Advanced Freshman


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


🔔ይህ ቻናል በ2017 freshman ለሚማሩ ተማሪዎች የተዘጋጀ እና በዉስጡ የተለያዩ የዩንቨርስቲ መረጃዎችን, አጋዥ መፅሐፍቶች, ቲቶሪያል, mid እና final ፈተናዎችን ሚያዘጋጅ እና ተማሪዎች ወደ ሚፈልጉበት ዲፓርትመንት እንዲገቡ ሚያግዝ ነው ::
📩For comment and ads :- @EEG12bot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


#ማስታወቂያ
በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ፡-

በ2017 የትምህርት ዘመን ከኢ. ፌ. ዴ. ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች የ2017 የትምህርት ዘመን መግቢያ ቀን ታህሳስ 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን እናስታዉቃለን፡፡

#ማሳሰቢያ 1

1.ምዝገባ (በአካል ቀርበው)  ታህሳስ 21 እና 22 ቀን 2017 ዓ.ም
2.አጠቃላይ ገለፃ (orientation) ታህሳስ 23 ቀን 2017 ዓ.ም
3.ትምህርት የሚጀመረው ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️

5.2k 1 133 66 56

#DiredawaUniversity

የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የጥሪ ማስታወቂያ

በ2017 ዓ.ም ወደ ድሬ ደዋ ዩኒቨርሲቲ በሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 3 እና 4/2017 ዓ.ም ሲሆን የማመልከቻ ቀን ጥር 5/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲዉ ያሳዉቃል፡፡

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️

10.2k 1 235 40 60

#BorenaUniversity

የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የጥሪ ማስታወቂያ

በ2017 ዓ.ም ወደ ቦረና ዩኒቨርሲቲ በሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 22 23/2017 ዓ.ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት ብቻ በመሆነ· በተባለዉ ቀን ቦረና ዩኒቨርሲቲ ግቢ ዉስጥ በመገኘት ምዝገባ እንድታካሄዱ ዩኒቨርሲቲዉ ያሳዉቃል፡፡

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️


Репост из: Remedial 2017
#UniversityofGonder

በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ተፈትነው በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ለመከታተል ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች የማመልከቻ ቀናት 👉 ጥር 01 እና 02/2017 ዓ.ም. መሆኑን አሳውቋል።


የምዝገባ ቦታ፡- ለማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች ማራኪ ግቢ እና ለተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች አጼ ፋሲል ግቢ መሆኑንም ዩንቨርሲቲው ጨምሮ አሳውቋል።

💥ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ስትሄዱ ከዚህ በታች የተገለጹትን ይዛችሁ እንድትሄዱ

✓ የ8ኛ ክፍል ውጤት ዋናውን እና የማይመለስ ኮፒ

✓ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውን እና የማይመለስ ኮፒ

✓ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርቲፊኬት ዋናን እና የማይመለስ ኮፒ

✓ ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ

✓ አንሶላ፣ ብርድ ልብስና የትራስ ልብስ

(ሬጅስትራር ጽ/ቤት)

@Remedial2017batch⭐️

7.3k 0 39 37 32

#BahirDarUniversity

በ2017 ዓ.ም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) ተማሪዎች ምዝገባ ከጥር 5-7/2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ግሽ አባይ ግቢ እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN ⭐️


#HaramayaUniversity #Remedial

በ2017 ዓ.ም. በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ በሪሜዲያል ፕሮግራም ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ በ2017 ዓ.ም. ትምህርት ዘመን በሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች በጥር 02፣ 03 እና 04፣ 2017 ዓ.ም. ሀረማያ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ግቢ በአካል ተተኝታችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ ዩንቨርሲቲው ገልጿል።

#ማሳሰቢያ
1ኛ. የህብረተሰብ ሳይንስ ተማሪዎች በቨተርነሪ (Veterinary) ካምፓስ እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ (Technology) ካምፓስ ሪፖርት የምታደርጉ መሆኑን እናሳውቃለን።

2ኛ. ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ የ8ኛ ክፍል ካርድ፣ ከ9ኛ አስከ 12ኛ ትምህርት ያጠናቀቃቸሁበትን ትራንስክሪፕት እና የ12ኛ ከፍል ሰርትፍኬት ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ 4 ፓስፖርት መጠን ያላቸው ጉርድ ፎቶ እንዲሁም በማስታወቂያው የተጠቀሱ የግል መጠቀሚያ ቁሳቁሶችን ይዛቹህ እንድትሄዱ ዩንቨርሲቲው ጨምሮ አሳስቧል።

ተማሪዎች የዶርም ምደባችሁን ከዩንቨርሲቲው ዌብሳይት (www.haramaya.edu.et) ላይ በመግባት መለያ ቁጥራችሁን ተጠቅማቹህ መመልከት ትችላላቹህ።

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN ⭐️

14.5k 1 148 58 71

#Wachamouniversity

በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለአቅም ማሻሸያ ትምህርት ወደ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ የምዝገባ ጊዜ እንደሚከተለው መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል፣

👉ለመደበኛ Remedial ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው ታህሳስ 21 እና 22/2017 ዓ.ም ሲሆን ትምህርት የሚጀምረዉ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ይሆናል፤

⚡️በቅጣት ምዝገባ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ይሆናል፤

👉በግል ለመማር ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች ትምህርት የሚጀምረዉ ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም ይሆናል፤

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN ⭐️


Remedial ተማሪዎች ሚጠቅማችሁን ቻናል እንጠቁማችሁ

የዘንድሮ Remedial ተማሪዎች የቀራችሁ ጊዜ አጭር መሆኑ ይታወቃል:: እናም ለ ዝግጅታችሁ በጣም አስፈላጊ የሆነ እና በቀራችሁ አጭር ጊዜ ብዙ ምትጠቀሙበት ቻናል🥰
     
🎁በዉስጡ👇

🔺Remedial Exams
🔹Short notes
🔺Work books
🔹Solved EUEE
🔺Tips and tricks
🔹Study tips and references በነፃ ማግኘት እና መጠቀም ትችላላችሁ📔

አሁኑኑ ተቀላቀሉን👇👇
      
@BrightAcademy9_12 
      
@BrightAcademy9_12 
      
@BrightAcademy9_12

9.5k 0 54 10 39

#️⃣በወጥነት ይተገበራል የተባለው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሜኑ ይሄን ይመስላል🙂

እንዴት አያችሁት 🙌

JOIN:
@ADVANCED_FRESHMAN ⭐️


ADVANCED FRESHMAN TUTORIAL

✅ለአዲስ የፍሬሽማን ተማሪዎች ምዝገባ እንደቀጠለ ነው!🦋

📌በፍሬሽማን ቆይታችሁ አሪፍ ዉጤት ሰርታችሁ እና በመረጣቹት department እንድትገቡ የሚያግዛቹ Tutorial class ምዝገባ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ::በርካቶች ተመዝግበው የAFT Class ቤተሰብ ሆነዋል::እናንተስ❓

💥በጥርጣሬ ጊዜ ሳንገድል ከሚፈጠረው ጭንቀት ዛሬውኑ የAFT Class ቤተሰብ በመሆን አሪፍ ዉጤት ያስመዝግቡ::

ለመመዝገብ 👉@Freshman_tutorial_bot

📌ክፍያ ጨርሳቹ ደረሰኝ ስትልኩልን ወድያውኑ ወደ ዋናው ቱቶሪያል ትቀላቀላላቹ ። ጊዜው እየሄደባቹ ነው ቶሎ ጀመራቹ ከስር ከስር ያሉባቹን ኖቶች ብትጨርሱ ቡኋላ ላይ ከሚደርስባቹ ጭንቀት እንድታርፉ ይረዳቿል።

☎️ለመመዝገብ ይሄን Bot⬇️ይጠቀሙ :-@Freshman_tutorial_bot

👤ለበለጠ መረጃ:- @FTC_admin_bot

JOIN:
@ADVANCED_FRESHMAN⭐️


ግቢ ከገባችሁ ቦኃላ ያስቸገራችሁ ነገር ምንድነው❓️
Опрос
  •   ምግቡ🙁
  •   ትምህርቱ😐
  •   ገንዘብ😑
  •   የአየር ሁኔታው
  •   ዶርም life
2817 голосов

12.1k 0 11 238 108

Cheers🥂በግቢ ምግብ ስትማረሩ ለነበራችሁ😁

15k 0 8 177 296

#update

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።

ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን የምግብ ሜኑ ተቀራራቢ እንዲሆን እየሰሩ ነው።

ወቅታዊውን የምግብ ዋጋ መጨመር መነሻ በማድረግ ትምህርት ሚኒስቴር ጥናት ያደረገ ሲሆን በጥናቱ ውጤት መነሻነትም የከፍትኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ በጀት በቀን ወደ 100 ብር ከፍ እንዲል ተደርጓል። በተደረገው የበጀት ማሻሻያ መሰረት በተቋማቱ የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን በባለሙያዎች ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።

በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ ወቅታዊ የምግብ ዋጋ ንረትን ግምት ውስጥ በማስገባት የምግብ በጀት ማሰተካከያ መደረጉን ገልጸዋል።

ዶ/ር ሰለሞን አክለውም በሀገራችን ባሉ ዩኒቨርስቲዎች ያለው የምግብ ሜኑ ተቀራራቢ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው በአዲሱ የበጀት ተመን መሰረት ለዩኒቨርስቲዎቹ ባላቸው ተማሪ ቁጥር ልክ ገንዘቡ እንደሚለቀቅላቸው ጠቁመዋል።

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️


የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን ማሻሻያ ተደረገ🥪

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ለገንዘብ ሚኒስቴር የፃፉት ደብዳቤ 👇

< ከመ/ቤታችሁ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም በቁጥር 1/143/150/17 በተጻፈ ደብዳቤ አሁን በስራ ላይ ያለው የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን ከወቅቱ የገበያ ዋጋ አኳያ ተማሪዎችን ለመመገብ በቂ ባለመሆኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን ማሻሻያ ጥናት በማካሄድ የተመን ማሻሻያው እንዲፈቀድ መጠየቃችሁ ይታወሳል:: የቀረበውን የምግብ በጀት ተመን ማሻሻያ ጥናት ከወቅቱ የገበያ ዋጋና ከመንግሥት የመክፈል አቅም አኳያ በማየት የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን በቀን በአንድ ተማሪ የነፍስ ወከፍ ወጪ 100 ብር (አንድ መቶ ብር ) ሆኖ ከታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ እንዲውል ተወስኗል።

በዚህም መሰረት የሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት በወጥነት እና ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲከናወን መስሪያ ቤታችሁ ከምግብ በጀት ተመን ማሻሻያው ጋር የተጣጣመ ስታንዳርድ የምግብ ሜኑ በማዘጋጀት ዩኒቨርስቲዎች አንዲጠቀሙበት እና በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉን ክትትል እንድታደርጉ በጥብቅ አስታውቃለሁ፡፡ >

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN


#OdaBultumUniversity

በ2017 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ታህሳስ 7 እና 8/2017 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- የ8ኛ ክፍል ስርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- አራት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

የምዝገባ ቦታ፦
ጭሮ ከተማ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው አዲሱ ካምፓስ

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️

13k 1 45 44 36

📣 አንድ Field ማስተር ከማረግ የተለያዩ Field ይዞ መሯሯጥ አይከፋም!


👨‍💼 ብዙዎች ግቢ ላይ መንግስት የመደባቸውን ፊልድ ብቻ ገግመው ይማራሉ ነገር ግን በዚህ የውድድር አለም አንድ ሳብጀክት ማስተር ከማድረግ የተለያዩ ሳብጀክቶችን ይዞ መሯሯጥ አይከፋም ። እናም ቢያንስ ሁለት ከበዛ 3 ዲግሪ ይዛችሁ መውጣት ይኖርባቸቹሃል..!

📚 ለምሳሌ ፦ ሶፍትዌር ኢንጅነሪግ ተመድባቹ  በሳምንት 4 ቀን ከሆነ የምትማሩት ቅዳሜ እና እሁድ አልያም የማታ በዲስታንስ በመማር አንድ ዲግሪ በኖርማል ከምትማሩት  ወጣ ያለ ፤  ለምሳሌ ማኔጅመነት አልያም ኢኮኖሚክስ ብትማሩ አሪፍ ነው ። በዲስታንስ መማር አልያም ቅዳሜ እና እሁድ መርጣቹሁ ዮኒቨርስቲው በሚያመቻቸው ዕድል መማር ትችላላቹህ ። በርቀት ስለሆነ ለፈተና ግዜ እያነበቡ ፈተናውን በመውሰድ መመረቅ ይቻላል የኖርማል ሳብጀክቱን ሳይጋፋባችሁ የሶሻል ትምህርቶች በ3 አመት ስለሚያልቁ በሁለተኛው አመት ጀምራቹሁ በአራተኛው መጨረስ ትችላላቹሁ በመጨረሻው አመት ሙዱም ስለማይኖራቹሁ GC ስትሆኑ ሌላ ዲግሪ በማኔጅመንት ወይም በመረጣችሁት ይኖራቹሃል ።

💬 በመጀመርያው አመትም መጀመር ትችላላቹሁ ግቢውን እስክትላመዱ ሊያስቸግራቹሁ ስለሚችል አንድ አመት ታግሳችሁ ቢሆን ግን ይመረጣል ።

   የክፍያው ነገር 

📚 ክፍያው የተጋነነ አይደለም በወር 400- 500 ብር ነው ፤ በ10 ሺ ብር ከጎበዛቹሁ አንድ ዲግሪ ማለት ነው ። ያውም ከኖርማሉ ቀድማቹሁ ። ሲኒየሮችን ብታናግሩዋቸው ታዲያ ያግዙአቿል ።

   ነጥብ

📚 የርቀት ወይ በማታ ስለሆነ ብዙ የሚከብድ ፈተና የለም ። ትንሽ ካነበባችሁ ከ 2.8 በላይ ማምጣት ቀልድ ነው ። ኖርማሉንኮ ስንቶች በ2 ነው ሚመረቁት ታዲያ ትዕግስት ይጠይቃል ። አንዳንዴ ኖርማል ክላስ ጋር ክላሽ ሊያረግ ይችላል ።  ምንግዜም ለኖርማሉ ነው ቅድሚያ መስጠት ያለብን ።

ሶስተኛዋ  ዲግሪስ

🎓በካንፓስ ቆይታቹሁ በጣም የምታቃጥሉዋት ግዜ ክረምት ነች ። ብዙዎች ዕረፍት በሚል ይቀመጣሉ ። እናት እና አባትህ አንተ ተስፈ አርገው ፤ በየአመቱ 100 ሺ ህዝብ እየተመረቀ ስራ በሚያጣበት ሀገር ማረፍ ዘበት ነው ።  ደሞስ ቁጭ ብሎ ድንጋይ ከመሞቅ ፥ ፊልም ከማየት 24 ሰዓት  ከመጋደም አንድ ዲግሪ ብትጨምር አይሻልም ። አብዛኞቹ ካንፓሶች (summer course) ሰመር ኮርስ ይሰጣሉ  ። በክረምት ለ3 አመት በመማር አንድ ዲግሪ መጨመር ትችላላቹሁ ። 3ተኛ ዲግሪ ማለት ነው ።ከትምህርተ ወደ ትምህርት  ከደበራችሁ  ደሞ ሌላ ከህይወታቹ ጋር የሚገናኝ ነገር ። ፊልም መማር ፤ ሙዚቃ መማር ፤ መንጃ ፍቃድ ፤ ቋንቋ መማር ፤ ብቻ አለመተኛት ።ግዜን አለማቃጠል ነው ። ዕረፍት የለሽ በመሆን መማር ነው ።

💬 አንዳንድ ልጆች ክረምቱን ገንዘብ ለመሸቀል በት በት ይላሉ ይሄም በጣም አሪፍ ነገር ነው ። ቤተሰብ ማስቸገር በጣም አስጠሊ ነገር ነው ። ብቻ ክረምታችሁን በአልባሌ ጉዳይ ማሳለፍ የለባችሁም አንደኛችሁን ታርፋላችሁ ። በርትቶ ሰግጦ መማር ነው ።

   ኧረ ልፋቱስ

📚 አዎ አድክም ነገር ነው ። ነገር ግን ቀልድ አይደለም በሶስት ዲግሪ መመረቅ ቀልድ አይደለም ። ስራ በአንዱ ብታጡ እንኳ በአንዱ አታጡም ደሞ አንዱን ማስተር ማረግ ከቻላችሁ ያበደ CV ያዛቹሁ ማለት ነው ። የትኛውም ድርጅት ቢሆን ሊቀጥራቹሁ ይንገበገባል ። ወይስ በአንድ ተመርቆ ድንጋይ ማስጣት ይሻላላል ። የእናንተ ምርጫ ነው ።

☎️ለመመዝገብ ይሄን Bot👇ይጠቀሙ :-@Freshman_tutorial_bot

💬ለበለጠ መረጃ👇
     @FTC_admin_bot

©️ቀለሜ
JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️
                   

13k 0 74 3 65

#BuleHoraUniversity

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በ2017 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ታህሳስ 7 እና 8/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
- ስምንት 3X4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- ትራስ ጨርቅ፣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️

13k 0 32 65 45

ለአርሲ ዩንቨርስቲ እንዲም ተገጥሞ ነበር ለካ😁

I can't 😂

📍@ADVANCED_FRESHMAN⭐️

12.3k 0 99 17 177

ስለ አንዳንድ ዲፓርትመንቶች ማብራሪያ የሰጠንበትን post ለማግኘት ከታች ያሉትን ሊንክ ተጠቀሙ

👾Architecture ⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1322

🖊 Management⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1329

💻 Software engineering⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1334

🔨 Law⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1350

💊Radiology⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1354

👨‍⚕️Medicine⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1361
https://t.me/Advanced_Freshman/1384
https://t.me/Advanced_Freshman/1392

💵Economics⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1367

🎙Journalism⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1370

💻Computer science⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1374

💰Accounting and finance⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1377

ሁሌም ለላቀ ዉጤት


JOIN:
@ADVANCED_FRESHMAN⭐️



Показано 20 последних публикаций.