«««ካዕባ»»»
ኢብኑ ተይሚያ፦
"......እንደሚታወቀው የተለያዩ ነገስታት ምሽጎችን፣ ከተሞችንና የተንጣለሉ ህንፃዎችን በከበሩና ታላላቅ በሆኑ የግንባታ ቁሶች፣ ማእድኖችና እጅግ በረቀቀ የምህድስና ጥበብ ይገነባሉ። ነገር ግን እነዚህ ሰገነቶችና ህንፃዎች ብዙ ዘመናት ሳይቆዩ በተለያዩ ምክንያቶች ይደረመሳሉ። ይንኮታኮታሉ። የአላህ ቤት የሆነው ካዕባ ግን አዝመራ በሌለበት ሸለቆ ውስጥ በጥቁር ድንጋዮች ተገነባ። በዙሪያው ነፍስ ከምትሻው ሁሉ ከአትክልት፣ ከፍራፍሬ፣ ከመናፈሻ፣ ከውሃ ከሌሎችም ማግኘት አይታሰብም ነበር። ከጠላት የሚጠብቀው የተደራጀ ሰራዊትም አልነበረውም። ወደ ካዕባ በሚያደርሰው መንገድም ነፍስ የምትደሰትበት ነገር በፍፁም አይገኝም። እንደውም ወደ ካዕባ የሚያደርሰው መንገድ በፍርሀት፣ በድካም፣ በጥማት፣ በረሀብና አላህ ብቻ በሚያውቃቸው መከራዎች የተሞላ ነበር። ነገር ግን አላህ ለዚህ ቤት በምድር ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ እንዲዋደቁ አድርጓል። ለዚህም ሲባል ታላላቅ ነገስታትና መሪዎች ይህን ቤት አስበው ተናንሰውና እንደተራ ሰው ሆነው እስኪመጡ ድረስ ልቅናን፣ ክብርንና የበላይነትን አጎናፅፎታል።
ይህ ከካዕባ ክብር ሚስጥር ጀርባ ያለው እውነታ ከሰው ልጆች አካላዊና መንፈሳዊ ሀይል የላቀ መሆኑን በግዴታ ያሳውቀናል። የገነባውም ከሺዎች አመታት በፊት አልፏል።"
[الصفدية :1/222]
https://t.me/abdurezaq27