Ashara Media - አሻራ ሚዲያ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Криптовалюты


ስልክ፥ +251984190114 / +251993111700

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Криптовалюты
Статистика
Фильтр публикаций




#ነበልባሎቹ_ቲሊሊ ‼

ዘንገና ዘንገና ብርጌድ አሁንም ጠላትን እየረፈረፈው ይገኛል።
ከረፋዱ 4:00 የጀመረዉ ዉጊያ ከቲሊሊ ከተማ ወጦ ወደ ሽንዲ ወንበርማ የተንቀሳቀሰውን የአራዊት ቡድን ወንጀላ ቀበሌ ላይ ዙሪያውን ከቦ ይቀጠቅጠዉ ሲቀጥል፤ ካምፕ የቀረዉንም በተመሳሳይ የእጅ በጅ ዉጊያ ተያይዞታል።

ዝርዝሩን እናደርሳለን ‼

ላናሸንፍ አልጀመርነዉም‼




ጎጃም አገው ምድር ክፍለ ጦር

ተቋማችን የአማራ ፋኖ በጎጃም ካሉት ጠንካራ ፣ የማይሰበሩ እና ተቀራራቢ አቅም ካላቸው ዘጠኙ ክፍለጦሮች ውስጥ በዘመን ተሻለ ሰብሳቢነት ፣ በኮለኔል አደመ ጦር አዛዥነት እና በጠንካራ ስራ አስፈፃሚ አባላት የሚመራው የጎጃም አገው ምድር ክፍለጦር አንዱ እና ዋናው ነው ። ይህ ክፍለ ጦር
ብዙ ቃላት ቢደረደሩ የማይገልፁት ፣ የነገረ አገው ሸንጎን እና የብአዴንን ጋብቻ ሰባብሮ የወጣ ፣ የሰማ ጥሩነህን ሴራ ወደ ስራ የቀየሩ አናብስቶች የተፈጠሩበት ፣መከራን አልፎ ነፃነት መኖሩን የተረዳ ፣የ ፋኖ ኤፍሬም አጥናፉ እና የፋኖ አዲሱ ቢተውን አላማ የተሸከመ ከዚህ ውጭ የማይሞቀው የማይበርደው ፣ ከጠላት ክላሽ ፣ስናይፐር ፣ መትረጊስ እና ዲሽቃ ሬዲዮ መገናኛ ፣ ጥሬ ብር መማረክ መታጠቅ እና እደገና ማርኮ ማስታጠቅ አዲስ የማይሆኑበት ፣ በየ ጊዜው እጅን በአፍ የሚያስጭኑ ድሎቹን ጠላቶቹ እስኪ መሠክሩ ድረስ እያስመዘገበ ያለ ፣ ከድሮን ጄት ፔንፔ እና መሠል ማሣሪያዎች ሲያስጮህ ቢከርምም መከረኛው ትምህርት ቤት ፣ ተራራ እና ባህር ዛፍ ከመቃጠል ውጭ በዘመን ተሻለ እና በኮለኔል አደመ የሚመራው የጎጃም አገው ምድር ክፍለ ጦር ፋኖ ዳንግላ ፣ አዲስ ቅዳም፣ ኮሶበር፣ ቲሊሊ፣ ሰከላ፣ ዱርቤቴ እና የመሣሠሉትን ከተሞች ዘና ብለው ገብተው ባንዳን እና የባንዳ ዘበኞችን አጫውተዋቸው ከመሠለስ የሚያድናቸው የብልግና መንደራዊ ሀይል የለም ።

ይሄ አካባቢ በታሪክ ሲታወስ ቢተወድድ አያሌው መኮነን፣ የብዕር አርበኛው አቤ ጉበኛ፣ ቢተወደድ መንገሻ ጀንበሬ፣ የቀኝ አዝማች ስሜነህ ደስታ ፣ የኛ አርያ ከሆኑት ውስጥም ፋኖ ኤፍሬም አጥፉ ፣ፋኖ አዲሱ ቢተው እና የመቶ አለቃ አሳየ የበቀሉበት ምድር ሰለሆነ ዛሬም ለዘር ምስክርነት የተፈጠሩት የጀግና ዘሮች እንደምድር አሽዋ አካባቢው ላይ በዝተው ወፈፌውን የአብይን ተላላኪ ባንዳ ቡዳ እንደበላው ማስለፍለፍ ከጀመሩ አመት አልፏቸዋል ። ዛሬ ላይ ከጠላት ማርከው እና እረሽነው እልፎች ባለ ትጥቅ ያደረጉ ተምሳሌቶቹም ጭምር ናቸው ። ይህ ክፍለ ጦር ዛሬ ግዙፍ ጦር ከመሆኑ በፊት አርበኛ ዘመነ ካሴ የዛሬ አመራሮቹን ማረሚያ ቤት ሁኖ ነበር በ 4 የ F 1 ቦንብ እና በ 20,000 ብር ሞራል ተስፈኞቹን ያደራጃቸው ። ጀግኖቹ አደራቸውን በሚገባ ተወጠው ዛሬ እልፎቹን አየማረኩ በአለም አደባባይ ሲያሳዩ ሲታይ ቀድሞ የሠራቸው መሪ ምን አይነት ህልመኛ መሪ እንደቀረፃቸው ለመገመት አያስቸግርም። ለዚህም መሪያቸን አርበኛ ዘመነ ካሴ ከልብ እናመሠግንሐለን ።

ከሰከላ እስከ ዳንግላ ፣ ከአቸፈር እስከ ኮሶበር ድረስ አካቶ የያዘው ክፍለ ጦሩ በዘመን ተሻለ እየተመራ ከሁሉም የአማራ ፋኖ በጎጃም ክፍለ ጦሮቹ በዘመቻ መቶ ተራራዎች 1ኛ መውጣቱን በአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል ሰብሳቢ እና ወታደረዊ አዛዢ ሺ አለቃ ዝናቡ ልንገረው ሲመሠከር ሰምተን እጅግ ተደሰተናል ።

በመጨረሻም ሁሉም የጎጃም አገው ምድር ክፍለ ጦር አመራሮች ፣ አባሎች እና ደጀኑ ህዝባችን ከሌሎች በየደረጃው ከሚገኙ የተቋሙ አመራሮች ጋር በአንድነት በመሆን ተቋማችን እና መሪዎቻችን በመጠበቅ ለተሻላ ወትሮ ዝግጁነት እንድትገኙ ወንድማዊ ምክሬን መስጠት እፈልጋለሁ ሲል የአማራ ፋኖ በጎጃም ም/ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ፋኖ ግሩም ምሳሌ ለአሻራ ገልጿል።

አዲስ ትውልድ ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ !
ፋኖ ግሩም ምሳሌ


ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም
  አሻራ ሚዲያ

አሻራ ሚዲያን ይወዳጁ
ዩቱዩብ
@asharaashara-124?si=iM_9tCLjVjVhx-0N' rel='nofollow'>https://youtube.com/@asharaashara-124?si=iM_9tCLjVjVhx-0N
ረምብል
https://rumble.com/v5etpbu-327231354.html
ቴሌግራም
  @asharadaily?si=OOO1RL2rDjF-2ngM' rel='nofollow'>https://youtube.com/@asharadaily?si=OOO1RL2rDjF-2ngM

https://t.me/ashara_media
ፌስቡክ

  https://t.me/ashara_media

https://www.facebook.com/profile.php?id=61554383356900
በተጨማሪም ማነኛውም አይነት መረጃ ለማድረስ
በቀጥታ የስልክ መስመር
👇👇👇👇
0993111700  ወይም
በቴሌግራም
👇👇👇👇
@asharamedia2
ማድረስ ይችላሉ።




የ ኮሌኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ ግዮን ሻለቃ በሰሜን ሜጫ ወረዳ ዳጊ ከተማ ጠላትን ረፈረው‼


በሰሜን ሜጫ ወረዳ ዳጊ ከተማ በተደረገው ከፍተኛ አውደ ዉጊያ ላይ የአንደኛ ክፍለ ጦር አካል የሆነው ኮሬኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ ግዮን ሻለቃ ዛሬ 26/2017 ዓ.ም ከጥዋቱ 1:30 ሰዓት _ 3:40 ሰዓት ከጠላት ጋር ትንቅንቅ አድርጎ ጠላትን መረፍረፍ ችሏል።

ጠላት የነበረባቸውን ሶስት ምሽጎች ማስለቀቅ የቻሉ ሲሆን ለቁጥር የሚታክት ሙትና ቁስለኛ ማድረግ መቻላቸውን የአማራ ፋኖ በጎጃም 1ኛ ክ/ጦር ኮሌኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ ህዝብ ግንኘነት ኃላፊ ፋኖ ጌታነህ ጎዴ ከአሻራ ሚዲያ ጋር በነበረው ቆይታ ተናግሯል ።

የአማራ ፋኖ በጎጃም ፩ኛ ክፍለ ጦር ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ ጊዮን ሻለቃ በቀን 26/02/2017 ዓ.ም ከጥዋቱ 1:30 እስከ 3:40 በፈጀ አዉደ ውጊያ በሜጫ ወረዳ ዳጊ ከተማ የተሳካ ኦፕሬሽን ተካሄደ።

በዚህም የምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ ጨፍጫፊ ሰራዊት በዳጊ ከተማ ደቡብ አቅጣጫ ግንባታ ከምትባል ታዳጊ ከተማ እና በዳጊ ከተማ ምዕራብ አቅጣጫ ሰርጃ ወንዝ ለማስፋት እንቅስቃሴ ቢጀምርም በነበልባሎቹ ጊዮን ሻለቃ አማካኝነት ተለብልቦ ያሰበው ሳይሳካ ሙትና ቁስለኛ ሆኖ ተመልሷል።

በዚህ የጠላት ኃይል 18 በላይ ሲደመሰስ የወገን ጦር ያለምንም ጉዳት ያሰበውን ኦፕሬሽን አሳክቶ ተመልሷል።
መረጃውን ለአሻራ ያደረሰው የአማራ ፋኖ በጎጃም ፩ ኛ ክ/ጦር ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ጌታነህ ጓዴ ነወ።

ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም
  አሻራ ሚዲያ

አሻራ ሚዲያን ይወዳጁ


ከአዴት _አይቫር_ ብር አዳማ _አበስከን ወይም ቋሪት ያለው መስመር በጥንቃቄ ይታይ ዘንድ

ቋሪት
ሰከላ
ይልማና ዴንሳ
ዋሸራ ይድረሳቼው

መረጃው ሸርርርርር

መናበብ ያስፈልጋል።
ዝርዝር አያስፈልግም።


ቲሊሊ‼️

የአማራ ፋኖ በጎጃም የዘንገና ብርጌድ ቲሊሊ ከተማን ተቆጣጠረ።


#ጠላት_እየተገረፈ_ነው‼️

የአማራ ፋኖ በጎጃም የራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም/5ኛ/ክ/ጦር በተለያዪ ግምባሮች ጠላት እያስጨነቀው ይገኛል።

1ኛ: ደጃች አሰቦ ቡሬ ዳሞት ብርጌድ፣ ወምበርማ ብርጌድ፣ጓጉሳ ብርጌድና ወርቅአባይ ብርጌድ በጥምረት ቡሬ ከተማ በመክበብ ጠላትን እየገረፉት ይገኛሉ

2ኛ.ገረመው ወንዳወክ ብርጌድና እና አረንዛው ዳሞት ብርጌድ ፍኖተሰላም ዙሪያ ፣ ጅጋ እና ሆዳንሽ ግምባር ጠላትን እያርበደበዱት ይገኛሉ

                  ክፋት ለማንም
                  በጎነት ለሁሉም!!
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!

    ©የአማራ ፋኖ በጎጃም 5ኛ ክ/ጦር ሚዲያ ባለሙያ ፋኖ ዮሴፍ ሀረገወይን


ሰበር

የግዳን ወረዳ ዋና ከተማ የሆነችውን ሙጃ ከተማን በዋርካዉ ምሬ ወዳጆ የሚመራዉ የ አማራ ፋኖ በወሎ ተቆጣጥሯል።

8k 0 4 9 147

ዝህብስት ት/ቤት ሲወድም ንፁሀንም ተጨፈጨፉ !

         ዛሬ በጥዋቱ አገዛዙ በጣለው ድሮን ዝህብስት የመጀመሪያ ደ/ት/ቤት ሲወድም በዙሪያው የነበሩ ንፁሀን አርሶ አደሮች ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ተጨፍጭፈዋል።

ጎጃም 😭😭

8k 0 1 15 97



ታዴ ማሩ ይባላል። በአማራ እንቅስቃሴ በብዙዎች ይታወቃል። የተዋጣለት ሰዓሊም ኢንጅነርም ነው። ነዋሪነቱ ኒዘርላንድስ ሲሆን ከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ካላቸው ከተለያዩ ሀገራት ወደ ኔዘርላንድ ከገቡ ሰዎች ውስጥ ተወዳድሮ top 5 ውስጥ መግባት ችሏል። 1ኛ ለመሆን ምርጫው ሲጀመር የኛን ርዳታ ይሻል።

ሙሉ መልዕክት ከታዴ እንደሚከተለው ቀርቧል።

ሰሞኑን ጌታ ፈቅዶ በኔዘርላንድ ውስጥ Emigrants with higher education background (ከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ካላቸው ከተለያዩ ሀገራት ወደ ኔዘርላንድ ከገቡ ሰዎች ውስጥ) ዘርፈ ብዙ በሆኑ የውድድር መመዘኛዎች ተወዳድሬ ከምርጥ 5ቱ ውስጥ ገብቻለሁ። ውድድሩ ውስጥ የገባሁት በቀድሞ አስተማሪዬ ጥቆማ ሲሆን እኔን ምርጥ 5 ውስጥ እንድገባ ያበቁኝ ነገሮች በዋነኝነት:-

*በተለያዩ የማህበረሰብ ስራዎች ተሳትፎዬ
*ደች ቋንቋ Advanced level በአጭር ጊዜ በመጨረስ (በ8 ወር ውስጥ C1 ደረጃ በመጨረስ። C1 በ European reference frame ዩኒቨርስቲ ድረስ መማርም እንዲሁም አስከ B1 ድረስ ቋንቋ ማስተማርም ይቻላል።)
*የ2ኛ ማስተርስ ትምህርቴን በጥሩ ውጤት በማጠናቀቄ እና በቀጣይ grant አግኝቼ ምርምር ላይ እየሰራሁ መሆኔ
*በጋዜጦች እና በኢንተርኔት መገናኛዎች ላይ በመውጣት ለሌሎች inspiration መሆን መቻሌ እንዲሁም
*ከቋንቋ አስተማሪዬ ጋር ሆኜ የጻፍኩት የልጆች መጽሐፍ ናቸው።

በዚህ መድረክ ከጋዜጠኞች ጋር በነበረኝ ቃለ ምልልስ በይበልጥ በአማራ ወገኔ ላይ እያደረሰ ያለውን ሁሉን አቀፍ ጥቃት ያሳወኩበት ነበር። በተጨማሪም በ2008 ዓ.ም ወያኔን ለመጣል በነበረው ትንቅንቅ እና ከጓደኞቼ ጋር ያሳለፍነውን አሰቃቂ ሁኔታ የገለጽኩበትም ነበር።

ከምርጥ አምስቱ 1ኛ የወጣውን ለመለየት ከህዳር መጨረሻ ጀምሮ የOnline ምርጫ ይካሄዳል። በመጨረሻም ታህሳስ ወር አጋማሽ ላይ ሚንስትሮችን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት እና በግል ደረጃ የተጋበዙ ሰዎች በተገኙበት አንደኛ የሚወጣው ተወዳዳሪ ይታወቃል።

ለዚህም የonline ምርጫው ሲጀመር በምርጫው እንድትሳተፉ እጠይቃችኋለሁ።


#ሜጫ

ጠላት በማታለልም በማስገደድም የአማራን ህዝብ እንዲጨፈጭፉለት ካሰማራቸው የሰራዊት አባላት መካከል በርካቶች እየተቀላቀሉን ነው።

ዛሬ ብቻ ሜጫ ላይ አንድ ጋንታ የመከላከያ ኃይል ከነ ሙሉ ትጥቋ የወገንን ኃይል ተቀላቅላለች። የጠላትን ካምፕ ለቀው ለሚመጡ ወንድሞች ደረጃዉን የጠበቀ አቀባበል ይደረጋል፤ እየተደረገም ነው።

በነገራችን ላይ አማርኛ ተናጋሪ ያልሆኑ ወንድሞቻችንን ለመቀበል ያመች ዘንድ  ሁሉም ክፍለ ጦሮቻቻን አስተርጓሚ እንዲያዘጋጁ መመሪያ ተሰጥቷል።

ስቦ መምታት እና ስቦ ማስከዳት ይቀጥላል።

©አስረስ ማረ ዳምጤ


ነገሩ እንዲህ ነው👇

የመከጡሪ ከተማ ከንቲባ በአካባቢው ያሉ የፋኖ ሃይሎችን ብዛትና አሰላለፍ ጥናት ካደረገ በኋላ ተጨማሪ የጥላት ኃይል ወደቦታው እንዲመጣ በማድረግ የፋኖ ኃይሎች ላይ ጥቃት ሊያደርስ ተንቀሳቀሰ ።

ከንቲባው በሞተር ከአንድ ትራፊክ ፖሊስ ጋር በመሆን መከላከያን መንገድ በመምራት ላይ ነው ። ሰተት ብለው መከጡሪ ዙሪያ ቄራ እና ደብረ ፅጌ የተባ ቦታ ገቡ ። ታዲያ በዚህ ሰአት በቦታው የነበረው የፋኖ ኃይል አስቀድመው መረጃው ደርሷቸው ነበርና ቦታ ቦታቸውን ይዘው ሲጠብቁት ቆዩ ። ከዚያማ አስቀድሞ መንገድ ይመራ የነበረ ከንቲባውን እና የትራፊክ ፖሊሶን ከአፈር ቀላቀሉት። ቀጥሎም ምድር ቁና ሆነች።(ጠብበች) ቀየው በየት በኩል እንደሚተኮስ በማይታወቅ የጥይት ሀሩር ተግተልትሎ የገባውን መከላከያ ሰራዊት ተብየ ሲያጋድሙት ቆይተው የውጊያ ግምባሩ እየሰፋ በመሄዱ የፋኖ ኃይሎች አሰላለፋቸውን በመቀያየር አስቀድመው ልምምድ ያደረጉበት ቦታ በመሆኑ ነገሩን ቀላል አድርጎላቸው ነበርና በራሳቸው እቅድ ጠላትን ወደ መግደያ ወረዳ ስበው በማስገባት ይገርፉት ይዘዋል ፣ከሚወድቀው ሰራዊት እየተነጠለ እግሬ አውጭኝ ብሎ ሚፈረጥጠውን እናጅሬ እግር በእግር እየተከተሉ ይለቅሙት ይዘዋል እግሩ ወዳመራው ሚሮጠው አሸባሪ አርሶ አደር ቤት በመግባት ለመደበቅ ቢሞክርም ንስሮቹ ከገባበት ተከትለው በመያዝ አሻፈረኝ ያለውን እርምጃ ሲወስዱበት፣እጅ የሰጠውን አንጠልጥለው ወስደዋል ። የፋኖ ኃይሎች በዚህ ውጊያ በጣም እረክተዋል። ውጊያው ቀጥሎ ውሎ አድስ የገባውና በቦታው የነበረ ጥምር ጦር ጭምር የአሞራ ሲሳይ ሆነ። የውጊያው ድምር ውጤት ሲታይ የመከጡሪ ከተማ ከንቲባን ጨምሮ 106 የአገዛዙ ጥምር ጦር  ከአፈር የተቀላቀለበት እለት ነው።

የፋኖ ኃይሎችም ስራቸውን ሰርተው ሲጨርሱ ወደ ገዥ ቦታቸው በንፍስ ፍጥነት ከትመው ከድል በኃላ ሲጨፍሩ አምሽተዋል ።

NB- የተገደለው ከንቲባ ነባሩ ከንቲባ ስልጣኑን በፍቃዱ ሲለቅ አድስ የተሾመና ልቡ ያበጠበት ባንዳ ነበር።

ይህ እርምጃ ከተወሰደ በኋላ አካባቢው ላይ አንድም ምሊሻ የለም ።
👉ከወገን በኩል 3ፋኖ ሲሰዋ ቀላል ቁስለኛ ደግሞ 7 ናቸው።

ከተመልካች


ጎንደር‼️

"ጭልጋ ሰራባ የአምሓሮች ኦሽዊትዝ የመከራ ከበባዊ ዐጥር ሆኗል'" የድረሱልን ድምጽ ተሰምቷል። ከ200 በላይ ንፁሃን አስከፊ ሁኔታ ላይ ናቸው።

ከምዕራብ ጎንደር ዞን ልዩ ልዩ ወረዳ እና ቀበሌዎች በፋሽስቱ መከላከያ ታግተው 
በማዕከላዊ ጎንደር ጭልጋ ወረዳ ሰራባ መከላከያ ካምፕ የታሰሩ ከ 200 በላይ የሚሆኑ አምሓራዎች ሰቆቃዊ ድብደባ እና አሰቃቂ ግፍ እየተፈፀመባቸው መሆኑ ተሰምቷል።
አብዛኛዎቹ የአካል ጉዳተኛ ሲሆኑ፣ በሞት እና ህይወት መካከል የሚገኙም አሉ ተብሏል።

ከምዕራብ ጎንደር ወረዳዎች እና ከተሞች ታዋቂ እና ተሰሚነት ያላቸውን አምሓሮች በመምረጥ አግተው ወደ ሰራባ ወታደራዊ ኮንሰንትሬሽች ካምፕ ካስገቡ በኋላ፣ ርሃብ
ግርፋት እና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት የሚያስከትሉ ግፎች እየተፈፀመባቸው እንደሆነ የውስጥ ምንጫችን ለሞዐ ሚዲያ አድርሶናል።

በነዚህ ንፁሃን አምሓሮች ላይ የሚፈፀመው ግፍ ዋና መሪ የፋሽስታዊ አገዛዙ መሳሪያ መከላከያ ቢሆንም የቅማንት ማህበረሰብ ወካይ ያልሆኑ የአካባቢው የቅማንት ተወላጅ ሚሊሻዎች… የአምሓሮችን መከራ እና ግፍ ፈፃሚ ሆነው ታይተዋል ተብሏል።

እንደ ምንጫችን መረጃ ከሆነ፣ እነዚህ ከጎንደር ልዩ ልዩ ወረዳዎች ታግተው የተሰበሰቡ ሲቢል ነዋሪዎች ከወራት በፊት ወደ ጭልጋ ሰራባ ወታደራዊ ካምፕ የገቡ ሲሆን… አብዛኛዎቹ አካል ጉዳተኛ ተደርገዋል ብሏል።


በሰሜን  ሰዋ ዞን ደብረ ብርሃን  ከተማ ነዋሪ የሆነ ግለሰብ አቢወት የሚባል  ባንዳ ቀድሞ የፋኖ አስልጣኝ ነኝ የሚል አሁን ላይ የፋኖ ቤተሰብ እና ደጋፊ ናቸዉ እያለ እያሳፈሰ እና እያስረሸነ ነው እና ማንም የፋኖ አባላት የስልክ ግንኙነት  እንዳያደርጉ መልዕክት ይድረስ በቀን 25/02/2017አ/ም ብቻ ከአንድ ግለሠብ ቤት ሁለት ሚሊየን አዘርፏል።


ምሽጉን አዲስ ቅዳም ከተማ አድጓሚ ተራራ ያደረገዉ እና በእነ ታገል እጅጉ የሚመራዉ ፀረ አማራዉ የብልፅግና ቡድን ዛሬም በቀን 25/02/2017 ዓ/ም የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ፋኖዎችን ቅጥቀጣ ለማምለጥ ወደ ሁዋላ በመፈርጠጥ ላይ እያለ  በአዲስ ቅዳም ክ/ከተማ ስር በሚገኝ ጉላ ቀበሌ ዉስጥ  ጤፍ በማጨድ ላይ ያለን አቶ "የኔዉ ወርቁ ጋሸ" የሚባል አርሶ አደር ማሳዉ ድረስ በመሄድ በጥይት ደብድበዉ ገድለዉታል። መረጃውን ያደረሰን ተሻገር አደመ የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ህ/ግንኙነት ነው።


የአማራ ፋኖ በጎጃም የራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም/5ኛ/ክ/ጦር ከሚመራቸው ብርጌዶች ውስጥ የሆነው ወምበርማ ብርጌድ አንዱ ነው። ከዚህ በፊት 5/ኛ ክፍለ ጦር ከተለያዩ እምነትእና ቋንቋወች ከሚናገሩ ፋኖ ጋር ውይይት ማረጉ ይታወቃል።

ትናንት 24/2/2017ዓም በወምበርማ ብርጌድ ጂዋቢ ቀበሌ በመገኘት ከሙስሊም እምነት ተከታይ ፋኖዎች እና ከትላልቅ የእምነቱ አባቶች ጋር ውይይት አድርገናል።
የውይይት ነጥቦችም፦

1ኛ, የአማራ ፋኖ አሁናዊ ቁመና በተመለከተ
2ኛ, ወራሪው የብልፅግና ስርአት አማራ የሆነውን ሁሉ የሚገድል መሆኑን።ለአብነትም በወለጋ ሰማይ ስር ወላሂ እኔ አማራ አልሆንም ብላ የተገደለች በምነቷ ሳይሆን በማንነቷ መሆኑን።

3ኛ የሙስሊም ማህበረሰብ ከሌሎች እምነት ተከታይ የአማራ ፋኖወች ጋር ጠላትን መፋለም እንዳለባቸው ተወያይተን መግባባት ላይ በመድረስ እኛም ጠላትን ለመምታት ዝግጁ ነን ሲሉ የጂዋቢ ፋኖ ሰብሳቢ ፋኖ ዳወድ ሞላ  ተናግረዋል።
                 
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!
የአማራ ፋኖ በጎጃም 5ኛ ክ/ጦር
ሚዲያ ባለሙያ ፋኖ ዮሴፍ ሀረገወይን


ጥንቃቄ‼️
አሁናዊ መረጃ
የጠላት ጦር በአዴት አድርጎ ወደ ቋሪት ለመግባት እንቅስቃሴ እያደረገ ነው።
የሚል መረጃ ደርሶኛል✊

Показано 20 последних публикаций.