TGStat
TGStat
Введите текст для поиска
Расширенный поиск каналов
  • flag Russian
    Язык сайта
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Вход на сайт
  • Каталог
    Каталог каналов и чатов Поиск каналов
    Добавить канал/чат
  • Рейтинги
    Рейтинг каналов Рейтинг чатов Рейтинг публикаций
    Рейтинги брендов и персон
  • Аналитика
  • Поиск по публикациям
  • Мониторинг Telegram
ዓምደ ➕ ኃይማኖት

12 Jul 2019, 09:28

Открыть в Telegram Поделиться Пожаловаться

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን።
. #እንኳን አደረሳችሁ።

👇አጭር ታሪክ ስለ ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ👇

አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ግብጻዊ ሲሆኑ እስከ 300 ዓመታቸው ድረስ በጾም
ጸሎት ሲያገለግሉ ከቅዩ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ
ያዛቸዋል፥ በቅዱስ ገብርኤል አማካኝነት በንፋስ ሰረገላ ከሶስት አንበሶች እና ነብሮች ጋር
አድርጎ በ11ኛው መቶ ክ/ዘመን በንጉስ ላሊበላ ወቅት ወደ ኢትዮጵያ ያመጣቸዋል።
አባታችን ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላም በጾምና ጸሎት ስለ ኢትዮጵያ ሕዝቦች አጥብቀው
ይጸልዩ ነበር፤
በዚህም ጸሎታቸው ምክንያት ጌታ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፥ ሆኖም አባታችን የሚፈልጉት
ሙሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲማርላቸው ነበር፥ በዚህም በጸሎት እየተጉ ሳለ ሰይጣን ውኃ
በተጠማ ቁራ ተመስሎ ጸሎታቸውን ለማስታጎል ከአይናቸው ውስጥ ያለውን ውኃ ቢጠጣም
ጸሎታቸውን አላቋረጡም ነበር።
አባታችን በአጠቃላይ ለ562 ዘመን የኖሩ ሲሆን ዕረፍታቸውም እንዲህ ነበር፦
መጋቢት ፩ በዕለተ ዕረቡ ብሔረ ሕያዋን በመሄድ በዚያ ከሚኖሩ ቅዱሳን ጋር ቆይተዋል።
መጋቢት ፪ ሐሙስ ዕለት ከብሔረ ሕያዋን በመመለስ ገድላቸውን አጽፈዋል።
መጋቢት ፫ አርብ ይታመማሉ።
መጋቢት ፬ ቅዳሜ በጸና ቢታመሙም ከጸሎታቸው አልተስተጓጎሉም ነበር።
ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ በጸና በመታመማቸው መሬት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ይቀመጣሉ፥
በዚህን ጊዜ ከሰማይ ወደ ምድር እንደሚዘረጋ መሠላልን የመሠለ ነገር ቁልቁል ይወርዳል፤
በዚህም ጌታችንና እናቱን ጨምሮ ቅዱሳን ሰዎችና መላዕክት አባታችን ወዳሉበት ይመጣሉ፥
በዚህ ጊዜ መሬት የጌታዋን መምጣት ስትመለከት ወደ ኋላዋ ትሸሻለች፥ ጌታችንም መሬትን
ምነው ሸሸሽ ቢላት እነሆ በቃል ብቻ አዝዞ የፈጠረኝ ጌታ ወደ እኔ ሲመጣ ከበደኝ ብላ
ትመልስለታለች፥ ጌታችንም በዚያ ያለችውን ሥፍራ ምድረ ከብድ ብሎ ሰየማት።
ጌታችን ለጻዲቁ እነሆ እኔ ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ? ሲላቸው ጻድቁም እነሆ
ስለሁሉም ነገር ስምህ የሚመሠገን ጌታ ሆይ የኢትዮጵያን ምድር ማርልኝ ብለው
ይማጸኑታል፤ ጌታም እነሆ ያልከው ይፈፀማል፥ ስምህን ለጠራ ዝክርህንም ለዘከረ እስከ 15
ትውልድ ድረስ እምርልሀለው፥ ኢትዮጵያንም የአስራት ሀገር አድርጌ ሰጥቼሀለው ብሎ ቃል
ይገባላቸዋል።
አባታችንም በ562 ዘመናቸው አረፉ፥

የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው። መዝ᎐፻፲፪፥፮ ምሳ᎐፲፥፯

አሜን አሜን አሜን።
እንኳን አደረሳችሁ

Join For More👇

@amde_haymanot
@amde_haymanot

1.8k 0 0
Каталог
Каталог каналов и чатов Подборки каналов Поиск каналов Добавить канал/чат
Рейтинги
Рейтинг каналов Telegram Рейтинг чатов Telegram Рейтинг публикаций Рейтинги брендов и персон
API
API статистики API поиска публикаций API Callback
Наши каналы
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Почитать
Академия TGStat Исследование Telegram 2019 Исследование Telegram 2021 Исследование Telegram 2023
Контакты
Справочный центр Поддержка Почта Вакансии
Всякая всячина
Пользовательское соглашение Политика конфиденциальности Публичная оферта
Наши боты
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot