አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
መጋቢት 2-የኒቅዮስ ኤጲስቆጶስ አባ መከራዊ በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡
+ ከሮሀ አገር የተገኘውና የተሠወረውን ሁሉ የሚያይ የጻድቃንን ማደሪያና የኃጥአንንም ኩኔን በገሃድ የተመለከተ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዕረፍቱ ነው፡፡
ሰማዕቱ አባ መከራዊ፡- ይኽም ቅዱስ ከደቡባዊ ግብጽ ከእስሙናይን የተገኘ ነው፡፡ የኒቅዮስ አገር ኤጲስቆጶስ ሆኖ በተሾመ ጊዜ በክርስቲያኖች ላይ ታለቅ ስደትና መከራ ሆነ፡፡ አረማዊ መኮንን ወደዚያች አገር ገብቶ ብዙዎቸን በሰማዕትነት ገደለ፡፡ አባ መከራዊንም ጭፍሮቹን ልኮ ካስመጣቸው በኋላ እምነቱን እንዲክድ አስገደደው፡፡ አባ መከራዊ ግን በእምነቱ ስለጸና በጽኑ ግርፋት አስገረፈው፡፡ ዳግመኛም ብርና እርሳሰ አቅልጠው በአፉ ውስጥ እንዲጨምሩበት አዘዘ፡፡ እንደታዘዘውም ባደረጉ ጊዜ ጌታችን አባ መከራዊን አጸናውና ምንም ጉዳት እንዳላገኘው ሆነ፡፡
ከዚህም በኋላ ይህ ከሃዲ መኮንን አባ መከራዊን ወደ እስክንድርያው ገዥ ወደ ኄርሜኔዎስ ላከው፡፡ እርሱም አሠረው፡፡ አባ መከራዊም በእሥር ላይ እንዳለ ብዙ ተአምራትን አደረገ፡፡ የአቅፋስ ከተማ ሹም የሆነውን ልጅ እጅና እግሩ ሽባ ነበርና አባ መከራዊ በጸሎቱ ፈወሰው፡፡ እስክንድርያው ገዥ ወደ ኄርሜኔዎስም ይህንን ሲሰማ በአባ መከራዊ ላይ ሥቃይ አበዛበት፡፡ ሕዋሳቶቹ ሁሉ እስኪቆራረጡ ድረስ በመንኮራኩር ውስጥ ጨምሮ አሠቃየው፡፡ ዳግመኛም ለተራቡ አንበሶች ሰጡት፣ በባሕር ውስጥ አሰጠሙት፣ በእሳት ምድጃ ወስጥ ጨመሩት ነገር ግን በእነዚህ መከራዎች ሁሉ ጌታችን ፈጽሞ ያድነው ነበር፡፡
በመጨረሻም መኮንኑ ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ አንገቱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ፡፡ አባ መከራዊም በዛሬዋ ዕለት አንገታቸውን ተሰይፈው ሰማዕትነታቸው በድል ፈጸሙ፡፡ ቅዱስ ሥጋቸውንም በመርከብ አድርገው ወደ አገራቸው ሲወስዱ እግዚአብሔር ያርፍ ዘንድ የወደደበት አገር ላይ ሲደርስ መርከቧ አልንቀሳቀስ አለች፡፡ ከአባ መከራዊም ሥጋ ‹‹ሥጋዬ በውስጡ እንዲኖር እግዚአብሔር የፈቀደው ቦታ ይህ ነው›› የሚል ቃል ወጣ፡፡ ይህንንም ለዚያች አገር ሰዎች በነገሯቸው ጊዜ በዝማሬ በእልልታ ቅዱስ ሥጋቸውን ተቀብለው ወስደው በመልካም ቦታ አስቀመጡት፡፡ የአባ መከራዊ መላ ዘመናቸው 131 ዓመት ነው፡፡
ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!!!
+ + +
አቡነ ጎርጎርዮስ ረዓዬ ኅቡዓት፡- ይኽም ቅዱስ በሌላኛው ስሙ ጎርጎርዮስ ዘሀገረ ሮሐ እየተባለ ይጠራል፡፡ ረዓዬ ኅቡዓት ማለት ምስጢራትን የተመለከተ ማለት ነው፡፡ ይህም ጻድቅና ሊቅ በቅዳሴው፣ በሃይማኖተ አበው፣ በስንክሳር፣ በገድለ ሰማዕታትና በገድለ ቅዱሳን ስሙ ተደጋግሞ ተጠቅሷል፡፡ በመጀመሪያ የክርስቲያኖች ጠላት የነበረ ሲሆን ዐመጸኛና ኃጥእ ነበረ፡፡
ክርስቲያኖችንም እየፈለገ ያሠቃይና ይገድል ነበር፡፡ አንድ ቀን ድንገት ሳያስበው መልአክ መጥቶ ነጥቆ ወስዶ የኃጥአንንም የመከራ ቦታዎችንና ሲኦልን አሳይቶ መልሶ አምጥቶ መሬት ላይ ሲጥለው እጅግ ደንግጦ በፍጹም ንስሓ ተመልሶ ሐዲሳትንና ብሉያትን ጠንቅቆ በመማር በብዙ ተጋድሎ መኖር ጀመረ፡፡
በሌላ ጊዜ አሁንም መልአኩ በረድኤት ተገልጦለት ነጥቆ ወስዶ ገነትን፣ ብሔረ ሕያዋንን፣ ብሔረ ብዑዓንን፣ መንግሥተ ሰማያን ሁሉ አሳየው፡፡ ከዚህም በኋላ ከአመፁ ወደ እግዚአብሔር በንስሓ ተመልሶ መነኮሰ፡፡ በምንኩስናም ሆኖ በብዙ ተጋድሎ ኖረ፡፡ ከዚህም በኋላ የተሰወረውን ሁሉ የሚያይ ቅዱስ አባት ሆነ፡፡ በሊቀ ጳጳስነት ተሾሞ በማገልገል ብዙ ጣዖታትን አፈራርሶ አብያተ ክርስቲያናትን ሠራ፡፡ በመጨረሻም ሹመቱን በመተው በዓቱን አጽንቶ ብዙ ከተጋደለ በኋላ መጋቢት 2 ቀን በክብር ዐርፏል፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!!!