ኢቶዮጵያ ታሪክሽን እወቂ ለዓለም ኣሳውቂ !!
ኣፄ ራማናልኬ (ናልክ) ፵፯ (47) ዓመት በንግስና ቆይቶ ሲሞት ልጁ አፄ ሉዚ ቤዛ (ባዜን) ነገሰ ባዜንም በነገሰ በ ፰ (8) ተኛው ዓመት ድንቅ መካር ፣ሀያል ኣምላክ ፣የሰላም አለቃ፣ መምህራችን ጌታችን መድኀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ እነሆ ተወለደ ።
እነሆም ጊዜው ዘመን ከተቆጠረ እንደ ሱባውያን እና ኣዜባውያን ኣቆጣጠር ፯፻፹፭ (785) ሱባኤ ከ ፭ (5) ዓመት ወይም 5500 ዓመት ነበር ።
ኢየሱስም፡በይሁዳ፡ቤተ፡ልሔም፡በንጉሡ፡በሄሮድስ፡ዘመን፡በተወለደ፡ጊዜ፥እንሆ፥ሰብአ፡
ሰገል፦የተወለደው፡የኣይሁድ፡ንጉሥ፡ወዴት፡ነው፧ኮከቡን፡በምሥራቅ፡አይተን፡ልንሰግድለት፡
መጥተናልና፥እያሉ፡ከምሥራቅ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጡ ። (ማቴ ፪:፩)
እንግዲህ ዋናውና ትልቁ ነገር እንዲህ የተነገረላቸው የምትመለከቷቸው ሰብአሰገል ኢትዮጵያዊያን ነበሩ እንደሚከተለው አስቀምጬላችኋለሁ ።
፩. በደሸት ከተማ ጎንጅ ጎጃም የሚቀመጠው በተስፋ ሲጠባበቅ የኖረው የጋፋት ንጉስ የእግዚአብሔር ሰው ንጉስ "አጎጃ ጃቦን" ዮጵ የሚባለውን የግዮን ቢጫ ወርቅ ፣ እንቁዮጳዝዮን፣ ሱል ድንጋይ የወርቅ ሐመልማል ይዞ በስሩ ሶስት ነገስታቶችን "አጊጃ" ፣ "ጃቦ" ፣ "አማናቱ" አስከትሎ ከጣና ደሴት ተነስተው ኮከቡ ወደሚያመራበት ምድር ጉዞአቸውን ቀጠሉ ።
፪. ከፋና ወለጋን ሲገዛ የነበረው ከመደባይ ጎሳ ከአናርያ ዙባ ከተማ የሚቀመጠው የደንጊና የሰገል የማጂና የአርመን ንጉስ "መጋል" ከኤውላጥ ንጉስ "መካድሺ" ከአቢል ንጉስ "አውር" ከአፋር ንጉስ አፍሪካ ንጉስ "ሙርኖ" ጋር ሆኖ ከወርቅ ሐመልማል የተሰራ መጎናፀፊያ ፣ እጀ ጠባብ የሰንደል እንጨት፣ እጣን ፣ ከርቤ፣ የከበረ ሉል ፣ ወርቅ ይዘው ኮከቡ ወደሚያመለክተው ሀገር ወደ ኢየሩሳሌም በጥናቱ ናግራ ኤደን በዛሬው የመን አድርገው ጉዟቸውን ቀጠሉ ።
፫. ከዋይዝ ከተማ በተርሴስ ደሴት በዛሬው አፋር የሚቀመጠው የአዜባውያን አዛል-አዳል የአፍርሴካውያን ንጉሥ "አጋቦን" በኢንኤ ጌዘር ከአውባው ንጉሥ "ሳዱንያ ሀጂሶን" ባል "ሜሌኩ ኢቡል ሰላም" ከሳባ ከተማ የሚቀመጠው "አርስጣ" ጋር ሆነው ወርቅ፣ እጣን ፣ ከርቤ ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም ቀይ ባህርን ተሻግረው ኮከቡ ወደሚያመለክተው ሀገር አመሩ ።
እነዚህ ነገስታቶች ሁሉም ዘውድ የደፉ ንጉሶች ናቸው (ነበሩ) የሄዱት ነገስታቶች በዋናነት ሶስቱ ይሁኑ እንጂ በስራቸው ከነበሩት ነገስታቶች ጋር እስከ አስራ ሁለት እንደሚደርሱና እያንዳንዳቸውም ብዙ ሺህ ሠራዊቶች አስከትለው ነበር ነገር ግን በጉዞ ላይ ሳሉ ድንገት ጦርነት ተነሥቶ አብዛኞቹ ሲያልቁ ገሚሶቹ ደግሞ ወደ የመጡበት ተመልሰዋል በመጨረሻም 3ቱ ነገስታት ቤተልሔም ደርሰዋል የሚሉ ፀሐፍትም አሉ ።
እነዚህ ንገስታቶች በግመሎቻቸውና በፈረሶቻቸው ከምድራቸው የእህልና የወርቅ የከርቤ ፣ የእጣን አይነቶች፣ ልዩ ልዩ ልብሶች፣ ገፀ በረከቶች የንጋቱ ኮከብ ብርሃኑን ለሚያመለክታቸው የሰላም ንጉስ "ጋዳ" ገፀ-በረከት ለማቅረብ ጉዟቸውን አድርገዋል ።
የሁሉም የበላያቸው በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አክሱም የሚቀመጠው ንጉሠ ነገሥት አፄ ሉዚ ቤዛ (ባዜን) ነው ።
ዓለም በእነዚህ የሰብአሰገል ታሪክ በጣም ሀያል እና ጠንካራ ክርክሮችን አስተናግዳለች የኢትዮጵያ ትንታግ ሊቀውንትም እውነታውን በመያዝ ጠንካራ ማስረጃ አቅርበዋል እውነቱም ከላይ እንዳነበባችሁት ኢትዮጵያዊ እንደሆኑ መስክሯል ዋናው እና ማንም ሊክደው የማይችለው ትልቁ ማስረጃ ግን የመፅሐፍ ቅዱስ ምስክርነት ነው ።
"በፊቱም፡ኢትዮጵያ፡ይሰግዳሉ፥ጠላቶቹም፡ዐፈር፡ይልሳሉ። ፤የተርሴስና፡የደሴቶች፡ነገሥታት፡ስጦታን፡ያመጣሉ፤የዐረብና፡የሳባ፡ነገሥታት፡እጅ፡መንሻን፡ያቀርባሉ ። " (መዝ ፸፩:፱-፲)
፤የግመሎች፡ብዛት፥የምድያምና፡የጌፌር፡ግመሎች፥ይሸፍኑሻል፤ዅሉ፡ከሳባ ይመጣሉ፥ወርቅንና፡ ዕጣንን፡ያመጣሉ የእግዚአብሔርንም፡ምስጋና፡ያወራሉ።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ ፷: ፮)
እውነት አሁን ላይ ያለነው ትውልዶች ታዲያ የነዚህ ጠቢብ ልጆች ነን ራሲችሁን ጠይቁ ?
የአባቶቻችን የሰብአሰገል በረከታቸው ይድረሰን !!
ምንጭ :-
-በመጀመሪያ መለኮታዊ ስልጣን ያለው መተማመኛችን "መፅሐፍ ቅዱስ" ።
-ሊቀ ጠበብት አለቃ አያሌው ታምሩ የኢትዮጵያ እምነት በሦስቱ ሕገጋት መጽሐፋቸው ።
-ሊቁ መጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ ።
-ክብረ ነገስት ።
-መራሪስ አማን በላይ የጥንቷ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ታሪክ ።
-መራሪስ አማን በላይ ጉግሣ መጽሔት 3ኛ ዓመት ቁጥር 1 ሐምሌ 1993 ዓ/ም ገፅ 29 ።
-ከጋምቤላ እስከ ሑመራ!
ለሱዳን መሬት ከተሰጠ ይመጣል መከራ!
ገፅ 22-23 እትም 2001 በአማረ አፈለ ብሻው ።
-መሰረተ ስብሀት ለአብ ትውፊታዊ ሐሳብ ዘመንና ታሪክ ገፅ 36 ።
-ገብረ ዮሐንስ ገብረማርያም ክርስትና በኢትየጵያ ገፅ 52 ።
-ቃለ አዋዲ መፅሔት ቁጥር 2 ሚያዚያ 1990 ገፅ 5 ።
- William Leo Hansbery E and Harper Johnson "Africa’s Golden Past Historical facts challenging notion that Christianity isn’t religion of West" በሚለው ጽሁፋቸወው ላይ እንዲህ ሲሉ ያትታሉ ".....But it is in general agreed that the reverent visitors were members’ of the order of the Magi and they are usually identified as Caspar king of Ethiopia; Melchior king of Nubia (Ethiopia); and Balthazar king of Saba which was for a thousand years the capital city of the African Kingdom......."
-ታላቁ ተመራማሪ ጆን ጃክሰን "ethiopian and the origin of civilization" በሚለው ድንቅ መጽሐፉ ገፅ 28
ተፃፈ በሐብተስላሤ አባተ
ከ"ኢዛና ወ ሳይዛና" ነገስታት ከንጉስ "አርማህ" እንዲሁም ከጃንደረባ "ባኮስ" ቅድስት ሐገር ሰማይ ስር ።
🔵
ሼር ኣድርጉት
@Yegna_Tarikoch