Фильтр публикаций


"የኢትዮጵያ ብልጽግና ጉዞ አይቀሬ ነው"

የብልጽግና ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፓርቲው ሁለተኛው ጠቅላላ ጉባኤ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ብልጽግና ሀገር በቀል እሳቤ ነድፎ የመጣ የመጀመሪያው ፓርቲ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአንድ ፓርቲ ዋና እስኳሉ ሃሳብ እንደሆነ በጉባኤው ላይ የተናገሩት የብልጽግና ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ሃሳብ ያለው ፓርቲ ለውጥ መፍጠርም መምራትም ይችላል ብለዋል።

በዘመቻ የጀመርናቸው ስራዎች ባህል መሆን አለባቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ፕሮጀክቶችን ጀምሮ መጨረስ እንዲሁ ባህል ልናደርገው ይገባል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የፓርቲዎች ጉባኤ ታሪክ መላው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰብ ተወካይ ኖሮት የሚደረግ ጉባኤ የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ብቻ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ብልፅግና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲ ልምምድ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀገር በቀል የሆነ እሳቤ ነድፎ የመጣ ፓርቲ መሆኑንም አመልክተዋል።

ብልፅግና ለኢትዮጵያ ፍቱን መድሀኒቱ መደመር ነው ብሎ ሲመጣ ላለፉት ስድስት አመታት ብልፅግናን መክሰስ እንጂ ማንም አማራጭ ሃሳብ ይዞ አለመምጣቱ የሚያሳዝን ነው ብለዋል።

ይህም ሆኖ በተቀዱ ሃሳቦች ላለፉት በርካታ አመታት የገጠሙንን ችግሮች ስለምናውቅ የኢትዮጵያን ተፎካካሪ ፓርቲዎች አማራጭ ሀገር በቀል ሃሳብ ቢያቀርቡ ብልፅግና ለመማር ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

ሃሳብ የነጠፈበት አካባቢ ማፍረስ ቢቀልም መልሶ መገንባት ግን መከራ ይሆናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለዚህም አማራጭ የፖለቲካ ሃሳብ ቢፈጠር ለመማር ዝግጁ ነን ብለዋል።

#prosperity


አፋር በሀዘን ተውጣለች…😭
.
የጅቡቲው አምባገነን የኢትዮጵያን ድንበር ዘልቆ በመግባት በኤሊዳዓር ወረዳ ሲያሩ ቀበሌ በድሮን ብዛት ያላቸውን አርብቶ አደሮችን ጨፍጭፏል። እስከ አሁን ሰዓት ድረስም ስምንት ሰው መሞቱንና ብዙ ሰዎች መቁሰላቸውን እየሰማን ነው። በድሮን የተጨፈጨፉ አርብቶ አደሮች በቀብር ሰነ ስርዓት ላይ የነበሩ መሆናቸውን ከስፍራው ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል። 😭

3k 0 7 16 28



በደቡብ ሱዳን በተከሰተ የአውሮፕላን አደጋ የ20 ሰዎች ህይወት አለፈ

በደቡብ ሱዳን ዩኒቲ ግዛት አነስተኛ አውሮፕላን ተከስክሶ የ20 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ።

አውሮፕላኑ ከግዛቷ ተነስቶ ወደ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ በማቅናት ላይ እያለ መከስከሱን የግዛቱ ኮሙኒኬሽን ሃላፊ ጋትዌች ባይፓል መግለጻቸውን ሬውተርስ ዘግቧል።

በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት የቻይናው ብሔራዊ ፔትሮሊየም ኮርፖሬሽን እና የደቡብ ሱዳን መንግስት ተቋም የሆነው ናይል ፔትሮሊየም በጋራ የመሰረቱት ግሬተር ፐዮኔር ኦፕሬቲንግ ካምፓኒ ሰራተኞች መሆናቸውን ሃላፊው ተናግረዋል።


አሳዛኝ ሰበር ዜና

1,713 ኢትዮጵያዊያን ተጠርንፈው ሊባረሩ ነው

በዶናልድ ትራንፕ አስተዳደር ዉሳኔ ምክንያት ወደ ሀገራቸዉ ከሚመለሱ ሰነድ አልባ ዜጎች መካከል 1,713 ኢትዮጵያዊያን ተለይተዋል ተብሏል።

የትራምፕ አስተዳደር ላሁኑ ዙር ለማባረር ካዘጋጃቸው 1.4 ሚሊዮን ዶክመንት የሌላቸው ስደተኞች ውስጥ 1,713 ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል

የሚያሳዝነው አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን እርስ በርሳቸው የአሜሪካ መንግስት ላስቀመጠው የብር ሽልማት ብለው እየተጠቋቀሙ መሆኑ ተሰምቷል

4.9k 0 19 14 51

ተጠንቀቁ….⚠️

አደገኛ መተግበሪያ በማኅበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ መሆኑን ንግድ ባንክ አስታወቀ

መተግበሪያው ያለደንበኛው ፈቃድ ገንዘብ ይቆርጣል

ጥር 20/2017 (ጋዜጣ+)፡- ደምበኞች በዋትስ አፕ እና በቴልግራም የሚሠራጭ Pharma+/CBE Vacancy መተግበሪያን እንዳይጭኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሳሰበ።

ባንኩ ባስተላለፈው የማስጠንቀቂያ መልዕክት፤ ባደረገው ምርመራ መሠረት አደገኛ መተግበሪያ ማግኘቱን ገልጿል።

ይህ Pharma+/CBE Vacancy የተሰኘ አሳሳች መተግበሪያ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በሰፊው እየተሰራጨ እንደሆነ በመጥቀስ፤ ይህ መተግበሪያ በቴሌግራም እና ዋትስአፕ ወደ ደንበኞቹ እየደረሰ መሆኑን ጠቁሟል።

መተግበሪያው በስልክ ላይ ከተጫነ ያለ ፈቃድ ገንዘብ ማስተላለፍ እንደሚችልም አሳውቋል።

ባንኩ ከዚህ አይነት አደጋ ለመጠበቅ ከቴሌግራም ወይም ዋትስአፕ መተግበሪያዎችን አታውርዱ ብሏል።

ደንበኞች መሰል ተግባራት ሲገጥሟቸው በ951 ነጻ የስልክ መስመር ደውለው እንዲያሳውቁ አሳስቧል።


ህወሓት ጦርነት እየጎሰመ ነው‼️

“የኢትዮጵያ መንግስት እና ምርጫ ቦርድ ፥ ህወሓትን ለማፍረስ እና አመራራችንን በመከፋፈል ፤ ህዝባችንን ባርነት ውሰጥ ለማስገባትና ብሎም ለማጥፋት የተለያዩ ሴራዎች እያሴረ ነው” ሲል በደብረፅዮን የሚመራ የህወሓት ቡድን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ገለፀ።

በደብረፅዮን የሚመራ የህወሓት ቁጥጥር ኮምሽን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፦ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ህወሓት ጉባኤ እንዲደግም የጠየቀው ጥያቄ ተቀባይነት እንደሌለው እና ጉባኤ እንደማይደግም አመላክቷል።

የጦርነት ሱሰኞች

ምንጭ ~ግዕዝ ሚዲያ


የአፍሪካ ብቸኛ ተወካይ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር በWhite House. ይገባዋል...🇪🇹


ይህ አሜሪካዊ ስሙ ኢሳያስ ማቴዎስ ይባላል።
አሜሪካን አይዶል ላይ ቀርቦ እንዲህ አለ...

"ልጅ እያለሁ እንደንማኛውም ልጅ ብዙ ምኞትና ተስፋ ነበረኝ። አድጌ፣ ተመርቄ፣ ስራ ይዠ፣ ሚስት አግብቸ፣ ልጆችን ወልጀ፣ በቤተክርስቲያን በዘማሪነት እያገለገልኩ በደስታና በስኬት የመኖር ትልቅ ህልምና ተስፋ ነበረኝ። ነገር ግን ከዚህ ሁሉ አንዱም አልተሳካልኝም። ምክንያቱም 18 ዓመት ሲሆነኝ በአንድ በተረገመች ዕለት ምንም በማላውቀው ጉዳይ ፖሊሶች በዘረፋ ተጠርጥረሀል አሉና ያዙኝ። ኧረ ንፁህ ነኝ ብልም የሚሰማኝ ጠፋና ተዘርፈዋል የተባሉት ሰዎች ይመስላል ስላሉ ብቻ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደብኝ። ያለ ጠያቂ ለ54 ዓመታት በአንድ ክፍል ውስጥ ተቆለፈብኝ።

መጀመሪያ አካባቢ ተስፋ ቆረጥኩ። ቆየት ብዬ ግን ይህ ነገር የእግዚአብሔር አላማ ይሆናል ብዬ በፀጋ መቀበል ጀመርኩ። ከዚያም ያለ አጃቢ ባንድ፣ ያለ ምንም ሙዚቃ መሳሪያ፣ በባዶ ክፍል ውስጥ በየቀኑ እግዚአብሔርን በመዝሙር ማመስገን ጀመርኩ። ብዙ አመታት ያለምንም ለውጥ ነጎዱ...

ከ54 ዓመታት በኃላ መዝገቤን በአጋጣሚ ሲያየው አላግባብ እንደተፈረደብኝ የተገነዘበ አንድ ወጣት የህግ ባለሙያ ወደእኔ መጣና ጉዳዬ እንደገና እንዲታይ(Judicial review) ሊያደርግ እንደሆነ ነገረኝ። ተስፋ ባላደርግበትም ይቅናህ አልኩት። በአጭር ጊዜ ውስጥ ጉዳዩን እንደገና አሳይቶ በ72 ዓመቴ በነፃ እንድለቀቅ አደረገኝ።
ስወጣ ግን ምንም ነገር አላገኘሁም። ቢሆንም እግዚአብሔር ይመስገን እዚያ እያለሁ በነፃነት በመኖራቸው እቀናባቸው የነበሩት ብዙዎች በህይወት የሉም። እኔ ግን ዛሬ ላይ ንፁህ አየር እየተነፈስኩ የማለዳ ፀሀይ በነፃነት እየሞቅኩ በህይወት አለሁ። በህይወት መኖር ብቻ ሳይሆን አንድ ቀን በህዝብ ፊት እዘምራለሁ ብዬ ስመኘው የኖርኩት ምኞቴ እውን ሆኖልኝ ይሄው በእናንተ ፊት ቆሜ እግዚአብሔርን ላመሰግን ስለሆነ ደስተኛ ነኝ" አለና በለስላሳ ድምፁ....
"በሀሰት በከሰሱኝ ጊዜ፣ የሚሰማኝ አጥቸ በተፈረደብኝ ጊዜ፣ ከ50 ዓመታት በላይ ያለበቂ ምግብና ልብስ፣ ያለጠያቂ ወገን በአንድ ክፍል ውስጥ በተዘጋብኝ ጊዜ፣ አለም ሁሉ በረሳኝ ጊዜ፣ አበቃልኝ ብዬ ተስፋ ቆርጨ ቀኑም ሌቱም በጨለመብኝ ጊዜ ከጎኔ ያልተለየኸው አባቴና አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ ከልቤ አመሰግንሀለሁ!" እያለ በእንባ ታጅቦ መዝሙሩን ያንቆረቁረው ጀመር።
ይህኔ ከአወዳዳሪዎች እስከመድረክ አስተናባሪዎች፣ ከታዳሚዎች እስከጥበቃዎች አዳራሹ በሙሉ በለቅሶ ተናጋ።

መልካም ጊዜ!
©ከሀቅ እና ድንቅ ገጽ የተወሰደ




እጅግ የምስራች የሆነ ዜና 🔥

ዶናልድ ትራምፕ አስገራሚ ወሳኔ በበዓለ ሲመታቸው ወቅት ወሰኑ! ከደቂቃዎች በፊት ቃለመሃላ የፈጸሙት ትራምፕ ከተፈጥሯዊዉ የጋብቻ ስነስርዓት ውጪ ወንድ ለወንድ ሴት ለሴት ምንም ጋብቻ በአሜሪካ ተቀባይነት እንደማይኖረውና ይህንን የሚያደርጉ ሁሉ ከባድ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አስጠነቀቁ።

7.3k 0 7 17 196

ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ባለቤታቸው ሜላኒያ ትራምፕ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና ቀዳማዊት እመቤት ጂል ባይደን ጋር በዋሽንግተን ዋይት ሀውስ ተገናኝተዋል።

#ሮይተርስ


የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳይ ጠቅላይ ምክር ቤት በአክሱም ት/ቤቶች የሒጃብ ክልከላ በመቃወም ነገ በሚደረገው ሰልፍ ሁሉም እንዲገኝ ጥሪ አቅርቧል።

ሸኽ አደም አደም ዓብዱልቃድር ዛሬ በሰጡት መግለጫ መጅልሱ ሒጃብ ከተከለከለበት ከጥቅምት ጀምሮ ጉዳዩ በውይይት እንዲፋታ ለወራት ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ከታች የመጅልሱ መዋቅር ከወረዳው ጀምሮ ጉዳዩ በቀጥታ ወደ ሚመለከታቸው መ/ቤቶችና የስራ ኃላፊዎች በአካል በመቅረብና ለቁጥር የሚታክቱ ደብዳቤዎች በመፃፍ ሁሉም ብዙ ጥረት ማድረጋቸውን አስተውቀዋል። ነገር ግን ድካሙ ውጤት ማምጣት አልቻለም። ስለዚህም ለነገ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተናል። በሰልፉም ስለፍትህ የሚያሳስበው፣ የእህቶቹና ልጆቹ መበደል የሚያስጨንቀው ያለልዩነት ሁሉም ተገኝቶ ድምጹን እንዲያሰማ ጥሪ አቅርበዋል።

ሒጃቧ ትለብሳለች
ትምህርቷም ትማራለች‼️



Показано 14 последних публикаций.