📚መንፈሳዊ መጽሐፍት📔


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ይህ ቻናል በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሰረቱ መንፈሳዊ መጽሐፍቶችን ፣ መጽሔቶችን ፣ ክርስቲያናዊ የድረ-ገጽ ጽሁፎችን በሰፊው ለአንባቢያን ለማድረስ ይጥራል። የመጽሐፍ ምረቃ ማስታወቂያ ፣ ሀሳብ እና አስተያየት ካሎት በ .... ላይ ያድርሱን።
Buy ads: https://telega.io/c/amharicspritualbooks

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅም ሆነ!

የጌታ ልደት ረቂቅ ነው። በፍጥረት ታሪክ ከሆኑ ክንውኖች አምላክ ሰው የሆነበት ክስተት እጅግ ድንቁ ነው። ይኽን ግዙፍ አጽናፍ የፈጠረ ከመታወቅ ያለፈው ምጡቁ፥ አምላክ በፈቃዱ ሰው ሆነ(ዮሐ 1፥14 ፣ ፊሊ 2)። ብርቱው አምላክ በፈጠው ደካማ ፍጥረት እጅ ለመሞት ፈቃደኛ ኾነ። በማንም ሊቀረብ የማይችል አምላክ በደካማይቱ ማህጸን ለመጸነስ በቃ። ይኽን እውነት እንድናውቅ ጸጋውን ያበዛልንን እግዚአብሔር እንዴት ልናመሰግን ይገባ ይኾን?

የኾነው ሆኖ አምላክ ሰው ስለሆነበት ረቂቅ ሚስጥር ለማውራት አይደለም መነሻዬ። ጌታ ኢየሱስ ከተወለደበት አበይት አላማ መካከል አንዱን እንድናነሳ ወድጃለሁ። ጌታ ብዙ ነገር ሆኖልናል ከዚህ ውስጥ ክብሩን በመተው ሰው የሆነበት እውነት አንዱ ነው(ዮሐ 1፥14፣ ፊል )። በአንድ ወቅት በአምላክ መኖር ማያምን የነበረው ባለአእምሮ የስነ ጽሁፍ ምሁሩ ሲ.ኤስ. ሌውስ "የሰው ልጆች የአምላክ ልጆች እንዲሆኑ ያስችል ዘንድ የአምላክ ልጅ የሰው ልጅ ኾነ።"* ማለቱ ይታወሳል። ወላጅ አልባ አልነበርንም አስቀድሞ የማን ልጆች እንደነበርን ይታወቃል።

ከክንዱ ማንም ከማያስመልጠን በኃያሉ አምላክ ቁጣ ስር ስለነበርን መጽሐፍ "ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን" ይለናል(ኤፌ 2፥3) ለዚህም ነው አሁን እንኳን በኢየሱስ በማያምን ላይ "የእግዚአብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም" የሚለን(ዮሐ 3፥36)። "የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ የተገለጡ ናቸው። ጽድቅን የማያደርግና ወንድሙን የማይወድ ከእግዚአብሔር አይደለም።"(1 ዮሐ 3፥10) እንደሚል ኃጢአትን እያደረግን እንደገዛ ፈቃዳችን እንመላለስ ስለነበር የጨካኙ ዲያብሎስ ልጅ ነበርን ማለት ይሆናል(ኤፌ 2፥1-5)። በግራም ነፈሰ በቀኝ አባታችን እግዚአብሔር አይደለም።

"የሰው ልጆች የእግዚአብሔር ልጆች እንዲሆኑ ያስችል ዘንድ የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ ሆነ!"፣ ጌታ ተወለደ ፣ የአለም መድኃኒት በበረት ግርግም ተወለደ፤ በዚህም ምክንያት በኢየሱስ አምነን የእግዚአብሔር ልጆች እንሆን ዘንድ ስልጣን ተሰጥቶናል። "የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለ ፍቅር እንደሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን።" 1 ዮሐ 3፥1

የጌታን ልደት ስናስብ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያደረገውን ድንቅ ነገር እያሰበን ይሆን። የጌታን ልደት ስናስብ መድኃኒቱን ባለማወቃቸው እየጠፉ ያሉ አእላፍ ሕዝብ በመጸለይ ይሁን።

መልካም በአል!
*“The Son of God became a man to enable men to become sons of God." -C.S Lewis

Amanuel A.
©መንፈሳዊ መጽሐፍት

3k 0 36 5 63


6.8k 0 55 20 50

Elias እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ።


እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ ወንድሜ፣ አሁንም መለገሶን አያቆሙ።


Yoft@he እግዚአብሔር አብዝቶ ያባርክህ! 👏🏻👏🏻👏🏻


መንፈሳዊ መጽሐፍት ቻናል ስም ትንሽም ቢሆን ተቆርሰናል። በጥንቷ ቱርክና ሰሜን አፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ላይ ከሆነው የተማርን ከሆነ እንዲህ ለወንጌል አስቸጋሪ የሆኑ ቤተ ክርስቲያንን ቸል ልንል አይገባም።


ለዳሎቻ ቤተ ክርስቲያን ድጋፍ እናድርግ!

ዳሎቻ ቃለ ሕይወት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በስልጤ ዞን ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እጅግ ረጅም አመታትን በብዙ መከራና ስደት የጌታ የኢየሱስን ወንጌል ስትሰብክ የቆየች ባለብዙ ታሪክ ቤተ ክርስቲያን ናት(ይህን ታሪኳን ለሌላ ጊዜ ላቆየው)። ታዲያ በብዙ መከራ የምትፈተነው ይህቺ ቤተ ክርስቲያን በወንጌል ምክንያት ከሚደርስባት መከራ በተጨማሪ እንደልቧ የአምልኮ ስፍራዋን መገንባት አለመቻሏ(እዚህ ላይ በገንዘብ እጦት መሆኑ ይታወቅ) እና የተስተካከለ የአምልኮ መሳሪያ አለመኖሩ ቤተ ክርስትያኒቱን እየናጣት ያለ ጉዳይ መሆኑን ከደብዳቤ መረዳት ይቻላል(ምስክርም መጥራት እንደምችል ላረጋግጥ እችላለሁ)።

ስለዚህ በተለያየ አይነት መንገድ ድጋፍ በማድረግ ማለትም ትርፍ የሙዚቃ መሳሪያዎችን በመለገስ፣ በገንዘብ፣ በጸሎት ፣ መልዕክቱን ለሌሎች በማጋራት ፣ ሙያዊያዊ ድጋፍ በማድረግ፣ ቦታው ድረስ በመሄድ ስልጠናዎችን በማዘጋጀት እንዲሁ በወንጌል ሥራ ልዩ ልዩ ድጋፍ በማድረግ እንዲሳተፉ በጌታ ፍቅር እናሳስባለን። ለተጨማሪ መረጃና ጥያቄ በደብዳቤው ላይ በተቀመጡ ስልኮች የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች ማግኘት ይችላሉ።

በባንክ የላካችሁ screenshot እያደረጋችሁ በግሩፓችን ብትልኩልን እዚህ የምንለቅ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን። ከቆይታዎች በኋላ በቤተ ክርቲያኒቱ ያሳለፈችውን ልብን ሰቅዞ የሚይዝ አሳዛኝ ታሪኮችንና ጥቂት ስለቤተ ክርስቲያኒቱ መረጃዎችን ይዤላችሁ እመጣለሁ። እስከዛ ግን ከአንድ ብር ጀምሮ ማደረግ ይምትችሉትን ያህል አድርጉ።

ማሳሰቢያ፡ በደብዳቤው ለዚሁ አላማ ብቻ ተብሎ ከተከፈተው አካውንት ውጪ ምንም አይነት መላላኪያ መንገድ እስከ ጊዜው የሌለ መሆኑን ማወቅ ያሻል። ለምታደርጉት ማንኛውም ድጋፍ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካቹሁ።

©መንፈሳዊ መጽሐፍት




tehadiso-1.PDF
2.2Мб
በኦርቶዶክስ መምህር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መታደስ ላይ የተጻፈች ጥሩ መጽሐፍ ናት!

📔ርዕስ፦ ተሐድሶ ማለት ምንድን ነው?
👤ጸሐፊ፦ ኣባ ብእሴሰላም ጓሌ
📑የገጽ ብዛት፦ 225
__
በተያያዘ ርዕስ፦
*የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ተሃድሶ(ቅጽ-1) በጸጋአብ በቀለ
*ደቂቀ እስጢፋኖስ "በሕግ አምላክ" በፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ
*የአቡነ እስጢፋኖስ የደሙ ድምጽ!
👆👆የሚፈልጉትን መጽሐፍ ይጫኑ።


በኦርቶዶክስ መምህር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መታደስ ላይ የተጻፈች ጥሩ መጽሐፍ ናት!

📔ርዕስ፦ ተሐድሶ ማለት ምንድን ነው?
👤ጸሐፊ፦ ኣባ ብእሴሰላም ጓሌ
📑የገጽ ብዛት፦ 225
__
በተያያዘ ርዕስ፦
*የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ተሃድሶ(ቅጽ-1) በጸጋአብ በቀለ
*ደቂቀ እስጢፋኖስ "በሕግ አምላክ" በፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ
*የአቡነ እስጢፋኖስ የደሙ ድምጽ!
👆👆የሚፈልጉትን መጽሐፍ ይጫኑ።


በእውነቱ ይገባሃልና!

መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።

(የዮሐንስ ራእይ 5:9-10)

https://t.me/+cSEr5ad0xoc3OWQ0


ብሉይ ኪዳን.zip
943.1Мб
አዲስ ኪዳን.zip
290.8Мб
የብሉይና የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ በድምጽ
___
መጽሐፍ ቅዱስ ለማግኘት፦
*የልጆች መጽሐፍ ቅዱስ ፓት አልክሳንደር እንደተረከው
*አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከማጥኛ ጋር
*ሕያው ቃል መጽሐፍ ቅዱስ

9.7k 0 113 17 80

ፍኖተ-5.pdf
1.7Мб
ፍኖተ-4.pdf
1.9Мб
ፍኖተ-3.pdf
2.5Мб
ፍኖተ-2.pdf
3.4Мб
ፍኖተ-1.pdf
1.5Мб
📔ርዕስ፦ፍኖተ መንግስት
👤ጸሐፊ፦ መርዓዊ ንጉሴ
📑የገጽ ብዛት፦ 464
___
የደራሲው ሌሎች ስራዎች፦
*የተራራው ትምህርት
`


በቅርቡ በመንፈሳዊ መጽሐፍት የሚለቀቅ

"ፍኖተ መንግስት" መርዓዊ ንጉሴ
___
የደራሲው ሌሎች ስራዎች፦
*የተራራው ትምህርት
`


የካታኮምቡ ሰማዕት.zip
44.3Мб
የካታኮምቡ ሰማዕት በትረካ መስማት ለምትፈልጉ! ተራኪው ግን አንደኛ ነው። ቆመን አጨብጭበናል።

መጽሐፉን በpdf ለምንትፈልጉ እዚህ ይጫኑ!

10.4k 0 127 17 69

Next week ሕትመቱ ይደርሳል። እና ሰኞ፣ እሮብ፣ አርብ፣ ቅዳሜና እሁድ ከሰዓት ከ6:30-7:40 ባለው ውስጥ ፒያሳ፣ ሜክሲኮና ሳርቤት (ETC) በቀረባቸው ቦታ እኔ ራሴ ለሚፈልጉ ሰዎች አቀብላቸዋለሁ። ያንን ሰዓትና ቀን የመረጥኩት class ስላለብኝ ነው...
እዚህ የሚኖር የቅርብ ሰው ካለህ እሰጥልሃለሁ። ወይም ሌላ መንገድ እንፈልጋለን።

(ቁጥር የምሰጠው ሲወጣ በቁጥሩ መሠርት አቀብላለሁ)

Price: 400ETB/5$

የሺህጥላ ይገዙ @homme45


ግብረ ሰዶማዊነት በምዕራቡ ዓለም እያስከተለ ያለው ዋጋ ቀላል አይደለም! የአለም መንግስታት እያስከተለየ ያለውን የማንነት ቀውስ ጆሮ ዳባ ብለው ሕጋዊ ከለላ እየሰጡት ይገኛል ይህ ብቻ አይደለም በቤተ ክርስቲያንም በአምላክ የተጠላውን ይህን እርኩሰት መለማመድ መጀምሯ ነገሩን እጅግ አስፈሪ ያደርገዋል። በግብረ ሰዶማዊነት ላይ ዶ/ር ግርማ በቀለ "ቤተ መቅድስ ሲረክስ፣ የዓለም ጠረን የበለጠ ይሸታል።" ርዕስ ያቀረቡትን ዘለግ ያለ ጽሁፍ እንዲህ አዘጋጅተናል። ከታች INSTAN VIEW የሚለውን በመጫን ያንብቡ!


በረከት ወይስ መርገምt-1.pdf
1.9Мб
በረከት ወይስ መርገም-2.pdf
2.1Мб
የጭንቀት ሕይወት ከመምራት የመገላገያው ዘዴ

📔ርዕስ፦በረከት ወይስ መርገም አንዱን ምረጥ!/Blessing or curse: You can choose!
👤ጸሐፊ፦ ዴሪክ ፕሪንስ
🗣ተርጓሚ፦ የማነህብርሃን እንዳለ
📑የገጽ ብዛት፦ 200
__
የደራሲው ሌሎች ስራዎች፟፦
*የእግዚአብሔር ማዳን ለተተውና ለተናቁ
*የጸሎት ተጋዳይ ምስጢራት
__


በቅርቡ..... የሚለቀቅ

"በረከት ወይስ መርገም አንዱን ምረጥ!" በዴሪክ ፕሪንስ

https://t.me/+cSEr5ad0xoc3OWQ0


ምን ላድርግ @AmharicSpritualBooks-2.pdf
2.3Мб
ምን ላድርግ @AmharicSpritualBooks-1.pdf
2.1Мб
📔ርዕስ፦ ምን ላድርግ?/What shall this man do?
👤ጸሐፊ፦ ዎችማን ኒ/Watchman nee
🗣 ትርጉም፦ደርበው አዱኛ እና ጳውሎስ ፈቃዱ
📑የገጽ ብዛት፦197
____

የደራሲው ሌሎች፦
*ከእምነት ወደ እምነት (ተርጓሚ ዘካርያስ ጥላሁን)
*ክርስትና እንዲህ ነው! / The Normal Christian Life
*ድል ነሺ ሕይወት (ተርጓሚ ነብዩ ኢሳይያስ)
* የተሸነፈ አለም(ተርጓሚ ጳውሎስ ፈቃዱ)
* የዘላለም ኪዳን(ተርጓሚ ጳውሎስ ፈቃዱ)
*መጻሕፍትን መርምሩ(ተርጓሚ በአይሸሹም መኮንን)
*የፍርድ መንፈስ(ተርጓሚዎች ጌዲዮን ኃይሉ እና ይድነቃቸው ወርቁ)
*እጅግ የታመነ ምስክር(ተርጓሚ ሙሉጌታ ደምሴ)
*ከክብር ወደ ክብር(ተርጓሚ ዘካሪያስ ጥላሁን)
👆👆የሚፈልጉትን መጽሐፍ በመንካት ያግኙ። ለተጨማሪ መጽሐፍት በዚህ ሊንክ ያቀላቀሉን። https://t.me/+cSEr5ad0xoc3OWQ0

Показано 20 последних публикаций.