Remedial HUB


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


👩‍🏫በ2016 ሬሚዲያል(ማካካሻ) ትምህርት ለሚወስዱ ተማሪዎች ተበሎ የተከፈተ ቻናል!

Buy ads: https://telega.io/c/Remedial_Hub

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ውጤት ይፋ ሆኗል።

በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች ውጤት ተለቋል።

ተማሪዎች ውጤታችሁን በተከታዩ ሊንክ አማካኝነት መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

👇👇👇👇👇
https://result.ethernet.edu.et/

@Remedial_Hub

4.7k 0 159 183 76

🏆 Remedial HUB Special Class ምዝገባ በይፋ ተጀምሯል

🔛Remedial special Class ምንድን ነው?

ይሄን ይጫኑ 👉 Click here

🔺 ከአሁኗ ሰአት ጀምሮ መመዝገብ ትችላላችሁ

📲 ለመመዝገብ ይሄን Bot ይጠቀሙ :-
@RemedialHubBot

✈️ @Remedial_Hub


📣ሰለ REMEDIAL HUB ቲቶሪያል ሙሉ መረጃ እነሆ

➡️ REMEDIAL HUB ቲቶሪያል ምንድነው?

✅ መልስ:- Remedial Hub ቲቶሪያል ለ 2017 ሪሚዲያል ተማሪዎች ተብሎ የተከፈተ የትምህርት ማዕከል ነው።
@Remedial_Hub ✈️

➡️ ትምህርቱን እንዴት ያስተምራል?

መልስ :-እንደምናውቀው በሀገራችን አብዛኞቹ  ተማሪዎች Smartphone ተጠቃሚዎች ቢሆንም የInternet ተደራሽነት ውስን በመሆኑ በአንድ ግዜ የራሳችንን platform ተግባራዊ ማድረግ ለበርካታ ተማሪዎች ተደራሽ ለማድረግ እና ሁሉንም ያካተተ እንዲሆን በቂ የinternet connection አስፈላጊ ሆኗል።ለዚህም ቀላል መንገድ ቴሌግራም ነው። በዚህም  private የtelegram Channel በመክፈት ልምድ ባላቸው አስተማሪዎች ትምህርቶችን ቀላል እና ምቹ ለማድረግ እንዲሁም አሳታፊ እንዲሆን እንደየትምህርት አይነት ባህርይ👇

🔺በቂ ኖት እና አጋዥ መፅሐፍ ማቅረብ፣
🔺በ 4k video  ማብራሪያ ማቅረብ፣
🔺በተቻለ መጠን ጥያቄዎችን ከእነማብራሪያቸው ቀለል እና ግልፅ በመሆነ መሉኩ በቪዲዮ እናስረዳለን።

@Remedial_Hub ✈️


➡️ ትምህርቱን እንዴት መከታተል እችላለሁ?

መልስ:-  ትምህርቱን ማንኛውም telegram Application ያለው ሰው እና የtelegram ተጠቃሚ የሆነ ሰው መከታተል ይችላል።
ለመከታተል በመጀመሪያ መመዝገብ ያስፈልጋል፣በትክክል ስትመዘገቡ ትምህርቱ የሚሰጥበት ቻናል link ይደርሳል፣ ያንን link Join በማድረግ ብቻ መከታተል ትችላላችሁ።


@Remedial_Hub ✈️

❌ያልተመዘገበ ሰው በምንም መልኩ መከታተል አይችልም!

➡️ አንዴት ያለፈውን ትምህርት እንዴት ማግኘት እ
ችላለሁን ?

✅መልስ:- ከላይ  እንደተገለጸው  ትምህርቶቹ የሚ
ቀርቡት በቀጥታ ስርጭት ስላልሆነ አንዴ የቀረበውን ትምህርት እስከፈተናው ቀን ድረስ እዛው ቻናል ውስጥ ስለሚኖር በፈለጋችሁት ሰዓት እና ቦታ ማግኘት እና ማንበብ ትችላላችሁ።

@Remedial_Hub ✈️


📚ምዝገባ በቅርብ ቀን ይጠብቁን!

@Remedial_Hub

11.6k 0 21 157 131

የአብዛኛዎቻቹ ጥያቄ 🤔

የሬሚዲያል መቁረጫ ነጥብ ስንት ነው


መልስ:- እስካሁን ባለን መረጃ መሰረት የሪሚድያል መቁረጫ ነጥብ ከትምህርት ሚኒስቴር ይፋ እንዳልሆነ ነው። ነገር በቅርብ ቀን ይፋ እንደሚሆን ጥርጥር የለንም! ይፋ እንደሆነ ወዲያው የምናሳውቃችሁ ይሆናል ።
😊

@Remidial_2016 ❤️

13.1k 0 42 291 257

"Remedial Hub Tutorial Is coming"

@Remedial_Hub 💙


ከ 600 ለተፈተናችሁ አብዛኛዎቻችሁ ተማሪዎች ግራ እንዳያጋብችሁ መጥነን አቀረብንላቹ ! ላለፉ ሁለት ዐመታት ከ 600 የተፈተኑ መደበኛ የተፈጥሮ ተማሪዎች ስላልነበሩ የ ከ 700 የተፈተኑትን እንድታስተያዩ አቅርበንላችኋል!

©️Qesem Academy

@Remedial_Hub 💙

18.1k 0 267 407 132

📮የ Remedial መቁረጫ ነጥብ ስንት ሊሆን ይችላል ? [( አስታውሱ ግምት ብቻ ነው}

ለሁለት ዓመታት ከነብረው መረጃ በመነሳት የ 2016 ዓ.ም መቁረጫ ነጥብ እንደሚከተለው ይሆናል ብለን እንገምታለን!


💡 የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችል እድል ነው። አዲስ የፈተና ስርዓት ከወጣ ጀመሮ ይህ ፕሮግራም ለሁለት ዓመታት ለተማሪዎ
ች ሲሰጥ እንደነበር እናስታውሳለን! ትናንት በተሰጠው መግለጫም የትምህርት ሚንስቴሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፣የ Remedial Program እንደሚኖር ነገር ግን ካለፉት ዓመታት ያነሱ ተማሪዎችን እንደሚቀበሉ ተናግረው እንደነበር አይረሳም!

📚ስለ Remedial መቁረጫ ነጥብ ምንም የተባለ ነገር ባይኖርም ፣ ያለፉትን ሁለት አመታት መቁረጫ ነጥቦች እናይና ፣ የዘንድሮ ምን ሊሆን እንደሚችል በግምት እንደሚከተለው ለማስቀመጥ እንሞክራለን! አስታውሱ ከመንግስት ምንም የተባለ ነገር የለም ፣ ይህ የኛ ግምት ብቻ ነው። ከዚህ ከፍም ዝቅም ሊል ይችላል! ከዚህ በመነሳት የ 2016 ዓ.ም መቁረጫ ነጥብ እንደሚከተለው ይሆናል ብለን እንገምታለን!( አስታውሱ ግምት ብቻ ነው!)

©️Qesem Academy

@Remedial_Hub 💙

17k 0 157 59 84

2️⃣0️⃣1️⃣7️⃣

🌼 መልካም አዲስ ዓመት 🌼


Репост из: Freshman exams
biology entrance exam (astu-aastu) 2012-13.pdf
2.5Мб
📚Addis Ababa University መግባት ለምትፈልጉ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከዚ ቀደም ASTU & AASTU Biology መግቢያ ፈተና


@Qesem_Freshman ❤️


Репост из: Freshman exams
General psychology Freshman.pptx
5.2Мб
Phycololgy power point.pptx
466.2Кб
General Psychology Slides.pptx
2.1Мб
ለ Remedial ተማሪዎች

💢 Psychology 👌


Psychology ትምህርትን እንደኔ Lower grade ላይ ብንማረው ኖሮ እንደዚህ ግራ የገባው ትውልድ ባላፈራን ነበር 🤗 አሁንም ግን አልረፈደም ይሄው ይቺን ክረምት ቀጥቅጣቹ አንብቡት በተለይ ደግሞ Wolaita SODO እና Dilla University ውስጥ የ Remedial program የወሰዳቹ ልጆች ቀጣን First semester Psychology ስለምትማሩ ካሁኑ ተዘጋጁበት።

@Qesem_Freshman
@Qesem_Freshma
n


ቀጣይ ዓመት ፍሬሽማን ተማሪዎች ናችሁ

ብዙ ተማሪዎች ግቢ ገብተው ሚቸገሩበት ትልቁ ነገር አስፈላጊዉን መረጃ እና material  በጊዜው ማግኘት አለመቻል ነዉ😔 ለዚህም ነዉ ይህ ቻናል ለተማሪዎች በጣም ጠቃሚ የሆነው::

በዉስጡ
🔻🔸
የእያንዳንዱን ግቢ mid እና final exam
ስለ ዲፓርትመንት መረጃ
Module
Power point
Lecture slide
Study materials

በቃ ምን አለፋችሁ ሁሉንም በአንድ ላይ ምታገኙበት ፅድት ያለ ቻናል


✍️አሪፍ ዉጤት መስራት ከፈለጋችሁ የግድ ያስፈልጋቿልቅ ተቀላቀሉ ⬇️⬇️

@Qesem_Freshman ❤️
@Qesem_Freshman ❤️
@Qesem_Freshman ❤️


እምቢ በሉ (say NO)

ይህ መልዕክት ለእዉነት፤ለእውቀት እና ለፍትህ ዉዴታ ለሚሰማቸዉ፤ መጠቃትን፣መታለልንና ማስመሰልን እምቢ ለሚሉ ወገኖች  የቀረበ ነዉ።

ኤክስትሪም የተማሪዋች አጋዝ መጽሐፍት ላለፋት ሁለት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ግዜ በተማሪዋች የትምህርት እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ በጎ ተጽዕኖ ያሳደረ፣ የመምህራንን ሸክም ያቀለለ፣ በተማሪዋችም ዘንድ የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጡት አጋር የትምህርት መሳሪያቸዉ ነዉ።

በኤክስትሪም መጽሐፍቶች ተጠቅሞ ያፈረ የለም። ክልላዊም ሆነ ሀገር አቀፍ ፈተናዋች ዋነኛ ማጣቀሻቸዉ አድርገዉት እንደሚጠቀሙበትም የአደባባይ ሚስጢር ነዉ። ይህ ሁሉ የሆነዉ በጠንካራ የስራ ዲስፕሊን መስራት ስለተቻለና የብዙሀኑ ተጠቃሚዋችም ቀና ድጋፍና ትብብር ስላለ ነዉ።

እንዲያም ሆኖ ለእውቀት፣ ለሌሎች ሰዋች ሀቅ፣ለእውነትና ለፍትህ ያልቆሙ ከዚያ ይልቅ በሌሎች ስኬት ላይ በመጠላጠል መክበር የሚሹ አንዳንድ ወገኖች የመጽሐፎቻችንን ኤሌክትሮኒክስ ቅጅዋች በማዘጋጀት ካለ እኛ ፈቃድና ይሁንታ በተለያዩ የማህበራዊ መድረኮች ላይ ያለ አግባብ በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ።

እንዲህ መሰሉ ተግባር በአዕምሮአዊ ምዝገባ ባለስልጣን ተመዝግቦ በሚገኝ የንግድ ተቋም ላይ የሚደረግ ጥቃት በመሆኑ በህግ የሚያስጠይቅ ተግባር መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በዛዉ ልክ ደግሞ ባለማወቅና በመደናገር በመሰል ተግባር ላይ የተሰማሩ አይጠፋምና ከህገወጥ ተግባራቸዉ እንዲታቀቡ እንጠይቃለን።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ለመላዉ የኤክስትሪም መጽሐፍት ተጠቃሚዋችና አድናቂዋች ደግሞ የእምቢ በሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

📖 በህገወጥ መንገድ የሰዉን ስራ ለሚያሰራጩ ሰዋች ተግባር እምቢ በሉ

📖 በሌሎች ላብና ድካም ለመበልፀግ ለሚታትሩ ሰዋች ስራ ተባባሪ  ባለመሆን እምቢ በሉ

📖 ቴሌግራምን ጨምሮ በሌሎችም የማህበራዊ ትስስር ገፃች ለሚተላለፉ የሐሰትና የማጭበርበር ተግባራት ተሳታፊ ባለመሆን እምቢ በሉ

📖 ባልተሟላ ፣ ደረጃዉን ባልጠበቀና ወቅታዊ ማስተካከያ ባልተደረገባቸዉ ሆኖም በኤክስትሪም መጽሐፍት ስም ለሚሰራጬ የትኞቹም መረጃዋች ከሀቅና እዉነት ጎን በመቆም እምቢ በሉ

አዋ ዛሬም እንደከዚህ ቀደሙ ደረጃቸዉን የጠበቁ፣ጊዜዉ የደረሰበትን እውቀት ያካቱ፣ በየጊዜዉ ወቅታዊ ማስተካከያ የሚደረግላቸዉና ሁሉን በሁሉ የሆኑ የኤክስትሪም መጽሐፍቶቻችንን በላቀ የህትመት ጥራትና መጠን ማዳረሳችንን እንድንቀጥል ለእዉነት፤ለእውቀት እና ለፍትህ ዉዴታ ያላችሁ ሁሉ መጠቃትን፣መታለልንና ማስመሰልን እምቢ በማለት የተሳሳተ መረጃና መጽሐፍት በስማችን ከሚያሰራጩ ወገኖች እንድትጠበቁና እኩይ ተግባራቸዉን እንቢኝ በማለት ከእኛ ጎን እንድትቆሙ አጥብቀን እንጠይቃለን። ስላገለገልናችሁና ወደፊትም ስለምናገለግላችሁ ኩራት ይሰማናል። እናመሰግናለን።

CEO of Extreme book series
Arebu Abdella


Репост из: Freshman exams
ከ የት ፊልድ ብገባ ለኔ ይሻለኛል ?

🔰 በ ቀለሜ  የተዘጋጀ !


📌 ብዙወቻችን ከ final ፈተና ይልቅ በጣም ሚያጨናንቀን የት field ብንገባ የተሻለ እንደሆነ ማወቁ ላይ ነው? እንትን field መግባት እንፈልጋለን ግን ተመረቀን ወጠን ያለው የ ስራ ሁኔታ ያሳስበናል .... የሆነ ፊልድ ደግሞ ጥሩ ብር እና ስራ ያስገኛል ግን አንፈልገውም..... የ እኛ ፍላጓት ከ ምንፈልገው ፊልድ መግባት ነው ግን ቤተሰብ ሚፈልገው ከየላ እንድንገባ ነው .....ብቻ በ ብዙ ነገሮች ለመምረጥ በጭንቀት እንወጠራለን !  ከዚ ፊልድ ግቡ የማለት ሞራሉ ባይኖረኝም እኔ ያሳለፍኩት ነገር ስለሆነ በዚ ጉዳይ ዝም ከምል ትንሽ የቤተሰብነቴን ልበላችሁ ።

🎯 ከ መምረጣችሁ በፊት እነዚህን ከ ግምት ውስጥ አስገቡና እራሳችሁን ጠይቁ።

✳️ 1. ፍላጓት !

📌 በመጀመሪያ አንድን ፊልድ ለመምረጥ ከ መወሰናችን በፊት እውን ለዚያ የተለየ ፍቅር አለን? እናንተን የዛሬ ምናምን ዓመት የት ብታገኙት በራሳችሁ ትኮራላችሁ?  በቃ እኔ ወደዚች ምድር የመጣሁት ለዚ የስራ ዘርፍ ነው የምትሉትን ያዙ .......

✳️2. እራስን ማወቅ !

ይህ ወሳኝ ነጥብ ነው እራስን ማወቅ ..... የ ሂሳብ ትምህርቶች ናቸው ወይስ የ ኮንሴፕት (ሽምደዳ ) ትምህርቶች ናቸው  አናንተን ተሎ የሚገቧችሁ ?  ቁጭ ብሎ የማንበብ ባህሉ አላችሁ ወይስ አንዴ ከ ገባችሁ ድጋሚ ማየት አትፈልጉም ?  በረባ ባረባው ጭንቀታም ናችሁ ?  ...... ብዙ ነገሮችን እራሳችሁን ጠይቃችሁ እወቁ! .............እና አሁን እራሳችሁን አወቃችሁ የትኛው የ ሙያ ዘርፍ  ነው ከናንተ ጋር ሚሄድ ?  .................... ምንም እንኳን የ ናንተ ክህሎት ለምትፈልጉ ፊልድ አነስተኛ ቢሆንም ዋናው ነገር ፍላጓት ስለሆነ ፤ ሁሉም ነገር ደግሞ የሚለመድ ነውና ፍላጓታችሁን ከ ምትፈልጉት ፊልድ ጋር ትንሽም ቢሆን ራሳችሁን በማመዛዘን ለመምረጥ ብታስቡ የተሻለ ነው።

🎯 ከዚህ ላይ የኔን ሀሳቦች ላስገባ  ብዙዎችችን ሜዲስን ና  ጤና ነክ መግባት እንፈልጋለን ለምን ሲባል  ቅጥር አላቸው እና በ ማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይ ስለሆኑ።...... ዶ/ር ፣ ነርስ  ሲባልና  Engineer ሲባል የትኛው ባሁን ዘመን ክብር እንዳለው ለናንተ ልተወው... ግን ጤና እንደምናስበው አደለም ትልቅም ይሁን ትንሽ የ ጤና ፊልድ ከ ሁሉ የበለጠ ቁጭ ብሎ ማንበብን ይጠይቃሉ ፣ አስተዋይ በትምህርት ብቻ ሳይሆን በ አስተሳሰብም ብልህ የሆነ ሰው። ጤና ለመግባት i was asking Doctors እና ያሉኝ " ብር ምትፈልግ ከሆነ ሀሳብህን ቀይር ብር ብቻ እያሰብክ ድካሙን መቋቋም ስለማትችል ለ ምን Accounting አትማርም ባንኮች በጥሩ ገንዘብ ይቀጥሩህ አይደል..... ግን ሰውን ለመርዳት እና በነሱ መዳን  ውስጥህን የ ሚያስደስትህ ከሆነ ትግስተኛ ከሆንህ ጤና ግባ " ነበር ያሉኝ ...... እውነት ነው ብዙ ጓደኞቸ በሰው ግፊት ና ለ ቅጥር እያሉ ማይፈልጉት ና ከነሱ ጸባይ ጋር የማይሄድ ፊልድ ገብተው still now ሲያማርሩ ነው የማያቸው ። ጊዜ ያልፋል ነገ የ ሚመጻው ዘመን ደግሞ አይታወቅም ። በ መጨረሻም እንድትረዱት የምፈልገው ሁሉም ፊልድ ላይ ደስ ብሎን እየተማርን ፣ ጥሩ ውጤት መስራት ከቻልን ና በተማርነው ማህበረሰቡን የሚጠቅም ስራ ከሰራን እንደኛ ውጤታማ ሚሆን የለም ሁሉም ነገር Depend ሚሆነው በኛው ስለሆነ።

❗️መማራችሁ ካልቀረ የተሻሉ የሚባሉ የትምህርት መስኮችን ብትመርጡ ይሻላል ....ግን ከላይ የተዘረዘሩትን ነገሮችንም Consider አድርጉ ለማለት ነው።😊

በዚህ ጉዳይ ሀሳብ ካላችሁ Comment ላይ አስቀምጡ እንወያይበት .....

@Qesem_Freshman ❤️


Репост из: Freshman exams
ከትንሽ ጊዜ በኃላ ዩኒቨርስቲ ምርጫ እንድትሞሉ ትጠየቃላቹ፡፡  ዓምና ውጤት ከመጣ በኃላ በድጋሚ ዩኒቨርስቲ ምርጫቸውን እንዲያስተካከሉ እድል ተሰቶዋቸው ነበር ፤ በዚህ ዓመት ከተቀየረ አናቅም፡፡

ዩኒቨርስቲ ለዓመታት የምትቆዩበት ስለሆነ ፤ ዩኒቨርስቲ ስትመርጡ እነዚህን ማወቅ አለባቹ:

1. የምትመርጧቸው ዩኒቨርስቲዎች የምትፈልጉት field/department እንደሚሰጡ ማወቅ አለባቹ ይሄ ዋነኛው ነው። መማር የምትፈልጉትን field/department  ካልወሰናቹ ካሁኑ shortlist አድርጓቸው፡፡

2. ስለዩኒቨርስቲው ትምህርት ጥራት በተለይ እናንተ መማር የምትፈልጉት field/department  በደንብ አጣሩ፡፡

3. የምትመርጧቸውን ዩኒቨርስቲዎች እና ከተማውን youtube ላይ እዩ ፤ እዛ ዩኒቨርስቲው ውስጥ የሚማር ተማሪ ሰው በሰው ጠይቁ፡፡ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ወንድም / እህት ካላቹ ከእነሱ ጋር High school አብረው የተማሩ ሌላ ጊቢ የደረሳቸው ተማሪዎች ስለሚኖሩ እነሱ ሊያጠያይቁላቹ ይችላሉ፡፡

4. እንደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ (AAU) በጣም ሀሪፍ የሚባሉ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በጣም ተፈላጊ የሆኑ department እንደ Medicine, Software Engineering መግባት በጣም ከባድ ነው፡፡ ውጤት በደንብ ካልሰራቹ በስተቀር በጣም ተፈላጊ የሆነ department የማግኘታቹ እድል ጠባብ ነው ፤ ስለዚህ የመጀመሪያ ምርጫቹ ያልሆነ department ውስጥ ልትመደቡ ትችላላቹ፡፡

5. ዩኒቨርስቲ ምርጫ ስትሞሉ ከክፍል ጓደኞቻቹ ወይም ዩኒቨርስቲ ከሚማር ወንድም/እህታቹ ጋር አብሯቹ ሙሉ። የምትሞሉት ዩኒቨርስቲ እንደየፍላጎታቹ እና እንደምታገኙት ውጤት ሊለያይ ይችላል። ግን አብሯቹ ያሉት ጓደኞቻቹ ወይም ወንድም/እህታቹ ስለ አንዳንድ ዩኒቨርስቲ መረጃ ሊኖራቸው ይችላል፡፡

6. የምትመርጧቸው ዩኒቨርስቲ ከከተማቹ ውጪ ከሆነ ፤ ስለከተማው ደህንነት እና ጸጥታ መረጃ አሰባስቡ፡፡

7. ዩኒቨርስቲው ያለበት ከተማ አየር ጸባይ ከግምት ውስጥ አስገቡ። አንዳንድ ተማሪዎች በጣም ሞቃታማ ቦታ ለዓመታት መኖር ሊያስቸግራቸው ይችላል!

©️Ethio matric

@Qesem_Freshman ❤️


👨‍🏫 ቀጣይ አመት ዩኒቨረሲቲ ለምገቡ/Freshman ተማሪዎች ብቻ  ተብሎ የተከፈተ  ቻናላችን ነው በውስጡ :-

📌 FreshMan course exams
        -Mid exams
        -Final exams in PDF!
📚✍️
📚 Pdf Notes
📗 Assignment
📖 COC Exam 
📑 Mid & Final Exam ያገኛሉ!

ለመቀላቀል👇👇

@Qesem_Freshman ❤️
@Qesem_Freshman ❤️
@Qesem_Freshman ❤️


#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሪሚዲያል ተማሪዎች የፕሮግራም ድልድል የሚሰሩበትን መስፈርት አሳውቋል።

በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) በቀን ሐምሌ 10/2016 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።


በደብዳቤው የሪሚዲያል ተማሪዎቹን ወደ ፕሮግራም ለመመደብ በሚደረግ ድልድላ ተመሳሳይ መሰፈርት መጠቀም እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

ሁሉም ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና 20%፣ በአንደኛ ሴሚስተር አማካይ ውጤት 50% እና ወደ መስክ መግቢያ ፈተና 30% ብቻ የሚደለደሉ መሆኑን ደብዳቤው ያስረዳል።

@Remedial_Hub

18.8k 0 209 63 66

#FactCheck የትምህርት ሚኒስቴርን ስምና አርማ በመጠቀም ተዘጋጅቶ እየተጋራ የሚገኝ ይህ ደብዳቤ ትክክለኛ አይደለም

ይህ ምስሉ የሚታየው ደብዳቤ ከትምህርት ሚኒስቴር ለባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ እንደተፃፈ ተደርጎ በመዘጋጀት በማህበራዊ ትስስር ገፆች እየተጋራ አንደሚገኝ ተመልክተናል።

በምስሉ እንደሚታየው “ደብዳቤው” ሐምሌ 06፣ 2016 እንደተፃፈና ጉዳዩም የአንደኛ አመት ተማሪዎች የትምህርት መስክ (ዲፓርትመንት) ምደባን እንደሚመለከት ተጠቅሷል።

በዚሁ መሰረት አዲስ ገቢ ተማሪዎች ውጤት አያያዝ እንዴት መሆን እንዳለበት “በደብዳቤው” ተዘርዝሯል። 

የዚህን ደብዳቤ ትክክለኛነት እንድናጣራ የኢትዮጵያ ቼክ ተከታዮችም ጥቆማ የሰጡን ሲሆን እኛም የትምህርት ሚንሰትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን መረጃ ጠይቀናል። 

እርሳቸውም ይህ በማህበራዊ ትስስር ገፆች እየተጋራ የሚገኝ ደብዳቤ ሀሰተኛ መሆኑን ነግረውናል።

በተጨማሪም የደብዳቤው ይዘት ላይ ባደረግነው የፎቶፎረንሲከስ ምልከታ በርካታ አጠራጣሪና የተነካኩ ይዘቶች መኖራቸውን ተመልክተናል።

[ይህን መረጃ አጣርቶ ትክክለኛ አለመሆኑን ያረጋገጠው ኢትዮጵያ ቼክ ነው]

@Remedial_Hub


Репост из: Freshman exams
የጂኒየስነት ሚስጢር ክፍል አምስት..........!
 


📚 ከራሴ ልምድ በመነሳት ስለ አጠናን ዘዴዎች አንዳንድ ነገሮችን ላንሳላችሁ ፦

💭 በመጀመሪያ ስታጠኑ በተቻላችሁ መጠን ላለመጨናነቅ ሞክሩ። ስለ ውጤት መውረድ ወይም ስለትምህርቱ ክብደት እያሰባችሁ በጭራሽ ለማጥናት አትሞክሩ ምክንያቱም ምንም ትርፍ የለውም። ራሳችሁን ዘና አድርጉ motivated ሆናችሁ አጥኑ እመነኝ ትኩረት እስከሰጣችሁት ድረስ የማይሳካ ምንም ነገር የለም። አመናችሁኝ ❓ እንቀጥል ..!


💭 የተወሰኑ እኔን የጠቀሙኝን የጥናት ዘዴዎች ልንገራች ፤ ተከተሉኝ ፦



📍 ጥያቄ አውጡ ❓

📚 እስካሁን ከብዙ ሰዎች እንደሰማችሁት ጥያቄዎችን መስራት ውጤታማ የሆነ የጥናት ዘዴ ነው። የ worksheet , አጋዥ መፅሐፍት ፣ እንዲሁም text book  ጥያቄ መስራት ጠቃሚ እንደሆነ ታውቃላችሁ ብዬ አስባለሁ። ዛሬ እኔ ሌላ ቴክኒክ ላሳያችሁ....ምን በሉኛ ❓    በራሳችሁ ጥያቄ አውጡ።

📚 እኔ አስተማሪ ብሆን ኖሮ ምን ጥያቄ ነበር ልጆቼን የምፈትናቸው ብላችሁ አስቡ። ይሄንኑ ጥያቄ ራሳችሁን መልሳችሁ ፈትኑ። ከጓደኞቻችሁ ጋር ስሩት ። ለምን ይጠቅማል ያላችሁ እንደሆነ ከማንበብ በተጨማሪ የጥያቄ አወጣጥ (exam question concept) ታገኙበታላችሁ ።

ላውጋችሁማ ❓

📚 እኔ የማልረሳው አንድ ታሪክ አለ። የ elementary ተማሪ እያለሁ ሳይንስ አስተማሪያችን ፈተና ሲቃረብ አካባቢ አሳይመንት ሰጠን። አሳይመንቱ እኛ በራሳችን ጥያቄ አውጥተን ከነመልሱ ሰርተን ማስገባት ነው።  የሚገርመው ነገር እኔ ያወጣሁአቸውን ጥያቄዎች ፋይናል ፈተና ላይ በብዛት አገኘሁአቸው። የመምህራንን exam question psychology ስታገኙ ትምህርቱ ልክ እንደ ውሀ ቀላል ነው ሚሆንላችሁ።

    📍concept ያዙ ❓


📚 በጣም ብዙ ተማሪዎች በደንብ እያጠኑ ግን ውጤታማ ሳይሆኑ ሲቀሩ ይታያል።
ለምን ❓ ከተባለ የሚያነቡት መፅሐፉ ላይ ያለውን ፅሁፍ እንጂ Conceptun አይደለም። የምናነበው ነገር ስለምንድነው  እያወራ ያለው ❓ ምን እንድንይዝ ነው የተፈለገው ❓ ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን።



✏️ ቆይ ጥናታችን ውጤታማ እንዲሆን ምን እናድርግ ❓


💡 ክላስ አትቅጣ

📚 ይብዛም ይነስም teacherሩ የሚነግረን concept ዋጋ አላት። ጂኒየስም ይሁን አይሁን የሚያስረዳበት መንገድ ይጣፍጥም አይጣፍጥ ክላስ ተከሰት ።


💡 ከጓደኞቻችሁ ጋር ተጠያየቁ። 

📚 አሪፍ ጀማ ሰርታችሁ ጥያቄ ፍለጡ ፤ ጥሩ እና መልካም ጓደኞች ጋር የሚደረግ ጥረት ትልቅ effect አለው ።

💡 informal way ተጠቀሙ።

📚 በጨዋታ (በቀልድ) አስታካችሁ የያዛችሁትን ዕውቀት ልትረሱ ብትፈልጉ ራሱ አትችሉም ፣ በፌዝ መልክ አውሩት።

እንደ ጉርሻ ❓

📚 ከformal ጥናት ውጪ በሆናችሁ ጊዜ በማያጨናንቃችሁ መልኩ meditate አድርጉት ። ተመስዕጦ ራስን ለማግኘት ምርጥዬ መንገድ ነው ። (የግል ምክር )

🔎 በተለየ መልኩ ደግሞ 💭


📍 አልችልም የሚል ሀሳብን አስወግዱ። ትችላላችሁ ...! መቻልን ተሸክሞ የመጣ የለም ሁሉም በምድር በጥረቱ አበጅቶት ነው ። 

📍 በሚመቻችሁ ጊዜና ቦታ አጥኑ። ቀን or ማታ  ላይብረሪ ወይም ከሰው ጋር  ብቻ እናንተ በለመዳችሁት setting ( የምታውቁትን ጎበዝ ተማሪ ሳይሆን የራሳችሁን መንገድ ፍጠሩ ..!)


📍ፈታ በሉ ፤ ግን ከትምሮ መቼም አትራቁ። because ርቆ መመለስ ከባድ ነው ሚያረግባችሁ ...ስትኖሩ ተማሪ መሆናችሁን አትርሱ ...!


🔜 ክፍል 6 ይቀጥላል.........

@Qesem_Freshman ❤️



11.2k 0 120 10 39
Показано 20 последних публикаций.