~ የጸሎት ሰዓታችን ደርሷል
በሉ ለጸሎት እንነሳ ፥ እንደ ትናንቱም እንጸልይ
*~★★★~*
• እንግዲህ ዓለም ሁሉ የሞታችን ቁጥር ለመዘገብ አሰፍስፎ የባህር መዝገቡን ገልጦ እየጠበቀንም አይደል? ድኅነታችንን ዓይቶ እነሱማ ይረግፋሉ፣ ይረፈረፋሉ እያለንም አይደል? የድሆች አምላክ፣ ሞታችንን በህይወት ለውጦ፣ የጠላትን ቅስም ይሰብር ዘንድ ዛሬም እንደ ትናንቱ አጥብቀን እንጸልያለን።
• በዛሬው የጸሎት መርሀ ግብራችንም ሞት ለበረታባቸው ለጣልያናውያን እና ለእስፔናውያንም እንጸልያለን። ደግሞም ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው ዓለም ለተጨነቅን ሁሉ እግዚአብሔር በምህረቱ እንዲጎበኘንም እንጸልያለን።
#ETHIOPIA | ~ ህሊናችንን ሰብስብ አድርገን ጸሎታችንን እንጀምር !!
•••
ፍጹም በሆነ ሙሉ እምነት፥
ፍጹም በተመሰጠ ልቦና ፥
በፍጹም መጸጸት ፥ በንፁህ ልቦና
እሰግድ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
እሰግድ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
እሰግድ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ (አሐተ ስግደተ)
እንዘ አሐዱ ሠለስቱ ወእንዘ ሠለስቱ አሐዱ
ይሤለሱ በአካላት ወይትወሐዱ በመለኮት
እሰግድ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
እሰግድ ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተቀደሰ በደሙ ክቡር
መስቀል ኃይልነ፥
መስቀል ጽንዕነ፥
መስቀል ቤዛነ፥
መስቀል መድኃኒተ ነፍስነ፥
አይሁድ ክህዱ ንኅነሰ አመነ በኃይለ መስቀሉ ድኅነ።
•••
አምላኬ ሆይ
ስላደረግህልኝ ነገር
ስለምታደርግልኝ ነገር
ስላላደረክልኝና ስለማታደርግልኝም ነገር ሁሉ አመሰግንሃለሁ።
ምንም ብበድልህ በፍጹም ቸርነትህና ፍቅርህ ጠብቀህ በሕይወቴ ላይ ይቺን ሰዓት ጨምረህ በተቀደስወ ስፍራህ ስላቆምከኝ አመሰግንሃለሁ።
መላእክትን በጽርሃ አርያም፥
ሰማዕታትን በደም፥
ሐዋርያትን በአጽናፈ ዓለም፥
ጻድቃንን በገዳም ያጸናህ አምላክ፥ እኔንም በሃይማኖት፣ በጾም፣ በጸሎትና በምግባር እንድታጸናኝ እለምንሃለሁ።
አምላኬ ሆይ ምንም ዓይነት ፈተና ቢመጣብኝ እስከ መጨረሻዋ የህይወቴ ህቅታ ድረስ አንተን በማመን እንድታጸናኝ፣ በሕይወቴ ሁሉ አንተን በመፍራት እንድኖር፥ ሰው ሆኖ የማይበድል የለምና ዕድሜ ለንስሐ ለቅዱስ ቁርባንም እንድታበቃኝ እለምንሃለሁ፡፡
•••
እናቴ እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ፥ የእናት ልመና ፊት አያስመልስ፥ አንገትም አያስቀልስምና ከልጅሽ ከወዳጅሽ ተማልደሽ አማልጅኝ።
ለአባ ህርያቆስ
ለአባ ኤፍሬም
ለቅዱስ ያሬድ
ለቅዱስ ደቅስዮስ
ለበላኤሰብ የተለመንሽ እመአምላክ ለእኔም ለደካማው ለጎስቋላው ባሪያሽ ተለመኝኝ።
እናቴ ሆይ ምስጋናሽ በዝቶልኝ እንደ ልብስ ለብሼው እንደ ምግብ ተመግቤው እንደ ውኃ ጠጥቼው እኖር ዘንድ እርጅኝ።
የኔ ኃጢአት ያንቺን ንጽህና አያረክሰውምና በብርሃን እጆሽ ዳሰሽ ለነፍሴ የድኅነትን ምክንያት ሁኚያት።
•••
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ እስራኤላውያንን ከግብፅ ባርነት መርተህ ያወጣህ እኔንም ከዚህ ዓለም ባርነት ነፃ እንድታወጣኝ እለምንህሃለሁ።
የባህራን ወዳጅ የአፎምያ ረዳት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ እኔን ደካማው አገልጋይህን እርዳኝ
የሚፈታተነኝን ሰይጣን ዲያቢሎስን በበትረ መስቀልህ ከእግሬ ስር ቀጥቅጠህ እንድትጥልልኝ በሄድኩበትም ሁሉ እንድትጠብቀኝ እማፀንሃለሁ፡፡
•••
አምላከ ነበያት፥
አምላከ ሐዋርያት፥
አምላክ ደናግል፥
አምላከ መነኮሳት
ለቅዱሳንህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅ ፥ ለያዕቆብ የገባሃውን ቃልኪዳን አስበህ እንደ ክፋቴ፣ እንደ ጥፋቴ፣ እንደ በደሌ ሳይሆን እንደ ቸርነትህ ትምረኝ ዘንድ ቤተሰቦቼን፣ ሃገራችንን ህዝባችንን፣ ቤተክርስቲያናችንንና ሃይማኖታችንን ትጠብቅልን ዘንድ
ዝማሬ ዳዊትን፣
ተልዕኮ አርድዕትን ፤
ቅዳሴ መላዕክትን ፤
መስዋዕተ አቤልን ፤
ዕጣነ ዘካርያስን የተቀበልክ አምላክ የኔንም ጸሎት ትቀበል ዘንድ እለምንሃለሁ
• አባታችን ሆይ……