“ይህ ሁሉ ንብረት የአንድ ሰው ሕይወት አይገዛልኝም፤
ነገር ግን ንብረቱን አስቀድሜ ለወገኔ ብሰጥ ብዙ ሰው አተርፋለሁ፡፡”
አቶ ተሾመ ይቴ
ባለሀብቱ ባለአምስት ሰገነት ቤታቸውን እና አንድ መኪናቸውን የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት አገልግሎት እንዲውል ለገሱ።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ነዋሪው ባለሀብት የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል እና ድንገት በሽታው ቢከሰት ለለይቶ ሕክምና መስጫ የሚሆን ባለአምስት ፎቅ (ሰገነት) ሕንጻቸውን እና መኪናቸውን ሰጥተዋል።
የወቅቱ የዓለም የጤና ፈተና የሆነው ኮሮና ወረርሽኝ ደግነትን እና ክፉነትን አበጥሮ ማሳያ እየሆነ መጥቷል። “ክፉ ቀን ወዳጅና ጠላትን መለያ ይሆናል” እንዲሉ ይህ ክፉ ጊዜ ክፉ እና ደጎችን መለያ ሆኗል። አንዳንዱ የበሽታውን መከሰት ተገን በማድረግ የግል ጥቅሙን ለማካበት ሲያሯሩጥ ብዙዎች ደግሞ ለሰው እየኖሩ ነው።
አቶ ተሾመ ይቴ ይባላሉ፤ በጎንደር ከተማ አስተዳደር ነዋሪ ባለሀብት ናቸው፡፡ በሀገራችን ብሎም በዓለም ፈተና የሆነውን የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከል ያስችል ዘንድ ያላቸውን አካፍለዋል። በጎንደር ከተማ አስተዳደር አዘዞ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ አባ ሳሙኤል በሚባል አካባቢ የሚገኘውን ባለ አምስት ፎቅ ሕንጻቸውን እና አንድ ‘ኤፍ ኤስ አር’ መኪናቸውን የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት እንዲያገለግሉ አበርክተዋል።
ቤቱ አምስት ሰገነቶች ያሉትና በእያንዳንዱ ሰገነት (ፎቅ) ስምንት ክፍል ያለው በጠቅላላ 40 ክፍሎችን የያዘ ነው። ከስር ደግሞ ሰፋፊ ክፍሎች አሉት። አቶ ተሾመ ከአብመድ ጋር በነበራቸው ቆይታ “በወረርሽኙ ዓለም የተሸበረበት ወቅት ነው፤ ከእኛ ሀገር በሽታው ከተዛመተ ካለን የጥንቃቄ ጉድለት አንጻር ምን ያክል ልንጎዳ እንደምንችል በማሰብ ነው ለመስጠት የወሰንኩት” ብለዋል። ለአገልግሎት