መንገድ ዳር ተኝቶ መኪና ሲያልፍ ተከታትሎ የሚሮጥና የሚጮህ ውሻ የነበረው አንድ ገበሬ ነበር፡፡ ታዲያ ይህን ድርጊቱን ደጋግሞ ሲመለከት የነበረው ጎረቤቱ እንደው ስታስበው ይኸ ውሻህ የሚከተላቸውን መኪኖች የሚይዛቸው ይመስልሃል ሲል ጠየቀው፡፡ የውሻው ባለቤትም መች እሱ ሆነና የሚያስጨንቀኝ ወዳጄ እኔን የሚያስጨንቀኝ ብሎለት መኪናው ቢይዘው ምን ሊያደርገው እንደሚችል ነው፡፡ ብዙዎቻችን እንዲሁ የማይመለከተንና የማይጠቅመንን ስናሯሩጥ ትርጉም የሌለው ልፋት ስንለፋ እንዳይመሽብንና እንደ ውሻው አልቦ ግብ ሰዎች እንዳንሆን ያመላክተናል፤ ያስጠነቅቀናል፡፡
ምንጭ፡- MEANINGLESS GOALS
-----------------------
💎
💎 #ሼር_ያድርጉት
💎 @Shewamil
ምንጭ፡- MEANINGLESS GOALS
-----------------------
💎
💎 #ሼር_ያድርጉት
💎 @Shewamil