✍
ይህ ነገር የታዘበው አለ?? ዐይታችሁ እንደሆነ የሌላ እምነት ተከታይ የሆነ ሰው ወደ ስልጣን ሲወጣ ወይም ከትላልቅ ባለስልጣኖች ጋ የሚያገናኘው መስመር ላይ ሲደርስ እሱም የእምነቱ ተከታይ የሆኑ ወዳጆቹ ይደሰታሉ።
ምክንያቱን፦
እሱ ስልጣን ላይ በመውጣቱ ከቻለ በቀጥታ በመወሰን: ካልሆነም እንዲወሰን ድምፅ በመሆን ለዛ እምነት ተከታዮች ከመንግስትም ይሁን ከሀገሪቱ የሚፈልጉትን ሁሉ እንዲያገኙ ሽፋን ይሰጣል። ስልጣኑን በመጠቀም እምነቱ እና የእምነቱ ተከታዮች ሀገሪቷ ላይ ፍላጎታቸው እንዲሟላላቸው (ለእምነቱ) ወጥሮ ይሰራል።
በተቃራኒው አንድ ሙስሊም የሆነ ወንድም ስልጣን ላይ ከተመቻቸ: ወይም ከትላልቅ ባለ ስልጣኖች መቀማመጥ እና መወያየት ከጀመረ ነገሩ ከላይ ባየነው ተቃራኒ ይሆናል። አይደለም እስልምና ወይም ሙስሊሞች ሊረዳ ይቅርና እሱ ለራሱ
የራሱን እስልምና በግልፅ ለማራመድ ይሳቀቃል። ትላልቅ ወይም
"የሀላፊ ቢሮ" የሚባሉ ዐይነት ቢሮዎች ገብታችሁ እዛ ቦታ ላይ የሚቀመጡ ሙስሊሞች ብታዩ ለዚህ ሁነኛ ምስክር ናቸው።
ፂማቸው ከመከርከም ጀምሮ
ልብሳቸው ለማሳጠር ሁላ ይሳቀቃሉ። አንተ ገብተህ ራሱ
"አሰላሙ ዐለይኩም" ስትላቸው: አጠገባቸው ሌላ ሰው አለመኖሩ እርግጠኛ ከሆኑ ብቻ ነው ሰላምታህን ድምፃቸው እየሰማህ የሚመልሱልህ።
ከዚህ ሁሉ የከፋው………
እነዚህ በሀላፊነት ደረጃ ላይ የተቀመጡ ሙስሊም ባለስልጣኖች ከስሮቻቸው ወዳሉ ተቋሞች ሄደው ሌሎች ሙስሊሞች ላይ ጫና እንዲያደርጉ ይገደዳሉ። እነርሱም ይተገብሩታል። ለምሳሌ፦
አካዳሚ እያለን የጁሙዐ ሰላት ከመስገድ ስንከለከል እና እኛም የመስገድ መብታችን ስንጠይቅ "በትምህርት ስርዓት ላይ እስካለን መስገድ እንደማንችል" እንዲነግሩን ይላኩና ይመጡ የነበሩት ወረዳው ላይ የነበሩ ሙስሊም አመራሮች ነበሩ። "እኛ እንደናንተው መስገድ የምንፈልግ ሙስሊሞች ብንሆንም ያለንበት የስራ ህግ ስለማይፈቅድልን ወጥተን እንደ ማንሰግደው ሁሉ: እናንተም ትምህርታችሁ እስክትጨርሱ ድረስ አትስገዱ" ይሉን የነበረችው ማሳመኛ አሁን ድረስ ትታወሰኛለች።እውነቱን ለማውራት………
ከላይ የጠቀስናቸው ዐይነት ባለስልጣኖች ትምህርታቸው በሚማሩበት ጊዜ
"እንደምንም ተምሬ የሆነች ቦታ ልያዝና ቢያንስ ለእስልምና እና ለሙስሊሞች የሆነ ነገር አደርጋለሁ።" የሚል መልካም ምኞት የነበራቸው ናቸው።የኋላ ኋላ ግን ዕድሜያቸው የጨረሱበት የስልጣን እርከን ላይ ሲደርሱ
ያሳለፉት ድካም፣ የወንበሩ ምቾት፣ የገቢው ጥፍጥና እና የተገኘው ዕውቅና ተሰብስበው ይሸነግሉትና ለእስልምና የሆነ ነገር ቢፈይድ ከዚህ ወንበር እንዳይሰናበት እየፈራ
ለስልጣኑ ሰስቶ እስልምናውን ይደብቃል። እንዴት ያለ ሙሲባ ነው?? ለዚህ ሁሉ ውድቀት ምክንያቱ ከተጠየቀ ምላሹ አንድና አንድ ነው………
እነዚህ ሰዎች በየዋህነት ወደ ፊት እስልምና ለመርዳት አልመው እድሜያቸው በአካዳሚ ጨረሱ እንጂ:
ሊረዱት የተመኙት እስልምና ምን እንደሆነ ለመረዳት አንድም ቀን ጊዜያቸውን ሰጥተው እስልምናን ተምረው አያውቁም። እስልምናን የተማረው እና ያወቀው ሰውማ አይደለም ስልጣኑን ሕይወቱን ፊዳ ያደርጋል እንጂ በፍጹም እስልምናው ላይ አይደራደርም!!
በመሆኑም…………
አካዳሚም ይሁን ሌላ ዐይነት መስክ ላይ መሰማራት የፈለገ ሙስሊም: ከምንም ነገር በፊት እስልምናውን መማር እና ማወቅ አለበት።
ወላጅ ሆይ!!
"ልጆ ተምሮ ቦታ ይያዝና እስልምና ላይ የሆነ አሻራ ያሳርፋል" ብለህ አካዳሚ ላይ የምትማግደው ልጅህ ነገ ያሰብክለት ደረጃ ላይ ሲደርስ ለእስልምና አሻራ ሊያሳርፍ ሳይሆን
የራሱ እስልምና እንዳይንሸረሸር ከዚህ ትምህርት ውሰድና ቆም ብለህ አስብ!! 📖{قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ}
{ሰላቴንም እርዴንም መኖሬንም መሞቴንም የዐለማት ጌታ ለሆነው አላህ ነው በል።}🖊
ሐምዱ ቋንጤ ከፉርቃን ሰማይ ስር!!https://t.me/hamdquante👆
👇
https://t.me/abduselamabumeryem/5376