AWACH SACCOS Ltd.


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Экономика


ኅብረት ሥራ ማህበራችን የሚያከናውናቸው ተግባራት
የቁጠባ እና የብድር አገልግሎት
አነስተኛ የብድር መድህን አገልግሎት
የትምህርት ስልጠና እና የማማከር አገልግሎት
+251-11-557-97-98
+251-11-557-88-89
+251-11-557-98-99
+251-11-868-47-44
saccawach@gmail.com
https://www.facebook.com/AWACHSACCOS
@awachsaccos

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Экономика
Статистика
Фильтр публикаций








አዋጭ በንግድ ዘርፍ ለተሰማሩ አባላት በባለሞያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡

አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማኅበር ከታህሳስ 22-28/2017 ዓ.ም ለአባላት የገበያ ትስስር ለመፍጠር የገና በዓል ባዛር እያዘጋጀ እንደሚገኝ የሚታወቅ ነው፡፡ በመሆኑም  የሚያዘጋጀውን የገና በዓል በማስመልከት ለነጋዴ አባላቱ በደንበኛ አያያዝ ፣ በሂሳብ አመዘጋገብ  እና በንብረት አያያዝ  ላይ በባለሞያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡ ስልጠናውም በሁለት ፈረቃ ለ60 አባላት የተሰጠ ሲሆን አባላቱም በቂ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልፀው ሌሎች አባላት በዕለቱ በቦታው በመገኘት የገበያው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አስተላፈዋል፡፡








የኅብረት ሥራ ማኅበራችን የአባላትን መረጃ ወቅታዊ መሆኑን ለማረጋገጥ የሁሉንም አባላት ቋሚ መዛግብት በማዘመን ሂደት ላይ እንገኛለን ይህንኑ ተግባር ለማከናወን ይረዳን ዘንድ ከ ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ አቅራቢያችሁ በሚገኝ የኅብረት ሥራ ማኅበራችን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የቁጠባ ደብተር፣መታወቂያ እና አንድ ፎቶ ግራፍ ይዛችሁ በመቅረብ የተዘጋጀውን ቅጽ በመሙላት መረጃችሁን እንድታዘምኑ እና እርስዎን በተሻለ ሁኔታ እንድናገለግልዎ ያግዙን!!!

ለበለጠ መረጃ 6326
joinus.awachsacco.com






አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር በቅርቡ የተገበረውን ሪፎርም አስመልክቶ ከአጠቃላይ ሰራተኞቹ ጋር ዛሬ ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም በግራንድ ኤሊያና ሆቴል ውይይት አድርጓል።

ትግበራ ላይ የዋለው ሪፎርምን እና አንዳንድ በተቋሙ ውስጥ የተደረጉ የአሰራር ለውጦችን አስፈላጊነት ያስረዱት የኅብረት ስራ ማህበሩ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘሪሁን ሸለመ አዋጭ ከትንሽ ተነስቶ አሁን ላይ ከ380 በላይ ለሚሆኑ ሰራተኞች የስራ እድል መፍጠር በመቻሉ ደስተኛ ነኝ ብለዋል።
አክለውም ሰራተኞች በተመደቡበት የስራ መስክ የአገልጋይነት መንፈሳቸውን ይበልጥ በማዳበር በቅንነት እና በታማኝነት አባላትን እንዲያገለግሉ ጠይቀዋል።

የአዋጭ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ መስፍን ገ/ስላሴ ኅብረት ስራ የድህነት ማስታመሚያ ሳይሆን የሃብት ማፍሪያ መሆኑን አዋጭ በአባላቶቹ አረጋግጧል ያሉ ሲሆን ሰራተኞቹንም ከዚህ በላይ ጠንክራችሁ በመስራት የላቀ ውጤት ማስመዝገብ ትችላላችሁ በማለት አበረታተዋል።
የአዋጭ ሰራተኞች በበኩላቸው በተደረገው ሪፎርም መደሰታቸውን ገልፀዋል።











Показано 16 последних публикаций.