ባለ ፀጉራም ፊቱ ወጣት
የካቲት 28፣ 2017 (አራዳ ኤፍ ኤም) ህንዳዊው ወጣት ‘ፀጉራም ፊት’ በመያዝ ክብረ ወሰን ሰብሯል።
የ18 ዓመቱ ላሊት ፓቲዳር የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሲሆን፥ ከ1 ቢሊየን አንድ ሰው በሚጠቃበትና ‘የሰው ተኩላ’ ተብሎ በሚጠራው አፈጣጠር ሰለባ ነው።
ወጣቱ ከ95 በመቶ በላዩ የፊት ክፍሉ በፀጉር የተሸፈነ ሲሆን፥ ይህም በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገቦች (ጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ) እውቅና አግኝቷል።
ከሀገሩ ህንድ ወደ ጣሊያን በመሄድ በተደረገው በዚህ ማጣራትም የወጣቱ ፊት ላይ በስኩዌር ሴንቲሜትር 201 ነጥብ 72 የፀጉር ዘለላዎች መገኘታቸውን ጊነስ አስታውቋል።
በዚህም በሰው ፊት ላይ ብዙ ፀጉር ያለበት ወንድ በሚል ፀጉራማ ፊት ያለው ግለሰብ በሚለው መዝገብ ስሙን አስፍሯል።
ሃይፐርትሪኮሲስ የሚባለው ይህ አይነት አፈጣጠር ከ1 ቢሊየን ሰዎች አንዱ ላይ የሚከሰት ሲሆን፥ በፊት ላይ ያልተለመደ የፀጉር እድገትና ብዛት የሚከሰትበት ነው።
ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮም በምድራችን ላይ በዚህ አይነት አፈጣጠር ወደ 50 ሰዎች የተመዘገቡ ሲሆን ወጣቱም ከእነርሱ አንዱ ሆኗል።
ወጣቱ ከአፈጣጠሩ ጋር በተያያዘ በመጀመሪያው የትምህርት ቤቱ ቀን ችግር ገጥሞትና የክፍል ጓደኞቹም እጅግ ፈርተውት እንደነበር ተናግሮ ቀስ በቀስ ግን እንደ ማንኛውም ሰው መሆኔን ሲያውቁ ቀርበውኛል ብሏል።
“በአፈጣጠሬ አላፍርም፤ ይህ የእኔ ፀጋ ነው ይህን ለመቀየርም አልሞክርም በሁሉም ነገርም ደስተኛ ነኝ” ብሏል በጊነስ እውቅናውን ካገኘ በኋላ በሰጠው አስተያየት።
@Amazing_fact_433@Amazing_fact_433