በነቢዩ ﷺ ፍቅርና በዑለሞቻችን መንገድ ሕያው ነን!፣ ልዩ የመውሊድ ዝግጅት። አሉ¡
#ይህ ልዩ የመውሊድ ስጦታይ ነው።
በትግስት አንብባችሁ ለሌሎችም #Share አሰራጩት።
በየትኛው የነቢዩ ﷺ ፍቅር ነው ሕያው ነን የምትሉት??
ይህን ስያሜ የሰጣችሁት ለመውሊድ ፕሮግራም ነው፣ መውሊድ ደግሞ ነቢዩ ﷺ አይወዱም፣ ምክንያቱም በዲናችን የሌለ አዲስ መጤ ነገር ነው!፣ ነቢዩ ﷺ ደሞ በየ ሳምንት ጁምዓ አደራ በዲን ላይ አዲስ መጤ ነገርን ተጠንቀቁ ይሉ ነበር!!
ያውም በመውሊድ ቀን የሚባሉ ስንኞች የተለያዩ ድንበር ያለፉና ሺርክ የተሞላባቸው ናቸው። ታዳ አንተ የነቢዩን ﷺ ትእዛዝ በመቃረን ነው እንዴ ውዴታቸውን ምትገልፀው?? እንደሚታወቀው ደግሞ የሚወዱትን ሰው ይታዘዙታል፣ ሚያስከፋውን ነገር ይጠነቀቁለታል እንጂ ሚያስከፋው ነገር ለመተግበር ፈፅሞ አይታሰብም!። ምን ይህ ብቻ ከሚወደድ ነገር ሁሉ ኣቻ የሌለው ተወዳጁን አላህን እንኳን እንወዳለን ብለን ብንሞግት አላህ ነቢዩን ﷺ በትክክል እንድንከተል መስፈርት አድርጎብናል፣ እንዲህ በማለትም አዞናል:–
﴿قُل إِن كُنتُم تُحِبّونَ اللَّهَ فَاتَّبِعوني يُحبِبكُمُ اللَّهُ وَيَغفِر لَكُم ذُنوبَكُم وَاللَّهُ غَفورٌ رَحيمٌ﴾ آل عمران ٣١
“በላቸው:– አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ #ተከተሉኝ፣ አላህ ይወዳችኋልና። ኃጢያቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና። አላህ መሃሪ አዛኝ ነው።” ኣል ዒምራን 31
በትክክል አላህን እና ነቢዩ ﷺ የምንወድ ከሆነ በየትኛውም አቅጣጫ ከሚፈልጉት መንገድ ውጪ እየተጓዙ እወዳቸዋለሁ ማለት የማይታሰብ ነው!። ገጣሚው እንዲህ ይላል:–
تعصى الإله وأنت تدعي حبه هذا محال في القياس بديع
"አምላክህን ታምፃለህ፣ ነገር ግን እንደምትወደው ትሞግታለህ። ይህ ፈፅሞ የማይታሰብና ፈጠራ የሆነ (ቂያስ) ልኬት ነው።"
አንድ ሰው ፈጣሪውን እና ከፈጣሪው ዘንድ የተላከለትን ታላቁን መልእክተኛ ﷺ ቀርቶ፣ በጣም የሚወደውን ጓደኛውን እንኳን እየተቃረነውና ከርሱ ሀሳብ ተቃራኒ በሆነ መንገድ እየሄድ እወደዋለሁ አይለውም።
በተለይ ያ! ጓደኛው እነዚህን ነገሮች አትዳፈርቢኝ ብሎ በተለየ መልኩ ያሰመረበት ነገር ካለና ያንን ነገር ያለ ፈቃዱ ሚነካካና ከርሱ ሀሳብ ተቃራኒ ሆኖ እየተጓዘ እወድሃለሁ ቢለው፣ ጓደኛው የሚረዳው እያፌዘበት መሆኑን እንጂ ፈፅሞ እንደሚወደው አይደለም!። ነቢዩ ﷺ ዒርባድ ኢብን ሳሪያ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ባስተላለፈው ሀዲስ እንዲህ በማለት በዲን ላይ አዲስ ነገር ከመፍጠር (ከመጨመር) እንድንጠነቀቅ አሳስበውናል:–
«وإيَّاكم ومُحْدَثاتِ الأُمورِ، فإنَّ كلَّ مُحْدَثةٍ بِدْعةٌ، وإنَّ كلَّ بِدْعةٍ ضَلالةٌ»
“አደራችሁን (በዲን ላይ) አዳዲስ ነገሮችን ተጠንቀቁ!! ሁሉም (በዲን ላይ አዲስ መጤ) ፈጠራ ነው፣ ፈጠራ ነገር ሁሉም ጥመት ነው።” ኢማሙ አሕመድ በሙስነዳቸው የዘገቡት ሲሆን ሀዲሱም ሶሂህ ነው።
አላህን በትክክል የምትወድ ከሆነ አላህ ዲኑን ሙሉ አድርጌዋለሁ ብሏልና ስሜትህን በመከተል አዲስ ነገር ካልጨመርኩ ማለትህን ትተህ ሙሉ በሆነው ዲን ውስጥ ያለውን ነገር ተግብር።
{اليَومَ أَكمَلتُ لَكُم دينَكُم}
“የዛሬ ቀን ሀይማኖታችሁን ሙሉ አደረግኩላችሁ።” አልማኢዳ 3
አዎ! ዲኑ ሙሉ ነው!! አንተ ጎበዝ ከሆንክ ሙሉ በሆነው ዲን ውስጥ ያለውን የታዘዝከውን ተግብር። ትክክለኛ ውዴታ የሚገኘውም የሚወዱትን አካል ትእዛዝ በማክበር ነውና። በትክክል አላህን እና መልእክተኛውን ﷺ የምትወድ ከሆነ በዲኑ የሌለን አዲስ ነገር መፍጠር ትተህ ያዘዙህን ታዘዝ፣ ከከለከሉህ ነገር ሁሉ ተቆጠብ!።
እስቲ ልጠይቅህ/ሽ?
① » መውሊድ ከዲኑ ከነበረ ለምን እንደ 2ቱ ዒዶች በቁርኣንና በሀዲስ እንዴት መከበር እንዳለበት በዝርዝር አልመጣም??
② » በመልካም ነገር ሶሃቦችን ከማነሳሳታቸው በፊት ቀድመው ለራሳቸው የሚተገብሩት ታላቁ ነቢይ ﷺ መውሊድን አክብረውታል??
③ » አንተ ቢድዓ በሆነው መውሊድ ላይ እንደምትነቃቃው ለምን ሌሎች ግዴታ በሆኑ ዒባዳዎች ላይ አትነቃቃም (አትነሽጥም) ??
④ » ነቢዩን ﷺ ኮቴ በኮቴ እየተከታተሉ የሸኑበት ቦታ ሳይቀራቸው፣ በሸኑበት ቦታ እንኳን ሳይቀር ሄደው የሚሸኑ የነበሩት ብርቅዬ ሶሃቦች መውሊድን አክብረውታል??
⑤ » አንተ/አንቺ ለነቢዩ ﷺ ሱንና ከሶሃቦች የበለጠ ተቆርቋሪ ናችሁ??
⑥ » በዲኑ ላይ አዲስ ነገር በቁርኣንም በትክክለኛ (ሶሂህ) ሀዲስም የሌለን ነገር ለመጨመር ከመናፈቅህ በፊት፣ ቁርኣን እና ሀዲስ ውስጥ ያለውን ጨርሰህ ተግብረሃል??
» ነቢዩ ﷺ ልብሳቸውን ያሳጥሩ ነበር አሳጥረሃል?
» ነቢዩ ﷺ ፂማቸውን ያሳድጉ ነበር አሳድገሃል?
» የነቢዩ ﷺ እጅ ባእድ የሆነችን ሴት ጨብጣ አታውቅም አንተ ሴት መጨበጥ ትተሃል?
» ነቢዩ ﷺ የሌሊት ሶላትን እግራቸው እስኪሰነጣጠቅ ይሰግዱ ነበር፣ አንተስ እየሰግድከ ነው? እንደው የለይሉ ሶላት ቢቀር ዊትሯን ትሰግዳታለህ? ውትሯም ባትኖር እንዳው በጊዜ ተነስተህ የሱብሂ ሶላትን በጀመዓ ትሰግዳለህ?
» ነቢዩ ﷺ የምርጥ ስነ–ምግባር ባለቤት ነበሩ አንተስ ስነ–ምግባርህ ምንና ማንን ይመስላል?
» እንደምትለው እውነት የነቢዩ ﷺ ውዴታ ካሰመጠህ የአውሮፓ ተጫዋቾችን እና ዘፋኞችን፣የፊልም አክተሮችን ባህሪ እርግፍ አድርገህ ትተህ የነቢዩን ﷺ ስነ–ምግባር ለምን አትከተልም??
ይህን ማድረግ ሳትችል ነቢዩ ﷺ ካዘዙበት መንገድ ውጪ፣ ነቢዩን ﷺ እወዳለሁ ማለትህ የለየልህ ተወዳዳሪ የሌለህ ነገ ከሞት በኋላ ተቀስቅሰህ አላህ ፊት እርቃንህ መቆምህን የዘነጋህ በስሜት ምትነዳ ግልብ ውሸታም ነህ!!!
እህቴ ሆይ! እስቲ ልጠይቅሽ? በአላህ ይሁንብሽ! ለኔ ባትመልሺልኝም ቆም ብለሽ አስተውለሽ ጥያቄውን ለራስሽ መልሺው። ከላይም ከታችም ያለው ጥያቄ አንቺንም ይመለከታል!! ግን ተጨማሪ በሴትነትሽ የተወሰኑ ጥያቄዎችን ልጨምርልሽ ወደድኩ…
» መውሊድ ማከብረው ለነቢዩ ﷺ ውዴታ መግለጫ ነው ካልሽ ነቢዩ ﷺ በሚጠሉት በቢድዓ መንገድ ነው ምትገልጪላቸው?
ከልብሽ አስተውይ! አንቺን ባልሽ እወድሻለሁ እያለሽ አንቺ በእጅጉ የምትጠይውን ነገር እያወቀ ሚሰራ ከሆነ እውነትም ይወደኛል ብለሽ ታምኚዋለሽ?
» ወይስ የነቢዩን ﷺ ውዴታ ምትገልጪበት ሱናቸውን ሁሉ ጨርሰሽ ተግብረሽ ጭማሪ አስፈልጎሽ በመውሊድ ውዴታቸውን ለመግለፅ ነው የተነሳሽው?
» ቆይ ቆይ ግን አንቺ ነቢዩን ﷺ ከተወዳጁ የጓደኛቸው የአቢበክር ልጅና ሚስታቸው ከሆነችው ዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) የበለጠ ትወጂያቸዋለሽ?
» ታዲያ ይህች ውድ እናትሽ የታላቁ ነቢይ ድንቅና ውድ የሆነችው ምስታቸው ዓኢሻ፣ ለዚህ ህዝብ ዲኑን ያስተማረችው ምርጧ የዚህ ህዝብ እናት መውሊድን አክብራለች? የትና መቼ?
» ለመሆኑ በአለባበስሽ፣ በአመጋገብሽ፣ በአነጋገርሽ፣ ነቢዩ ﷺ ያዘዙሽን ፈፅመሻል?
» ብረት እንደሚገፋ ወንድ ሰውነትሽን ወጣጥረሽ፣ እንደ አርሶ አደር ገበሬ ቁንጣ የሆነ ቁርድ ለብሰሽ፣ ሰርግ ሳይኖር ሰርግ አስመስለሽ ድቤ እየደበደብሽ የሞቱበትን ቀን እያከበርሽ ነው እወዳቸዋለሁ ምትይኝ? ቤትሽ ውስጥ አህያ ቢኖርና መሳቅ ቢችል ይህን ሰምቶሽ ሁሌ እያስታወሰ በተግባርሽ ይስቅብሽ ነበር።
» ለመሆኑ ነቢዩ ﷺ "ሽቶ ተቀብታ ከቤቷ የወጣች ሴት ዝሙተኛ ናትና ወደ ቤቷ ተመልሳ የጀናባ ትጥበትን ትታጠብ።" እያሉ፣ ተቀባብቶ መውጣቱ ሀራም መሆኑን እያወቅሽ፣ ተቀብተሽ እየወጣሽ ተመ