. ጀግንነት እጣፈንታ ሲሆን!!😌
•••••○•••••••••••••••••••••••••••••◦
በጥንት ጊዜ ግብፅ ውስጥ የሆነ ነው አሉ፣ የፈርኦኑ ልጅ በጀልባ ሆና በናይል ወንዝ ላይ እየተዝናናች እያለ ድንገት ወደ ወንዙ ትወድቅና የጀልባዋ ሰራተኞች ለማትረፍ ቢሯሯጡም ያቅታቸዋል! ! በመሀል ከወንዙ ዳር ቆመው ይመለከቱ ከነበሩት ሰዎች አንዱ ወደ ወንዙ ዘሎ ገብቶ በመዋኘት የልጅቷን ነፍስ ያተርፋል!!
ፈርኦኑም የልጁን ነፍስ ባተረፈለት ወጣት ጀብዱ እጅግ ይደሰትና ወደቤተ መንግስቱ አስጠርቶ ይሸልመዋል!! ወጣቱ በሽልማት ደምቆ ወደ መኖሪያው ሲመለስ ታዲያ ባለቤቱ እጅግ ተገርማ
"እንዲያው ለመሆኑ ከሁሉ ቀድመህ እንዴት በጀግንነት ወደ ወንዙ ዘለህ ልትገባ ደፈርክ??!!" ስትል ትጠይቀዋለች።
"ኧረ እኔስ ዘልዬም አልገባሁ፣ እንዲያው ሁን ሲለው እንጂ!!"
"ዘለህ ካልገባህ ታዲያ እንዴት የልእልቷን ህይወት ልታተርፍ ቻልክ??!!" ሚስት በአግራሞት!!
ሰውየውም እንዲህ ሲል መለሰ
፨ "ማን ገፍትሮ ወደወንዙ እንደጨመረኝ እንጃ !!"
አንዳንዴ ጀግንነት ሳናስበው እንዲህ
አባሮ ይለጠፍብናል!!