ወጥታ በአስክሬኑ ላይ ትቀመጣለች፡፡ በዚህ ጊዜ መልአከ ሞት በጥፍሩ ወግቶ ቆንጥሮ በጥርሱ ቆርጥሞ አላምጦ 3 ጊዜ ይተፋታል፡፡ 3 ጊዜ መትፋቱ ስለምን ነው? ቢሉ ‹‹አንቺ ነፍስ በአርአያ ሥላሴ የተፈጠርሽው የሥላሴን አንድነት ሦስትነት አውቀሽ፣ ሃይማኖት ተምረሽ፣ ምግባር ሠርተሽ፣ ሰንበት አክብረሽ፣ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን በንጽሕና ተቀብለሽ፣ በሕግ በሥርዓት ሆነሽ ልትኖሪ ነበር፡፡ ይህን አላወቅሽም፣ አላደረግሽም ዐመፀኛ ነሽ…›› ሲል 3 ጊዜ እየቆረጣጠመ ይተፋታል፡፡ ‹‹ከመዝኑ ሞት መሪር-በውኑ ሞት እንደዚህ መራራ ነውን?›› እንዳለ ንጉሥ አጋግ፡፡ 1ኛ ሳሙ 15፡32፡፡
ዳግመኛም እኩሉ አጋንንት በሰማይ እኩሉ በምድር ሆነው 13 ጊዜ ወደ ሰማይ፣ 13 ጊዜ ደግሞ ወደ ምድር እያንቀረቀቡ ከምድር ላይ ያፈርጧታል፡፡ ስለምን 13 ጊዜ ወደ ሰማይ እያጓኑ ይጫወቱባታል? ቢሉ ‹‹አንቺ ነፍስ ጌታሽ አምላክሽ በዕለተ ዐርብ 13ቱን ሕማማተ መስቀል የተቀበለልሽ ለአንቺ መድኃኒት፣ ለአርአያ፣ ለቤዛ ነበር፡፡ አንቺ ግን ይህን አውቀሽ ሃይማኖት ተምረሽ፣ ምግባር ሠርተሽ፣ ሰንበትን አክብረሽ አልኖርሽም፤ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን በንጽሕና አልተቀበልሽም፤ ሕጉን ትእዛዙን አልጠበቅሽም፤ ዐመፀኛ ነሽ›› ብለው ስለዚህ 13 ጊዜ ወደ ሰማይ እያጓኑ፣ ከምድር ላይ እያፈረጡ ይጫወቱባታል፡፡ ዳግመኛም የፊጥኝ የግርግሪት የኋሊት አሥረው፣ በእሳት ልጓም ለጉመው፣ በእሳት ሰንሰለት አሥረው፣ አንቀው ይዘው በእሳት በሎታ ራስ ራሷን እየቀጠቀጡ ያስለፈልፏታል፤ ያስጨንቋታል፡፡ እርሷም በዚህ ታላቅ ጭንቅና መከራ ውስጥ ሆና ‹‹…ወዮ የሥላሴ ያለህ!›› ትላለች፤ ታማፅናለች፡፡ መላእክተ ጽልመትም ‹‹ከእኛ ዘንድ ስትመጪ ነው ሥላሴን የምታውቂያቸው? ከዚያ ሳለሽ ስለሥላሴ ብለሽ ሃይማኖት በተማርሽ፣ ምግባር በሠራሽ፣ ሰንበትን ባከበርሽ፣ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን በንጽሕና በተቀበልሽ፣ በሕግ በሥርዓት ሆነሽ በኖርሽ ነበር እንጂ…›› እያሉ ‹‹..በሏት ጨርሷት ቀጥቅጧት›› እየተባባሉ ያሠቃዩአታል፡፡ ዳግመኛም ‹‹…ወዮ ወዮ የመድኃኔዓለም ያለህ!›› እያለች ታማፅናለች፡፡ መላእክተ ጽልመትም ‹‹ከእኛ ዘንድ ስትመጪ ነው መድኃኔዓለምን የምታውቂው? ከዚያ ሳለሽ ስለመድኃኔዓለም ብለሽ ሃይማኖት በተማርሽ፣ ምግባር በሠራሽ፣ የታረዘ ባለበስሽ፣ በመጸውትሽ፣ ቤተ ክርስቲያን ስመሽ በኖርሽ፣ ሰንበትን ባከበርሽ፣ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን በንጽሕና በተቀበልሽ፣ በሕግ በሥርዓት ሆነሽ በኖርሽ ነበር፡፡ መድኃኔዓለምማ በመስቀል ተሰቅሎ፣ ሥጋውን ቆርሶ ደሙነ አፍስሶ የሰጠሸ ለአንቺ መድኃኒት አልነበረምን? ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን በንጽሕና አልቀበልም ብለሽ፣ ሰንበትን አላከብርም ብለሽ፣ ዐርብና ረቡዕን አልጾምም ብለሽ፣ ንስሓ አልገባም ብለሽ ነው እንጂ፡፡ ደግሞ በምድር ላይ ሳለሽ ነው እንጂ መጠንቀቅ…›› እያሉ ‹‹..በሏት ጨርሷት ቀጥቅጧት›› እየተባባሉ ስቃዩአን ያበዙታል፡፡
ያቺ ጉስቋላ ነፍስ ዳግመኛም ‹‹…ወዮ ወዮ የእግዝእትነ ማርያም ያለህ!›› እያለች ታማፅናለች፡፡ መላእክተ ጽልመትም ‹‹ከእኛ ዘንድ ስትመጪ ነው እግዝእትነ ማርያምን ያወቅሻት? ከዚያው ሳለሽ ነበር እንጂ ዝክሯን ማዘከር፣ በዓሏን ማክበር፣ ለተራበ ማብላት፣ ሕጉን ትእዛዙን አጽንቶ መኖር…›› እያሉ ‹‹..በሏት ጨምሩላት›› እየተባባሉ ስቃዩአን ያበዙታል፡፡ ከዚኽም በኋላ የፊተኞቹ እየጎተቱ የኋለኞቹ እያስጨነቁ ይዘዋት ይሔዳሉ፡፡
ከዚኽም በኋላ መላእክተ ብርሃን የጌታን ቃል ሳይሰሙ አይለቋትምና ራስ ራሷን እያዩ ይከታተሏታል፤ እንዲህ ሲከታተሉ ከባሕረ እሳት ይደርሳሉ፡፡ ከዚያም መላእክተ ጽልመት 3 ጊዜ ራሷን ቀጥቅጠው ባሕረ እሳቱን ‹‹ሂጂ ግቢ ተሻገሪው›› ይሏታል፡፡ እርሷም ‹‹ምን ጨብጬ፣ በምንስ ላይ ቆሜ ልሻገረው? ቀኙ እሳት፣ ግራው ውኃ፣ ውስጡ ገደል ነው፣ መንገዱም እንደጭራ የቀጠነ ነውና ምን ረግጬ በምን ላይ ቆሜ ልሻገረው?›› ትላለች፡፡ መላእክተ ጽልመትም ‹‹ለዚህማ መሻገሪያው ታንኳው ለተራበ ማብላት፣ ለተጠማ ማጠጣት፣ ለተቸገረ መርዳት፣ ሰንበትን ማክበር፣ አሥራት በኩራት ማውጣት፣ አንድ በዓል መዘከር፣ ጾም፣ ጸሎት፣ ትሕትና፣ ፍቅር፣ ትዕግሥት፣ ቁጡ አለመሆን፣ ቂም አለመያዝ ነበር፡፡ ዛሬ ከዚህ ደርሰሽ ‹ምን ጨብጬ በምን ላይ ቆሜ ብትይ› ይሆናልን?›› ይሏታል፡፡ እርሷም መልሳ ‹‹ይህስ እንዳለ ባውቅ ኖሮ ስንኳን ሃይማኖት መማር፣ ሰንበትን ማክበር፣ ሀብትን መስጠት ይቅርና እጄን እግሬን ቆርጬ በሰጠሁ ነበር! ብሰማም ዋዛ ፈዛዛ ይመስለኝ ነበር እንጂ›› ትላቸዋለች፡፡ መላእክተ ጽልመትም ‹‹ከእንግዲህ ወዲህ ተመልሰሽ ትሔጃለሽን? ሂጂ ግቢ አሁን ላይ ፀፀት አይረባሽም›› ብለው እነዚያ ክፉውን ሁሉ ሲያስተምሯት የነበሩት ወርውረው ከባሕረ እሳቱ ውስጥ ይጨምሯታል፡፡ እርሷም ከእሳቱ ወጥታ ከባሕሩ፣ ከባሕሩ ወጥታ ከእሳቱ…እያለች አርራ ከስላ ከእሳት እንደገባ ጅማት ተኮማትራ ትሻገራለች፡፡
ዳግመኛም ወዲያ ማዶ ያሉት ‹‹አንቺ ክፉ ምን ያባክንሻል? መንገዱ ይህ አይደለምን!? ፀጥ ብለሽ በመንገዱ አትሻገሪምን!?›› ብለው እየዘበቱባት መልሰው ከባሕረ እሳቱ ውስጥ ይደፏታል፡፡ እርሷም ከእሳቱ ወጥታ ከባሕሩ እያለች አርራ ከስላ እንደቁራ ጠቁራ ትሻገራለች፡፡
ሦስተኛም ወዲህ ማዶ ያሉት ‹‹አንቺ ክፉ ምን ያባክንሻል? መንገዱ ይህ አይደለምን!? ፀጥ ብለሽ በመንገዱ አትሻገሪም!?›› ብለው እየዘበቱባት ወርውረው ይደፏታል፡፡ እርሷም ከእሳቱ ገብታ ከባሕሩ እያለች አርራ ከስላ ትሻገረዋለች፡፡ ዳግመኛም ‹‹ይህንን ሁሉ ሲነግሩኝ ሐሰት ይመስለኝ ነበር›› ብላ እየተጨነቀች ትሻገረዋለች፡፡ ከዚህም በኋላ መከራዋን ስትፈጅ መላእክተ ብርሃን ተቀብለው ይዘዋት ይሔዳሉ፡፡ እርሷም ‹‹ወየው! ከጌታዬ ስደርስ እንዴት እሆን ይሆን…!?›› እያለች ትሔዳለች፡፡ ትሔድም ዛሬ በዚህ ዓለም ያለ ሰው ከንጉሥ አምፆ ተጣልቶ፣ ነፍስ ገድሎ፣ ተይዞ ሊገረፍ፣ ሊቆረጥ፣ ሊፈለጥ፣ ሊሞት እየተጨነቀ እያለቀሰ እንዲሔድ ያችም ጎስቋላ ነፍስ እንደዚያ እየተጨነቀች ትሔዳለች፡፡ ዳግመኛም በዚህ ዓለም ያለ ንጉሥ የሚፈልጥ የሚቆርጥ ሆኖ አስፍቶ ተቆጥቶ እንዲቆይ ሁሉ ፈጣሪዋም ተቆጥቶ ተገርሞ ይቆያታል፡፡ እርሷም በምድር ሳለች ያልተማረች ናትና ደርሳ ሰንግጣ ፈዛ ትቆማለች፡፡ ከዚህም በኋላ መልእክተ ብርሃን ‹‹አንቺ ክፉ፣ ኩሩ፣ ትዕቢተኛ፣ የወትሮው ኩራት አለ መስሎሻል? ፈጣሪሽኮ ነው! ስገጂ እንጂ!...›› ብለው ይገፏታል፡፡ እርሷም ሰግዳ ትቆማለች፡፡ ዕዝ 6፡9፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታ ይጠይቃታል፡፡ ምን ብሎ ይጠይቃታል? ቢሉ የወንድ ነፍስ እንደሆነች ‹‹አንቺ ነፍስ እንጨት መቁረጥ፣ መፍለጥ፣ ቤት መሥራት፣ ፈረስ መጋለብ ውኃ ዋና፣ ሰንጠረዥ፣ እርሻ፣ ቁፋሮ፣ በገና፣ ጸናጽል፣ ከበሮ፣ ጽሕፈት፣ ድጉሰት ታውቂያለሽን?›› ብሎ አይጠይቃትም፡፡ የሴትም ነፍስ ብትሆን ‹‹አንቺ ነፍስ አልሞ መደቆስ፣ አለስልሶ መፍተል፣ መፍጨት፣ ወጥ መሥራት፣ እንጀራ መጋገር፣ ጠጅና ጠላ መጥመቅ ታውቂያለሽን?›› ብሎ አይጠይቃትም፡፡ እንግዲያስ ምን ብሎ ይጠይቃታል? ቢሉ ‹‹አንቺ ነፍስ በማን ታመልኪያለሽ? አንድነቴን ሦስትነቴን፣ ምልዐት ስፋቴን፣ ርቀቴን፣ ከሰማየ ሰማያት መውረዴን፣ ከድንግል ማርያም መወለዴን፣ ወልደ አብ በመለኮት፣ ወልደ ማርያም በትስብእት በተዋሕዶ የከበርኩ መሆኔን፣ መገፈፍ መገረፌን፣ መሰቀል መሞቴን፣ መነሣት ማረጌን ታውቂያለችን? ብሎ ይጠይቃታል፡፡ እርሷም ያልተማረች ናትና ‹‹አምላኬ ሆይ! አላውቅም›› ትላለች፡፡ ‹‹ለሥጋዬ ስጥር