእምሮ ያደማል! ምን ያህል የአእምሮ ጉድለት እንዳለባቸው እያሰብን እናዝንላቸዋለን፡፡


ቅዳሜ ማለት ቀዳሚት ሰንበት (የመጀመሪያዋ ሰንበት) ማለት ነው
መጀመሪያነቷም ከሀዲስ ኪዳኗ ሰንበት ከእሁድ ነው
ይህችንም ቀዳሚት ሰንበትን እግዚአብሔር በመጀመሪያ፦ ዓለምን ፈጥሮ ጨርሶ አርፎባታል

ወአዕረፈ እግዚአብሔር እምኩሉ ግብሩ በሳብዕት እለት
እግዚአብሔርም በሰባተኛዋ ቀን ከስራው ሁሉ አረፈ
ዘፍ 2÷2
በሁለተኛ፦ በዚህ ምድር ሥጋ ለብሶ ሲመላለስ ሙታንን አስነስቶባታል ድውያንን ፈውሶባታል ለምጻሞችን አንጽቶባታል እውራንን አብርቶባታል

በሦስተኛ፦ ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር በልብሰተ ሥጋ ከተመላለሰ በኋላ በተለይም ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ወንጌልን ካስተማረ በኋላ በዕደ አይሁድ ተይዞ ተሰቅሎ ተገርፎ ሞቶ በመቃብር አርፎባት ውሏል

በአራተኛ ፦ በዓለም ፍጻሜ (ምጽዐት) የሰው ልጅ ሞቶ የሚያልቀው ዓርብ ነው ቅዳሜ የሰው ልጅ ሁሉ ከድካመ ሥጋ አርፎ ይውላል መሬትም አርፋ ትውላለች።

ይህችም ቀዳሚት ሰንበት ቅዳም ሥዑር ትባላለች
ቅዳም ሥዑር ማለትም የተሻረች ቅዳሜ ማለት ነው
ይህንን በመያዝ አንዳንድ ሰዎች የተሻረች ማለት ከበዓልነቷ መስሏቸው የስራ መስሪያ እለት የሚያደርጓት አሉ ይህ ግን ፈጽሞ ስሕተት ነው።
የተሻረች ማለት ግን ከመበላት ነው ፍትሐ ነገሥት ፍትህ መንፈሳዊ ሰንበታትን የሚያፆም ካህን ቢኖር ከክህነቱ ይሻር ይላል አን 15÷551
ስለዚህ በመጾም የተሻረች አለመጾሟ የተሻረባት መብል መጠጥ የተከለከለባት ማለት ነው ።

አክፍሎት፦ አክፍሎት ማለት ማክፈል ማለት ነው
ከምግብ ከመጠጥ ተከልክሎ ሳይበሉ ሳይጠጡ መዋል ይህንንም የጀመሩት ሐዋርያት ናቸው ሐሙስ ምሽት ጀምረው የተበተኑ ሐዋርያት ጌታ ከተሰቀለና ከሞተ ወደመቃብርም ከወረደ በኋላ ተሰብስበዋል ከዚህ በኋላም ሊመገቡ ሲሉ ከመካከላቸው አንዱ ያዕቆብ ጌታየ እሞታለሁ በሦስተኛው ቀን እነሳለሁ ብሏልና ትንሳኤውን ሳላይ አልነሳም አለ እርሱን አብነት አድርገው ሁሉም ሐዋርያት አክፍለዋል

የአክፍሎት ጊዜ ፦ የተቻለው ከሐሙስ ጀምሮ ያከፍላል ምክንያቱም ሐዋርያት ሐሙስ ምሽት በግዐ ፋሲካውን ከተመገቡ በኋላ እሑድ ነውና የተመገቡ ያልተቻለው ግን ዓርብ ይመገባል ቅዳሜን አክፍሎ ውሎ እሑድ አስቀድሶ የተቻለው ሥጋውን ደሙን ተቀብሎ ያልተቻለው ጸበሉን ጠጥቶ ይሔዳል

ሥርዐተ ቄጤማ ፦ በዚህች ዕለት አንዱና ጎልቶ የሚታወቀው ካህናትና ዲያቆናት በየቤቱ እየዞሩ ቄጤማ ያድላሉ ሲያድሉም አዳም ተመረመረ ዲያብሎስ ታሰረ እያሉ ነው ይህም ማለት የአዳምን ነጻ መውጣት የዲያብሎስን መጋዝ የሚያመለክት ነው ጌታ ተመረመረ ዲያብሎስ ታሰረም ይባላል ይህም ክርስቶስ በሄሮድስና በጲላጦስ ፊት ቆሞ ተመርምሮ ምንም እንዳልተገኘበት ለማመልከት ነው

ቄጤማ ፦ በኦሪቱ ብዙ በጎ ትውፊት አለው በኖኅ ዘመን ርግቧ ኀጸ ማየ አይኅ ነትገ ማየ አይኅ የጥፋት ውሃ ጎደለ ስትል ለኖኅ በአፏ ቀጤማ ይዛ መጥታለች
ካህኑም (ዲያቆኑ) ሐጸ ማየ ኃጢት ነትገ ማየ ኃጢአት የኃጢአት ውሃ ጎደለ ሲል ለሕዝቡ የምሥራች የለመለመ ቄጤማ ያድላል ።
መልካም የአክፍሎት ቀን 🌴🌴🌴🌴🌴🌴


👉 ልዩ ዕለት

የዛሬቱ ዕለት ከሁሉም ዕለታት ልዩ ዕለት ናት የድንቅ ምሥጢር መገለጫ ልዩ ዕለት
ወይእኅዛሁ ሰብዑ አንስት ለአሐዱ ብእሲ እንዲል ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይይዙታል ማለትም በሰባቱ ዕለታት ተፈጥረው የተመለኩ ፍጥረታት የአምላክን አምላክነት ይመሰክራሉ ማለት ነው የመሰከሩባት ልዩ ዕለት
አንድም ሰባቱ ተአምራት ተፈጽመው ጌትነቱን የሚሰብኩባት ልዩ ዕለት

➟ ፀሐይ የጨለመባት ልዩ ዕለት
➟ጨረቃ በደም የታጠበችባት ልዩ ዕለት
➟ከዋክብትም ጽናተቸውን የለቀቁባት ልዩ ዕለት
➟ካምስት መቶ ብቅ ከስድስት መቶ ዝቅ የሚሉ ሙታን ከመስቀሉ እግርጌ እንደ አሸን የፈሉባት ልዩ ዕለት
➟ መቃብራት የተከፈቱባት ሙታን የተነሱባት ልዩ ዕለት
➟ ድንጋዮች የተፈተቱባት ልዩ ዕለት
➟የቤተ መቅደሱ ከሦስት ካራት የተቀደደባት ልዩ ዕለት
➣ መድኀን ክርስቶስ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ሥጋው በፈቃዱ የለየባት ልዩ ዕለት
➣ ምእመንንም የሞሸረባት ልዩ ዕለት
➣ እጁን በደም ነክሮ ለኖረ ሽፍታ ወንበዴም ምሕረት የወረደባት
➣ገነት ለመጀመሪያ ጊዜ የተከፈተችባት ልዩ ዕለት ወዘተርፈ

በአጠቃላይ ከሰው ልጆች ይልቅ ደግሞ ግዕዛን የሌላቸው ፍጥረታት እግዚአብሔርነቱን የመሰከሩባት ልዩ ዕለት ናት

➣ እኛስ የፀሐይን ያህል መስክረን ይሆን ?
የጨረቃን ያህልስ እንባ አልቅሰን ደም ደም አልቅሰን እዝኅ በማለቅስ በእንባ በደም በመራጨት መስክረን ይሆን ?
የከዋክብትን ያህልስ መስክረን ይሆን ?
የሙታንን ያህልስ
የድንጋዮችን ያህልስ ልባችን ተሰንጥቆ ይሆን ?
የመጋረጃውን ያህል ምን ያህል ተብሰክስከን ይሆን ?
➟ ነገሩስ ከእነዚህ ሁሉ እንደምናንስ ምንም እንደማይሰማን ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ገልጾታል

እስኪ እንስማው
"ፀሐይ ሰኢኖ ጽዕለተ እግዚእ ጸዊረ ብርሃኖ ለጽልመት ሜጠ ወንሕነሰ እም ጽልመት አከይነ ወኢ እምልብነ ንፈቱ ንትነሳሕ መንጦላዕተ ቤተ መቅደስ እንዘ አልቦ ዘአበሰ ርእሶ ሰጠጠ ወንሕነሰ በእንተ ኀጢአትነ ኢተነሳሕነ ወኢ በልብነ ንፈቱ አጻብአ ፈረስ ወፀር ተንሢኦሙ አማሰኑ ብሔረነ ከመ ለእግዚአብሔር ፈሪሀነ ውስተ ንስሓ ንግባእ ወበዘሂ ኢተነሳሕነ ወኢደንገፅነ ንትነሳሕ እንከ"

➟ትርጉም
ፀሐይ እንኳ የጌታውን ስድብ መሸከም ተስኖት ብርሃኑን ወደጨለማ ለውጧል እኛ ግን ከጨለማ ከፍተናል ከልባችንም ንስሓ ለመግባት አልወድም የቤተ መቅደሱም መጋረጃ በደል ሳይኖርበት ራሱን ቀዷል እኛ ግን ስለኀጢአታችን ከልባችን ንስሓ ለመግባት አንወድም እግዚአብሔርንም በመፍራት ንስሓ ወደንስሓ እንድንመለስ የጠላትና የፈረስ እጣቶች ተነስተው ሀገራችንን አጥፍተዋል በዚህም ንስሓ አልገባንም ንስሓ ለመግባትም እንግዲህ አልደነገጥንም ።

ወንበዴውን የማረ ጌታ ይማረን

ከአብርሃም ፈቃዴ


የዕለተ ዓርብ አኗኗራችን የሚፈጸመው፦
ሥጋዊ ሕይወታችን የሕይወት እና የየኩነኔ ማኅተም በሆነው በሞታችን ሲዘጋ ብቻ ነው።
ሁሉንም የሚሽረው ሞት እና ጊዜ ነው
"ኲሉ ርዕስ ለሕማም ወኲሉ ልብ ለኃዘን-
ራስ ሁሉ ለሕመም ልብም ሁሉ ለድካም ይሆናል።"ኢሳ.፩፥፭


አራቱ የዓርብ መጻሕፍት
(የትኛውን መጽሐፍ እናንብብ ?)
፩, ➠ ጴጥሮስ ፦
መጀመሪያ በሐዋርያነት የተጠራ ጥሪውን አክብሮ ሁሉን ትቶ ከንድሙ እንድርያስ ጋራ የተከተለ
በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስም ሁለት ወንድማማች ጴጥሮስ የሚሉትን ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፥ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና እርሱም በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት ማቴ ፬ ÷ ፲፰

➠ ወልደ እግዚአብሔርነቱን ከሁሉ ቀድሞ የመሠከረ
እርሱም፦ “እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ፡” አለ።
ማቴ ፲፮÷ ፲፭
➠ ክርስቶስም ደግነቱን የመሰከረለት
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም ።
ማቴ ፲፮ ÷ ፲፯
➠ ከሁሉም ቀድሞ ከክርስቶስ ጋራ እንደሚሞት የተናገረ
ጴጥሮስም መልሶ ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እኔ ከቶ አልሰናከልም አለው ማቴ ፳፮ ÷ ፴፫

➠ ከሁሉም ቀድሞ ክርስቶስን የካደው
ጴጥሮስም ከቤት ውጭ በአጥሩ ግቢ ተቀምጦ ነበር፤ አንዲት ገረድም ወደ እርሱ ቀርባአንተ ደግሞ ከገሊላው ከኢየሱስ ጋር ነበርህ አለችው እርሱ ግን፦ “የምትዪውን አላውቀውም ብሎ በሁሉ ፊት ካደ ወደ በሩም ሲወጣ ሌላይቱ አየችውና በዚያ ላሉት ይህ ደግሞ ከናዝሬቱ ከኢየሱስ ጋር ነበረ አለች ዳግመኛም ሲምል ሰውየውን አላውቀውም ብሎ ካደ ጥቂትም ቈይተው በዚያ ቆመው የነበሩ ቀርበው ጴጥሮስን አነጋገርህ ይገልጥሃልና በእውነት አንተ ደግሞ ከእነርሱ ወገን ነህ አሉት
በዚያን ጊዜ ሰውየውን አላውቀውም ብሎ ሊራገምና ሊምል ጀመረ ወዲያውም ዶሮ ጮኸ ማቴ ፳፮ ÷ ፷፱~፸፭

➠ ፈጥኖ እራሱን በንስሓ የመረመረ
ጴጥሮስም፦ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ያለው የኢየሱስ ቃል ትዝ አለው ወደ ውጭም ወጥቶ መራራ ልቅሶ አለቀሰ ማቴ ፳፮ ÷ ፸፭

፪, ይሑዳ ፦
➠ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ሆኖ የተመረጠና የተጠራ
ቀነናዊውም ስምዖን ደግሞም አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ ማቴ ፲ ÷ ፬
➠ የገንዘብ ቤት (ሙዳየ ምጽዋት) ሹም ያደረገው
ቍራሽም ከተቀበለ በኋላ ያን ጊዜ ሰይጣን ገባበት እንግዲህ ኢየሱስየምታደርገውን ቶሎ ብለህ አድርግ አለው ነገር ግን ከተቀመጡት ስለ ምን ይህን እንዳለው ማንም አላወቀም ይሁዳ ከረጢቱን የያዘ ስለ ሆነ ኢየሱስለበዓሉ የሚያስፈልገንን ግዛወይም ለድሆች ምጽዋት እንዲሰጥ ያለው ለአንዳንዱ መስሎአቸው ነበርና እርሱም ቍራሹን ከተቀበለ በኋላ ወዲያው ወጣ፤ ሌሊትም ነበረ
ዮሐ ፲፫ ÷ ፳፯~፴
➠ አባቱን የሰለበ እናቱን ያገባ መምህሩን የሸጠ
3: ስለዚህ ይሁዳ ጭፍሮችንና ከካህናት አለቆች ከፈሪሳውያንም ሎሌዎችን ተቀብሎ በችቦና በፋና በጋሻ ጦርም ወደዚያ መጣ ኢየሱስም የሚመጣበትን ሁሉ አውቆ ወጣና ማንን ትፈልጋላችሁ አላቸው የናዝሬቱን ኢየሱስን ብለው መለሱለት። ኢየሱስ እኔ ነኝ አላቸው። አሳልፎ የሰጠውም ይሁዳ ደግሞ ከእነርሱ ጋር ቆሞ ነበር እንግዲህ እኔ ነኝ ባላቸው ጊዜ ወደ ኋላ አፈግፍገው በምድር ወደቁ ደግሞም ማንን ትፈልጋላችሁ? ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም የናዝሬቱን ኢየሱስን አሉት ኢየሱስ መልሶ እኔ ነኝ፡ አልኋችሁ፤ እንግዲህ እኔን ትፈልጉ እንደ ሆናችሁ እነዚህ ይሂዱ ተዉአቸው አለ ...................እንግዲህ የሻለቃውና ጭፍሮቹ የአይሁድም ሎሌዎች ኢየሱስን ይዘው አሰሩት፥
ዮሐ ፲፰ ÷ ፫~፲፫
➠ ንስሓን ጠልቶ በብልጠት ገነት ለመግባት የሞከረ
መፍቀረ ንዋይ ኘውና እርሱን በሠላሳ ብር ሸጬ እኔ ገንዘቤን አገኛለሁ እርሱም በተአምራት ይድናል ብሎ ነበር በተአምራት እንዳልዳነ ሠከራው እንደጸናበት አይቶ አይሁድን ገንዘባችሁን እንኩ እርሱን ግን ልቀቁት አለ አይሁድም ለአንተ የምትፈልገውን ሰጥተንሃል አንተም የምትፈልገውን አግኝተሃል እኛ ከአንተ አንተ ከእኛ ምን አለህ ? አሉት እርሱም ደንግጦ ራሱን ለማጥፋት ገመድ ይዞ ወደዛፍ ሄጀ ዘፏም አንደወንድምህ ጴጥሮስ ንስሃ ግባ አለችው እንቢ ብሎ ወደሌላ ዛፍ ሄደ እታነቃለሁ ሲል ወድቆ ቆሰለ በአርባኛው ቀን ሞተ ።
ይህ ሁሉ ግን ብልጠት ነበር ምክንያቱም ክርስቶስ ሞቶ ሲኦልን እንደ ሚበረብር ያውቅ ነበርና ቀድሞ ሲኦል ገብቶ ከነፍሳት ጋራ ለመውጣት ነበር ኃሳቡ
ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ
ማቴ ፳፯÷፭
፫, ዳክርስ ( ፀጋማይ በጌታ ግራ የተሰቀለ)
➠ ይህ ዳክርስ ጌታ ከመወለዱ አስቀድሞ በሽፍትነት የኖረ እንደ ይሁዳ ፍቅረ ንዋይ ያለበት እመቤታችንና ጌታ ወደግብፅ ሲሰደዱ ልብሳቸውን ቀምቶ አልሰጥም ያለ ጥጦስን (ጓደኛውን) አንተ አዳምን ቀድመህ ገነት ትገባለህ ሲለው የተዘባበተ ነው ።

➠ ኋላም ሠላሳ ሦስት አመት ከሦስት ወር በሽፍትነት ኖሮ ክርስቶስ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ አምላኪየ አምላኪየ እያለ ሲጮኽ ጥጦስ አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ ሲል እራሱን ማዳን ተስኖት ይጮኻል ስንኳን አንተን ሊያድን ብሎ የተዘባበተ መጨረሻም ወደተበረበረች ሲኦል ብቻውን የገባ ነው ።

፬, ጥጦስ ( የማናይ በጌታ ቀኝ የተሰቀለ)
➠ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በሽፍትነት የኖረ የጌታንና የእመቤታችንን ልብስ የቀማ ግን ራርቶ በእርሱ ልብስ ከዳክርስ ቀይሮ የእነርሱን ልብስ የመለሰ ነው ።

➠ እመቤታችን ልግዝሽ ብሎ ጌታን በትክሻው ተሸክሞ የሸኜ ሲሸኝ የእጁ ሰይፍ ተሰብሮበት በተአምራት ክርስቶስ እንደነበረው ያደረገለት የተሸከመበት ደመወዙ በከንቱ እንዳይቀርበት ልብሱን ሲያጥብ ሦስት መቶ ወቄት ወርቅ የሚያወጣ ገንዘብ ያገኘ ከዚያም አያይዞ አዳምን ቀድመህ ገነት ትገባለህ የሚል ተስፋ የሰነቀ ነው ።

➠ በኋላም ክርስቶስ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ ሳለ የሙታንን መነሳት የመጋረጃውን መሰንጠቅ የአዕባንን መሰነጣጠቅ የመቃብራትን መከፈት የከዋክብትን መርገፍ የፀሐይን መጨለም የጨረቃን ደም መሆን አይቶ ተዘከረኒ በውስተ መንግሥትከ በጌትነትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ ያለ ክርስቶስም ዛሬ ከእኔ ጋራ በገነት ትኖራለህ ያለው ነው።

ኢየሱስንም ጌታ ሆይ፥ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ አለው ኢየሱስም እውነት እልሃለሁ፥ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው ሉቃ ፳፫ ÷ ፵፪ ~፵፬
( የትኛውን መጽሐፍ እናንብ?)



Показано 20 последних публикаций.