ተፈተን ተመልሰናል !!
*~★★~*
#ETHIOPIA | ~ እንደ ንስር ጎልማሳነታችንን አድሰን፣ ነጭ በነጭ ሀጫ በረዶ መስለን በወዳጅ ዘመድ ቤት ፎቶ ተነሥተን ዳግም ከች ብለናል። እናንተ እንዴት ናችሁሳ ?
•••
“ ከሳሻችንን ሳናውቅ፣ ክሳችንም ሳይነገረን፣ እንዳንፅፍ፣ እንዳናወራ ተደርገን ከታሰርንበት የፌስቡክ መንደሩ ወኅኒቤት ዋስም ሳንጠራ፥ ይቅርታም ሳንጠየቅ ቅዳሜ ሌሊት ለእሁድ አጥቢያ እንዲሁ በብላሽ ተፈተን ወደ ፌስቡክ መንደራችን በሰላም ተመልሰናል። ”
•••
ነጭ በነጭ የሆነውን የውትድርና የደንብ ልብስ እንደለበስን ከመንሳዊው ዓለም ሠራዊት ጋር ውጊያው ተጠናክሮ ይቀጥላል። እጅ መስጠት ብሎ ነገር የለም። የጥሪ ጊዜአችን ደርሶ ወደ መቃብር እስክንወርድና እስከ ኢትዮጵያ ትንሣኤ ድረስ ድረስ እናንተ መስማት የምትፈልጉትን ሳይሆን እኛ መናገር የምንፈልገውን እውነት እውነቱን ያለ ሀሰት፣ ነጭ ነጯን ያለምንም መቀባባት፣ መለሳለስና መሞዳሞድ እንደወረደ ለእናንተ መናገራችንና መመስከራችንን እንቀጥላለን።
•••
እንደ አንድ ዜጋ በሃገራችን ጉዳይ፣ እንደ አንድ አማኝ በሃይማኖታችን ጉዳይ፣ ሕገ መንግሥቱም፣ ሕገ እግዚአብሔርም በሚፈቅዱልን መሠረት ሃሳባችንን ማንሸራሸራችንን እንቀጥላለን። የሚሰማን ካለ መልካም የሚሰማን ባይኖር ግን እንዲህ ብለን ምስክር ጠርተን እናልፈዋለን።
• ምድር ሆይ ስሚ
• ሰማያትም አድምጡ
• ቤተ ክርስቲያንም መስክሪ ።
•••
ሻሎም ! ሰላም !
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
መጋቢት 20/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።