በሃሰት የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] አለብኝ በማለት ወደ 8335 የደወለችው የጎንደር ከተማ ነዋሪ በፖሊስ በቁጥጥር ስር ዋለች። ወጣቷ ቀበሌ 16 በግል ስራ ተቀጥራ የምትሰራ ሲሆን ከአረብ ሃገር በቅርቡ እንደመጣች በመግለጽ የበሽታው ምልክት እንደታየባት እና እርዳታ እንደምትሻ ተናግራ ነበር ብሏል የከተማዋ ፖሊስ።
ይህንን ተከትሎም የክልል እና የዞን የጤና ባለሙያዎች ተነጋግረው ልጅቷን ሲያፈላልጉ ስልኳን በመዝጋት ተደብቃ የነበር ቢሆንም ፣ በ ጂ ፒ ኤስ ተፈልጋ ተገኝታለች ተብሏል።
በከተማዋ ፖሊስ መምሪያ የ4ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊው ረዳት ኢንስፔክተር ወንድምሁነኝ ተሻገር ለ ዶቼ ቬለ እንዳሉት፣ ወጣቷ ያለችበት ታውቆ በጤና ባለሙያዎቹ የሙቀት ልኬት ሲደረግላት ሙሉ ጤነኛነቷ ተረጋግጧል፣ የበሽታው ምልክትም አልተገኜባትም ብለዋል።
ወጣቷ ተፈልጋ እንደተገኘች መደወሏን ክዳ የነበረ ሲሆን ያንን ለምን እንዳደረገች ስትጠየቅ ምናልባት በሽታው ካለብኝ ወደ ማግለያ ክፍል ልወሰድ ስለምችል ያንን በመፍራት ነዉ ብላለች ብለዋል ኃላፊው።
(DW)
መጋቢት 18ቀን 2012 ዓ.ም
---------------------------------------------------
ክቡራን ቤተሰቦች ሀሳብ አስተያየታችሁን የዜና የመረጃ ጥቆማችሁን ከሰር ባለው ሊንክ አድርሱኝ:: አመሰግናለሁ
አቤል ብርሀኑ (የወይኗ ልጅ)
👉@abel21bot