ኮሮና እና ለአላህ እጅ መስጠት?
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ሰሞኑን አለምን
- ጭንቀት እና ፍርሃት ውስጥ የከተተ፣
- አውሮፕላን በረራዎችን ያስቆመ፣
- ትምህርት ቤቶችን ያዘጋ፣
- ሰዎችን ከመጨባበጥ ያገደ፣
- ኢኮኖሚን ያሽመደመደ………
በጣም የደቃቅም ደቃቅ፣ በአይን የማይታይው ኮሮና በመባል የሚጠራው ቫይረስ ነው፡፡ በጣም የሚገርመው ስንት የሀገራት መሪዎች፣ የአለም የጤና ሚኒስቴር፣ አብዛኛውም ማህበረሰብ ወደ አላህ እጅ መስጠት እና ብቸኛው ፈጣሪ ሆይ! ይህን እኛ መከላከል የማንችለውን አንተ ብቻ ማንሳት የምትችለውን መከራ አንሳልን ከማለት ፋንታ የተለያየ መግለጫ ሲሰጡ እንሰማቸዋለን፡፡
አይ የሰው ልጅ በአይኑ ማየት የማይችለውን በጣም ደቃቅ ቫይረስ መከላከል እንኳን አቅቶት እጁን ለብቸኛው አምላክ፣ ሁሉን ቻይ አላህ ላለመስጠት ኩራት ላይ ወድቋል፡፡
የደርግ መንግስት ኮሚኒዝም የሚባለውን ስርዓት ነበር የሚከተለው፡፡ ኮሚኒዝም በቁሳዊው አለም ነበር የሚያምነው፡፡ ለፈጣሪ እውቅና አይሰጥም ነበር፡፡ ነገር ግን ሀገራችን ላይ በ 1977 ከባድ ድርቅ ተከስቶ የስንቶችን ህይወት ሲቀጠፍ፣ ደርግ ፈጣሪን እንለምን ብሎ እጅ ሰጠ፡፡ ቢያንስ ያን መከራ ምንም ቢያደርግ ማንሳት እንዳልቻለ አምኖ፣ ሁሉን ማድረግ የሚችል ፈጣሪ እንዳለ በአንደበቱ መሰከረ፡፡
ዛሬ አለም ላይ አሉ የሚባሉ ዶክተሮች ቢፍጨረጨሩም ምንም ማድረግ አልቻሉም፡፡
ታድያ እኛ መቼ ነው
- ለአላህ እጅ የምንሰጠው?፣
- ወደ እሱስ በንሰሃ (በተውበት) የምንመለሰው?፣
ቻይና፣ አሜሪካ እና ሌሎች በቴክኖሎጂ፣ በወታደራዊ ሃይል፣ በኢኮኖሚ እና በብልፅግና ጣራ ደርሰዋል የሚባሉ እነሱም ጣራ ደርሰናል፣ ማን ይነካናል የሚሉ ሀገራት ጠቅላላ ይሀው መመከት የማይችሉት በጣም የደቃቆች ሁሉ ደቃቅ ቫይረስ የሀገራቱን በር እያንኳኳ ነው፡፡
ሃይልም ጥበብም የለም በአላህ ቢሆን እንጂ፡፡ እኛ አቅመ ደካማዎች ነን፡፡ ሁሉን ቻይ አላህ ከእንዲህ አይነት መከራዎች ይጠብቀን፡፡ ወደ እሱ በንሰሃ ከሚመለሱት ያድርገን፡፡ መጨረሻችንን ያሳምርልን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts