Edris Elias Nassir


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана



Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ኢብን አል-ቀይም

" ይህ እምነት በራሱ ስነ-ምግባር ነው። በመልካም ስነ-ምግባሩ የበለጠህ በእምነቱ በልጦሃል "

منقول

@abumahi


أنتي جميلة كفوز منتخب السعودية🇸🇦 على الأرجنتين 🇦🇷

✨🤍
___________________
@quotesandpic


ሰዎችን የምታከብረው ጥሩ ስለሆንክ ሳይሆን በመልሱ እንድትከበር ነው ። ለሰዎች ፍቅር የምትሰጠው መልካም ስለሆንክ ሳይሆን በመልሱ ፍቅርን እንድታገኝ ነው !

የናቅከው እንዲያከብርህ ፣ የዘነጋኸውም እንዲያፈቅርህ የምትከጅል ከሆነ '' ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ '' የሚለው ብሂል ላንተ ነው ። እንድትከበር አክብር ፣ እንድትደመጥ አድምጥ ፣ እንድትወደድ ውደድ ፣ እንዲሰጥህ ስጥ ።

ይህ የዱንያ ህግ ነው ' ከተቃረንከው የማያስደስትህን ውጤት ጠብቅ !
___________________
𝗝𝗼𝗶𝗻 || @abumahi


💥 مسألة وتعليق

🎙️ قال الإمام القرافي -رحمه الله- :
( ومن مات من أهل الضلال ولم يترك شيعة تعظمه، ولا كتاباً تقرأ، ولا سببا يخشى منه إفساداً لغيره ؛ فينبغي أن يستر بستر الله تعالى، ولا يذكر له عيب البتة، وحسابه على الله).
(الفروق :4/ 326)

✍️ قال مقيده غفر الله له ولوالديه :
أصول هذه المسألة ثمانية ، وهي :
📌- الأصل في معاملة المسلم الستر .
📌- الكلام في الناس حكم شرعي تكليفي وضعي معلق بسببه وشرطه وانتفاء مانعه .
📌- الغيبة محرمة إلا لحاجة .
📌- الكلام في المنتسبين إلى الشرع لا يباح إلا لغرض شرعي .
📌- مناط هجر الناس أو تبديعهم أو الرد عليهم معلق بالمصلحة الراجحة .
📌- يغتفر فيمن كان ضرره قاصرا ما لا يغتفر فيمن كان ضرروه متعديا .
📌- ضرر المعصية على الناس في الجهر بها .
📌- الأصل هو إعانة الناس على ترك المعاصي أو تقليلها ؛ وقد يكون السكوت أولى ؛ لأنه من باب تقليل الشر .

📚 فهذه أصول ثمانية ... وهي من عناوين الوسطية والاعتدال في الكلام على الناس …

_________________
@abumahi


እንግሊዛዊቷ አምበር ራሺድ እስልምናን ከተቀበለች በኃላ ለወላጅ እናት ቪኪ ኩክ ጥያቄ ቀረበላት

ልጅሽ እስልምናን መቀበሏ ስትሰሚ ምንድን ነበር የተሰማሽ?

" ስለ እስልምና ከሚዲያ ከምሰማው በቀር እውቀቱ የለኝም ፣
አምበር እጅጉን አስቸጋሪ ለእኔ የእናትነት ክብር የማትሰጠኝ ቁጡ ልጅ ነበረች
ከተለያዩ ወንዶች ጋር ስትዘል ውላ ሲላትም የምታድር

ጭፈራ ቤት አምሽታ ስክራ ሲነጋ ቤት የምትመጣ ፣ አንዳንዴ እራሷን ስታ ጓደኞቿ በር ላይ አድርሰዋት እኔ ደግፌ ነበር የማስገባት ፣
መስታወት ስር ተጥዳ ለምሽት እብደቷ በሜካፕ እራሷን ስትጋጊጥ ሰአታት የምታሳልፍ እና እርቃን በሚባል ሁኔታ ከቤት የምትወጣ ልጅ ነበረች
ሳዝንባት እና ሳለቅስላት ነበር የኖርኩት

እስልምና ከተቀበለች በኃላ
ለእኔ ያላት ክብር ቃላት አይገልፀውም ድምጿን ከፍ አድርጋ እንኳ አታወራኝም ፣ እጅጉን የተረጋጋች እና የሰከነች ሆናለች ፣
አልባሌ ቦታ ከሚወስዷት ጓደኞቿ እርቃ ከስራ ውጪ አብዛኛውን ጊዜዋን በፀሎት ፣ ቁርአን በማንበብ ከእኔ ጋር በመጫወት ነው የምታሳልፈው

እስልምና ልጄን መልሶልኛል ፣ ምኞቴን ሞልቶልኛል
በያዘችው እምነት እስከ መጨረሻ ትዘልቅልኝ ዘንድ ነው የምመኘው
እንዳልኩህ ስለ እስልምና አላውቅም ነገርግን ልጄን በባህሪ እንዲህ ያረቀልኝን እምነት ግን አከብራለሁ
@bilal Zeyd

@abumahi


{ وَمَا تَسْقُطُ مِنْ وَرَقَةٍ إِلَّا يَعْلَمُهَا }
#كيف_بدمعة_من_عين_مؤمن ؟

______________________
@quotesandpic


እንዴት ነው ሶብር ( ትዕግስት ) የምናደርገው ?

የመግሪብ አዛን እንደሚል እርግጠኛ ሆነን እንደምንፆመው !

_____________
@abumahi


የታገሉት ሸሪዓን ለማስፈን ነው። የደሙት የቆሰሉትም ስለኢስላም ክብር ነው። ከሰማይ የእሳት አሩር ከምድርም የጥይት ወላፈን እየለበለባቸው ለሀያ አመታት የተፋለሙት የአፍጋኒስታን መንግስት ጣሊባኖች በሀገሪቱ እንደ ብሄራዊ ክብረ በአል ተደርጎ ሲቆጠር የነበረውን መውሊድን ከብሄራዊ በአልነት ሰርዘው እለቱ የስራ ቀን ሆኖ እንዲያልፍ ወስነዋል።
Mahi Mahisho

@abumahi


ከዕለታት አንድ ቀን ልብህ በሀሴት ተሞልቶ እና የምኞትህ ደርሶ '' አሏህ ሆይ ! ስለምንህ የነበረው ይህንን እንድታሳካልኝ ነበርና የተትረፈረፈ ምስጋና ይገባህ '' የምትልበት ቀን ቅርብ ነው ። ተስፋ እንዳትቆርጥ ።

🤍✨
____________________
𝗝𝗼𝗶𝗻 || @abumahi


ከፊሉ ዘንድ የመላዒካ ያህል ንፁህና የተከበርክ ነህ ከፊሉ ዘንድ ደግሞ የሸይጧን ያህል የተረገምክና የተዋረድክ ነህ ። ሰዎች ስለ አንተ በሚሰጡት ፍርድ እራስህን አትመዝን ። አንተን ከማንም በላይ አሏህ ያውቅሃል ከርሱ ውጭ ካሉ ፍጡራኖች ደግሞ ስለእራስህ አንተው የተሻለ ዕውቀት አለህ ።

እራስህን በራስህ መዝን ክፋትህን ፣ ጥፋትህን ፣ ድክመትህና ስንፍናህን ማንም ሳይነግርህ ጠንቅቀህ ታውቃለህ ። እነዚህን.... ከእራስህ ጋር ስብሰባ ተቀምጠህ ተማመን ፤ ከዚያም ለመለወጥና ለመሻሻል ጥረት አድርግ ። ከእራስህ ጋር የውሸት ሳይሆን የዕውነት ኑር ። ምክንያቱም በመጨረሻ የዕውነት ትሞታለህ ።

የውሸት ኖሮ የዕውነት የሞተ ምንኛ ተጎዳ !

____________________
𝗝𝗼𝗶𝗻 || @abumahi


'' መውሊድ ረሱል ﷺ አክብሩ ስላላሉ አላከብርም '' ብለህ ስታበቃ መውሊድ የሚያከብሩ ሙስሊም ወንድምና እህቶችህን በትዕግስት በጥበብና በመልካም ከስህተታቸው በመመለስ ፈንታ የምትሳደብ ከሆነ....

ለአንተ አንድ ጥያቄ አለኝ , ረሱል ﷺ መች እና በየትኛው ሀዲስ ነው ስህተት የሚፈፅሙ ሰዎችን ስደቡ ያሉት ?

በተገራ አንደበት በጥበብና በዕውቀት ሰዎችን ማረም የማትችል ከሆነ ዝም በል ! ሰዎች በአንተ ግልፍተኝነት ሳቢያ ሀቅን እንዲጠሉ ምክንያት አትሁን ። ሰዎች ሀቅን እንዲጠሉ ሰበብ መሆን ምን አልባት መውሊድ ከማክበር ጋር የሚስተካከል ወንጀል ሊሆን ይችላል ።

ስሜትህን ግራ ... ሁሉም ሰው በአንድ ጀምበር አንተ የተረዳኸውን እንዲረዳ አትጠብቅ ። ዳዕዋ ፍሬ የሚያፈራው ከትዕግስት ጋር ሲቆራኝ ብቻና ብቻ ነው !

__________________
𝗝𝗼𝗶𝗻 || @abumahi


እጅህን ተሰበርክና መዳን ከጅለህ ወጌሻ ዘንድ ሄድክ ። ወጌሻው ህክምናውን ሲጀምር የተሰበረውን አጥንት እያዟዟረና እያሸ ህመምህን ይበልጥ ያበረታዋል ። ወጌሻው የተሰበረ እጅህን ነካክቶ ህመምህን የጨመረው ሊጎዳህ ስለፈለገ ነው ? አይደለም ! አንተም እንደዚያ አታስብም ። የሚያሳምምህ ሊጎዳህ ፈልጎ መሆኑን ብታምንማ ገና ሲነካ እብድ የሚያደርግ የተሰበረ እጅህን እንደፈለገ እንዲጨማምቀው አሳልፈህ አትሰጠውም ።

ሀዘን ፣ መከዳት ፣ ብቸኝነት ፣ ብሶት ፣ ማጣት ፣ ችግር ፣ ስቃይ ፣ መከራ ... ህይወትህንና ነፍስህን ሰባብሯታል ። ሰዎች ዘንድ ብርቱ መስለህ ውለህ ለብቻህ ስትሆን ተንሰቅስቀህ የምታነባው ፣ ለወጪ ለወራጁ ፈገግታህን ስትለግስ ቆይተህ ከራስህ ጋር ስትሆን ውብ ፊትህን ሀዘን ጨለማ የሚያወርሰው ድቅቅ ብለህ ስለተሰባበርክ ነው ። ከስብራትህ መዳን ትፈልጋለህ ?

ወጌሻውን አምነህ እጅህን እንደሰጠኸውና ሲያሽህ የተፈጠረውንም ህመም ጥርስህን ነክሰህ እንደታገስከው ወደ አሏህም ተጠጋና ስብራትህን አንድም ሳታስቀር ንገረው ። ሲያክምህና ሲጠግንህ የሚኖረውንም ህመም ጥርስህን ነክሰህ ታገስ ። አሏህ የሚያሳምምህ እንዳልታመምክ አድርጎ ሊያሽርህ ነው ።

ትዕግስት መራራ ነው ' ውጤቱ ግን የማይነጥፍ ጣፋጭ የማር ጅረት ነው !
_____________
@abumahi


በሰዎች ደስታ ካልተደሰትክና በሚገጥማቸውም ክፉ ካላዘንክ እውነተኛ ደስተኛ አትሆንም !

ኢስላም ከእራስ ባልተናነሰ ለሌሎች ማሰብን የሚያዝ እምነት ነው ። በራስህ ላይ እንዲሆን ማትሻውን ክፉ ሌሎች ላይ ስትመለከት እዘንላቸው ችግራቸውንም ማስወገድ ይችሉ ዘንድ የአቅምህን እርዳቸው ። በተቃራኒ አንተ ብታገኘውየሚያስደስትህን መልካም ነገር ሌሎች አግኝተው ከተመለከትክ ለደስታቸው ተደሰት ። በሌሎች ጉዳት ፣ ሀዘንና ማጣት ምንም የምታተርፈው የለም ። በደስታቸውና በማግኘታቸውም ከአንተ የሚቀነስና የምታጣው አንዳችም አይኖርም ።

አማኝ ሁሌም ደስተኛ እና አዕምሮው ሰላማዊ ነው ። ይህም የሆነበት ሚስጥር ለራሱ የሚመኘውን መልካም ሌሎችም በመውደዱና ፤ እርሱ ላይ እንዲሆን የማይሻውን ክፉ ለሌሎች በመጥላቱ ነው ።

'' አንዳችሁ ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ #አላመነም ''
[| ረሱል ﷺ |]
أخرجه البخاري، كتاب الإيمان(1/ 14)، رقم: (13)، ومسلم، كتاب الإيمان (1/ 67)، رقم: (45).

_____________________________________
https://www.facebook.com/profile.php?id=100079028036202


ካዕባ ላይ ምራቅህን ትተፋለህ ?
____________________________
አሁን ከካዕባ ፊት ቆመህ ቢሆን ካዕባ ላይ ምራቅህን ትተፋ ነበር ? የካዕባን ክብር በማይመጥን መልኩስ ትሰድበውና ልታረክሰው ትሞክር ነበር ?

እርግጠኛ ነኝ አንተም ሆንክ የትኛውም ብናኝ የምታህልን እምነት በልቡ የያዘ ሙስሊም ይህንን አያደርግም ። ኧረ እንደው ማድረጉ ቀርቶ እንዲህ ያለ ሰይጣናዊ ተግባር በሀሳቡ እንኳ ውል አይልበትም ።

ታድያ ምነው ከካዕባ የበለጠ ክብር ያለው ፍጥረት ላይ የተለያዩ በደሎችን ለመፈፀም እጃችንና ምላሳችን ቀለላቸውሳ ?! ከካዕባ በላይ ክብር ያለው ማን እንደሆነ ግር ብሎሀል ? እንግዲያውስ ረሱል ﷺ ይመልሱልህ

رأيتُ رسولَ اللَّهِ صلَّى اللَّهُ عليْهِ وسلَّمَ يطوفُ بالكَعبةِ ويقولُ ما أطيبَكِ وأطيبَ ريحَكِ ما أعظمَكِ وأعظمَ حرمتَكِ والَّذي نفسُ محمَّدٍ بيدِهِ لَحُرمةُ المؤمنِ أعظَمُ عندَ اللَّهِ حرمةً منْكِ مالِهِ ودمِهِ وأن نظنَّ بِهِ إلَّا خيرًا

በሆነ አጋጣሚ ረሱል ﷺ ካዕባን ጠዋፍ እያደረጉ እንዲህ አሉት '' ምንኛ አምረሃል መዐዛህም ምንኛ አምሯል ፣ ምንኛስ ተልቀሃል ክብርህም ምንኛ ተልቋል ...የሙሀመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ አሏህ ዘንድ አንድ ሙዕሚን ከአንተ የበለጠ የተከበረ ነው የእርሱ ገንዘቡም ደሙም ( አሏህ ዘንድ ከአንተ የበለጠ የተከበረ ነው ) ፣ ( አንድ አማኝ ) በመልካም እንጂ በሌላ ( በክፉ ) ላንጠረጥረውም ( ክብሩ ከአንተ ልቋል ) ''
[ በቀላል አተረጓጎም ወደ አማርኛ የተመለሰ ]

" السلسلة الصحيحة " رقم : 3420 و " صحيح الترغيب والترهيب " رقم 2441 ]

ዛሬ እንደቀልድ በተውረግራጊ ምላሳችን ከፍ ዝቅ የምናደርጋቸው ፣ ክብራቸው ያለ ርህራሄ የምንገፋቸው ፣ ባልተረጋገጠ መረጃ ላይ ተንተርሰን አሉባልታ የምንነዛባቸው አማኝ ወንድምና እህቶቻች አሏህ ዘንድ ከካዕባ የበለጠ የተከበሩና ውድ ናቸው ።

የካዕባን ክብር ለመዳፈር ብትሞክር ከአሏህ ዘንድ ምን ሊጠብቅህ እንደሚችል ማወቅ ከፈለግክ '' የአብረሃን '' ታሪክ በሱረቱ አል~ፊል ላይ መመልከት ይበቃሀል ። አሏህ ዘንድ ከካዕባ የበለጠ ክብር የተሰጠውን ሙዕሚን አሳዝነህ ደግሞ ምን ሊገጥምህ እንደሚችል አስበው ...

መልዕክቱ አብዝቶ ሴት እህቶችን ይመለከታል

___________________________
join || https://www.facebook.com/profile.php?id=100079028036202


አሏህ ምን ያህል ታላቅ ነው ?
_______________________________

ልጅ አባቱን እንዲህ ሲል ጠየቀ '' አባዬ አሏህ ታላቅ እንደሆነ ነግረኸኛል ግን ምን ያህል ታላቅ ነው ? '' አባትም የልጁን እጅ ይዞ ከቤት ወጣና በሰማይ ወደ ሚበር አውሮፕላን እያመላከተ '' ልጄ ያ የምትመለከተው አውሮፕላን ምን ያህላል ? '' ሲል ጠየቀው ። ልጅም '' እጅግ በጣም ትንሽ ነው '' ሲል መለሰ ። አባትም በድጋሚ የልጁን እጅ ይዞ ወደ አየር ማረፊያ አቀና ። እንደደረሱም አባት ከፊታቸው ወደቆመው እጅግ ግዙፍ የተጓዦች አውሮፕላን እያመላከተ '' ልጄ አሁንስ አውሮፕላን ምን ያህላል '' ብሎ ጠየቀው ልጅም '' እጅግ በጣም ግዙፍ ነው '' ብሎ መለሰ ። ይህንን አስከትሎም አባት ድንቅ መልዕክት አስተላለፈ...

'' ልጄ ሆይ , ከፈጣሪ ስትርቅ ፣ ስሜትህን ስትከተልና ወንጀል ውስጥ ስትዳክር ልክ ከርቀት እንደተመለከትከው አውሮፕላን ፈጣሪም በልብህ ውስጥ ያለው ቦታ ያንሳል ። በተቃራኒው ስለፈጣሪ ስታውቅ ወደርሱም ስትቀርብና መልካምነትህ ሲበዛ ፈጣሪ በአንተ ልብ ውስጥ እጅግ ትልቅ ይሆናል ! ''

إِنَّمَا يَخْشَى اللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ الْعُلَمَاءُ

አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ብቻ ናቸው
( سورة فاطر ٢٨ )
__________
@abumahi


የዩሱፍ ዐለይሂ ሰላም መገኘትን ተከትሎ በያዕቁብ ዐለይሂ ሰላም ልብ ውስጥ የተንቦገቦግሽው ደስታ ሆይ የእኛንም ቀልብ ዘይሪ

ያረብ , በዱንያም በአኺራም ደስታ ብቻ 🤲🏻
______________
@abumahi


አንድ ስመ-ጥር ባለ ስልጣንና ባለሀብት ያለህበትን ጭንቅና መከራ ተመልክቶ #አብሽር እኔ አለሁልህ ቢልህ ምን ይሰማሃል ? ደስታ አይደል ?!

እንግዲያውስ የመስጠትም የመንሳትም ስልጣን ፣ የመፍጠርም የማጥፋትም ኃይል ፣ የመሸለምም የመቅጣትም መብት ..... ያለው አሏህ ችግርህን በሚገባ ያውቃል , ብሶትህንም በሚገባ ይረዳል እናም እንዲህ ይልሃል

وَبَشِّرِ الصَّابِرِينَ ۝
" ታጋሾችንም አብስር "

አሏህ ታገስ ሲልህ ባልጠበቅከው መልኩና እጅግ በትልቁ ሊያስደስትህ ነውና ታገስ 🤌🏻
______________
@abumahi


አባት ልጁን ሊመግብ አስቦ ከጎኑ ቁጭ አደረጋትና ብርትኳን መላጥ ጀመረ ። ልጅ ለመብላት ጓጓችና ብርትኳኑን ለመቀበል እጇን ሰደደች ፣ አባትም '' ትንሽ ታገሺ ለአንቺው ነው የምልጠው '' አላት ። ልጅ መብላት ጓጉታለችና አልሰማ ብላ ለሁለተኛ ጊዜ ብርትኳኑን ከአባቷ ልትነጥቅ እጇን ላከች '' አባትም ግድ የለሽም ትንሽ ብቻ ታገሺ እየላጥኩ ያለሁትኮ ለራስሽ ነው ደግሞ ብሰጥሽም መላጥ ስለምትችዪ ትቸገሪያለሽ እስከነ ልጣጩ ብትመገቢው ደግሞ በጣም ይመርሻል እናም ትንሽ ጠብቂ '' አለ ። ልጅ አልታገስ ብላና በአባቷ አዝና ለቅሶዋን አስተጋባች ።

ወዳጄ , አንተስ ከፈጣሪህ ጋር ያለህ ሁኔታ ምን ይመስላል ? አሏህ የፃፈልህ ሲሳይ ትክክለኛ ጊዜውን ጠብቆ ተሽሞንሙኖ እስኪመጣ በትዕግስት ትጠብቃለህ ወይንስ ልክ እንደ ህፃኗ ትዕግስት አጥተው ከሚያማርሩትና ከሚወራጩት ነህ ?

ሁላችንም የየራሳችን ብርትኳን አለን ። የአንዳዳችን ቶሎ ተልጦ ሲመጣ የሌሎቻችን ደግሞ ለመልላጥ ተራውን እየጠበቀ ነው ። ታድያ አንታገስምን ?!


__________________
𝘑𝘰𝘪𝘯
@abumahi


ጤነኛ ፣ ደስተኛና ስኬታማ ለመሆን የሚረዱን ወሳኝ 7 ነጥቦች ፡፡

1 ) እራስህን ከማንም ጋር አታወዳድር !
2 ) እራስህን ከማንም ጋር አታወዳድር !
3 ) እራስህን ከማንም ጋር አታወዳድር !
4 ) እራስህን ከማንም ጋር አታወዳድር !
5 ) እራስህን ከማንም ጋር አታወዳድር !
6 ) እራስህን ከማንም ጋር አታወዳድር !
7 ) እራስህን ከማንም ጋር አታወዳድር !

የሀያት ዐይን ተለቅ ተለቅ ያለው ለደንታዋ ነው ፡፡ የአንቺውን ከእሷ ጋር እያወዳደርሽ ለምን በራስሽ ላይ ጉድለትንና ሽንቁርን ትፈጥሪያለሽ ፡፡ ሀያት በሀያትነቷ ቆንጆ ነች ፥ አንቺም ደግሞ ባለሽበት ውብ ነሽ ፡፡

አጨብጭበህ የገዛኸው nike ጫማ የማሜን adidass ስታይ ከደበረህ ችግሩ ያለው ከጫማው ሳይሆን ከአንተ ነው ፡፡ የተሰጠህንና ያለህን በእራስህ ዐይን እንጂ በሌሎች ለመመልከትና እነሱ ከተሰጡትም ጋር ለማወዳደር አትሞክር ፡፡ አልያ ደስታ የሚባልን ሽታውን እንኳ አታገኝም ፡፡

በጣም የሚገርመው ኸሊፋ እራሱን ከሸምሱ ጋር እያወዳደረ ደስታው ይሸሸዋል ፥ ሸምሱም በበኩሉ የራሱን ከኸሊፋ ጋር እያወዳደር ደስታን በመኮምኮም ፈንታ ይቆዝማል ፡፡

ጎበዞች , ሁላችሁም ልዩ ናችሁ ፡፡ ያላችሁበት ተጨባጭም ውብ ነው ፡፡ keep apreciating and being your self !


______________________
@quotesandpic


‏لاتُحرق كِتاب حياتك لأجل صفحة سَوداء :
إما أطوها بِلطف, أو أنزعها بعُنف .. 😊
__________________
@quotesandpic

Показано 20 последних публикаций.

1 345

подписчиков
Статистика канала