Фильтр публикаций




ለወራት ታስሮ የቆየው ጋዜጠኛ የሺሀሳብ አበራ ከእስር መፈታቱ ተሰማ::




አማራ ክልል ‘በጦርነትና በግጭት’ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት ከ100 ቢሊየን ብር በላይ ያስፈልጋል ተባለ

በአማራ ክልል “ከሰሜኑ ጦርነት ጀምሮ አሁን በክልሉ ባለው ግጭት” ምክንያት ጉዳት የደረሠባቸውን ትምህርት ቤቶች መልሶ ለመገንባት 112 ቢሊየን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

በጦርነቱ እና በአሁኑ ግጭት በርካታ ትምህርት ቤቶች መጎዳታቸውን የገለጹት የቢሮው ዕቅድ ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክተር ዘመነ አበጀ ለአብነትም በምሥራቅ ጎጃም ዞን ከ400 በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡


የትራምፕ ዋይት ኃውስ ትላንት እሁድ በኤክስ ገጹ ላይ ባወጣውና በአይስ በቁጥጥር ስር አውዬ ወደአገራቸው ዲፖርት አረጋቸዋለሁ ካላቸው ስደተኞች መኃከል አንዱ ኢትዮጵያዊ እንደሆነ አስታውቀዋል። ይህ ግለሰብ ያሬድ ገረመው መኮንን የሚባል ሲሆን በወሲባዊ ጥቃት ወንጀለኛ ተብሎ የተፈረደበት ግለሰብ እንደሆነ አክለው አስታውቀዋል።
በወቅቱ የ24 አመት ወጣት የነበረው ያሬድ መኮንን በሜይ 28 2017 ዓ.ም በዋሽንግተን ዲሲ በታክሲ አሽከርካሪነት ሲሰራ አንድ ምሽት በመጠጥ የሰከረች ሴት እንዳሳፈረና ሴትየዋ ራሷን ስታ እንደነበር። ስትነቃ ያሬድ ያለፍቃዷ በግብረስጋ እየተገናኛት እንደነበረ የፖሊስ ሪፖርት ላይ ተመዝግቧል። ይህን ጊዜ ተሳፋሪዋ ደንግጣ መጮህ ስትጀምር ያሬድ መኪናውን አስነስቶ መሄድ ይጀምራል። እንዲለቃት ብትለምነውም ሊለቃት ፈቃደኛ አልነበረም። ይህን ጊዜ ተሳፋሪዋ የመኪናውን መሪ በመያዝ መጮህ ጀመረች። ጩኸቷን የሰሙ የአካባቢው ሰዎች ታዲያ በ4900 block of 16th Street NW አቅራቢያ ታክሲውን አስቆሙት። ፖሊስ ሲመጣ ያሬድ የተባለውን አላረኩም ሲል ክዷል።
ያሬድ በ16 ስትሪት ሄይትስ አካባቢ በዲሲ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ በፍርድ ቤት ታይቶ የነበረ ሲሆን። በወቅቱም ወንጀለኛ ተብሎ ተፈርዶበት ነበር።
ያሬድ ታዲያ ባሳለፍነው ሰሞን ጃንዋሪ 24 2025 በኒው ኦርሊንስ በአይስ በቁጥጥር ስር እንደዋለ ዋይትኃውስ አስታውቋል።

@ኢትዮጲክ


ከወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ምሁራን ማህበር በወቅታዊ ሁኔታ አስመለክቶ የተሰጠ መግለጫ

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስር በመተዳደር ላይ ይገኛል፡፡ ዞኑ በክልሉ አንፃራዊ ሰላም እና መረጋጋት ከሚታይባቸው አከባቢዎች በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት አንዱ ነው፡፡ አከባቢው 1983 ዓ/ም በህውኃት መራሹ ኢህአዴግ መንግስት ትግራይ ክልል ተብሎ በሚጠራዉ ክልል፤ ህዳር 29/1987 የፀደቀው የኢፌዴሪ ህገ መንግስት ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት፣ ያለ ህዝቡ ፍላጎት እና ፈቃድ ህገ-ወጥ በሆነ መልኩ መካለሉ የሚታወቅ ነው፡፡ ከለውጡ በኃላ ጥቅምት 24/2013 ጀምሮ በተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ማህበረሰቡ ከትህነግ-ወያኔ ነጻ በመሆን፤ ተጠሪነቱ ለአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሆነ ከወልቃይት ጠገዴ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ መሰረት ያደረገ የዞን አስተዳደር በማደራጀት ራሱን በራሱ እያሰተዳደረ ይገኛል፡፡

ትህነግ-ህውኃት በፕሪቶርያው የዘላቂ ሰላም እና ተኩስ ማቆም ስምምነት በኋላ በ30 ቀናት ውስጥ ትጥቅ በመፍታት አከባቢው ወደ ዘላቂ ሰላም፣ መልሶ ግንባታ/Rehabilitation and restoration/፣ ሀገራዊ መግባባት እና አገር ግንባታ እንዲመለስ ግዴታውን መወጣት ሲገባው፤ ላለፉት 40 ዓመታት በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይ አማራዊ ማንነቱን ምክንያት በማድረግ እና ለታላቋ ሀገረ ትግራይ ምስረታ ምቹ ይሆን ዘንድ የፈፀመው የዘር ማፅዳት ወንጀል በካደ መልኩ ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ለመፈፀም ያቀዱትን ዘር ፍጅት እቅድ በሚያሳብቅ መልኩ፤ በሀገሪቱ ህግ እና ስርዓት የሌለ በስመ ተፈናቃይ የክልል ሉዓላዊነት እና ግዛት ማስመለስ በሚል የውንብድና እና ማጭበርበር ባህርይ በመጠቀም በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ የዳግም ወረራ እና ጦርነት ስጋት ፈጥሮ ይገኛል፡፡

የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ህግ እና ስርዓት ተከትሎ የወልቃይት ጠገዴ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ በማቋቋም ህጋዊ እና ፍትኃዊ የሆነ የአማራ ማንነት ጥያቄ ለፌደሬሽን ምክር ቤት እና በወቅቱ ለነበረው የትግራይ ክልል መንግስት ታህሳስ 7/2008 ዓ/ም ለትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳደር፣ ለትግራይ ክልል ህውኃት ፅ/ቤት፣ ለትግራይ ክልል ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ፅ/ቤት በፅሁፍ እና በአካል በመቅረብ ጥያቄውን አቅርበዋል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ተከትሎ የሰጠው ምላሽ አፈና እና ግድያ ነበር፡፡ ሐምሌ 05/2008 ዓ/ም የወልቃይት ጠገዴ ወሰን እና አስመላሽ ኮሚቴ በጎንደር ከተማ አመራሩ ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት እና በሽብር ወንጀል በመክሰስ እስከ ለውጡ ጊዜ ድረስ የፖለቲካ እስረኛ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

በለውጡ መንግስት በመላ ሀገሪቱ የነበሩ የማንነት እና ወሰን ጥያቄዎችን ምላሽ ለመስጠት የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮምሽን የተቋቋመ ሲሆን ትህነግ-ወያኔ በወልቃይት ጠገዴ አማራ ማህበረሰብ ያደረሰውን ዘር ማፅዳት ወንጀል ተጠያቂ ላለመሆን ይህን በሀገሪቱ ፓርላማ በአዋጅ የተቋቋመውን ኮሚሽን በ100% ድምፅ ውድቅ በማድረግ ወደ ክልሉ ገብቶ ምንም ዓይነት ስራ እንዳይሰራ፤ ለህግ እና ስርዓት ተገዢ አለመሆኑ አስመስክሮ አልፏል፡፡

ትህነግ-ህውኃት ለውጡን ባለመቀበል ክልላዊ ዲፋክቶ ስቴት [Defacto state] በሚመስል ሁኔታ ጥቅምት 24/2013 ዓ/ም ማዕከላዊ መንግስቱን በኃይል ለመቆጣጠር እና ለ30 ዓመታት የነበረው አንባገነናዊ የኢህአዴግ ስርዓት ለመመለስ ጦር መስበቁ የሚታወስ ነው፡፡ ይህን ተከትሎ በተለይ በወልቃይት ጠገዴ አማራ ማህበረሰብ ማንነት ተኮር የማይካድራ ጅምላ ጭፍጨፋ እና የሁመራ ንፁኃን አሰቃቂ ግድያ ከመፈፀም ባሻገር፤ ሀገሪቱ ለ2 ዓመታት የዘለቀ የእርስበርስ ጦርነት በመክተት ከባድ አገራዊ ኪሳራ አስከትሏል፡፡ ጦርነቱን ተከትሎ የፕሪቶርያ ስምምነት መፈራረም ቢቻልም፤ ትህነግ-ህውኃት የስምምነቱ ዋና ግብ እና ትኩረት የነበረው DDR በታቀደው መልኩ ለሁለት ዓመታት ሳይፈፀም እንዲቆይ ከማድረግ አልፎ በቅርቡ የተጀመረው የትግራይ ቀድሞ ተዋጊዎች ትጥቅ ማስፈታት ሂደት እንዳይቀጥል የእምቢተኝነት ዘመቻ የተሰኘ የአመፅ እና ግርግር ተግባር ላይ ይገኛል፡፡

ይህ የአመፅ እና ግርግር ተግባር መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና ሰላም ወዳድ የሆነው የዓለም ማህበረሰብ ሊቃወመው ይገባል፡፡ እንዲሁም የኤፌዴሪ መንግስት የወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት አማራ ማህበረሰብ የዘመናት የአማራ ማንነት ጥያቄ ምላሽ/እዉቅና በመስጠት እና በጀት በመፍቀድ ሀገሪቱ የጀመረችውን የሰላም ግንባታ የተሟላ እንዲሆን ጥሪያችን እያቀረብን በስመ ተፈናቃይ የሚሰበከውን የተሰኘ የውሸት ፕሮፖጋንዳ ዘመቻ፣ ህዝባችን ነፃ ለማውጣት በሚል ድራማ ሆነ የመገንጠል ፍላጎት ህዝባችንን ስለማይመለከተው ዳግም ዘር ፍጅት ለመፈፀም የሚደረግ ማንኛውንም እንቅስቃሴ እያወገዝን የህዝባችን የመኖር ተፈጥሯዊ መብቱ፣ ማንነቱ እና ኢትዮጵያዊነቱን ለመጠበቅ ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ እንዲሆን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
የማህበረሰባችን ዘርፈ-ብዙ ችግሮች ለመፍታት እንተጋለን!!!

የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ምሁራን ማህበር
ጥር/2017 ዓ/ም
ሁመራ


















(ዘ-ሐበሻ ዜና) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፖሊስ ትናንት በፃፈው ደብዳቤ ህወሀት ያካሄደውን ህዝባዊ ኮንፈረንስ ተከትሎ በኮንፈረንሱ የተላለፉ ውሳኔዎችን ለመደገፍ በሚል ዛሬ ጥር 18 ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ጥያቄ እንደቀረበለትና ባለው ሁኔታ "የፀጥታ ሽፋን መስጠት ስለማይቻል ሰልፉን ለሌላ ጊዜ እንዲያስተላለፉት ማሳሰቢያ" ቢሰጥም፣ ሰላማዊ ሰልፉ ግን በትግራይ የተለያዩ ከተሞች ዛሬ እየተካሄዱ መሆናቸውን ከስፍራው የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል።
ሰልፎቹ እየተካሄዱባቸው ካሉባቸው ከተሞች መካከል መቀሌና ሽሬ የሚጠቀሱ ሲሆን፣ ሰልፈኞችም የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተዋል።
ከነዚህም መካከል "የፕሪቶሪያ ስምምነት መፈፀም ለትግራይ እና ለአፍሪካ ቀንድ ህዝቦች የሰላም ዋስትና ነው!"፣ "ህወሀት ያካሄደውን ህዝባዊ ኮንፈረንስ፣ ድርጅታችን ህወሓት እና የትግራይ ሰራዊት ያሳለፏቸው ውሳኔዎች በአስቸኳይ ተግባራዊ መሆን አለባቸው!!"፣ "የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በአስቸኳይ ሊስተካከል ይገባል!!"፣ "የፕሪቶሪያው ስምምነት አሁኑኑ ተግባራዊ ይደረግ"፣ " የተፈናቀሉ እና የተፈናቀሉ ወገኖቻችን በአስቸኳይ ወደ ቤታቸው ይመለሱ!!"፣ "የፓርቲያችን ሕጋዊ እውቅና በአስቸኳይ ይመለስ!!"፣ "ሰራዊታችንን የማፍረስ ሴራ አንቀበልም!!"፣ "የውጭ ጣልቃ ገብነቶችን እንቃወማለን" የሚሉና ሌሎችም መፈክሮች እየተሰሙ ነው።


እንደምን አደራችሁ !!

የአገው ምድር ፈረሰኞች 85ኛ በዓል ጥር 23 በበዓሉ እንዲታደሙ ተጠርተዋል።
💚💛❤






ባሕር ዳር ሰባር ጊዮርጊስ ዓመታዊ በዓል ነገ ይከበራል !!

ጥርን በባሕርዳር በልዩ ልዩ ሀይማኖታዊና ባህላዊ ትርኢቶች በታላቅ ድምቀት እንደቀጠለ ነው ።



Показано 20 последних публикаций.