ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በንግድ ሀሳብ ፈጠራ ውድድር አሸናፊ ለሆኑ ተወዳዳሪዎች ሽልማት ሰጠ።
የዩኒቨርሲቲው የኢንተርፕርነርሺፕና ቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ዳይሬክቶሬት ባዘጋጀው የንግድ ፈጠራ ውድድር ላይ በባለሙያዎች ድጋፍና ክትትል የተደረገላቸው 23 የፈጠራና ንግድ ሀሳቦች ቀርበዋል።
በውድድሩ ከቀረቡ ሀሳቦች መካከል ከ1-3ኛ ደረጃ ላገኙ ተወዳዳሪዎች፥ ፈጠራቸውን ወደ ተግባር ለመለወጥ የሚያስችል የገንዘብ ሽልማት ተሰጥቷል።
አንደኛ ደረጃ ለወጣ የመነሻ ካፒታል ብር
200,000፣ በሁለተኛነት ለተመረጠ ብር
150,000 እንዲሁም በሦስተኛነት ለተመረጠው ብር
100,000 ሽልማት ተበርክቷል።
በውድድሩ ቀርበው አሸናፊ የሆኑት የፈጠራ ሀሳቦች የአካባቢውን ችግር ፈቺ መሆናቸው ተገልጿል። የቀረቡት የፈጠራ ሀሳቦች ምንድን ናቸው?
➦ የማይድኑ ነገር ግን በዘላቂነት መድኃኒት የሚሰጣቸው ታማሚዎቹ ባሉበት ሆነው የባለሙያ ድጋፍ እንዲያገኙ በቴሌ ሜዲሲን የሚታገዝ የፈጠራ ሀሳብ፣
➦ በአባቢያችን የሚገኙ ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻዎችን በመጠቀም የሚሰራ የተፈጥሮ ማዳበሪያ፣
➦ ተማሪዎችን ሊያግዝ የሚችል ሰው ሰራሽ አስተውሎትን የሚጠቀም መተግበሪያ። #ሀዩ
@tikvahuniversity