አሐዱ:ባንክ የኢንሹራንስ ክፍያን በተመለከተ የሦስትዮሽ ስምምነት አደረገ!አሐዱ:ባንክ በተነሣበት ከብዙዎች ለብዙዎች መርሕ ለብዙዎች ለመድረስ አጠናክሮ መቀጠሉን ኅዳር 27/2017 ዓ.ም ከአንበሳ ኢንሹራንስ እና ኢኮስ ኮሚሽን ኤጀንት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ጋር በሐመር አዳራሽ ያከናወነው የሦስትዮሽ ስምምነት ጉልህ ማስረጃ መሆኑ ተገልጿል::
የኢንሹራንስ ደንበኞች ለመኪናቸው የሚከፍሉትን ዓመታዊ የአረቦን ክፍያ 22% ብቻ በአሐዱ፡ባንክ በኩል ከቆጠቡ ባንኩ ፋይናንስ በማድረግ ዓመታዊ የኢንሹራንስ ክፍያቸውን እንደሚከፍልላቸው እና በ9 ወራት ጊዜ ውስጥ መክፈል የሚችሉበት ዕድል መመቻቸቱን የአሐዱ:ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰፊ ዓለም ሊበን በአፅንኦት ተናግረዋል::
የሦስትዮሽ ስምምነቱም የአሐዱ፡ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰፊ ዓለም ሊበን÷ የአንበሳ ኢንሹራንስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም መርሻ እንዲሁም ኢኮስ ኮሚሽን ኤጀንት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዐቢይ ዓለሙ በተገኙበት ተፈጽሟል::
አሐዱ፡ባንክ
ከብዙዎች ለብዙዎች
የአሐዱ፡ባንክ ማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ 👉
https://linktr.ee/Ahadu_Bank