ሥነ-ግጥም


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Telegram


____________________
ማንኛውንም ሃሳብ በ @Amharicpoembot ይላኩልን።

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Telegram
Статистика
Фильтр публикаций




የእርሳሶች ሀገር
(እንቅልፍ እና ሴት ከተሰኘው የግጥም መድብል።)

እርሳስ እድሜ ሁላ
መቅረጫ ሀገር ውስጥ - ገብቶ እየዞረ
ሲል - ያልቃል እያጠረ።

ቢቀርፁት ቢቀርፁት - መዶልዶሙ ላይቀር
በሚሏት - በእርሳሶች ሀገር
ማስተካከል ሳይሆን - መቅረፅ ነው ማሳጠር።


@amharic_poems


ህሊና ሲናገር
(ወንድዬ ዓሊ)

አልቅሰሻል አሉኝ
እርርን
ድብንን፡፡

ስለምን አስቀስሽ!?
አልቆረጥሽም እንዴ? ...
እንባ ማቆሚያ አለው
የቆረጡ ለታ፣
አለሁኝ እንጂ እኔ
አልቅሼው አይወጣ
ሞቼው አይረታ።

ነፍሰ ገዳይ እኔ
አንቺ ምን ሆንሽና
እኔው ለኔ ላልቅስ
እሽሩሩ ቢሉት
አይተኛ ህሊና፡፡

@amharic_poems








ክራር እና ፍቅር
(ኤፍሬም ስዩም)

ትግስት በሌላት በጨከነች ሌሊት
ወዳጅ ለወዳጁ ደብዳቤ ፃፈላት
ከመፃፉ በፊት ...
ከጥቁር ሰማይ ላይ ሦስት ኮከቦች አየ
ለጥቂት ቅፅበታት ከከዋክብቱ ላይ ሀሳቡን አቆየ

አንደኛዋ ኮከብ እጅግ የደመቀ ብርሃን ትረጫለች
ሁለተኛዋ ግን ደመቅ ትላለች ካንዷ ትሻላለች
ሦስተኛዋ ደሞ እርሱን ትመስላለች
በሁለቱ መካከል ፈዛ ትታያለች

እርሱን ለምትመስለው ብዕሩን አነሳ
ሁለቱን ከዋክብት ልቡን አወረሳ
አሁንም ዳግመኛ ከመፃፉ በፊት
ከአንድ አመት ቀድሞ በርሷ የተፃፈ ደብዳቤዋን አየው
የደብዳቤው ሀሳብ የደም ዕንባ አስነባው
እንባው ማፍቀሯ ነው መፈቀሩም እንባው
የሀሳቧም ሀሳብ ለሁለት ዘላለሞች አፈቅርሃለሁ ነው

በትንሹ ታምኖ ብዙ ያልወደደ
ስለተፈቀረም ትንሽ ካላበደ
በትንሽነቱም ያልተወላገደ
ፍቅርን እንዴት ያውቃል እንዴት ይረዳዋል

ምን ነበር የፃፍሽው ምንድን ነበር ያልሽው
የሆነ መስመር ላይ አስተውለው ብለሽ ከታች ያሰመርሽው
ፊደል እስኪጠፋው እጁን ያሰርሽበት
የፍቅር ቀለማት የማይጠፉ ቃላት
የእውነት መገነዣ ሌላ ያንቺ እውነት
ያንቺ እውነት ፍቅር የርሱ ፍቅር ፊደል
ካፈቀረስ በቀር ፍቅርን ማን ይገልፃል
ማንበብ ክፉ ነገር መፃፍ መገላገል
ይሄ አይደል መታደል

ምን ነበር የፃፍሽው ምንድን ነበር ያልሽው
አስተውለው ብለሽ የሆነ መስመር ላይ ከታች ያሰመርሽው
ይልቅ ያን አስታውሰሽ የክራሩን ድምፅ አሰሚኝ
የዜማ ድምፅ ከዚያ ይውጣ
እኔም ክሩን ሆኜ ባንቺ ጣት ልቀጣ
እኔና አንቺ እንዲያ ነን በሁለት አንድነት ዝንት አለም የታሰርን በቅኝት ቢወጣ ጣት እና ክር ነን
ወይም ድምፅ እና ክር
ፍቅርን ጣት አርገነው ባንድነት ምንዘምር

ምን ነበር የፃፍሽው ምንድን ነበር ያልሽው
በፃፍሽው መስመር ላይ መብረቅ ፍቅር አለ
የዝናብ ድምፅ የለም ደመና ግን አለ
ከደመናው በፊት የደብዳቤሽ ቃላት
አንተ ማለት ባህር እኔ ማለት ትነት
በፀሀይ ፈገግታ ጨውን የምንፈጥራት
አንተ ማለት ጸጸት እኔ ማለት መዳፍ
የቀደመ ዕንባህን ካይንህ ላይ የምገፍ
አንተ ማለት ጥማት እኔ ደሞ እርካታ
በበርሀ ንዳድ የምገኝ ጠብታ

ማንበቡን ቀጠለ
የመብረቅ ብልጭታ የዝናብ ድምፅ አለ
በጥቁር ደመና ቀድሞ የታዘለ
ደብዘዝ ያለ ብርሃን የማትታይ ፀሀይ
የተኳረፈ ፍቅር ያረገፈ አደይ
በሁለታችን አዝኖ የተከፋ ሰማይ

ይህ ሁሉ ቢሆንም
መዳፍሽ እርቋል
ጨውነቱም ጠፍቷል
ቃሎችሽ ሰክረዋል
በዚያ ታላቅ ዝናብ ምድር ስትቀጣ
በመብረቅ ብልጭታ ነፍሳችን ስትወጣ
እኮ በምን እግሬ ከደጃፍሽ ልምጣ
አንቺ እንደሆን ንግስት የመኳንንት ልጅ
ህንፃ ፍቅር ልብሽ ጉብዝናን የሚያስረጅ
እኮ በምን ሀይሌ ልርገጠው ያንቺን ደጅ
ማን በምን ጉልበቱ በየት ጀግንነቱ
ዝም ባለ ቅፅርሽ ያንቺ ጉርፊያ ነግሶ
ፊትሽን ፍራቻ ልቦናዬ ፈርሶ
በሳምንት ዘመንሽ ዐይኔ ደም አልቅሶ
እኮ በምን አቅሙ እንዴትስ ተደፍሮ ደጅሽ ይረገጣል
አይኑስ እንዴት ደፍሮ ዕንባውን ጠራርጎ ያንቺን ዐይን ያያል
ምን ነበር የፃፍሽው ወይስ እኔ ፃፍኩኝ
ከፍቅርሽ ላይ ወይን ደብልቄ ጠጣኹኝ

ፍቅር እና ወይን
የሁለት አንድነቱን የጣትና ክሩን
በስልት የተቃኘ ክር ድምፅነትን
ፍቅርን ጣት አርገነው በተነካን ቁጥር
በስሱ ከላይዋ እንደተመታች ክር
በራሳችን ቃና በራሳችን መዝሙር
ለዘላለም እድሜ ባንድ ተገመድን
ወይስ ምንም ሆንን
እውነት ምንም ሆንን

ዜማ ሰጭ ፍቅራችን ተበጠሰ ላላ
የኛ ቅኝታችን በኔነት ተበላ
ያለሙያው ገብቶ ያለመጠን ነክቶ
ያለስልቱስ ቃኝቶ
ክራር ፍቅራችንን ክሩን ማን በጠሰ
በምን አይነት ስልትስ ዜማችን ታደሰ

ከሐሳቡ ነቃ

በራሱ ክር ላይ የራስ ስልቱን ቃኘ
ለደብዳቤዋ መልስ ሊመልስ ተመኘ
ላንተ ያለችውን ላንቺ ብሎ ፃፈ
በራስ የቃል ስልቷ ቃሉን አከነፈ

ረስቶት ነበረ ...
ከጠረቤዛው ስር በፅዋ ተሞልቶ ወይኑ ተቀምጧል
ጥቁር የወይን ደም ከፅዋው አንስቶ አንደዜ ጠጣለት
አንዱን ሳያጣጥም ፅዋዉ ወደቀበት
የፈሰሰው ወይን ልብሱን አረጠበው መሬቱን አራሰው
ፍንጥቅጣቂው ደሞ አይኑን አስለቀሰው
የብርጭቆው ፅዋ አልተሰባበረም
ሁሉም ፈሶበታል የተረፈ የለም

ለመፃፍ ከበደው
ደብዳቤው ቀፈፈው
መሬት አጎንብሶ እጁን ተንተርሶ
ስለሆነው ሁሉ ያስተውል ጀመረ

እንቆቅልሽ
የወደቀ ፅዋ ያልተሰባበረ
የፈሰሰ ወይን ባንድ ጉንጭ የቀረ
ያላለቀ ፅሑፍ በረቂቅ የኖረ
ያኮረፈች ፍቅር ደጇ የታጠረ
አራቱ ሚስጥሮች ሳይተረጎሙ ሳይመረመሩ
ባፍቃሪው ልቦና እንቆቅልሽ ሆነው ለዘላለም ቀሩ

@amharic_poems


የተጣለ ፈረስ
(በእውቀቱ ስዩም)

ዘመኑ ያለፈ
ጋማው የረገፈ ፤
የጎድን አጥንቱ ፤ ማበጠርያ መሳይ
ጠዋት ህያው ፍጡር፥ ሌሊት የጅብ ሲሳይ
ከተማው መግቢያ ላይ
አቧራ የሚቅም
የተጣለ ፈረስ አጋጥሞሽ ፤ አያውቅም?

“ካሁን አሁን መጥቶ፤
ይወስደኛል ነድቶ
ከጋጣው አግብቶ ፤ ያበላኛል እብቅ “
እያለ ጌታውን ፥ተግቶ የሚጠብቅ
የዛሬ ተጎታች ፤ የትናንቱ ሰጋር
ተባብሮ የከዳው፤ ጊዜ ከጌታው ጋር
የቸገረው አቅም፥
የተጣለ ፈረስ ፤ አጋጥሞህ አያውቅም?

ደሞስ መች ይጠፋል? ካንቺም ከኔም መንደር
የቀድሞ ወታደር፥
በጨነቀን ጊዜ ፥“በናት ሀገር ጥሪ “
የምናጣድፈው፥
በድል ቀን ከድግስ፥ የማናሳትፈው
ከነጣቂ መዳፍ ፥ አገር የሚያስመልስ
በገዛ አገሩ ላይ፥
መብቱ ከወፍ አንሶ፤ ጎጆ የማይቀልስ፤

ደሞ መች ይጠፋል፤ ከኔም ካንተም ቀየ
መንገድ ላይ ምናልፈው፥ አይተን እንዳለየ
የቀድሞ አስተማሪ
ላብ እያጣቀሰ ፊደል አስቆጣሪ
ቀሪ ሀብት ባይኖረው፤
የቀረውን ዘመን፤ እያሰላ ኗሪ፤

ቪላችንን ሞልተን፥ በሱ ጎጆ ጉድለት
ማሰብ አስተምሮን ፥ የማናስበለት
ቀኖቹን በትኖ፤ ሌሊቶቹን ዘርቶ
ናላውን፥ ጉልበቱን ፥ ውበቱን ሰውቶ
የሚጎተት አገር፥ ከግቡ ለማድረስ
ሺህ መንገድ አቅንቶ፥ ሺህ ገደሎች መውረስ
ሰው ቢሉት ሰው ነው ወይ?
የተጣለ ፈረስ።


@amharic_poems


የተዘጋበት ቁልፍ
(ኤፍሬም ሥዩም)

የተዘጋን ጎጆ የተቆለፈን በር
የተራበ ህፃን ለመክፈት ሲታገል
በታላቅ ሰንሰለት የታሰረን አጥር
ማን ዘጋው እያለ ጎበዙ ሲያማርር፡፡

ሌሊት ይመስለኛል ተኝቼ በህልሜ
ካንድ ታላቅ ባህር አጠፋብ ላይ ቆሜ፡፡
የተዘጋውን በር የቆሙት ሲያንኳኩ
ተስፋ የቆረጡት ወድቀው በየመስኩ፡፡
ተመልክቼ ነበር በትንሿ እድሜዬ
ከእንቅልፌ ላይ ባለች በህልም ጊዜዬ።

ለካስ በዚያች ሀገር….
እያንኳኳ ነበር ትውልድ የሚኖረው
እልሁ በርትቶ በሩን እስኪሰብረው
አዎ በዚያች ሀገር!...
አባት በልጁ ላይ ቆልፎበት ነበር
በእዳ በተሰራ በታላቅ ብረት በር።
የዚያች ምስኪን ሀገር ቁልፉ ግን የጠፋው
ከደጂ አልነበረም ውስጥ ጓዳዋ ነው፡፡

እውነት የትኛው ነው?
ፍሬ ነው አበባ ወይስ የፍሬ ግንድ
መጥፎ ነው ተብሎ ተጥሎ እሚማገድ
ቁልፉን የጣለው ነው በሩን የሚሰብረው
ከተጠያቂነት ነፃ የሚባለው?

እናም በዚች ሐገር መፍትሔ እሚባለው፣
ቁልፉን ማግኘት ሳይሆን በሩን መስበር ላይ ነው፡፡
እውነት የትኛው ነው?
ፍሬ ነው አበባ ወይስ የፍሬ ግንድ
መጥፎ ነው ተብሎ ተጥሎ እሚማገድ
ቁልፉን የጣለው ነው በሩን የሚሰብረው?

አዎ በዚች ሀገር!...
የእናቶች እንባ ሰማያትን ቀዷል
የህፃናት ጩኸት በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት፣
እንደ ጭቃ ሆኗል
አዎ በዚች ሀገር…
የሚያንኳኩ እጆች ቁጥሮች ጨምሯል
ተስፋ የቆረጡ እርማችን ነው ያሉ ባህር ተሻግረዋል።

እኛስ ለምንድነው ለዘመን ዘመናት
በሩን የምንመታው ቁልፉን ዘግተውበት
በዚች ሀገር እኮ! መፍትሔ እሚባለው፣
ቁልፉን ማግኘት ሳይሆን በሩን መስበር ላይ ነው!!!


@amharic_poems


ሕይዎትና ስንኝ
(ደሱ ፍቅርኤል)

እኔና አንቺ ማለት…….
እንደ መንቶ ግጥም ባለ መንታ ስንኝ
ዜማቸው ቅርፃቸው
ምጣኔ ምታቸው ሆነው ተመጣጣኝ
ሃሳባቸው ግና
እንደሚለያዩ የታችኛው ስንኝ ከላይኛው ስንኝ
እንደዚያ ማለት ነን
ምሳሌ
.
.
አውሮፕላን መጣ እየገሠገሠ (አንድ)
በዘፈን አንደኛ ጥላሁን ገሠሠ (ሁለት)
.
.
እነዚህ ስንኞች
ዜማና ምታቸው ምጣኔ ቅርፃቸው
ተመጣጣኝ ናቸው ተመሳሳይ ናቸው
የያዙትን ሃሳብ ካስተዋልሽ ግና
የዘፋኙ ክብር ካ'ውሮፕላን ጉዞ የለውም ዝምድና
እና?
ማይገናኝ ሃሳብ ደንጉሬ 'ምዘጋ ምርጥ ሃሳብ ስትከፍቺ
ሁለት ማለት እኔ አንድ ማለት አንቺ
ወይም ወይም ደግሞ
ነፍሴን አስጨንቄ አንድ ሃሳብ ሳመጣ
ከሃሳቤ ጋራ ዝምድና የሌለው ቃል ካ'ፍሽ ሚወጣ
ቤት መዝጊያሽ የማይጥም እንደ ግልብ ቅኔ
ሁለት ማለት አንቺ አንድ ማለት እኔ
ማጠቃለያ
ትዳር ባሉት ጣጣ
ጎጆ ባሉት ፈሊጥ አብረን ብንሆንም
አንድ ቤት ነው እንጅ አንድ ህልም የለንም
አንድ ሃሳብ የለንም
.
.

@amharic_poems


ሴትየዋ ሴት ናት
(መስፍን ገ/ ማርያም፣ 1979)

አላፊና አግዳሚው የብርቅነሽ ባይላት
ለሴትነት ወጉዋ ባትገባ ጫጉላ ቤት
ዳቦው ባይቆረስ ባይታይ የደሙ ሻሽ
ጋብቻ አንቆላጵሷት ሥሟ ባይሞካሽ
ሚዜው አቀንቅኖ አሞራ በሰማይ ሳያያት ባይውል እንኲ
የወገቧ ቅጥነት በስንዝር ባይለካ
ባቷ አወራረዱ ስሜት ባያሸፍት
ጡትዋ አጎጥጒዋጤዋ እንደ ጦር ባይቀፈት
አይኗ ብር አለሎ ጥርሷ ባይመስል ወተት
ዳሌዋ ባይኮራ አንጀቷ ባይኮትት
ከንፈርዋ ባይሳም ሙዳ ሥጋ ከብዶት
የእጆቿ ጣቶች ባይሆኑም አለንጋ
ተረከዟ ተርፎ እንደ ጦር ቢዋጋ
የሰራ አከላትዋ ወንድነት ቀስቅሶ ልብ ባያጕዋጒጒ
ደምግባት ዛላዋ ከሩቅ ባይጣራ
ጠረኗ ከሽቶ ተዋህዶ ባይሰራ
የአረማመድ ስልቷ ሰልጥኖ ባይገራ
ፊቷ ጠለስ መስሎ ቢወረውም ማድያት
ባትወደስ እንኲዋን ቅኔ ባይቀኙላት
ደግሞ እንደሚባለው ጥሩ ውሀ ባይዋጥ እሷ ባለችበት
ቸርነት ቢነፍጉዋት የውበት አማልክት
እንደ ሞናሊዛ ባይዋጣላት ውበት
ሰንደቅ ባያሰቅል የቁመቷ ርዝመት
ይህን ሁሉ ውበት ባትታደለውም
ለፍቅር ወክለው ባይተራርኩላት
እማዬዋ ወልዳ አባዬዋ ስሞ አመል ትሁን ያሏት
........................ገብርዬ ሲወዳት ።
ከዋርካ ዛፍ ጥላ የሷን ተቀብሎ የሱን ያቀበላት
እስትንፋስ ወስዶ እስትንፋስ የሰጣት
እኮ ለገብርዬ ውስጡዋን ለተረዳው ውስጧን ለፈተሻት
ጣቱን እስኪጠባ ወየው የምታሰኝ ሴትየዋ ሴት ናት ።
ጎማዳ አፍንጫዋ ሸካራ ገላዋ
ምስጢር የደበቀው ጅላጅል ዛላዋ
እንደ ክራር ጅማት የሚቆጣጠረው አውላላ ግንባርዋ
ደብቆ ያኖረው
ማንም ያልዳሰሰው
ማንም ያልፈተሸው
እንቁ የታደለች
ምስጢሯን መስጥራ እንደ ድንግል መሬት
ወየው የምታሰኝ የውስጧን በውስጧ አምቃ የያዘች
ሴትየዋ ሴት ናት
ማንም ያልቀመሳት
ማንም ያልተጋራት
ገብርዬ ብቻውን የኔ የኔ ሚላት ።


@amharic_poems


#እወድሻለሁ !!!

የአምላክን ትዕዛዝ ልቤ እሺ ቢልም ፣
ካንቺ ጋር የሆንኩት ኃጢያት አይባልም ፤

ነውር እንደሆነ የእብድ እሳትን ማጥፋት ፣
ነውር እንደሆነ ለማኝ ላይ መትፋት ፣
ነውር እንሆነ መሽናት በተስኪያን ዳር ፣
ነውር እንደሆነ ያለ እድሜ መዳር ፣
ነውር እንደሆነ ኪዳነ ወልድን ትቶ ቃል አውቃለሁ ማለት ፣
ነውር እንደሆነ ረስቶ መቀመጥ የግሸንን ስለት ፣
ነውር እንደሆነ በጁማአ መሐል ሶላትን ማቋረጥ ፣
ነውር እንደሆነ በቆሞስ ወንበር ላይ ጉብ ብሎ መቀመጥ ፤

እንደዚያ ነውር ነው አንቺን አለመሳም ፣
የወደደ ሲያብድ ለነገው አይሳሳም ፣
አልሳሳም ለነገ አልሳሳም ለተስፋ ፣
ትዕዛዝ አይባልም ፅድቅ የሚሉት ነገር ፍቅርን ከገፋ ፤

እወድሻለሁ !!!

✍️ ኤልያስ ሽታሁን



@amharic_poems
መልካም ቀን  💚


ቀለበት ስናስር
(ባሴ ሀብቴ)

የመርሳት ነገር ተነሳና
እንደ ዘበት ስናወራ
የስንት ዘመን ፍልስፍና

ያልዘለቀዉን ጎራ
የስሜትን ጉራንጉር
የኔ ምን ሆ'ንን ምስጢር

እንደ ድንገት አገኘነዉ፤ _
. . . ቦታዉን ጎበኜነዉ
እና. . . .
ፍልስፍናዉን በመሙላት
የመርሳትን ነገር ልንገለዉ
የምንረሳዉ ምንድነዉ?
የማይረሳ ማነዉ?
አልን
እንደገና ከሥሩ
ሳይገባን መጀመሩ
የኔ ምን'ሆን ምስጢሩ
የስሜት ጉራንጉሩ


@amharic_poems


ነገ
(ወንድዬ ዓሊ)

ነግ - ማለት . . .
ቆርጠን . . . የማንሸርጠው፣
በሳንዱቅ . . . የማንከተው፣
የማርያም መቀነት - ዓይነት ነው፡፡

ቀስተ ደመና . . .
የኅብረ ቀለሟ ቅይጥ . . . በስሜት ቅርብ-ሩቅነት . . . ሲባጎ፣
ምጥን ምሥጢሯ፡- . . . በመሰወር ሸራ ልባስ . . . ተሸሽጎ፣
ውብነቷን፣
መዋብ - አምሮን፣
ፈዘን - ቆመን፣ . . .
በመገረም ነሁልለን ስናይ፣
ለመጋደድ እየከጀለን - ከየዓይነትያ ቅመሟ፣
ጨልፈን ብልቃጥ ሳንዶላት፣
ትቅድመናለች መክሰሟ፡፡
በቃ! . . . ነግ ማለት፣
የዚሁ - ዘር ናት፤
ብያችሁ ነበር፡፡

@amharic_poems


ምድጃ ዳር የተተወ ፍቅር
(ኑረዲን ኢሳ)

ሽው እልም ሽው እልም
አትበልብኝ ባይኔ
እንደ ዘሃ ዘጊ
ባተሌ ሸማኔ
የተቋጨ ኩታ
ስፈትል ስፈታ
ምንሆንሽ ያለኝ የለም
ከጧት እስከማታ
ሆዴ ያንተስ መውደድ
ያንተውስ ፍቅር
ልብ እያባዘተ
አንጀት የሚፈትል
ማዶ ማዶውን ሳይ
ናወዘ ምድጃው
በሆዴ አመድ ለብሼ
ዋልኩኝ እንደጉልቻው
ደጅ የተኛው ውሻ
ተክዞ አስተከዘኝ
ወይ ነክሶት ባልሆነ
እኔን የነከሰኝ
ይሞቀኛል ያልኩት
ወይራና አባሎ
መች አመድ የሚሆን
መስሎኛል በተሎ
እንደሄድክ ቀረህ
አልል አንድ ፊቱን
ሽው ሳትልብኝ
አታድርም ሌሊቱን
ሽው እልም ሽው እልም
አትብልብኝ ባይኔ
እንደ ዘሃ ዘጊ
ባተሌ ሸማኔ
ሰው እንዳልሆን ሲያውቁት
አንተን ካጣሁ ጎኔ
እንዴት ነሽ ይሉኛል
እንደምን ነኝ እኔ?



@amharic_poems


አንፃር
(ኤፍሬም ስዩም)

"የማውቀው ሦሥት ዓመት
ምን ይሉት ፈሊጥ ነው
ካስር ዓመት በፊት እያሉ ላገሩ በመጽሃፍ ማውራት"

ብለሽኛል አሉ።   .  .  .
አለች ብለውኛል
እኒያ ጓደኞችሽ በማኪያቶ ግብዣ ሚደለሉ ሁሉ ሚደልሉሽ ሁሉ
በርግጥ አውነት አለሽ  .  .  .
የሁለታችን ፍቅር ረዥሙ ዕድሜ ሦሥት ዓመት ብቻ ነው
ለምን የሁለታችን? ያብዛኛው እንዲያ ነው
ግን
የወንዱ ይቅርና
በሴት አቆጣጠር ሦሥት ዓመት ሥንት ነው?

@amharic_poems


ስርቆሽ
(ሜሮን ጌትነት፣ ዙረት የግጥም መድብል ገፅ 13 )

አልመለስ ያለ ትውልድ
አዳኝ መርከቧን ንቆ
በጥፋት ውሃ ሰጠመ
በዝሙት ሃጥያት ወድቆ
ኀላም ውሃው እንደጠፈፈ
ምድርን 'ሀ' ብሎ ሲያቀና
ኖህ በኩራት እንደቆመ
ፍጥረቱን ሰበሰበና
በቅደም ተከተላቸው
በጥምረት እንዳሳፈረ
ከመርከቡ ሊያወርዳቸው
አንድ በአንድ እየቆጠረ
አጋር የሌለው ፍጥረት
መጀመሪያ ያልነበረ
አንድ እንስሳ ትርፍ ቀረ
ለካስ የዝሙት መንፈስ
ከአህያ ጋር ተሳፍሮ
ሚስቱን እየደበቀ
ከፈረስ ፍቅር ጀምሮ
ከማይሆን ተኝቶ ኖሮ
ከመርከቡ እንደወረደ
መሃን በቅሎን ወለደ!

እንግዲህ ከኖህ ጀምሮ
ዘመን ዘመንን አያደሰ
የጥፋት ውሃም የለ
ዝሙትም እዚህ ደረሰ፡፡


@amharic_poems


ፈገግታሽን ብቻ
(አስታወሰኝ ረጋሳ)

ነግሬሽ አልነበር
አይን እስካለ ድረስ ቀሚስ አለ የትም
ለፈገግታሽ እንጂ ለገላሽ አልሞትም

ምንጊዜም ዝቅ አርጊው
የቀሚስሽን ጥለት
ሁሌ ገላ አይቀዱም ወሸላና ስለት

መዶልዶም
መደነዝ
ማርጀት ይፈርድማል
የዕድሜ ስልጣን ቁጣው
ዛሬ የረካሽበት
መሽኛሽ ብቻ ሆኖ ይቀጥላል ዕጣው

መልሼልሽ ነበር
ዲዛይነሩ ሁሉ
ባጭር እየሰፋ በስሜት ቢለክፈን
ይሄ ውብ ቀሚስሽ
አብሮሽ አይቀበርም ይተካል በከፈን

ሁሉም ትርጉም አለው ሰዋሰው እና አቻ
መተንተን የሚከብድ ፈገግታሽን ብቻ


@amharic_poems


ሀገር አትታይም
(ደሱ ፍቅርኤል)

"አገር አገር አትበይ አንቺ አገረ ብርቁ፤
የኔም አገር አለኝ የሚታይ በሩቁ"
ብዬ ብዘፍንላት - ባ'ሽሙር እያየችኝ፣
"የታለች አገርህ?" ብላ ጠየቀችኝ፡፡
በኩራት ላሳያት...
ፈጥኜ ብጠቁም እጆቼን ወዳ'ገር፣
ቁመቴ አጠረና...
አላሳየኝ አለ የቆምኩበት መንደር፡፡
ከተራራው አናት...
ከከፍታው ሆኖ እጁን ካልጠቆመ፣
አገር አትታይም መንደር ላይ ለቆመ፡፡


@amharic_poems


"ዝም በል"
(ኤልያስ ሽታኹን)

ከሳሽህ ፊት ዘንበል
ሰዳቢህ ፊት ዘንበል
በነፍስህ ተናገር በቃልህ ዝም በል።

ዝም

እሺ በል አጎንብስ
ፊደል አታገግበስብስ
ዝም በል ጭጭ ጭጭ
ስንፍናን በልምጭ
ዝምታህን እቅጭ

ነው ብለህ ተቀበል
ዝም ብለህ አስጩህ እንደቅዱስ ፀበል::

አስብ ዝም ብለህ
እንደሊቅ ተራቀቅ
እንደንጉሥ ውደቅ::

ዝም ብለህ ሞክር
ዝም ብለህ ጨክን
ዝምበል ተንገዳገድ
ማስራዳት ሲያስብ ነው ሰው የሚወላገድ::

ዝም::

እግዜርን ተመልከት
ሊያስረዳህ ሲሞክር አታየውም ሲጥር
መች ብዙ አወራ ዓለምን ሲፈጥር።

(ዝም ብለህ ቀጥል…..


@amharic_poems

Показано 20 последних публикаций.

7 656

подписчиков
Статистика канала