Bahir Dar WikiLeaks - BW


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


ባሕር ዳር ዊክሊክስ - የአማራውያን የወል ድምፅ!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


የአረጋ ከበደ ዲስኩር ከአፉ ሳይርቅ ውሃ በላው

ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ጆሮችን በደንብ እያዳመጠልን አይደለም። ለምሳሌ በይህ ሰሞን እነ ቀንድ አውጣ አረጋ ከበደ "ፋኖን በ3 ወር ውስጥ እንደመስሰዋለን" ነው ያለው ወይስ "ፋኖ በ3 ወር ውስጥ ጠራርጎ ያጠፋናል?" ነው ያለው።

አራዊት ሰራዊቱ ሰሞኑን በየአቅጣጫው የወዳደቁ ጓዶቻቸውን እንኳን ሳያነሱ፣ ካምፓቸውንም ሳይቀር እየለቀቁ ሲፈረጥጡ ስንሰማ ጊዜ… ቸገረን እኮ

ስለመጣችሁብን ሳይሆን፣ መገስገስ ስላለብን በመንገዳችን ላይ የቆመን አራዊት ሰራዊት እንዲሁ ደፍጥ[ጠ]ነው እናልፋለን። አይዟችሁ 😁


የቅድመ ጥንቃቄ መረጃ

በሰሜን ጎጃም ሙሉውን በሚባል ደረጃ የሚደረግ የድሮን ቅኝት እንዳለ የባህርዳር ዊክሊክስ ምንጮች ገልፀዋል። በተመሳሳይም በቋሪት ቆላማ ቦታዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የሚደረግ ቅኝትም እንደታሰበ ለማወቅ ተችሏል።

ቅኝቱ በጨቅላው የወረቀት ድሮን ይሆን ይሆንን? ልክ ደብዛው ጠፍቶ እንደቀረው የወረሙማ ነዳጅ ወይም ሳተላይት 😁


የዳበረ የቀደዳ ልምድ በብልፅግናው ምናባዊ ዓለም

"እንኳን ደስ አላችሁ፤ ኢትዮጵያ በሶማሌ ክልል ከፍተኛ የነዳጅ ክምችት በማግኘቷ ምክንያት፣ በቅርብ ኢትዮጵያ ለዓለም ገበያ ነዳጅ ታቀርባለች።"

ለጨቅላው አብይ አህመድ የሽንት ጨርቅ ከውጭ የምታስገባው አገር "ዛሬ ደግሞ ድሮን በሃገር ውስጥ ማምረት በመጀመሯ" የብልጽግናን መንጋ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን¡


ቃል ለምድር ቃል ለወደብ ይሁንብን… ጭብጦዋ አብይ አህመድ ሱሪ ኖሯት ኤርትራ ላይ አንዲት ጥይት እንዲያው አንዲት ፊኛም ትሁን ከተኮሰች እስከወዲያኛው ከሚዲያ እንጠፋላቸዋለን። የውስጥ ጉልቤ መሳዩዓ ወረምቲቲ ይህን ካደረገች ቃላችንን እንጠብቅላቸዋል። ግን እናውቅሻለን ጭራሽን ቆልፈሽ ከሶስት ቀን በኋላ ቁጭ ትያታለሽ። የናትናኤል መኮንን ምላስ እግረኛ ጦር አይሆን 😁


"ጨው ውሃ ልትቀዳ ወንዝ ዳር ወርዳ ቀልጣ ቀረች"

ዛዲሳ? እየሆነ ያለው እንዲያ ነው። የጨቅላዋ አብይ አህመድ ጭብጦ አገዛዝ እንደልማዷ ሰሞኑንም አዲስ እቅድ ብላ ፉን ፉን ምንቅር ምንቅር እያለች ነው። ይህኛው እቅድ ለስንተኛ ጊዜ የወጣ እንደሆነ ቁጥሩን እንኳን እኛ ወርቅነህ ገበየሁም አይጠራውም 😁

የሆነው ሆኖ የጨቅላዋ አብይ አህመድ አገዛዝ አቅም ያላት መስላ ለመታየት ከኤርትራ ጋር ጦርነት ለመግጠም እየተዘጋጀሁ ነኝ ትላለች፤ በጎንም ሁሉንም እዝ አስገብታ "ፋኖን በ3 ወራት ልደመስስ ነው" የሚል የህልም ዓለም ኑዛዜም ታሰማለች።

በነገራችን ላይ ይህ አካሄድ ውጥንቅጥ የበዛበት ይምሰል እንጅ አንድ የሚሊቴሪ ስትራቴጂ ነው። The Art of War በሚል መፅሐፍ ላይ የተቀመጠን ግሩም አባባል እዚህ ጋር ብናነሳ የጨቅላዋን ጭብጦ አካሄድ በደንብ ያስረዳልናል። እንዲህ ይላል
"Appear weak when you are strong, and strong when you are weak"

የዚህ አባባል የአማርኛ ትርጉም "ጥሩ ቁመና ላይ ባለህ ጊዜ፣ ደካማ ምሰል። አቅምህ በደከመና ጉልበትህ በደቀቀ ጊዜ ደግሞ

▪︎በኤርትራ ላይ የምላስ ጦር አዝምት
▪︎በዮክሬን ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ ያሉትን አሜሪካንንና የአውሮፓ አገራትን ሁላ አስጠንቅቅ
▪︎በሁለት ዓመታት ውስጥ ቅልጥምህን አፍስሶ አዲስ ሰልጣኝ ያስናፈቀህን ኃይል ለመደምሰስ በሚል ለ918ኛ ጊዜ አዲስ እቅድ አውጣ።

እናም የጨቅላዋ አብይ አህመድ አገዛዝ የሰሞኑን ፉን ፉን ማለት ለእኛ ለምኒልክ የልጅ ልጆችና የአሳምነው የበኩል ልጆች ግልፅ ናት፤ የጦዘች ጥልቸል፣ የተኛን አንበሳ የዘረረች ይመስላታል። ለማያውቅሽ ታጠኝ።

እንግዲህ ይህች ጭብጦ አገዛዝ ይህንን እቅድ አዲስ የለብ ለብ ተመራቂ አራዊት ሰራዊቶች ከፊት አሰልፋ ቀጠና ለማስፋት በሚል እንቅስቃሴ ጀምራለች። ነገር ግን ውሃ ለመቅዳት ወንዝ እንደወረደችው ጨው ሟሙታና ቀልጣ እየቀረች ለመሆኑ የሰሞኑን የአውደ ውጊያ መረጃዎች ያስረዳሉ።

በነገራችን መጨረሻ አገዛዙ የ3 ወር እቅድ ሲል ክረምቱን ከመፍራት በዘለለ፣ በሁሉም ቀጠና ፋኖዎቻችን አስደማሚ ሰራዊት እያደራጁ በመሆኑ እነኝህን እቅዶቻችንንም ለማደናቀፍ ያለመ ነው። የሆነው ሆኖ ስለመጡብን ብቻም ሳይሆን መገስገስ ስላለብን ይህን የጨው ሰራዊት እቅልጠን እናሟሟዋለን። ህዝባችን መረጃ ከማቀበል ጀምሮ ሁለንተናዊ እገዛውን ለፋኖዎቻችን እንዲያደርግ በዚሁ አጋጣሚ መልዕክታችንን ለማስተላለፍ እንወዳለን።

ደና ውለሽ ነው ወረሙማ 😁 ጭብጦ ሁላ!


የአማራ ፋኖ በጎጃም የ24 ስዓት አበይት ሁነቶች

ሀ. አውደ ውጊያ

1. 3ኛ ጎጃም አገው ምድር ክፍለጦር የአቤ ጉበኛ ብርጌድና ቢትወደድ አያሌው መኮንን ብርጌድ ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ውለዋል።

የአብይ አህመድ አሸባሪ ሃይል ከሊበን፣ቁንዝላና ዱርቤቴ ተወጣጦ ወደ ዝብህስት ህዝብን ለመጨፍጨፍ ለመግደል ና ለመዝረፍ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ጀግኖች አቸፈሬዎች ደግሞ ወደ ቀደምት ላሊበላ / ዲላሞ / በመሄድ የጠላትን ምሽግ በመስበር ከተመዋን መቆጣጠር ችለዋል። በዚህ ውጊያም 2 ብሬን የነፍስ ወከፍ መሳሪያ እና በርካታ ሰራዊት መማረክ ተችሏል።

2. 1ኛ ክፍለጦር ለተከታታይ 4 ቀናት ጠላትን ሲቀጠቅጠው ሰንብቷል።

ባህርዳር ብርጌድ እና የጣናው መብረቅ ብርጌድ በዛሬው እለትም ወደ ደና ማርያም / ጭንባ አካባቢ / የተንቀሳቀሰን ጣላት አይቀጡ ቅጣት ቀጠውታል። ከፍተኛ የሆነ ኃይል ሲመታበት ቁስለኛውን ሰብስቦ እሬሳውንተሸክሞ ወደ መጣበት ተመልሷል።

3.ተፈራ ዳምጤ 2ኛ ክፍለጦር ደጋዳሞት ብርጌድ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ቀጦታል።

በከተማው ዙሪያ ያለን ወጣት እያፈነ እወስዳለሁ ብሎ የተንበሳቀሰን የአፉኝ ሰራዊት በገባበት ገብተው ሲያሯሩጡት ውለዋል።

4. ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለጦር ቀስተ ደመና ብርጌድ

ወደ ጎፍጭማ አወጣለሁ ብሎ የተንቀሳቀስን ጠላት የቀስተደመና ብርጌድ ፋኖዎች መገንጠያ የሚባል ቦታ ላይ በመድፈጥ በአብይ አህመድ አሸባሪ ሃይል ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አድርሰውበታል። ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ጠላትን እረፍት እየነሱት ይገኛሉ። ከዚህ ጋር ተያይዞ በደብረኤልያስ ከተማ ሕዝብ በእድር 30 የሚኒሻ ሰልጣኝ ካላመጣችሁ እንገላችኋለን ፣እንረሽናለን፣ ከዚህ አትቀመጧትም እያለ ህዝብን እያሸበረ መሆኑን አረጋግጠናል።

5. 9ኛ ሳሙኤል አወቀ ክፍለጦር አባይ ሸለቆ ብርጌድ ጀብድ ፈፅሟል።

ከጉንደወይን ወደ አርብ ገብያ ለመሄድ የተንቀሳቀሰን ጠላት ሲቀጠቅጡት ውለዋል። ጠላትም የፋኖን ብትር መቋቋም ሲያቅተው ወደ ጉደወይን ሬሳውንና ቁስለኛውን ይዞ ተመልሷል ።

ለ. የካራማራ ድል
ጀግኖች ለሀገራቸው የከፈሉትን ዋጋ ትኩረት መስጠት እንደማገባ ተገለፀ።

በካራማራ ውጊያ ብዙዎች የሀገራቸውን ልዑአለዊነት እና ዳርድንበር አላስደፍርም ብለው አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍሰዋል። ከነዚህ መካከልም ኮረኔል ታደሰ ሙሉነህ የሚጠቀሱ ናቸው። ኮረኔሉ ሚግ አብራሪ የነበረ የአየር ጥቃትን በብቃት የመከተና በወቅቱም የወርቅ ሜዳሊያ የተሸለመ ጀግና ነው።
ዛሬም የሱን መንፈስ የተላበሱ የሜጫ አናብስቶች የሱን ፈለግ ተከትለው በስሙ ብርጌድ ሰይመው ህዝብን ሊያጠፋ ፣ሀገርን ሊቆርስ የመጣን ጠላት እየረፈረፉት ይገኛሉ።
እንኳን ለካራማራ ድል አደረሳችሁ!!!

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
/የአማራ ፋኖ በጎጃም!/
የካቲት 26/2017 ዓ.ም

© የአማራ ፋኖ በጎጃም


ወረታ ዙሪያን ጨምሮ በፎገራ ወረዳ አራዊት ሰራዊቱ እንቅጥቅጥ እየዘፈነ ይገኛል። በአካባቢው ካለ የወገን ኃይል ተጨማሪ አራዊት ሰራዊት እንቅስቃሴ እንዳያደርግ ማድረግ የሚጠበቅ ነው። እፍን!


የቅድመ ጥንቃቄ መረጃ - #አዛምቱት

በደቡብ ጎንደር ጋይንት ቀጠና፣ በላስታ ቡግና ቀጠና እና በምዕራብ ጎጃም ብራቃት እና ምስራቅ ጎጃም ሞጣ (ወይን ውሃ) አካባቢዎች የድሮን ቅኝቶች እንዲደረጉ ታዟል። የአካባቢው ፋኖዎቻችን ከዚህም ዘርዘር ያለ መረጃን እኛ ጋር ማግኘት ትችላላችሁ።


የኢቢሲ ዜና ምን አለ… "በዮክሬን ቀውስ ውስጥ ተሳትፎ እያደረጉ ያሉ አካላት (አሜሪካና አውሮፓን መሆኑ ነው) ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ አስጠነቀቁ" ይላል። ጉድ ነው ዘንድሮ! አሁን እችን ጭብጦ ጨቅላ እንኳን አሜሪካና አውሮፓ ይቅር ዝናሽ ታያቸው ትሰማታላች?

ደግሞ እኮ "ኢትዮጵያ በአውሮፓ ውስጥ ያሉ ለውጦች በጥንቃቄ እየተመለከተችም ነው ብለዋል" ይላል። ተከታትለህስ?

ጥንቸል ሰክራ እራሷን ስታ ስትነሳ በሩቅ አንበሳ ወድቆ ታያለች። ከዛ ምን አለች… "እኔ እኮ ስሰክር ማደርገውን አላውቅም፤ ዘረርኩት?" አለች አሉ።

23.9k 0 40 34 422

አንዳንዱ አቃቂራም ግርርርርም ይለናል። አንድ ወሳኝ መረጃ አጋርተን፣ "አዛምቱት" ስንል ከማዛመት ይልቅ አቃቂር ለማውጣት ምላሱን ያሾላል። አዛምቱት የምንለው ደውለን ወይም መልዕክት አስቀምጠን በቀጥታ ፋኖዎቻችንን ማግኘት ሳንችል ቀርተን ወይም ደግሞ ማጋራቱ ሚዛን የሚደፋ መሆኑን አጢነን የሚለቀቅ ነው።

ለምሳሌ የተመስገን ጥሩነህን የአንድ ፋብሪካ ጉብኝት መረጃ ፖስት ከማድረጋችን በፊት መረጃውን ለፋኖዎቻችን ለማድረስ ያደረግነውን ጥረት በዚህ መመልከት ይቻላል። እና ከቻልክ አግዝ ካልቻልክ ግን የአዞ አፍክን አትክፈትብን፤ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሆነህ በጥቁርና ህፀፅ ፍለጋ የምትዳክር ጨለምተኛ አትሁን።

23k 0 7 5 240

ሰሊጥ የጫኑትን መኪኖች የአገዛዙ ኃይሎች አቃጠሏቸው ወይም እገሌ አቃጠላቸው የሚለውን ክርክር ለጊዜው እንተወውና…

ጋሳይ ላይ በኮሎኔል ጀዋር ጦር ከተደፈሩ 69 ተማሪዎች በላይ ወይም እስቴ ወይም አማሪት በድሮን ካለቁ ወገኖቹ በላይ "ሰሊጥ" ሲባል ከየጉድጓዳቸው እየዘለሉ የሚወጡትን አይጠመጎጦችን ስም ዘርዝር።

የጃዊም ሆነ የሁመራ ሰሊጥ (ብቻ ድንቡሎ ሰሊጥ) ከአማራ ወገኑ ለሚበልጥበት ደቂቅ ፍጡር ሁላ ከፊደላቱ "ሰ"ን አስቀርተንለት ቀሪውን ብንሰጠውስ?


የእነ ተመስገንና አረጋ ከበደ ሩጫ

ተመስገን ጥሩነህ በባህርዳር ከተማ ይባብ አካባቢ ያለን የብረታብረት ፋብሪካ ለመጎብኘት እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን ገልፀን መረጃ አውጥተን ነበር (መረጃውን ፌስቡክ አጥፍቶብናል፤ ቴሌግራም ላይ ግን አለ)።

ታዲያ ይህ መረጃ በብርሃን ፍጥነት ለባለቁንዳላዎቹ ተመስገን ጥሩነህና አረጋ ከበደ በመድረሱ ጉብኝት አቋርጠው ሱሪያቸውን ለመሮጥ ተገደዋል። መረጃውን ለሞርተር ጥቃት እንዲመች አድርገን ያወጣነው በመሆኑ "ተመስገን ኧረ እናቴ ጥሪኝ" እያለ ቢሮጥ አይገርምም።

እኛን ዊክሊክሶችን ብአዴናውያን ለምን እንዲህ አንደምትፈሩን አይገባንም እኮ - ቢበዛ ብናስነድላችሁ ነው 😊


መረጃ

የጨቅላው አብይ አህመድ ቡችላ የሆነው ተመስገን ጥሩነህ በባህርዳር ከተማ ልዮ ስሙ ይባብ አካባቢ ወዳለ ብረታብረት ፋብሪካ በአሁኗ ሰዓት አምርቷል፤ ደርሷል።

ሰዓት - በኢትዮጵያ አቆጣጠር 9:20


በደብረታቦር የሆነው እንዲህ ነው!

አራዊት ሰራዊቱ በሌሊት ከደብረታቦር ከተማ በመነሳት በእብናት መሥመር ወደ መሎ ሀሙሲት በነገረ በኩል ወደ ዘንግ ሊያቀና እንደሆነ ከውስጥ አርበኞች ለነበልባል ፋኖዎቻችን ይደርሳል። ከዛም አራዊት ሰራዊቱ ገና መንቀሳቀስ እንደጀመረ በከተማው የቀረውን የአገዛዙን ኃይል ነበልባሎቻችን በትኩስ በትኩሱ ፉት ፉት ፉት አሉት። በዚህም ምክንያት ዛሬ በደብረታቦር ከተማ ሁሉም የመንግስት ተቋማት ትምህርት ቤቶች ጨምሮ ባንኮች ሁሉም ዘጋግተዋል

መናበብ ይልሃል ይሄ ነው። የውስጥ አርበኞች ከደብረታቦር ዙሪያ ፋኖዎች፣ የደብረታቦር ዙሪያ ፋኖዎች ደግሞ ከእብናት አካባቢ ፋኖዎች… በመካከል ደግሞ ህዝባችን አራዊቱ እዚህ ደርሷል በሚል መረጃ… በቃ ይህንን አይነት መናበብ ሁሉም ቦታ ያስፈልጋል።

አራዊቷ ሰሞኑን እንቅስቃሴ ስለምታበዛ እንዲህ እየጠበቁ ፉት ነው። ህዝባችንም መረጃዎችን ያጋራን።

19k 0 5 1 261

አራዊት ሰራዊቱና ሌሎች የአገዛዙ ኃይሎች በደብረታቦር ከተማና ዙሪያዋን ነፍስ ውጭ፣ ነፍስ ግቢ ላይ መሆናቸው ታውቋል፤ አይን ፍጥጥ ጥርስ ግጥጥ 😃😁 የአካባቢው የወገን ኃይል ደግሞ አስልተህ ማድረግ ያለብህን እንድታደርግ መልዕክት ይድረስህ።


የመሪያችን መልዕክት

መሪያችን አርበኛ ዘመነ ካሴ የዓድዋ በዓልን ምክንያት በማድረግ ካስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት የተወሰደ…

ከአድዋ አባቶቻችን የምንማረው አንዱ ቁም-ነገር በመካከላችን ያሉ ልዩነቶችን ሁሉ ወደ ጎን በመተውና ለጊዜው በማቆየት በዋናው ጠላታችን ላይ ማበር ያለብን መሆኑን ነው። ስለሆነም ከመቼውም ጊዜ በላይ ዛሬ በአንድነት እንድንሰለፍ ጥሪያችን እናቀርባለን።

እንኳን ለ 129ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ ።

አዲስ ትውልድ ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ !
አርበኛ ዘመነ ካሴ ባውቄ


በደጋዳሞት ዛሬም ተደግሟል!

በደጋዳሞት ከህዝብ እንዲወግኑ ተደጋጋሚ ምክር እየተሰጣቸው የተለቀቁ የአገዛዙ የፖለቲካና የፀጥታ አመራሮች ነበሩ። ህዝብን መናቅ ሆነና ምክሩንም ሳይሰሙ አገዛዙ ጋር ድስቴ ግጣሜ መባባሉን ቀጠሩ። ሁሉም ባልታወቁ ኃይሎች ተነደሉ፤ ከምድርም በታች ሆኑ። ሲጋልባቸው የነበረው አገዛዝም ከእናካቴው ረሳቸው።

ደግሞ ሌላ የአገዛዙ ትክ የፖለቲካና የፀጥታ አመራሮች ተመደቡና ቦታ ያዙ። ዛሬ አዲሶቹ በድንቅ ኦፕሬሽን አለቁ። አገዛዙ እነዚህን አፈር ሳይቀምሱ ይረሳቸዋል። ተረኛው ማን ይሆን?

ከዋናው ጠላትም በላይ ብአዴንን ማፅዳት የፅድቅ ስራ ነው። ደበረህ?


በኮሎኔል ታደሰ ህልፈተ ህይወት እጅጉን አዝነናል። ነገር ግን አንድ ነገር ተምረንበትም ታዝበንም አልፈናል።

ዛሬ ስለኮሎኔሉ ህልፈት በፀፀት የሚፅፈው፣ ቁጭቱን የሚገልፀው እና ወዳጄ ነው ባዮ በርከት ብሎ አየነው። ነገር ግን ከዚህ በፊት በጥቂት እኩያን የተጠለፉ ወንድሞችን በጅምላ የአደረጃጀት ፍረጃ ከማራቅ ይልቅ፣ ማቅረቡ ይሻላል ስንል "የተመረዘ ድርጅት ነው፣ ሁሉም አይጠቅሙም" የሚል የግብታዊ አካሄዶችን ተመልክተናል፤ ሃሳቦችም ደርሰውናል። ጭራሽ ውሃና ዘይትም ያለም ነበር። ዋናው ጥያቄ ግን ለአንድነት ቀናዒ የሆኑትን፣ ለአማራ ሕዝብ ፍላጎት ቅድሚያ ሰጠው ግለሰባዊ ፍላጎቶችን ገሸሽ ካደረጉት ጋር መስራቱ ላይ ነው።

ዛሬ ላይ መሰል የህልፈት ዜናዎች ሲሰሙ፣ በየትኛውም ደረጃ ቁጭት ብንሰማ ስላቅ መስሎ የሚሰማ ትርጉም አልባ ነው። መፈራረጁን አቁሞ የአደረጃጀት መስመሮችን ደፍሮ ማለፍ ያስፈልጋል። በአፋህድ በኩል ላሉት የኮሎኔል አሰግድ ጥቅም የገባቸው ገፍተውት ገፍተውት ኮሎኔል ከተያዘ በኋላ ከሆነ፣ በሌላው በኩል ያለው ደግሞ የኮሎኔል ታደሰ ጀግንነትና ቅንነት ትዝ ያላቸው ከህልፈቱ በኋላ ከሆነ… ከዚህ በላይ የግብታዊ አካሄድ ማሳያ የለም። ያልተሰሉ ስሜታዊ አካሄዶችና የጅምላ ፍረጃዎች ለእኛ የወል ውርደትን፣ ለጠላት ደግሞ ጥቂት ጥቂት ተደጋጋሚ ድልን የሚያስገኙ ይሆናሉ።

አሁን ላይ በሁሉም አቅጣጫ የሚያስደምም የፋኖ ሰራዊት ግንባታ ስራዎች እየተሰሩ ነው፤ የፖለቲካና ወታደራዊ ስልጠናው አስደማሚ ነው፤ የከባድ መሳሪያ ትጥቅ ለጉድ ነው። ይህ በሙሉ ለነጋችን ትልቅ ስንቅ ነው። ነገር ግን ማሸነፍ ካለብን ቢያንስ ቢያንስ ከልዮነቶች ይልቅ በሚያግባቡን ነገሮች ላይ በመስራት እንጀምር። አሁን አሁን የምንታዘበው ነገር ቢያንስ እንኳን አንዳንድ አመራሮች የአደረጃጀት ልዮነቶችን ለማጥበብ ንግግር ሲያስቡ እየፈሩ ያለው የስሜት ጋላቢውን ጩኸት ነው። ቢያንስ እንኳን አዋጭውን መንገድ በእራሳቸው አቅደው እንዳይፈፅሙ ስጋት የሆነባቸው፣ እንደቁራ የሚጮኸውን ታርጋ ለጣፊን መንጋ ነው።

በእንዲህ አይነት ሁኔታ ደግሞ ማሸነፍ አይቻልም። ሕዝባችን እንደ ሕዝብ አንድነትን ናፋቂ ነው። ስለዚህ ለሕዝብ ይበጃል ያላችሁን የተሰላ አካሄድ መከተላችሁ፣ ለአንድነትን መትጋታችሁ የሚያስጮኸው የማህበራዊ ሚዲያ መንጋ ካለ… እንደፈለገ ሲያጎራ ይኑር፤ ሲፈልግም በጅምላ ወይም በችርቻሮ ይታነቅ እንጅ ስምን እየፈሩ ወደኋላ የለም። ዛሬም ደግመን እንላለን - አሸናፊ የሚያደርገን "ስሜትን የገራና ከእኔ በላይ እኛ" የሚል አካሄድ ነው። የድል ቀናችንን የሚያቀርበውን አዋጭ መንገድ መርጦ፣ ሕዝባችሁ የሚወደውን ስሩ። ከዛ ግን የጮኸ ቁራ ሁሉ ምን ሊፈጥር? ምንም።

ነፍስህ በሰላም ትተፍ፣ ኮሎኔል!

እንኳን ለአድዋ ክብረበዓል አደረሳችሁ! ምኒልክነት መለያ ክብራችን ነው።


The brief visit by the infant Abiy Ahmed to Somalia might perhaps be recorded as the fastest state visit in world history. The heroes of Somalia did give him time to catch his breath, (they didn't even give the kid a second to pee 😀) and promptly rushed him back to Ethiopia. We are deeply saddened by your actions - you shouldn't have missed this guy 😉

የጨቅላው አብይ አህመድ የሶማሊያ ጉብኝት በዓለም ታሪክ ፈጣኑ ጉብኝት ነው። ብርሃኑ ጁላ ከጎርጎራ ሱሪውን ይዞ እንደሮጠው ሁሉ፣ ጨቅላው አብይ አህመድም ገና ከመድረሱ ሶማሊያውያን ሲያራውጡት ኧረ ጥሪኝ ዝናሽ እያለ እንዲፈረጥጥ አደረጉት። ለሁለት ቀን የታሰበው ጉብኝት ለ2 ሰዓት አለቀች 😄

23k 0 2 30 259

ሁለት መረጃዎች

1) #የቅድመ_ጥንቃቄ_መረጃ ፦ በምስራቅ ጎጃም የድሮን ቅኝቱ እንዲቀጥል በጨቅላው አብይ አህመድ አገዛዝ መመሪያ ተላልፏል። ከዚህም በተጨማሪ የድሮን አሰሳ መረጃን መሰረት በማድረግ ወደ ባህርዳር የጄት እንቅስቃሴ ለማድረግም መታቀዱ ታውቋል።

2) #የኤርትራ_ጉዳይ ፦ ከምንጮቻችን እንዳገኘነው መረጃ ከሆነ በኤርትራ መንግሥት የተወረሱት ሶስት መርከቦች ውስጥ ተተኳሾች፣ ራዳር፣ መለዋወጫ እና የአገዛዙ ሰዎች በሪፓርታቸው ላይ ልዩ ልዩ ብለው ያቀረቧቸው የውጊያ ቁሳቁሶች ይገኙበታል። አስገራሚው ነገር የጨቅልው አብይ አህመድ አገዛዝ በቅርቡ ይህንን ክስተት ለመካድ በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ለማወቅ ችለናል። እንደውሻ ጭራቸውን ቆልፈው ይገባሉ ብለን ነበር እኮ 😄 ኦህዴድ ወረምቲቲ በምን አቅሟ ኤርትራን ትሳፈጥ 😄

26k 0 8 18 209
Показано 20 последних публикаций.