Zena Adis Ethiopia


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


ይህ ዜና አዲስ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
This news is a gathering place for members of the New Ethiopia family, as well as a platform for exchanging information and messages.
#ኢትዮጵያ_ትቅደም!!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


የቭላድሚር ፑቱን ልጅ በማለት በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የተጋራ ምስል እያነጋገረ ነው

ሾልኮ የወጣ የቭላድሚር ፑቲን 'ሚስጥራዊ ልጅ' ፎቶ መነጋገሪያ ሆኗል። ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው ፎቶ ኢቫን ቭላድሚሮቪች ፑቲን ወይም የቭላድሚር ፑቲን እና የቀድሞ የሴት ጓደኛው አሊና ካባኤቫ ልጅ ነው ተብሏል።

ኢቫን ቭላድሚሮቪች ከፍተኛ ጥበቃ በተደረገለት ቤተ መንግስት ውስጥ እንደሚኖር ተነግሯል። የቭላዲሚር ፑቲን "ሚስጥራዊ ልጅ" የ10 አመቱ ኢቫን ቭላድሚሮቪች የመጀመሪያው ፎቶ ሾልኮ ወጥቷል ሲል the mirror አስነብቧል።

ፎቶውን የተጋራው በሩሲያ ፀረ-ክሬምሊን የሆነው የቴሌግራም ቻናል አማካኝነት ነው። ፑቲን ከጂምናስቲክ ባለሙያ የሆነችው አሊና ካቤቫ ጋር ነበረው የተባለው ልጅ ከሩሲያውያን ተደብቆ እንደነበረ ይህ የቴሌግራም ቻናል ይፋ አድርጓል። ይህው የቴሌግራም ቻናል እጅግ ሚስጥራዊ እና የፑቲን ልጅ ፎቶ አግኝቷል ሲል the mirror ዘግቧል።

የፑቲን ልጅ ከሌሎች ልጆች ጋር አይግባባም፤ ሁሉንም ጊዜውን ከጠባቂዎች ፣አስተዳዳሪዎች እና አስተማሪዎች ጋር ያሳልፋል ሲል ዘገባው አመላክቷል። ሾልኮ በወጣው ፎቶ ላይ ያለው ልጅ ፑቲን ጋር እንደሚመሳሰል ተነግሯል። ኢቫን ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግለት ቤተ መንግስት ውስጥ ይኖር እንደነበር ተገልጿል። ይህ አፈትልኮ የወጣው ምስል ታድያ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ ሆኗል።

እንደ ቢዝነስ ኢንሳይደር መረጃ ከሆነ ፑቲን ከቀድሞ ሚስታቸው ሉድሚላ ሽክሬብኔቫ ሁለት ሴት ልጆችን ወልደዋል። ሁለቱም ሴት ልጆች በ30ዎቹ ዕድሜ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ ተነግሯል። ማሪያ በ1985 በሴንት ፒተርስበርግ ከተማ የተወለደች ሲሆን ካትሪና ደግሞ በ1986 በጀርመን ተወልዳለች።

@ZenaAdis_Ethiopia


ሰበር ዜና
ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ተሰጥቶ የነበረው
የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው ታግዷል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚሰሩ ኦርቶዶክሳውያን የሚዲያ ተቋማት በአንድ ማዕከል  እንዲያገለግሉ፣ የመረጃ ፍሰቱ ወጥነት ያለውና ተቋማዊ መሆን ይችል ዘንድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የሁለት ቀናት ሥልጠና ተሰጥቶ የቤተ ክርስቲያን መሠረት እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮና ትውፊት አክብረው በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ዘገባ ማከናወን የሚችሉበት ፈቃድ ከመምሪያው መሰጠቱ ይታወሳል።

ከእነዚህ የሚዲያ ተቋማት መካከልም የፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን አንዱ ሆኖ ዘገባዎችን ሲያሰራጭ ቆይቷል።

ሆኖም ግን በፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በዕለተ ስቅለት "ቅድስት ድንግል ማርያም ቤዛዊተ ዓለም አትባልም።" በሚል ርእስ  የተላለፈው ትምህርትን ውዝግብ በማሰነሳቱና ቋሚ ሲኖዶስ በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ ለመስጠት ለረቡዕ ሚያዚያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ የያዘ በመሆኑና ጉዳዩ በሚገባ ተጣርቶ ውሳኔ እስከሚሰጠው ድረስ ከመምሪያችን ለፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን የተሰጠው የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው የታገደ መሆኑን እንገልጻለን።

                ሚያዚያ ፲፭ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
                     አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ

          የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
                      ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

#ዜና_አዲስ_ኢትዮጵያ


ሚስቱን ገድሎ ሊሰወር የሞከረዉ ግለሰብ በፖሊስና በሕብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ሊዉል ችሏል‼️

🗣 የጋሞ ዞን ፖሊስ

በአርባ ምንጭ ከተማ ባለቤቱ ገድሎ ሊሰወር የነበረ ግለሰብ መያዙን ፖሊስ ገልጿል።

ኮማንደር ሬታ ፤ የገዛ ባለቤቱን በመሳሪያ ተኩሶ በመግደል ሊሰወር የሞከረዉ ተጠርጣሪ በሕዝቡና በፖሊስ ትብብር በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል።

ተጠርጣሪው አቶ ነብዩ ጌታቸው ኤፍሬም እንደሚባልና ከሟች ጋር በትዳር ዓለም አብረዉ እንደነበሩ በመካከላቸዉ በነበረው አለመግባባት ሟች ወላጆቿ  ጋር በመሄድ ላለፉት 5 ወራት ከቤተሰቦቿ  ጋር ትኖር እንደነበር ገልፀዋል።

በትናትናዉ ዕለት ተጠሪጣርዉ አስቦና አቅዶ ጧት 4 ሰዓት ገደማ " ላናግርሽ እፈልጋለሁ " በማለት ካስጠራት በኋላ ሰዉ የማያይበትን ሁኔታ በማመቻቸት በሽጉጥ አንገቷ ስር ደቅኖ ተኩሶ እንደ ገደላት አስረድተዋል።

በኃላም ለመሸሸግና ለመሰወር ሲሞክር  በፖሊስ ክትትልና በሕብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ዉሎ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ተጠርጣሪዉና ሟች በትዳር አብረዉ በነበሩበት ወቅት አንድ ልጅ አፍርተዉ እንደነበርም የፖሊስ መረጃ ያመለክታል።

ተጠርጣሪዉ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመበትን ሽጉጥ ወንዝ ዉስጥ እንደጣለ ቢገልፅም ፖሊስ ባደረገዉ ማጣራት ከደበቀበት በኤግዚቢትነት ይዞታል።

@Zena_adis_Ethiopia


የህንድ እርምጃ በፓኪስታን
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ከሀያ በላይ ንፁሀን ቱሪስቶች በካሽሚር መገደላቸውን ተከትሎ ህንድ በፓኪስታን ላይ ከፍተኛ እርምጃ ልትወስድ መሆኑን አሳውቃለች።

የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቪክራም ሚሲሪ ከጥቃቱ ኋላ አስቸኳይ የፀጥታ ካቢኔ ስብሰባ ስለመጠራቱ ለጋዜጠኞች ገልፀዋል።

በዚህም በአስቸኳይ ስብሰባ ህንድንና ፓኪስታንን የሚያዋስኑ ዋና ዋና ድንበሮችን ለመዝጋትና የኢንዱ ወንዝ ውሀ የማካፈል የውሀ ስምምነት ለማራዘም መወሰኑ ተናግረዋል።

አክለውም ወደ ህንድ በልዩ ቪዛ የሚጓዙ ፓኪስታናውያን እንዲታገዱም የገቡትም በ48 ሰአት ህንድን ለቀው እንዲወጡ አሳስበዋል።

የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር የህንድን እርምጃና አደጋውን ተከትሎ ማብራሪያ እንዲሰጡ በብሄራዊ ፀጥታ ኮሚቴ ጥሪ እንደቀረበላቸው ታውቋል።

ለ26 ንፁሀን ህልፈት ለበርካቶች መቁሰል ምክንያት የሆነው የካሽሚር የሽብር ጥቃት ቲ አር ኤፍ የተሰኘ አማፂ ቡድን ሀላፊነቱን ወስጃለሁ ብሏል።

ይህ ሀይል በፓኪስታን ድጋፍ ይደረግለታል ስትል ህንድ ተደጋጋሚ ክስ ታቀርባለች።

ጥቃቱንና የህንድን ምላሽ ተከትሎ ከሀገራቱ አልፎ ቀጠናው ውጥረት ውስጥ እንዳይገባ ተሰግቷል።

ዘገባው የአልጀዚራ ነው።

@ZenaAdis_Ethiopia


ሀማስ ሁሉንም ታጋቾች መልቀቅ አለበት !

NBC Ethiopia
። ። ። ። ። ። ። ። ።
የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ሙሀመድ አባስ፣ ሀማስ ሁሉንም የእስራኤል ታጋቾች በፍጥነት መፍታ አለበት ማለታቸው ተገለጸ፡፡

በጋዛ ያለውን ቀውስ ያባባሳው እና እስራኤል የተጠናከረ ጥቃት እያደረሰች ያለው ሀማስ አግቶ በያዛቸው ሰዎች ምክንያት ስለሆነ አሁኑኑ ታጋቾችን መልቀቅ እንዳለበት ሙሀመድ አባስ ጥሪያቸውን አሰምተዋል፡፡

አባስ በራማላህ በነበራቸው ስብሰባ "እኔም ህዝቤም ዋጋ እየከፈልን መቀጠል የለብንም" ሲሉም ተደምጠዋል፡፡  አክለውም በየቀኑ ሞት ማስተናገድ ሰልችቶናል፤ በጋዛ ያለውን ህዝብ ሰላም ለመጠበቅ ሀማስ ቀሪ ታጋቾችን መልቀቅ አለበት ብለዋል፡፡

እንናተ ማትረቡ ከጋዛ ህዝብ ላይ እጃችሁን አንሱ በማለት ሀማስን መዝለፋቸውም ታውቋል፡፡

የሀማስ ከፍተኛ መሪ ባሲም ናኢም በበኩሉ፤ የአባስ ዘለፋን በማውገዝ ተቀባይነት የሌለው ሲል አጣጥሎታል፡፡

ቢቢሲ፤ ገልፍ ቶዴይ እና ሮይተርስ ዘግበውታል፡፡

@zenaadis_ethiopia


የትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ከፑቲን ጋር ለመነጋገር  ወደ ሩሲያ ይጓዛሉ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ልዩ መልእክተኛ ዊትኮፍ ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በዩክሬን ስላለው ጦርነት ለመደራደር በዚህ ሳምንት ወደ ሩሲያ እንደሚጓዙ ዋይት ሀውስ ማክሰኞ አረጋግጧል፡፡

ክሬምሊንም  ልዩ መልእክተኛው በዚህ ሳምንት ሞስኮን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል አስታውቋል፡፡

የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ  ካሮሊን ሌቪት ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት "ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ እየተጓዝን ነው ብለን ተስፋ እናደርጋለን። እናም ልዩ መልዕክተኛው ስቲቭ ዊትኮፍ በዚህ ሳምንት ወደ ሩሲያ እንደገና  በማቅናት ከቭላድሚር ፑቲን ጋር መነጋገራቸውን ይቀጥላሉ" ብለዋል።

ትራምፕ ከሦስት ዓመታት በላይ የዘለቀውን ጦርነት ለማቆም በዚህ ሳምንት ሩሲያ እና ዩክሬን ከስምምነት ላይ ሊደርሱ የሚችሉበት "በጣም ጥሩ ዕድል" እንዳለ ሰኞ መናገራቸውን አናዶሉ አስታውሷል፡፡

ሚያዚያ ሶስት ፑቲን እና ዊትኮፍ  ከዩክሬን ጋር ስላለው ግጭት አፈታት  ዙሪያ  4 ሰአት ከ50 ደቂቃ የፈጀ ውይይት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው ፡፡

@zenaadis_ethiopia


ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ቅድስት ድንግል ማርያምን በማስመልከት ባስተላለፉት ትምህርት ዙሪያ ተወያየ !

ቋሚ ሲኖዶስ ዛሬ ማለዳ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ባሳለፍነው አርብ በስቅለት ዕለት በፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በቅድስት ድንግል ማርያም ዙሪያ ያስተላለፉትን ትምህርት በተመለከተ ውይይት አድርጓል።

በብፁዕነታቸው  የተላለፈውን ትምህርት ዝርዝር ሁኔታን በመመርመርም ውሳኔ ለማስተላለፍ  ይቻል ዘንድ ሁሉም የቋሚ ሲኖዶስ አባላት በምልዓት በተገኙበት  ለአርብ ሚያዚያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ ተይዞል።

በተያያዘ ዜና የሮም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ በሆኑት በፖፕ ፍራንሲስ ሥርዓተ ቀብር ላይ ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ቤተ ክርስቲያናችንን በመወከል እንዲገኙ ተወስኗል።

©የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
@zena_adis_ethiopia


በቱርክ በሬክተር ስኬል 6.2 የተመዘገበ ርዕደ መሬት ተከሰተ
***

በቱርክ በሬክተር ስኬል 6.2 የተመዘገበ ርዕደ መሬት መከሰቱን የሀገሪቱ አደጋ ስጋት አመራር ባለስልጣን ለአናዱሉ ኤጄንሲ ገልጿል።

ከኢስታንቡል ሲልቨር ክፍለ ከተማ የተነሳው ርዕደ መሬት መላ ከተማዋን እና በዙሪያዋ የሚገኙ ግዛቶችን መናጡን ተከትሎ ሰዎች በፍርሃት ከመኖሪያ ህንጻዎች እየለቀቁ ይገኛሉ ተብሏል።

@ZenaAdis_Ethiopia


ትራምፕ ወደ መካከለኛው ምስራቅ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሚቀጥለው ወር ወደ መካከለኛው ምስርቅ ብቅ ሊሉ ነው ተባለ፡፡

ሪፐብሊካኑ ትራምፕ ሳውዲ አረቢያን፣ ኳታርን እና አረብ ኤሚሬቶችን ግንቢት ላይ ይጎበኛሉ፡፡

ወደ ቀጠናው ከፈረንጆቹ ግንቦት 13 እስከ 16 ሲመጡ በርካታ ጉዳዮችን ግምት ውስጥ አስገብተው ነው ተብሏል፡፡

በመጀመሪያው ዙር የፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው ትተውት የሄዱትን የመካከለኛው ምስራቅ ፖለቲካ በአሁኑ  ጉብኝታቸው እንደማያገኙትም ተነግሯል፡፡

ኢራን እና ሳውዲ አረቢያ በቻይና አማካኝነት መታረቃቸው እንዲሁም  እስራኤል እና ሃማስ የገቡበት ጦርነት እንግዳ ጉዳይ ይሆንባቸዋል ተብሏል፡፡

ትራምፕ ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚጓዙት ፖለቲካዊ መፍትሄ ለማምጣት ነው የተባለ ሲሆን እስከዛው ግን ከኢራን ጋር ያለው ውጥረት ወይ ይረግባል  አሊያም ይለይለታል የሚል መረጃ ወቷል፡፡
  በየመን ከሁቲዎች ጋር ያለው ውጥረትም አብሮ ፖለቲካዊ ግምት ውስጥ የሚገባ ጉዳይ ነው ብሏል የፕሬዚዳንቱ ቢሮ ዖቫል ኦፊስ፡፡

ፕሬዚዳንቱ እስከዛው የጋዛውን ጦርነት መቋጨት ካልቻሉም በመካከለኛው ምስራቅ መልካም አቀባበል አይጠብቃቸውም እየተባለ ነው።

የዶናልድ ትራምፕ ጉዞ ከፍተኛ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ትርጓሜ እንደሚኖረው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

አልጀዚራ እንዳስነበበው፡፡

@ZenaAdis_Ethiopia


የአሜሪካና ቻይና ተስፋ

። ። ። ። ። ። ። ። ።
ዋይት ሀውስ ከቻይና ጋር የንግድ ስምምነት ላይ ለመድረስ በአግባብ እየሰራሁ ነው አለ፡፡

የዋይት ሀውስ ፕረስ ሴክሬታሪ ካሮላይን ሊቪት በጋዜጠኞ ጥያቄ ቀርቦላቸው ሲመልሱ "ስራዎች እየተሰሩ ነው" ብለዋል፡፡

በዕርግጥ በቂ ጊዜ አለ፥ ስኔ ላይ ጠይቁኝ ማለታቸውም አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

የዶናልድ ትራምፕ በሶስት ወራት የተራዘመው የታሪፍ የጊዜ ገደብ ሲጠናቀቅ ሁሉም ነገር መልስ ያገኛል ባይ ናቸው ካሮላይን ሊቪት'፡፡

ስምምነት ላይ ለመድረስ በተቻለ ፍጥነት መሪዎቹ  እየሰሩ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ከቻይና ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ በጎ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ያሳወቁት የዋይት ሀውስ ፕረስ ሴክሬታሪ፣ በጊዜ ሂደት ግን ሁሉም ነገር ይፈታል ብለዋል፡፡

አሜሪካ እና ቻይና ግልጽ የታሪፍ ጦርነት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ የዓለም ፖለቲካም አብሮ መታመስ ከጀመረ ዋል አደር ብሏል፡፡

ቤይጂንግ በአሜሪካ ምርቶች ላይ የ125 በመቶ ታሪፍ ስትጥል፤ አሜሪካ ደግሞ 145 በመቶ የቤይጂንግ ምርቶች ላይ ቀረጥ መጣሏ አይዘነጋም፡፡

ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡

@ZenaAdis_Ethiopia


"ክሪሚያን አንሰጥም"ዘለንስኪ

፡፡፡፡።፡፡፡፡።፡፡፡፡።፡፡፡፡።፡፡፡፡።

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ" ክሪሚያ የሩሲያ ግዛት ናት ብዬ እውቅና አልሰጥም" አሉ።

ክሪሚያ በፈረንጆቹ 2014 በሩሲያ ሀይሎች ወደ ሩሲያ ፌደሬሺን መጠቃለሏ ይታወሳል።

"ኪዬቭ በጭራሽ ክሪሚያን አሳልፎ ስለመስጠት ከሞስኮ ጋር ለድርድር የምታቀርበው ጉዳይ አይደለም" ብለዋል ዘለንስኪ፡፡

ዋሽንግተን ሚያዚያ 15-8-17(ረቡዕ) ከዩክሬን እና ከአውሮፓ አጋሮቿ ጋር ስትመክር ክሪሚያን የሞስኮ ግዛት አድርጎ ዕውቅና የመስጠት ሀሳብ አላት ሲል ዋሽንግተን ፖስት አስነብቧል፡፡

ግጭቱን ለማስቆም አሜሪካ እንደአማራጭ ልታቀርበው አስባለች የሚለው መረጃ  ከዩክሬን ፖለቲከኞች በኩል በጎ አቀባበል አላገኘም፡፡

“ክሪሚያ ግዛታችን ነው  ፣የዩክሬን ህዝብ ግዛት ነው  ፣በዚህ ጉዳይ ላይ የምንነጋገረው ነገር የለም፣ከህገ-መንግስታችን ውጭም ነው” በሚል አሻፈረኝ ብለዋልም ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ፡፡

ከክሪሚያ ባሻገር ዛፖሬዢያ  ፣ሉሃንስክ ፣ዶኔትስክ እና ኼርሶንም በአሁኑ ሰዓት በሩሲያ ሀይሎች ስራ መሆናቸው ጉዳዩን ለዩክሬን ቀላል አያደርገውም።

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ፑቲን ግዛቶቹን ለዩክሬን መልሰን አንሰጥም ማለታቸውም  የሚዘነጋ አይደለም፡፡

አር ቲ እና ዋሽንግተን ፖስት እንደዘገቡት፡፡

@Zenaadis_Ethiopia


ሞቃዲሾ

ወደ ሞቓዲሾ እየገሰገሰ የነበረውን የአልሸባብ እንቅስቃሴ ለመግታት የቱርክ መከላከያ ሰራዊትን የያዙ 2 የጦር አውሮፕላኖች ሶማሊያ ሞቃዲሾ አርፈዋል።

በዚህም በመጀመሪያ 500 የቱርክ ኮማንዶ ከስፍራው ደርሰዋል።

ባለፉት ቀናት ውስጥ አልሸባብ በሶማሊያ ጦር ላይ ከፍተኛ የማጥቃት ዘመቻ መጀመሩን ተከትሎ የሶማሊያ ጦር የመፈራረሰ አደጋ ውስጥ መግባቱን የተመለከተችው ቱርክ በሁለት አንቶኖቭ አውሮፕላን 500 ሰራዊት ከበቂ መሳሪያ ጋር ወደ ሞቃዲሾ ልካለች።

#ዜና_አዲስ_ኢትዮጵያ


ሩሲያ እና ዩክሬን ከ500 በላይ የጦር እስረኞችን ተለዋወጡ

ሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ትልቅ ነው የተባለውን ከ500 በላይ የጦር እስረኞችን መለዋወጣቸው ተገለፀ።

የእስረኞች ለውውጡ የተከናወነው የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጊዜያዊ የፋሲካ የተኩስ አቁም ባወጁበት ወቅት ነው፡፡

የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር 246 የሚሆኑ የሩሲያ ወታደሮች በልውውጡ መመለሳቸውን ገልጿል፡፡

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በበኩላቸው 277 የሚሆኑ የዩክሬን ወታደሮች መፈታታቸውን አረጋግጠዋል።

[Hagergnamedia]

@ZenaAdis_Ethiopia


#MoE

በሰኔ 2017 የሚሰጠውን የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና #ዳግም ለመፈተን እየተጠባበቁ ያሉ አመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ሚያዝያ 14 /2017 ዓ.ም እስከ ግንቦት 05/2017 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

የመመዝገቢያ ቅፅ https://exam.ethernet.edu.et ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በሟሟላት መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ገልጿል፡፡

ፈተናው የሚሰጥበት ቀን ወደፊት ይገለፃል ተብሏል፡፡

ፈተናውን ለመውሰድ የብሔራዊ (ፋይዳ) መታወቂያ መያዝ ግዴታ ሲሆን ፤ የአገልግሎት ክፍያ (500 ብር) በቴሌብር በኩል ብቻ የሚፈፀም መሆኑ ተገልጿል፡፡

@Zenaadis_Ethiopia


Репост из: 🎙Zena Adis Ethiopia🎙
በኮሪደር ልማቱ ላይ ጉዳት ያደረሱ 13 ከብቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ!

ሚያዝያ 10፤2017 በቦሌ ወረዳ 12 አስተዳደር የኮሪደር ልማት ላይ ጉዳት ያደረሱ 13 ከብቶች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን አሁን ላይ ባለቤቶች ተጠርተው በአንድ ከብት 5 ሺህ በአጠቃላይ 65ሺህ ብር ቅጣት ከፍለው ከብቶቻቸውን ተረክበዋል።

የወረዳው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ማህበረሰቡ ከመሰል ድርጊት እንዲቆጠብ አሳስቧል ።

@Zena_Adis_Ethiopia


#EOTC

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሮም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ በሆኑት በብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ ፍራንሲስ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ለመላው የሮማ ካቶሊካዊ መሪዎች እና በመላው ዓለም ላሉ ምእመናን እንዲሁም በኢትዮጵያ ላሉ ካቶሊካውያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም ገልጸዋል።

https://t.me/ZenaAdis_Ethiopia


Репост из: 🎙Zena Adis Ethiopia🎙
ፖፕ ፍራንሲስ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፖፕ ፍራንሲስ በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል፡፡

@zena_Adis_Ethiopia

Показано 17 последних публикаций.