#Update
የጤና ተመራቂዎች የሙያ ብቃት ምዘና (COC) አመልካቾች ምዝገባ ከነገ የካቲት 22/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ቀናት ክፍት እንደሚሆን ይጠበቃል።
የሙያ ብቃት ምዘና ለመውሰድ እየጠበቁ የሚገኙ የጤና ተመራቂዎች ምዝገባ በየካቲት መጀመሪያ ለማከናወን ዕቅድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች መዘግየት አጋጥሟል።
አሁን ላይ አጋጥመው የነበሩ ችግሮች መፍትሔ በማግኘታቸው ከነገ ቅዳሜ የካቲት 22/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ጥቂት ቀናት የአመልካቾች ምዝገባ (በድጋሜ ተፈታኞችን ጨምሮ) እንደሚደረግ ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
@tikvah_tena