ባህረ ጥበባት


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Видео и фильмы


"ህዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል" ት. ሆሴዕ 4:6
አለማወቅ እያጠፋን ነውና እንወቅ።
ለማንኛውም አስተያየትና ጥያቄ @Filoppader

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Видео и фильмы
Статистика
Фильтр публикаций






~ ትዝ ይላችኋል የ2012ቱ ትንቢት

"ወይ አዲስአበባ ወይ አዲስአበባ
ድንገት ሳታስበው ልትሆን ነው ገለባ
ወደ ጫካ ቢሮጥ ወደ እንጦጦ ቢሮጥ
ምልክት ከሌለ አይቻልም ማምለጥ
ሜክሲኮ ካዛንቺስ ቦሌና ሳሪስ
ለምሳ ሳይበቁ አለቁ በቁርስ..."

ለበለጠ ዝርዝር ፋይል አገላብጡ 😊

ትንቢቱን ስፖስት የሳቃችሁ የተሳለቃችሁ የት ናችሁ አሁን???

መልካም እለተ ሰኞ

አነ ውእቱ ሰሎሞን እምዛቲ ምድር




ህዳር 26 የፃድቁ አባታችን የአቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ልደታቸው ነው።

፨ ገድልህን ቆሞ የሰማ 80 ዓመት
ተቀምጦ የሰማ 40 ዓመት የሰራው ሀጥያቱን ይቅር እልልለታለሁ።

፨ በበዓልህ ቀን ለቤተክርስቲያን በስምህ ቄጤማ እንኳ የጎዘጎዘ፣ ወጥ በመሰራት፣ እንጨት በመፍለጥ በመሳሰሉት የበረከት ስራ የተሳተፈ 15 ትውልድ ድረስ እምርልሀለው። የሚል ታላቅ ቃልኪዳን የተቀበሉ አባት ናቸው። አዲስ አበባ ውስጥ ጽላታቸው 72 ንቡ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ ብቻ ይገኛል። ዋናው ገዳማቸው ያለው ትግራይ ውስጥ ነው። በረከታቸው ይደርብን።




















🛑 የመፀሀፍ ቅዱስ ጥናት ወደተሰሎንቄ ሰዎች 1ኛ መልእክት
https://youtu.be/bNE3BwblY04




🔔 "ጾመ ነቢያት [የገና ጾም] " 🔔
#ኅዳር 1⃣5⃣ ቀን 2017 ዓ/ም ይገባል።

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት የዘንድሮ የገና ጾም ኅዳር 15 ቀን 2017 ዓ/ም በዕለተ እሑድ ይጀመራል።
ይህ ጾም ከ7ቱ አጽዋማት (ዐቢይ ጾም፣ ጾመ ፍልሠታ፣ ጾመ ሐዋርያት፣ ጾመ ነቢያት፣ ጾመ ድኅነት፣ ጾመ ነነዌ ና ጾመ ገሃድ) መካከል አንዱ ነው፡፡

#ጾም_ምንድን_ነው?
- በፊደላዊ (የቃሉ) ትርጉሙ፡-
ጾም ተወ፣ ታቀበ፣ ታረመ ካለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ቃል ነው፡፡ የቃሉ ፍችም ምግብ መተው፣ መከልከል መጠበቅ ማለት ነው፡፡

#ምሥጢራዊ_ትርጉም፡-
ሰውነትን ከመብልና ከመጠጥ ከሌላውም ክፉ ነገር ሁሉ፤ መጠበቅ መግዛት፣ መቆጣጠር፣ በንስሐ ታጥቦ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር መቅረብና እሱንም ደጅ መጥናት፣ ማረኝ ይቅር በለኝ በማለት ቅድመ እግዚአብሔር በመንበርከክ ምሕረትን ከአምላክ ለመቀበል መዘጋጀት ነው፡፡
🔔“ጾም” በታወቀ ዕለት፣ በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ የሚከለከለው መከልከል ነው፡፡” /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፲፭/

#ስለ_ጾመ_ነቢያት_ፍትሐ_ነገሥታችን_እንዲህ_ይላል፦
ወይከውን ከመ ረቡዕ ወዓርብ፤ ወውእቱ ጾም ዘይቀድም እምልደት፤
ወጥንተ ዚኣሁ መንፈቀ ህዳር ወፋሲካሁ በዓለ ልደት።
የነቢያት ጾም እንደ ረቡዕና እንደ ዐርብ የሆነ፤ ይኸውም ከልደት አስቀድሞ የሚጾም መጀመሪያው የሕዳር እኩሌታ ፋሲካው የልደት በዓል የሆነ ጾም ነው። ፍትሐ ነገሥት (፲፭፥፭፻፷፰)
በቅዳሴ (በመንፈቀ ሌሉቱ የኪዳን ምስጋና) ክፍል እንዲህ የሚል ቃል ይገኛል ፦
ዘበመስቀልከ አቅረብከነ ኀበ አቡከ መልዕልተ ሰማያት
#በወንጌል_መራሕከነ
#ወበነቢያት_ናዘዝከነ
#ዘለሊከ_አቅረብከነ_አምላክ
"በመስቀልህ በጌትነት ወዳለ ወደባሕርይ አባትህ ያቀረብከን አምላክ በወንጌል መራኸን ፣ በነቢያት ያረጋጋኸን (በሥጋ ተገልጠህ በኩነት) ወደራስህ ያቀረብከን አምላክ ፈጣሪ … "
ነቢያት እግዚአብሔር በተስፋ ፍጥረትን ያረጋጋባቸው «የሕዝብ ዐይኖች» ፣ ከሰው ልጆች ጋር የተነጋገረባቸው «የእግዚአብሔር አፎች» ናቸው!

ይህንን ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ብዙ ቅዱሳን ጾመውታል፤ በዚህም ምክንያት የሚከተሉት ስያሜዎች አሉት፡፡ እነርሱም፤
#ጾመ_አዳም
#ጾመ_ነቢያት
#ጾመ_ሐዋርያት
#ጾመ_ፊልጶስ
#ጾመ_ማርያም
#ጾመ_ስብከት
#ጾመ_ልደት
✅ #ጾመ_አዳም ይለዋል ፦ ለአዳም የተነገረው ትንቢት ስለ ተፈጸመለት፤
✅ #ጾመ_ነቢያት ይለዋል ፦ ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ስለተፈጸመበት።
✅ #ጾመ_ሐዋርያት ይለዋል፦ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጹመን እናከብራለን ልደትን ምን ሥራ ሠርተን እናከብራለን ብለው ሐዋርያቱም ጹመውታልና።
✅ #ጾመ_ፊልጶስ ይለዋል ፦የአፍራቅያ ሰዎች ፊልጶስን በህዳር በ፲፯ ቀን ገደሉት ደቀመዛሙቱ እንቀብራለን ብለው ቢሔዱ ተሠወራቸው ሱባዔ ገቡ በለው ቢሔዱ ተሠወራቸው ሱባዔ ገቡ በሦስተኛው ቀን ትገለጸላቸው እሱን ቀብረው ጾሙን ጀምረን አንተውም ብለው ጹመውታል።
✅ #ጾመ_ማርያም ተብሏል፦ እመ ትሕትና እመቤታችን ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ ብላ ጹማለች።
✅ #ጾመ_ስብከት_፤ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት፥ የሰው ልጆች ተስፋ የተመሰከረበት፥ የምስራች የተነገረበት ስለሆነ ጾመሐዋርያት ይባላል።
✅ #ጾመ_ልደት_፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት ስለሆነ ‹‹ጾመ ልደት›› ይባላል፡፡
🔔“ጾም ቁስለ ነፍስን የምትፈውስ፤ ኃይለ ፍትወትን የምታደክም፤ የበጎ ምግባራት ሁሉ መጀመሪያ፤ ከእግዚአብሔ ጸጋን የምታሰጥ፤ የወንጌል ሥራ መጀመሪያ፤ የጽሙዳን ክብራቸው፤ የድንግልና የንጽሕና ጌጣቸው፤ የንጽሕና መገለጫ፣ የፀሎት ምክንያት ናት፤ የዕንባ መገኛ መፍለቂያ፤ አርምሞን የምታስተምር፤ ለበጎ ሥራ ሁሉ የምታነቃቃ፤ ሰውነትን በአግዚአብሔር ፊት ራስን በማዋረድ ትሕትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ መድኃኒተ ነፍስ ናት” /ማር ይስሐቅ አንቀጽ ፬÷፮/
🔔“ጾም ተድላ ሥጋን የምታጠፋ የሥጋን ጾር የምታደክም ቁስለ ነፍስን የምታደርቅ፣ በጎልማሶች ጸጥታንና ዕርጋታን የምታስተምር ከግብረ እንስሳዊነት የምትከለክል ሰው መላእክትን መስሎ የሚኖርባትና ኃይል መንፈሳዊ የሚጎናጸፍባ ደገኛ መሣሪያ ናት” /ፆመ ድጓ/
🔔በጾመ ነቢያት ነቢያቱን በማዘከርና በስማቸው በመማጸን ደጅ እየጠናን እንድንቆይ አምላከ ቅዱሳን ሁላችንንም ያበርታን!
ካህኑ በቅዳሴው ፍፃሜ
«ያብእክሙ ኀበ ሀለዉ ማኅበረ ነቢያት ቅዱሳን» እንደሚል ቅዱሳን የሚሆኑ ነቢያቱ ወዳሉበት ማኅበር በቸርነቱ ሁላችንን ያግባን!
🔔 Share ይደረግ
አምላከ ነቢያት ፆሙ የበረከት የድኅነት ፆም ያድርግልን፤ ጾሙ በሰላም አስጀምሮ በሰላም ያስፈጽመን። አሜን
===================
መልካም ንባብ !!!
ህዳር 13/03/2017 ዓ/ም
ፍንጭ: መ/ር ሚኪያስ ዳንኤል Facebook page







Показано 20 последних публикаций.