้̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥̥ 📖 አል ቁርዓኑል ከሪም


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


🎀 አብደሏህ ኢብኑ መስዑድ እንዲህ ብለዋሉ፦
«ዕውቀትን ከፈለጋቹ ቁርዓንን አሰራጩ፤
ምክኒያቱም በቁርዓን ውስጥ
የመጀመሪያም የመጨረሻ
እውቀት አለበት።»
🌹የፈለጋቹትን ከቻናሉ በመውሰድ
ዱዓቹን ብቻ አስቀምጡልኝ!!!
t.me/joinchat/AAAAAEOse9AXbhxosKsF0g
ሀሳብ ካሎት
@AlQuranulKerimb

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


قُل لَّن يُصِيبَنَا إِلَّا مَا كَتَبَ اللَّهُ لَنَا هُوَ مَوْلَانَا ۚ وَعَلَى اللَّهِ فَلْيَتَوَكَّلِ الْمُؤْمِنُونَ

«አላህ ለኛ የጻፈልን (ጥቅም) እንጂ ሌላ አይነካንም፡፡ እርሱ ረዳታችን ነው፡፡ በአላህ ላይም ምእመናን ይመኩ» በላቸው፡፡


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


فَسَتَذْكُرُونَ مَا أَقُولُ لَكُمْ ۚ وَأُفَوِّضُ أَمْرِي إِلَى اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ بَصِيرٌ بِالْعِبَادِ

«ወደ ፊትም ለእናንተ የምላችሁን ምክር(ቅጣትን በምታዩ ጊዜ) ታስታውሳላችሁ፡፡ነገሬንም ሁሉ ወደ አላህ አስጠጋለሁ፡፡አላህ ባሮቹን ተመልካች ነውና

ቃሪእ አቡበክር አል-ሻጥሪ


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram




የባለስልጣናትን ግፍ የፈራ ሰው

اَللَّهُمَّ رَبَّ السَّمَاوَاتِ السَّبْعِ، وَرَبَّ الْعَرْشِ الْعَظِيْمِ، كُنْ لِيْ جَارًا مِنْ فُلاَنٍ بْنِ فُلاَنٍ، وَأَحْزَابِهِ مِنْ خَلاَئِقِكَ، أَنْ يَفْرُطَ عَلَيَّ أَحَدٌ مِنْهُمْ أَوْ يَطْغَى، عَزَّ جَارُكَ، وَجَلَّ ثَنَاؤُكَ، وَلاَ إِلَـهَ إِلاَّ أَنْتَ.

አልሏሁምመ ረብበስሰማዋቲስሰብዒ ወረብበል ዐርሹል ዐዚይም ኩን ሊይ ጃረን ሚን ፋላኒ ኢብኒ ፋላን ወአህዛቢሂ ሚን ኸላኢቂከ አን የፍሩጠ ዐለይየ አሐዱን ሚንሁም አው የጥጋ አዝዘጃሩከ ወጀልላ ሰናኡከ ወላኢላህ ኢልላ አንተ የሰባቱ ሰማያትና የታላቁ ዓርሽ ጌታ ሆይ! እገሌ የእገሌ ልጅ ከሆነውና ፍጡራኖችህ ከሆኑት ረዳቶቹ (ይቃት) ጠባቂ ሁነኝ፡፡ አንዳቸውም እንዳይበድሉኝ÷ ጥቃትም እንዳይፈፅሙብኝ፡፡ ጥበቃህ ላቀ፡፡ ልዕልናህ ከፍ አለ፡፡ ከአንተ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡

اللهُ أَكْبَرُ، اللهُ أَعَزُّ مِنْ خَلْقِهِ جَمِيْعًا، اللهُ أَعَزُّ مِمَّا أَخَافُ وَأَحْذَرُ، أَعُوْذُ بِاللهِ الَّذِيْ لاَ إِلَـهَ إِلاَّ هُوَ، الْمُمْسِكِ السَّمَاوَاتِ السَّبْعِ أَنْ يَقَعْنَ عَلَى اْلأَرْضِ إِلاَّ بِإِذْنِهِ، مِنْ شَرِّ عَبْدِكَ فُلاَنٍ، وَجُنُوْدِهِ وَأَتْبَاعِهِ وَأَشْيَاعِهِ، مِنَ الْجِنِّ وَاْلإِنْسِ، اَللَّهُمَّ كُنْ لِيْ جَارًا مِنْ شَرِّهِمْ، وَجَلَّ ثَنَاؤُكَ وَعَزَّ جَارُكَ، وَتَبَارَكَ اسْمُكَ، وَلا


┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

👔 አዲስ ልብስ ሲለበስ

اَللَّهُمَّ لَكَ الْحَمْدُ أَنْتَ كَسَوْتَنِيْهِ، أَسْأَلُكَ مِنْ خَيْرِهِ وَخَيْرِ مَا صُنِعَ لَهُ، وَأَعُوْذُ بِكَ مِنْ شَرِّهِ وَشَرِّ مَا صُنِعَ لَهُ.

‘አልሏሁምመ ለከል ሐምዱ፣ አንተ ከሰውተኒሂ፣ አስአሉከ ሚን ኸይሪሂ ወኸይሪ ማ ሱኒዐ፣ ወአዑዙ ቢከ ሚን ሸርሪሂ ወሸርሪ ማ ሱኒዐ ለሁ

አላህ ሆይ! ምስጋና ለአንተ የተገባ ነው፡፡ አንተ ነህ ያለበስከኝ፡፡ የዚህን (ልብስ) በጐ ገጽታና የተሰራበትን በጐ አላማ እንድትለግሰኝ እጠይቅሃለሁ፡፡ ከዚህ ልብስ መጥፎ ገጽታና ከተሰራበት መጥፎ አላማ ባንተ እጠበቃለሁ፡

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

@HisenullMuselimBot
@fedailZiker


ለሌሎችም ሼር ያድርጉት




Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


ጥያቄ፡- የኢድ ሶላት ሁክም ምንድን ነው?

መልስ፡- በእኔ አመለካከት የኢድ ሶላት በያንዳንዱ ሰው ላይ ግዴታ (ፈርዱ ዐይን) ነው፡፡ ወንዶች መተው አይፈቀድላቸውም፡፡ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሠለም አዘውበታልና፡፡ እንዲያውም ከቤት የማይወጡ  ልጃገረዶችም ሳይቀሩ ለኢድ ሶላት እንዲወጡ አዘዋል፡፡ የወር አበባ ያለባቸውንም ሴቶች ወደ ኢድ ሶላት እንዲሄዱ አዘዋል፡፡ ነገርግን ከመስገጃው ቦታ ገለል ብለው ይቀመጣሉ፡፡ ይህ የሚያሳየው ጉዳዩ ጠንከር ያለ መሆኑን ነው፡፡
ስለዚህ ይህ አቋም ይበልጥ ተቀባይነት ያለው ከመሆኑም በላይ የሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያም አቋም ነው፡፡ ነገር ግን ልክ እንደ ጁምዓ ሶላት ሁሉ ካመለጠ ቀዷ አይወጣም፡፡ ቀዷ ማውጣት ግዴታ እንደሚሆን የሚያሳይ ማስረጃ የለምና፡፡ በምትኩም ሌላ ሶላትም አይሰገድም፡፡

ሙስሊም ወንድሞቼን የምመክራቸው አላህን እንዲፈሩና ይህንን መልካም ስራ፡- ዱዓን፣ የሰዎች እርስ በርስ መተያየትን፤ መቀራረብን እና መዋደድን ያካተተ ሶላት እንዳይተውት ነው፡፡ ሰዎች የማይጠቅም ወይም ጨወታ ብቻ ለሆነ ስብሰባ ቢጠሩ እየተቻኮሉ ይሄዳሉ፡፡ ታዲያ ይህንን ከአላህ ምንዳ ወደ ሚያገኙበት እና ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሠለም ወደ ጠሯቸው የሶላት ግብዣ ይበልጥ ተቿክለው መሄድ አልነበረባቸውምን!?

ሴቶች ግን ለዒድ ሶላት ከወጡ ወንዶች ካሉበት ቦታ ራቅ ብለው መቀመጥ አለባቸው፡፡ ለዚህ ሶላት ሲወጡም ተውበውና ሽቶ ተቀብተው ወይመም ተገላልጠው መውጣት የለባቸውም፡፡ ነብዩ ሴቶች ለኢድ ሶላት እንዲወጡ ሲያዟቸው ሴቶቹ ነብዩን ‹‹የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! አንዳዶቻችል ጅልባብ አናገኝም›› ብለው ሲጠይቋቸው ነብዩም ‹‹እህቷ ከጅልባቧ ታልብሳት›› ብለው መሉሱላቸው።

[1]  ጅልባብ አባያ የሚመስል ሙሉ ሰውነትን የሚሸፍን ልብስ ነው፡፡ ሴት ጅልባብ ለብሳ መውጣት ግዴታዋ እንደሆነ ይህ ሀዲስ ያስረዳል፡፡ ምክንያቱም ነብዩ- ጅልባብ የሌላት ሴት ምን ማድረግ እንዳለባት ሲጠየቁ ያላትን ነገር ለብሳ ትውጣ አላሉም፤ ‹‹እህቷ ከጅልባቧ ታልብሳት፡፡›› ነው ያሉት፡፡ ይህም ካሏት ጅልባቦች አንዱን ትስጣት (ታውሰዋት) ማለት ነው፡፡

ኢማሙ ኹጥባ ሲያደርግ ሴቶች የማይሰማቸው ከሆነ ለነሱም ለብቻቸው ኹጥባ ሊያደርግላቸው ይገባል፡፡ የሚሰሙ ከሆነ ግን መድገም አያስፈልግም፡፡ ይሁን እንጂ በኹጥባው መጨረሻ ሴቶችን የሚመለከት መልዕክት በማካተት ሴቶችን መገሰጽ፣ መምከርና ማስታወስ የተወደደ ነው፡፡ ነቢዩ - ለወንዶች በኢድ ሶላት ላይ ኹጥባ ካደረጉ በኋላ ወደ ሴቶች በመሄድ ይገስጹና ይመክሩ ነበርና፡፡


ጥያቄ፡የሁለቱ ኢድ ሶላቶች አሰጋገድ እንዴት ነው?

መልስ፡- የኢድ ሶላቶች አሰጋገድ ኢማሙ ተገኝቶ ሁለት ረከዓ ያሰግዳል፡፡ መጀመሪያ ለኢህራም ተክቢራ ያደርጋል፡፡ ከዚያም ስድስት ጊዜ ተክቢራ ያደርጋል፡፡ ከዚያም ፋቲሃ ቀጥሎም የሱረቱለረ ቃፍ ምዕራፍ ይቀራል፡፡ ይህ መጀመሪያ ረከዓ ላይ ነው፡፡ ለሁለተኛው ረከዓ ሲነሳ ተክቢራ አድርጎ ይቆማል፡፡ ከቆመ በኋላ አምስት ጊዜ ተክቢራ ያደርጋል፡፡ ከዚያም ፋቲሃን ቀጥሎም ሱረቱል ቀመርን ይቀራል፡፡ እነዚህን ሁለቱን ሱራዎች-ቃፍና አልቀመርን-  ነብዩ- በኢድ ሶላቶች ይቀሯቻ ነበር፡፡

[2] ከፈለገም በአንደኛው ረከዐ ላይ ‹‹ሰቢህ ኢስመ-ረቢከል አዕላ››ን በሁለተኛው ረከዓ ላይ ደግሞ ‹‹ሀል-አታከ ሀዲሱል ጋሺያ››ን መቅራት ይችላል፡፡

[3] የጁምዓና የኢድ ሶላቶች ሁለት ሱራዎችን ይጋራሉ፡፡ በሁለት ሱራዎች ደግሞ ይለያያሉ፡፡ የሚጋሯቸው ሁለቱ ‹‹ሰቢህ›› እና ‹‹አል-ጋሺያህ›› ናቸው፡፡ የሚለያዩባቸው ሁለቱ ደግሞ ‹‹ቃፍ›› እና ‹‹አል-ቀመር›› ለኢድ ብቻ ሲሆኑ ሱረቱል ‹‹ጁምዓ›› እና ‹‹አል-ሙናፊቁን›› ለጁምዓ ሶላት ብቻ መሆናቸው ነው፡፡ ኢማሙ እነዚህን ሱራዎች በመቅራት ሱናውን መተግበርና ሰዎችንም ማስለመድ ይጠበቅበታል፡፡ ከሶላት በኋላ ኹጥባ ያደርጋል፡፡ ኢማሙ ነብዩ - እንዳደረጉት በኹትባው ውስጥ ሴቶች ብቻ የሚመለከት በመጨመር መፈጸም ያለባቸውን ትዕዛዛት እንዲፈጽሙ እና መከልከል ካለባቸው ነገሮች እንዲከለከሉ ሊመክራቸው ይገባል፡፡

ሼር ∆∆

@AlQuranulKerim

ዒድ
ሙባረክ


تكبيرات العيد
بأجمل صوت ستسمعه في حياتك
لنجعلها تملأ العالم كله الآن!!!


ምርጥ ማራኪ የኢድ ተክቢራ ተጋበዙ


የአረፋ ቀን ፆም መፆም እንዳትረሳ!

ከአቢ ቀታዳ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ፡ ነቢዩ (ﷺ) ስለ አረፋ ቀን ፆም ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል፦

﴿يُكَفِّرُ السَّنَةَ الماضِيَةَ والْباقِيَةَ﴾

“ያለፈውንና የመጪውን አመት ወንጀል ያስምራል።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1162

ማስታወሻ፦ የአረፋ ቀን ፆም የሚፆመው ቅዳሜ ሰኔ 8 ነው።


የዙልሒጃ ወር ነገ ጁመዓ እንደሚጀምር ታወቀ

በሂጅሪ አቆጣጠር 12ኛው የዙልሒጃ ወር የመጀመሪያ ቀን ነገ ጁመዓ እንደሚሆን የታወቀው በዛሬው እለት አዲስ ጨረቃ በመታየቱ ነው። በዚህም መሠረት ዛሬ ሐሙስ የዙልቀዕዳ ወር የመጨረሻ ቀን ይሆናል።

በሌላ በኩል የዘንድሮው ዓመት የዒድ አል አድሓ በዓል በወሩ አሥረኛው ቀን እሑድ ሰኔ 9/2016 ይከበራል።


Mataaf today!


የዙልሂጃ አስር ቀናት ትሩፋት እና በነዚህ ቀናት መተግበር የሚወደዱ ስራዎች

▪️ አላህ ለባሮቹ የአምልኮን ልዩ ቀናት አሰናድቷል።
▪️ እድለኛ ማለት በዚህ የአምልኮ መድረክ ምንዳን የሸመተ ሰው ነው።
▪️ አስሩ የዙልሂጃ ቀናቶች ከነዚህ ልዩ ቀናቶች አንዱ ነው።

አስሩን የዙልሂጃ ቀናት በምን መልኩ እንቀበለው?

🔺በነዚህ ቀናቶች በርካታ ምንዳዎችን ለማካበት በመቁረጥ
🔺 እውነተኛ ተውባህ (ንስሀ) በመግባት
🔺 ከወንጀሎችና ሀጢአቶች በመራቅ

የአስሩ ዙልሂጃ ቀናቶች ትሩፋቶች

👉 አላህ እንዲህ በማለት ምሎባቸዋል። [ وَالْفَجْرِ وَلَيَالٍ عَشْرٍ]
{በጎህ እምላለው በአስሩ ለሊቶችም}
(አል ፈጅር)


👉 የታወቁ ቀናቶች ናቸው። አላህ እንዲህ ብሏል
[وَيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ فِي أَيَّامٍ مَّعْلُومَاتٍ]
{በታወቁ ቀኖችም ውስጥ የአላህን ስም ሊያወሱ} (አል ሀጅ)

👉 ከነዚህ ቀናቶች ውስጥ አንዷ የእርድ ቀን ናት።  ይህም በአመት ውስጥ ከሚገኙ ቀናቶች ሁሉ ታላቅ ቀን ነው።

[أعظم الأيام عند الله يوم النحر ثم يوم القر]
رواه ابو داود والنسائي

{አላህ ዘንድ ታላቅ ቀን የእርድ ቀን ነው በመቀጠል የውመል ቀር ነው} አቡዳውድ እና ነሳኢይ ዘግበውታል ።
የውመል ቀር ማለት የዙል ሂጃ 11ኛ ቀን ነው።


👉 በእነዚህ ቀናቶች የአምልኮዎች ሁሉ ቁንጮ የተባሉ ተሰብስበው ይፈፀማሉ። ከነሱም መሀል (ሶላት ፣ ፆም ፣ ሀጅ ፣ ሶደቃ)

👉 በዱንያ ውስጥ ካሉት ባጠቃላይ ቀናቶች በላጭ ናቸው። የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል
[ أفضل أيام الدنيا أيام العشر] ......
( ከዱንያ ቀናቶች ውስጥ በላጩ አስሩ የዙልሂጃ ቀናቶች ናቸው)

👉 ከነዚህ ቀናቶች ውስጥ አንዱ የዐረፋ ቀን ነው። ይህም አልሀጁል አክበር (የሀጅ ታላቁ ቀን) ነው። ይህ ቀን ወንጀል የሚማርበት እና ከእሳት ነፃ የሚወጣበት ቀን ነው።

ለሙስሊም የምንሰጠው ምክር

▪️ ለእነዚህ አስር ቀናት ተጨማሪ የሆነ ትኩረት እና ቦታ በመስጠት መለየት።

▪️ በእነዚህ ቀናቶች አምልኮ ለመስራት ነፍስን በመታገል ላይ መትጋት እና መጓጓት።

▪️ በተለያዩ አምልኮ እና የመልካም ስራ መስኮች ላይ ማብዛት።

ቀደምት አበዎች (ሰለፎች) የሚያልቋት ሶስቱ  አስር ቀናቶች

▪️የረመዷን የመጨረሻ አስር ቀናት
▪️የዙልሂጃ የመጀመሪያው አስር ቀናት
▪️ የሙሀረም የመጀመሪያው አስር ቀናት

በእነዚህ አስር ቀናት መተግበር የሚወደዱ ስራዎች

▪️ ሱና ሶላቶች .......
▪️ የሀጅ እና ዑምራ ተግባሮችን መፈፀም .....
▪️ አላሁ አክበር እና አልሀምዱሊላህ ማለት ማብዛት .....
▪️ ላኢላሀ ኢለላህ እና ሌሎችንም ዚክሮች አብዝቶ ማለት .......
▪️መፆም
▪️  መመፅወት እና ለተቸገሩ ወጪ ማድረግ

————————————


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
🥹💛


يَا أَيُّهَا النَّاسُ اعْبُدُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُمْ وَالَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

እናንተ ሰዎች ሆይ! የፈጠራችሁን እነዚያንም ከናንተ በፊት የነበሩትን (የፈጠረውን) ጌታችሁን ተገዙ፤ (ቅጣትን) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡

Показано 20 последних публикаций.

6 717

подписчиков
Статистика канала