ፕሮፌሰር አደም ካሚል ፋሪስ ኢትዮጵያን ወክለው አሸነፉ
የዳእዋ እና የጥናት ማህበር በአፍሪካ
ድርጅቱ የሚመራው በልኡል ዶክተር በንደር ቢን ሰልማን ቢን ሙሃመድ የሳውድ አረቢያ ንጉስ አማካሪ ሲሆኑ ይህ ድርጅት ከተቋቋመ 28 አመት አስቆጥሮዋል :: በየአመቱ የአፍሪካ ታዋቂ ሊቃውንቶችን እና አዋቂዎችን በመጋበዝ ኮንፍረንሶች
ያካሂዳል የዘንድሮው የ29ኛው የድርጅቱ እቅድ “ እስልምና በአፍሪካ ” በተመለከተ ጥናቶች በማሰባሰብ ትልቅ “ ኢንሳይክሎፒዲያ ” ለማዘጋጀት ያቀደ ስለሆነ በዲሴምበር 30 2019 በአፍሪካ በተለያዩ ሀገራት ለሚኖሩ ሊቃውንቶች
እስልምና እና አፍሪካን በተመለከተ ጥናት እንዲያደርጉ እና በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ለድርጅቱ እንዲያቀርቡ ጥያቄ የቀረበ ሲሆን ኢትዮጵያን በተመለከተ ፕሮፌሰር አደም ካሚል ፣ ዶክተር አብደላህ ኸድር እና ሼኽ ሙሀመድ ሀሚዲን የተመረጡ
ሲሆን የጥናት ርእስ ክፍፍል በተደረገው መሰረት ፕሮፌሰር አደም ካሚል የሚከተሉትን ርእሶች እንዲይዙ ተደረገ :
አንደኛ : ኢትዮ አረብ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት
ሁለተኛ : ኢስላማዊ ስደት ወደ ሀበሻ አላማው እቅዱ እና ውጤቱ
ሶስተኛ : እስልምና በኢትዮጵያ የሚሉ ናቸው ::
እነኚህን ርእሶች በተመለከተ አስፈላጊውን መረጃዎች በማሰባሰብ ከ50 ገጽ ያላነሰ ጥናት በማዘጋጀት ለድርጅቱ እንዲደርሰው ተደረገ ድርጅቱም ከያንዳንዱ የአፍሪካ ሀገራት የቀረቡለትን ጥናቶች በመገምገም የሚከተለውን ደረጃ ለመስጠት ችሎዋል ::
አንደኛ ደረጃ : ኢትዮጵያ 9619 ነጥብ በማምጣት
ሁለተኛ ደረጃ : ናይጄሪያ 9476 ነጥብ በማምጣት
ሶስተኛ ደረጃ : ታንዛኒያ 4883 ነጥብ በማምጣት
አራተኛ ደረጃ : ማሊ 4367 ነጥብ በማምጣት
አምስተኛ ደረጃ : ሴኔጋል 4074 ነጥብ በማምጣት
በዚህ ውጤት እንደ ሀገር ኢትዮጵያ የምታገኘው እድል የሁጃጆች ቁጥር ከዚህ ቀደም ከነበረው ኮታ የሚጨምርበት እድል መኖሩን ድርጅቱ አስታውቆዋል ::
በመጨረሻም ለውድ ባልደረቦቼ ዶክተር አብደላህ ኸድር ; ሼኽ ሙሀመድ ሀሚዲን እንዲሁም ፉአድ ኸሊፋ እንኩዋን ደስ አላችሁ ልፋታችሁ ውጤት አፍርቶዋል በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ::
ፕሮፌሰር አደም ካሚል ፋሪስ