ሐሽማል ቤተ-መዘክር


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Книги


👉Only for readers
👋መግቢያ👋
መግቢያ ለመግባቢያ
ገታ አርገነዋል የቃላትን ግልቢያ
እናም በዚህ ሀሳብ ከተስማማህበት
ያንኳኳኸዉን በር የገለፅከዉን ገፅ ፈቅደናል ግባበት
ምንጭ - ካልታወቀ ገጣሚ
Join the group
@amharicbooksforeadersgroup
አድሚኑን በ ቀጥታ ለማናገር ይህንን ቦት ተጠቀሙ @Digitallibraryofhashmal_bot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Книги
Статистика
Фильтр публикаций


ልክ እንደ ወተት ጥርስ የነቀልነው ወተት ልብ ኖሮን ይሆን እንዴ ጥላቻችን መስመር ያለፈው .. እላለሁ አንዳንዴ

ፍቅር አናውቅም ጥላቻ በደማችን እንደገባ አንድያ ነገር ያንገበግበናል ..

✍️ሔኖክ






Репост из: Sost Kilo
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


መሬት የወደቀው ቅጠል ንፋሱን ሰደበው

"የጣልኸኝ አንተ ነህ"



ንፋሱም መለሰ

"እኔ ድንገት ሳልፍ ነው እኮ አንተ የወቅኸው።
ግንዱን እየው አልወደቀም
ቅርንጫፍህን እየው አልተሰበረም"

ቅጠሉ
"አንተ ባትገፋኝ ባታወዛውዘኝ አልወድቅም ነበር" አለው



ንፋስ ሳቀ።

" ሁሉም ራሱን ቢያጠነክር ይድን ነበር። ያለፈ ያገደመ የሚጥለህ ራስህን ስለጣልክ ስላቀለልክ ነው።
አየህ
የወደቁ ሁሉ ሁሉ የተገፉ አደሉም! "


ኤልያስ ሽታኹን


የመጀመሪያው ፍቅር ያዘኝ።የመጀመሪያው ፍቅር፤የእናትና የልጅ ፍቅር ነው።ከእናቴ ፍቅር ያዘኝ።ብን.....! አልኩ፥ እፍፍፍ...!በየደቂቃው ራሴን ፍለጋ ዐይን ዐይኗን ማየት ሆነ፨በፍቅር አበድኩላት።ፍቅር ማለት ለካስ ራስን በሌላው ውስጥ ማየት ነው።ሳድግ ለምን እንዲህ ውስብስብ መሰለኝ!? እሷም እንዲሁ ዐይኔ ዐይኔን ስለምታየኝ ፍቅር ሳይዛት አልቀረም!መተያየት በመተያየት ሆንን።

አንዳንድ ጊዜ እናቴ ዐይን ዐይኔን ስታየኝ ትቆይና በዚያው እ..ል..ም ትላለች።ብጠብቅ አትመለስም፥ብጠብቅ...፤እቁነጠነጣለሁ..ምንም መልስ የለም።አተኩሬ ዐይኗን ሳይ፤እኔም ዐይኗ ውስጥ የለሁም።የት እየሄደች ነው? እላለሁ።በብዙ ጉትጎታና መቁነጥነጥ ትመለሳለች።ስትመለስ ታዲያ የዐይኗ ነጭ፤ቀይ ደመና ያረግዛል።ትንሽ ቆይቶም ከዐይኗ ደመና፤ከፊያ ዝናብ መንጠባጠብ ይጀምራል።እኔ እረበሻለሁ።ደስ አይለኝም።ለምን እና ለማን እንደሆነ ሳላውቅ አጅባታለሁ።እናት ስታለቅስ ታሳዝናለች።ለቅሶዋ መቼም ቢሆን ስለ ራሷ አይደለም።

📓ርዕስ፦አለማወቅ
✍️ደራሲ፦ዳዊት ወንድምአገኝ




ካይኔ እንደገባህ ካይንህ ለመግባት ስል
ቀመሬን ስጀምር ገና ሳብሰለስል
ቅርፅና ቀለሜን ባንተ ልክ ቀይሬ
መዋል መመሳሰል እንድውል አብሬህ
ጉዞዬን ጀመርኩኝ ወደልብህ ዛሬ

ዉሎ አኗኗርህን ካጠናው በሗላ
የዘራሁት ፍሬ መስሎኝ የሚበላ
የበረሀ አትክልት ሳጠጣ ሳጠጣ
በለሱ ተንሳፎ አመጣብኝ ጣጣ

በልክህ ባይሰራኝ እግዜር ለኔ አስቦ
ልቤ አልሰማ ብሎ ተጨንቆ ተጠቦ
ባልተሰራለት በር ለመግባት ሲሞክር
እንቢታህ ሲጠና እኔ ዙሩን ሳከር
አንዲት ግድ ሳይሰጥህ እኔው እንደዳከርኩ
ያልሆንኩትን ስሆን የሆንኩትን ከሰርኩ

ሳስበው አፈርኩኝ
ያንተ እንቢ ማለት የኔ ካልሰጠኹኝ
ፍቅሩ ወደ እልህ ሲቀየር ባንድ አፍታ
ተራዬ እንዲደርሰ እኔም ድል ልመታ
ሌላ ፋብሪካ ውስጥ ሌላ ቀለም ሆኜ
አዲስ ቅርፄን ይዤ ወጣሁ ተቀጥቅጬ

ያችኛዋ ፍቅር ይቺ በቀል አምጡ
ተለያዮ ቢባል ካንተ አላመለጡ
እንዲቆጭህ ብዬ ያሴርኩትን ሴራ
ያልሆንኩትን ስሆን አሁንም ኪሳራ


ለቀልድ እንኳ ተይኛ በቃ ያልኳት እንደው እንደ አራስ ነብር ቁጣዋ ልክ የለውም ...

እያለ እያለ በሷ ምክንያት ቀልድ አቆምኩ....

✍️ሔኖክ




Репост из: Sost Kilo






Репост из: ጥበብ 🚶‍♂️🧑🏿‍መንገደኛ
"በጥጋባቸው ዓድዋ ላይ ተዋግተው ድል ሆኑ። እኔ ግን በድንቁርናቸው ብዛት የእነዚያን ሁሉ ሰዎች ደም በከንቱ መፍሰሱን እያየሁ ድል አደረግሁ ብዬ ደስ አላለኝም"

አፄ ምኒልክ ለአውሮፓዊው ዲፕሎማት ሙሴ ሸፍኔ በመጋቢት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. በጻፉት ደብዳቤያቸው ከገለጹት




ድርሰት ትሞክራላችሁ?

እስኪ ረፍዷል የሚለውን ቃል ሳትጠቀሙ ረፍዷል በሉ 😊

Via TikTok




የቀበጡ እለት


አባባሉን ብዙም አልወደውም ግን አንዳንዴ ሳንወደው የምንለው ነገር አለን አይደል ...?

ሁላችንም ሰዎች በሚያስብል ሁኔታ እንደ ደመና ለማይጨበጥ የዚህ አለም ሀሳብ ተገዝተን አለን

ጠዋት ታይቶ እንደሚጠፋ ጤዛ የሆነውን ዝና ፣ ክብር ፣ ገንዘብ ፣ እውቀት... ገለመሌ አሳዳጆች ሆነናል ።

መቼም የቀበጥን እለት ተው የሚለን ሁሉ አጥፊያችን ይመስለናል ያልተውነው ነገር ደሞ መጥፊያችን ነው ብሎ መቀበል ይከብደናል ...

ይ.....


✍️ ሔኖክ


ተማሪዎቿን አንድ በአንድ የምትከታተል አንድ ብርቱ መምህር አለች።

ከተማሪዎቿ አንዱ አያወራም፣ ከተማሪዎች ጋር አይጫወትም፣ ልብሱ ዝብርቅርቅ ያለ ነው፣ ክፍል ውስጥ አይሳተፍም መምህቷም በዚህ ተማሪ ደስተኛ አይደለችም።

መምህርቷ የተማሪዎችን የቤት ሥራ እና ፈተና ባረመች ጊዜ ሁሉ የዚህ ተማሪ ፈተና በትልቁ ኤክስ (X) የምታደርግ እና በብስጭት ስንፍናውን የምትጽፍ ሆነች በፍጹም አልወደደችውም።

በትምህርት ቤቱ ሕግ ደግሞ የእያንዳንዱን ተማሪ የቀድሞ ዓመታት የውጤት ፋይሎችን አሁን ያሉ መምህራኖች ማየት ግዴታ ስለሆነ መምህርቷ ይህንኑ ስታደርግ የሁሉንም ፋይል ዓይታ የዚሁ ተማሪ መጨረሻ ላይ ቀረ።

መምህርቷ የተማሪውን ውጤት አነበበችው ተገረመችም ደነገጠችም...!

የአንደኛ ክፍል መምህሩ "በጣም ጎበዝ ተማሪ ነው! ፀባዩም ሸጋ ነው ንፁህ እና ብሩህ ተማሪ ነው" ሲል ሀሳብን አስፍሯል።

የሁለተኛ ክፍል መምህሩም " ጎበዝ ተማሪ ነው ነገር ግን በዚህ ዓመት እናቱ በጠና ስለታመመች በውጤቱ ቀንሷል"ሲል ጽፏል።

የሶስተኛ ክፍል መምህሩ ደግሞ " በእናቱ ሞት ተጎድቷል! አባቱም በሀዘን ስለተጎዳ ትኩረት የሚሰጠው ሰው የለም" ሲል ስለተማሪው ጽፏል።

የአራተኛ ክፍል መምህሩም "አባቱን በሞት የተነጠቀው ይህ ተማሪ ብቸኛ ነው ከማንም ጋር አያወራም ውጤቱም በጣም ወርዷል"ሲል ጽፏል።

እለቱ የገና ዋዜማ ነው ተማሪዎች ለመምህራኖቻቸው ስጦታ የሚሰጡበት ዕለት ነው ሁሉም ተማሪዎች ለመምህራቸው የሚያምሩ ስጦታዎችን እየሰጡ ነበር።

በስተመጨረሻ ይህ በትምህርት ደካም እና ጎስቋላ የሆነው ተማሪ መጣ...

በእጁ ጌጣቸው የረገፈ አምባር እና ሊያልቅ ቂጡ ላይ የደረሰ ሽቶ ይዟል...

...የእናቱ የእጅ አምባር እና ሽቶ ነበር።

የክፍሉ ተማሪዎች ይህንን ዓይተው ሳቁ መምህሯ ግን ተማሪዎቹን ፀጥ አሰኝታ አምባሩን አጠለቀችው ሽቶውን ተቀባች ተማሪውንም አቀፈችው።

"ዛሬ እናቴን መስለሻል... እናቴን እናቴንም ሸተሻል" አላት እንባ እየተናነቀው...

መምህርቷ ተማሪዎች ከሄዱ በኃላ ለሰዓታት ብቻዋን አለቀሰች።

...ከዚያ ግዜ ጀምሮ መምህቷ ተማሪውን በሚገባ ተከታተለችው እርሱም አላሳፈራትም ጎበዘ ሆነ ትምህርቱንም በትኩረት ይከታተል ያዘ።

...ዓመቱ መጨረሻ ላይ ጥሩ ውጤት አመጣ።

በትምህርት ቤቱ ውስጥ "የመምህራኖቹ ተመራጭ እና ለብዙ ተማሪዎች ምሳሌ ሆነ ...

በፀባዩም ምስጉን፣በባህሪው ደግሞ ተግባቢ እንዲሁም ደስተኛ ሆነ።

መምህርቷም ሁልግዜም ዓለምን የማይበትን መነጽር እንድቀይር ያደረግኝ እርሱ ነው ስትል ትናገራለች

✨ እንማር


✅ሁሉም ሰው ማስታወስ ማውራት የሚፈልገው ትናት የለውም አንዳንድ ሰው ትናቱን ይሸሻል መርሳት ይፈልጋል

✅ሁሉም ትናት አዝናኝ ተናፋቂ አደለም አስቀያሚ አሳዛኝ ትናትን ያለፉ ይሄን ትናት የሚሸሹ ማስታወስ የማይፈልጉ ሰዎች አሉ

ሰዎች ፈቅደው ሊያወሩላቹ ስላልፈለጉት ነገር ለማወቅ አታስጨንቁ አትበርብሩ እንድታውቁ የተፈቀደላችሁን ካወቃቹ በቂ ነው

✅ከዚ በፊት የምታውቋቸውን ሰዎች ለሌሎች በጋራ ለምታውቋቸው ሰዎች እንዲ ነበሩ እንደዛ እያላቹ ሊያስታውሱት ሊያወሩት ያልፈለጉትን ፍቃዳቸውን ሳትጠይቁ ምንም ነገር አትናገሩ መንገር ከፈለጉ እነሱ ይናገራሉ ታውቋቸው እንደነበር ከተናገራቹ በቂ ነው

የሆነ ሰው ተለውጦ ስታዩ ዛሬ የደረሰበትም የምታዩትን ስኬትም ሆነ የፀባይ መሻሻል ላለመቀበል እንዲ ነበር blah blah ምንም ነበር በቃ ዛሬ ሌላ ሰው ነው ይሄን ተቀበሉ በተለይ ጥሩ ያልሆነ ማንነት ከነበረው ሰዎች እራሳቸውን እንዳይቀይሩ ወደኋላ አንጎትት

ማንም ይሁን ምንም ይሁን ጥፍቱ ሁለተኛ ዕድል ያስፈልገዋል የሰው ልጅ ሊረሳው የሚፈልገውን ትናት ባለማስታወስ እንተባበረው

✅ሁሌም ስለሰዎች ማወቅ የምትፈልጉትን ነገር ባለቤቱን መጠየቅ ልምድ አድርጉ እንዲሁም የሰማችሁትን ነገር ከባለቤቱ እርግጠኛ ለመሆን ጥረት አድርጉ ቅድሚያ በሰማችሁት ነገር ከመፍረድ ከመወሰን ከመቀየማቹ በፊት ነገሮች ሁሌም ሌላ ጎን አላቸው ኧ

✈️ እንማር

Показано 20 последних публикаций.