የአፍሪካ ሀገራት በሀገር ውስጥ ምንዛሬ እንዲገበያዩ ጥሪ ቀረበ በ57ኛው የአፍሪካ የገንዘብ፣ የዕቅድ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎች የአፍሪካ መንግስታት የንግድ እና ሌሎች ግብይቶችን በአገር ውስጥ ምንዛሬዎች ለመፍታት አማራጮችን እንዲፈልጉ አሳስበዋል። የሀገር ውስጥ ምንዛሪ ፋይናንስን ማስቀደም የአፍሪካን ኢኮኖሚ ከውጭ ጥገኝነት ለመጠበቅ እና የበለጠ ጠንካራ የፋይናንሺያል ስነ-ምህዳር ለመፍጠር ንቁ እርምጃ ነው ሲሉ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ኢኮኖሚስት ሃናን ሞርሲ በስብሰባው ተናግረዋል።
ሌላው በአፍሪካ ልማት ላይ ለውጥ የሚያመጣው የፓን አፍሪካ የክፍያ ስርዓት እድገት ሲሆን ይህም በአገር ውስጥ ምንዛሬዎች መገበያየት ያስችላል” ያሉት ሞርሲ፣ አፍሪካ በዩናይትድ ስቴትስ ዶላር ላይ ከፍተኛ ጥገኛ መሆኗ ኢኮኖሚያዊ ተጋላጭነትን እንዳስከተለ ተናግረዋል። የአፍሪካ ንግድ ፖሊሲ ማዕከል አስተባባሪ አቶ መላኩ ደስታ፣ አፍሪካ የምትገበያይበት እንደ ዩናይትድ ስቴትስ ዶላር አህጉሪቱን በዓመት 5 ቢሊዮን ዶላር ያስወጣል።
አንድ የአፍሪካ መገበያያ ገንዘብ ንግድን ለማሳደግ፣ በአፍሪካ ህብረት አባላት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር ለማሳደግ እና በአህጉሪቱ ፈጣን እድገትን እንደሚያበረታታ ሽንዋ ዘግቧል። የግብይት ወጪዎችን ለመቆጠብ ትልቅ እድሎች እንዳሉ እና የአፍሪካ ኩባንያዎችን የበለጠ ተወዳዳሪ ብሎም እርስ በርስ ለመገበያየት ያስችላል ተብሏል።
ለበርካታ አስርት ዓመታት የአፍሪካ መንግስታት በአህጉሪቱ ውስጥም ሆነ ከአለም አቀፍ አጋሮች ጋር በውጭ ምንዛሬዎች ማለትም በዩናይትድ ስቴትስ ዶላር፣ በዩሮ እና በመጠኑም ቢሆን የእንግሊዝ ፓውንድ ይገበያሉ ይህ ጥገኝነት ታሪካዊ የኢኮኖሚ ትስስር፣ ከቅኝ ግዛት በኋላ የባንክ ተቋማት እና የአለም አቀፍ የንግድ ዘይቤዎች ውጤት ነው። የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) ሴክሬታሪያት ዋና ጸሃፊ ዋምከለ ሜኔ፥ አፍሪካ ከወዲሁ ወደ አንድ ገንዘብ እየተሸጋገረች ትገኛለች ብለዋል።
@Addis_News