Ethiopian educations


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Telegram


ይህ የሁሉም የ ትምህርት ተቋማት የተለያዪ አመት ፈተናዎች እና ወርክ ሽቶች ያሉበት ቻናል ነው።
@alluexams
For promotion ✍️@alluexam_bot
ask any thing on @alluexam_bot

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Telegram
Статистика
Фильтр публикаций


ኢትዮጵያ ኮከብ ተጨዋቿን አጣች‼️

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የባህርዳር ከነማው ድንቅ የአማካይ ተጨዋች አለልኝ አዘነ በድንገት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።

በቅርቡ የጋብቻ ስነ ስርዓቱን በቤተክርስቲያን የፈፀመው አዲሱ ሙሽራ ድንገት ዛሬ ለሊት ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል ።

ለአርባምንጭ ታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው፤ ለሀዋሳ ከተማና አሁን ለባህርዳር ከተማ በሊጉ የሚጫወተው አለልኝ አዘነ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ጥሪ ተደርጎለት አገልግሎት ሰጥቷል።

አመለ ሸጋው ተጨዋች አለልኝ አዘነ ላለፉት ሁለት አመታት በጣና ሞገዶቹ ቤት አስደናቂ ብቃቱን በማሳየት ክለቡንና ሀገሩን እያገለገለ የሚገኝ ወጣት ተጨዋች ነበር።


@alluexams


ወደ ትምህርት ቤት እየሄደች የነበረች ህጻን በጅብ ተነክሳ ህይወቷ አለፈ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ቸሃ ወረዳ በጅብ የተነከሰች የሰባት አመት ህፃን ህይወቷ ማለፉን የዞኑ ፖሊስ ገልጿል።

በወረዳዉ የፌቅ ጠረቅ አንደበራ ቀበሌ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 2፡00 ሰዓት ገደማ ወደ ትምህርት ቤት በመሄድ ላይ ሳለች መንደር ዉስጥ ባደፈጠ ጅብ ስትያዝ የተመለከቱ ሁለት ጓደኞችዋ ሮጠዉ ማምለጣቸዉ ተነግሯል።

ሁለቱ ህፃናት ወደ ትምህርት ቤት ሄደዉ ታዳጊዋ በጅብ መያዟን በመናገራቸዉ ፈጥነዉ ወደ ስፍራዉ በደረሱ መምህራን የታዳጊዋ ከፊል በድን ገላ ከጅብ ማስጣል ተችላል ሲል የጉራጌ ዞን ፖሊስ መግለጹ ተመላክቷል፡፡

©(መናኸሪያ ሬዲዮ

@alluexams


Репост из: 🅗︎🅓︎ 🅜︎🅞︎🅥︎🅘︎🅔︎🅢︎ 🅐︎🅝︎🅓︎ 🅢︎🅔︎🅡︎🅘︎🅔︎🅢︎
በትርጉም በጥራት

🅢︎🅗︎🅐︎🅡︎🅔︎➽ @HD_movies_ent
🅢︎🅗︎🅐︎🅡︎🅔︎➽ @HD_movies_ent




Notcoin 6 ቀን ቀረው .....

#Not Coin Pre-Market ጀምሯል እና 10M Notcoin ከ$2000 በላይ እየተገመተ ነው😋

ምን ያህል ሰርታችኋል እስከአሁን ? የረሳችሁት ደግሞ ቀጥሉ ማን ያውቃል አሪፍ ገንዘብ ሊያሳፍሰን ይችላል 🤑



April 1 ያቆማል። ከዛ በኋላ እናንተ ወደ ፈለጋችሁት ገንዘብ መቀየር ትችላላችሁ። ከእናንተ የሚጠበቀው ገብታችሁ መጫወት ብቻ ነው👇👇👇

https://t.me/notcoin_bot?start=r_581063_25629895
https://t.me/notcoin_bot?start=r_581063_25629895


በኋላ ከመፀፀት አሁን በእጃችሁ ያለውን ወርቃማ እድል ተጠቀሙበት


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በሞስኮ ክሮካስ ከተማ ጥቃቱን ካደረሱት መሀል የተያዘ ታጃኪስታናዊ የሰጠው ቃል


ትላንት ምሽት በሩሲያ ሞስኮ ክሮከስ ከተማ በሚባለው ቦታ በታጣቂዎች በደረስ የተኩስ እና የፍንዳታ ጥቃት ከ 115 ሰዎች በላይ ህይወት አለፈ

በነጭ መኪና ለማምለጥ ሲሞክሩ ከነበሩት ውስጥ ሁሉቱ ተይዘዋል በዜግነት ታጃኪስታናዊ የሆኑ በሩሲያ የሚኖሩ መሆናቸው ተረጋግጧል


በቴሌግራም የሆኑ ሰዎች ግማሽ ሚሊዮን ሩብል መድበዎልን ይህን እንድሰራ ታዘን ነው ያሉት ተጠርጣሪዎች ስላመለጡ ጉደኞቻቸው መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል


#NationalExam

" የ12ኛ ክፍል ፈተና ዝግጅት እየተገባደደ ነው ፤ ... በቀጣይ የፈተናው ሕትመት ይጀመራል " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ለ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የፀጥታ ችግር በሌላባቸው አካባቢዎች ብቻ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች በስተቀር በአብዛኛው ሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የተማሪዎች ምዝገባ ተካሂዶ መጠናቀቁን የገለጸው መ/ቤቱ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለብሄራዊ ፈተናው ምዝገባ ማከናወናቸውን ጠቁሟል።

የፀጥታ ችግር ባለባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የሚገኙ ተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ በዚህ ሣምንት ይከናወናል ብሏል።

የፈተና ዝግጅት ሥራው የሀገሪቱን ሥርዓተ ትምህርት የተከተለ እና ተማሪዎቹን በአግባቡ መመዘን በሚያስችል መልኩ መዘጋጀቱን አገልግሎቱ ገልጿል።

የፈተናው ዝግጅት እየተገባደደ መሆኑን አመልክቶ በቀጣይ #የፈተናው_ሕትመት እንደሚጀመር አሳውቋል።

የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የመስጫው የጊዜ ሰሌዳ ወደፊት ይፋ እንደሚሆንም የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ኢዜአ ዘግቧል።

ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
@alluexams


#MoH

ባለፈው ወር በትምህርት ሚኒስቴር እና በጤና ሚኒስቴር በጋራ የተሰጠውን የመውጫ እና የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዳችሁ የጤና መስክ ተመዛኞች ውጤታችሁን ኦንላይን መመልከት ትችላላችሁ፡፡

http://hple.moh.gov.et/hple/candidates/index4 ላይ በመግባት፣ ሙሉ ስም እና በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Username) በማስገባት የብቃት ምዘና ፈተና ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

በውጤታችሁ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎች ያላችሁ ተመዛኞች ከመጋቢት 04/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት በስልክ ቁጥር 0118275936 በመደወል ወይም በኢሜይል አድራሻ regulatory.moh@moh.gov.et ብቻ ሙሉ ስም፣ ሙያ እና የፈተና መለያ ቁጥር (Username) በማስገባት ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

የማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ ተመዛኞች ስም ዝርዝር ለክልል የጤና ተቆጣጣሪ አካላት የሚላክ በመሆኑ በየክልላችሁ በመሔድ የሙያ ሥራ ፍቃድ ማውጣት የምትችሉ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

@alluexams


#ረመዳን #ዐቢይ ፆም

የሁለቱ ታላላቅ ሃይማኖቶች የተከበሩ የፆም ወቅቶች በአንድ ቀን ነገ ሰኞ መጋቢት 02/2016 ይጀምራል።

ይህን መሰል ግጥምጥሞሽ ከ33 ዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ሊከሰት የሚችል ድንቅ ግጥምጥሞሽ ነው።

ፈጣሪ ፀሎታችንን ይስም፤ምድራችንን ሰላም ያድርግልን 🤲


➡️ @alluexams


አስተማማኝ እና ውጤታማ የመስመር ላይ አስተማሪን ይፈልጋሉ? ከ The Tutor Spot የበለጠ ተመልከት! የአካዳሚክ ግቦችዎ ላይ እንዲደርሱ እና በጥናትዎ የላቀ ውጤት እንዲያመጡ የኛ ቡድን ልምድ ያላቸው አስተማሪዎች አሉን። በ The Tutor Spot፣ ለማንኛውም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ይህ ክፍለ ጊዜ ከእርስዎ የግል ፍላጎቶች እና የመማሪያ ዘይቤ ጋር የተጣጣመ የማጠናከሪያ ክፍለ ጊዜዎችን እናቀርባለን። በሂሳብ፣ በሳይንስ፣ በእንግሊዘኛ ወይም በሌላ በማንኛውም ትምህርታዊ ጉዳዮች ላይ እገዛ ከፈለጋችሁ፣ የእኛ አስጠኚዎቻችን ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈልግዎትን ድጋፍ እና መመሪያ ሊሰጡዎት እዚህ አሉ። የእኛ የመስመር ላይ መድረክ ለእርስዎ በሚመች ሁኔታ ክፍለ ጊዜዎችን መርሐግብር ለማስያዝ ቀላል ያደርገዋል፣ ስለዚህ ከቤትዎ ምቾት ሳይወጡ የሚፈልጉትን እርዳታ ማግኘት ይችላሉ። በተለዋዋጭ የመርሃግብር አማራጮች እና በተመጣጣኝ ዋጋ፣ Tutor Spot ለተጨናነቁ ተማሪዎች ውጤታቸውን ለማሻሻል እና በራስ የመተማመን ስሜታቸውን ለማሳደግ ምርጥ መፍትሄ ነው።
የአካዳሚክ ፈተናዎች ከአሁን በኋላ ወደ ኋላ እንዲገቱህ አትፍቀድ። ዛሬ በTutor Spot ለመማሪያ ክፍለ ጊዜዎች ይመዝገቡ እና ውጤቶችን ማየት ይጀምሩ!



ለመመዝገብ👇👇


@AEliasJr10


✨አስደሳች ዜና ለተማሪዎች እና ለ ተማሪ ወላጆች

📝 ተማሪዎችን በኦንላይን ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል ።

📝ከ9-12 (በተለየ የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቅያ ፈተና ለሚወስዱ

📝ዘንድሮ ለመፈተን በመጠባበቅ ላይ ላሉ በ ተለያዩ የመንግስት ዩንቨርስቲ ከፍተኛ ውጤት ባላቸው(seniors) እና አምና አሪፍ ውጤት ባመጡ ተማሪዎች በጣም ልዪ የሆነ ይሰጣል ።

⭐️በምስል እና በድምጽ የታገዘ tutorial ጠቃሚ የሆነ pdf lectures ይሰጣል

📂 በዚህ የ ቀድሞ ማትሪክ (10ኛ ክፍለ ) ላይ ሲሰጥ የነበረውን እንዲሁም የዩንቨርስቲ መግቢያ ጥያቄዎች ይሰራሉ ።


📃 ከ 9-11 በነባሩ እና የ 12 ኛ ክፍል አዲሱ ስርአተ ትምህርት የሚያጠቃልል ውን ሀገር አቀፍ ፈተና ባማከለ መልኩ tutorial እንሰጣለን

📝 እጅግ በጣም ጠቃሚ አጫጭር ጹፎችን(short notes) ለየ ትምህርት አይነቱ ይሰጣል ።

📝ለ ሀገረ አቀፍ ፈተና የቀረው አጭር ጊዜ እንደመሆኑ መጠን ጊዜአችንን በአግባቡ ለመጠቀም የተቻለውን ያደርጋል ።

ማሳሰቢያ

📌የምዝገባ ሂደቱ ላይ ቪዲዮ ተሰርተዋል (info how registered ) ሚለውን ማየት ይቻላል



@tutorspot1_bot


#tutor

✨የ 12 ክፍል ፈተና ግንቦት ወር ውስጥ እንደሚሰጥ ይታወቃል ።


✨ከ 9-11 ክፍልን የድሮ የትምህርት ስርዓት 12ኛ ክፍል አዲሱን የትምህርት ስርዓት ፈተናው ያጠቃልላል ።


✨ tutor spot አስጠኚ ተማሪዎች ከከፍተኛ ውጤት እንዲያመጡ ለማገዝ ለ ተማሪዎች የ online course አዘጋጅቷል


✨በየቀኑ ጠቃሚ ይለቀቃሉ።


✨ የ ምስል( 📽️) እና የ ድምጽ(🎤 ) ትምህርቶች ከፍተኛ ውጤት ባላቸው የግቢ ተማሪዎች ይሰጣል

✨አምና ከፍተኛ ዉጤት ባመጡ ተማሪዎች የአጠናና ዘዴ ፣ የገዜ አጠቃቀም ፣ የምርጫ ጥያቄዎች መስሪያ መንገድ
ሚሰጥ ይሆናል ።


✨ሁሉንም < subject > ደሞ በ 100
ብር ማግኘት ይቻላል።


✨ከተፈታኝ ውጪ ላላቸው 👇

ለ9 እና ለ 10, 50ብር

ለ11 አና ለ 12 80 ብር


✨✨ማሳሰቢያ

📌የምዝገባ ሂደቱ ላይ ቪዲዮ ተሰርተዋል (info how registered ) ሚለውን ማየት ይቻላል

📌ኦንላይን ትምህርት ከ ጾታዊ ትንኮሳ ነጻ ነው ቶሎ ተመዝገቡ 👇

@tutorspot1_bot


Share for all high school students 🙏


ኦነግ ሸኔ በዝቋላ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አራት አባቶችን መግደሉን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስታወቀች‼️

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሚገኘው ጥታዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም እራሱን ኦነግ ሸኔ ብሎ በሚጠራው ቡድን የገዳሙን መጋቢ ጨምሮ አራት አባቶችን መግደሉን ገዳሙ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኢኦተቤ ቴቪን ዋቢ በማድረግ ሰኞ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት ታጣቂዎቹ ሦስት አባቶችን አግተው ወደ በረሃ ከወሰዱ በኋላ የታገቱትን ለማስለቀቅ ገዳሙ ጥረት በሚያርግበት ወቅት የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ተጨማሪ አባቶችን በመያዝ

1. የገዳሙ መጋቢ አባተክለማርያም ዐሥራት
2. የገዳሙ ጸሐፊ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን
3. የገዳሙ የመጽሐፍ መምህርና ቀዳሽ አባ ገ/ማርያም አበበ
4. በአመክሮ የሚኖሩ መናኝ ኃይለማርያም ወልደሰንበት የተባሉት የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች እንደተገደሉና አብረው ከነበሩት አንድ አባት ብቻ ማምለጥ መቻላቸውን እንደተረዱ የገዳሙ ኃላፊዎች ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል፡፡

የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች ቡድኑ ከዚህ ቀደም ገዳሙን በመዝረፍ ለከፋ ችግር አጋልጦት መቆየቱን አስታውሰው ገዳሜ ጸጥታውን የሚያስከብረበት መሣሪያች በቡድኑ በመወረሳቸው ለከፋ የጸጥታ ችግር መጋለጡን ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ገዳማውያ በስጋት ላይ መሆናቸውንና የመንግሥት የጸጥታ አካላትን እገዛ እንደሚሹ አስታውቀው መረጃውንም በየደረጃው ለሚገኙ የሀገረ ስብከቱና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ማሳወቃቸውን ገልጸዋል፡፡

@alluexams


Maths workbook.pdf
3.6Мб
Maths euee 2009-2013 questions with detail explanation
By haftu


Falcon academy


Share🙏🙏
@alluexams


#tips_grade_12_exam_takers


1, ለረጅም ሰአት አታንብቡ ይልቅ ዋና ነጥቦችን እረፍት እየወሰዳቹ አንብቡ🥶

2,ከዚ በፊት የተሰጡ ፈተናዎችን በደምብ ስሩ በተላይ ያለፈው ሁለት አምት ፈተናዎችን🥳

3,ቲዎሪ ለሚበዛባቸው ከአጋዥ መጽሐፍ ይልቅ መመሪያ መጸሐፍት (text book) ተተቀሙ🤩🤩

4,aptitude ፈተና ለመስራት ሚያግዝአቹንየሚባለውን ድረገጽ ተተቀሙ😇😇

5,worldwide ለ ኢንግሊሽ ፈተና ለማትስ ለ ፊዚክስ extreme ተተቀሙ😎😎

6,ለ 8 ሰአት ተኙ✨😴

7,ጥናታቹ በቀን ቢሆን የተሻለ ነዉ🤠

8,በቡድን ማንበብ በጣም ጠቃሚ ነው🤗
9, ሶሻል ሚድያ ምትተቀሙበት ሰአት ገድቡ😑


10,online tutor በክፍያ ልምድ ባላቸው መምህራን ከፈለጉ👇👇👇

@tutorspot1_bot ላይ ይመዝገቡ


11,ሁሌም ፈጣሪያቹን አመስግኑ 🙏


" ብሔራዊ መውጫ ፈተናውን ሁሉም በላቀ ውጤት አልፈዋል። ... 70% የማዕረግ ምሩቃን ናቸው " - አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በነገው እለት የካቲት 9 ቀን 2016 ዓ/ም 249 #የህክምና_ዶክተሮችን እንደሚያስመርቅ አሳውቋል።

ከነዚህ ተመራቂዎች መካከል 70 በመቶ የማዕረግ ምሩቃን ናቸው።

የብሔራዊ የመውጫ ፈተናውን ደግሞ ሁሉም ተመራቂዎች (100%) በላቀ ውጤት አልፈዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ነገ 22 ተማሪዎች በአንስቴዥያ የህክምና ዘርፍ የሚመረቁ ይሆናል።

Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
https://t.me/Temhert_Minister
https://t.me/Temhert_Minister
#MoE


#ጥቆማ

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ፤ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ #በግል_ከፍለው የአዉሮፕላን አብራሪነት ስልጠና ለሚፈልጉ ጥሪ አቀረበ።

ዩኒቨርሲቲው ፤ ለአዉሮፕላን አብራሪነት ስልጠና ለአጭር ጊዜ የሚቆይ የ10% ቅናሽ ማድረጉንም አሳውቋል።

" በግል ከፍለው የአውሮፕላን አብራሪ ለመሆን ለሚማሩ ስልጠናውን ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ " ያለው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩንቨርስቲ አመልካቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው ብሏል።

1ኛ. የትምህርት ደረጃ ፦ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት የወሰዱ፣ እንዲሁም ፦
* በሂሳብ፣
* በእንግሊዘኛ
* በፊዚክስ ዉጤት አመርቂ አፈጻጸም ያስመዘገቡ

2ኛ. ዕድሜ ፦ 18 እና ከዚያ በላይ

3ኛ. እንግሊዘኛ ፦ ደረጃ 4

4ኛ. ቁመት፦ 1ሜ 62 ሴ.ሜ እና ከዚያ በላይ

5ኛ. የጤና ሁኔታ፦ ደረጃ 1 የጤና ሰርተፊኬት

የስልጠናው ርዝማኔ 1 አመት ከ 3 ወር ነው ተብሏል።

" የተደረገው ቅናሽ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ነው " ያለው ዩኒቨርሲቲው ፤ " የምዝገባ ሂደቱን ለማወቅ እና ለበለጠ መረጃ በኢሜል አድራሻ ፦ etauinfo@ethiopianairlines.com / eaainfo@ethiopianairlines.com ያነጋግሩን " ብሏል።

ስልክ በመደወል መረጃ ለመቀበል የምትፈልጉም +251-115174600/8598 ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈ የዩኒቨርሲቲውን ድረገፅ መመልከት ይቻላል ፦
@alluexams


የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ይፋ ሆኗል‼️
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከየካቲት 3 እስከ የካቲት 30/2016 ዓ.ም ብቻ እንደሚካሄድ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

በዘንድሮው ዓመት የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚፈተኑ ተማሪዎች የምዝገባ ሂደትን ለመጀመር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውም ተገልጿል፡፡

በመደበኛ እና በማታ መርሐ ግብር ከ872ሺህ በላይ ተማሪዎች ብሔራዊ ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተገልጿል፡፡

የ2016 ዓ.ም የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከየካቲት 3 እስከ የካቲት 30/2016 ዓ.ም ብቻ እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን ሙሉ በሙሉ በኦንላይን የሚካሄድ ይኾናል ተብሏል።



@alluexams


#tutor

✨የ 12 ክፍል ፈተና ግንቦት ወር ውስጥ እንደሚሰጥ ይታወቃል ።


✨ከ 9-11 ክፍልን የድሮ የትምህርት ስርዓት 12ኛ ክፍል አዲሱን የትምህርት ስርዓት ፈተናው ያጠቃልላል ።


✨ከእኛም የተማሪዎችን ጭንቀት ለመቀነስ < maths&physics > በ 50 ብር ከ9-12ኛ ክፍል ያለውን እንድሁም ድሮ 10 ኛ ከፍል ሲሰጠ የነበረውን አና ኢንተራንስ ጥያቄዎችን ይሠራል ።


✨በየቀኑ ጠቃሚ ይለቀቃሉ።


✨አምና ከፍተኛ ዉጤት ባመጡ ተማሪዎች የአጠናና ዘዴ ፣ የገዜ አጠቃቀም ፣ የምርጫ ጥያቄዎች መስሪያ መንገድ
ሚሰጥ ይሆናል ።


✨ሁሉንም < subject > ደሞ በ 100
ብር ማግኘት ይቻላል።


✨ከተፈታኝ ውጪ ላላቸው 👇

ለ9 እና ለ 10, 50ብር

ለ11 አና ለ 12 80 ብር


✨✨ማሳሰቢያ

📌የምዝገባ ሂደቱ ላይ ቪዲዮ ተሰርተዋል (info how registered ) ሚለውን ማየት ይቻላል

📌ኦንላይን ትምህርት ከ ጾታዊ ትንኮሳ ነጻ ነው ቶሎ ተመዝገቡ 👇

@tutorspot1_bot


Share for all high school students 🙏

Показано 20 последних публикаций.