ባርሴሎና ከ ቤንፊካ የተጫዋቾች ሬቲንግ!!
ዎይዤክ ሼዝኒ 7.0🇵🇱ከባለፈው ሳምንት በተቃራኒ ብዙ ሙከራ አልተደረገበትም!!
ዡል ኩንዴ 8.0🇫🇷ኩንዴ ትላንት ልክ እንደሁልጊዜው ምርጥ ነበር። በትላንትናው ጨዋታ 98% የማቀበል ስኬት የነበረው ዡል ኩንዴ 2 ጊዜ ብቻ ኳስን ተነጥቋል። በአጠቃላይ በጨዋታው ድንቅ ነበር።
ሮናልድ አራውሆ 7.8🇺🇾ሮናልድ በደርሶ መልስ ከቤንፊካ ጋር እጅግ በጣም ድንቅ ነበር። በጨዋታው 5 የተሳኩ ታክሎችን ያደረገው ሮናልድ 4 ጊዜ ኳሶችን ከአደጋ ክልል ማጽዳት ሲችል በጨዋታውም ድንቅ ነበር።
ኢኒጎ ማርቲኔዝ 7.7🇪🇸ኢኒጎ በትላንትናው እጅግ ጥሩ የሚባል እንቅስቃሴን ማድረግ ችሏል። 3 የተሳኩ ረዥም ኳሶችን ያቀበለው ኢኒጎ 75% የአየር ኳስ የማሸነፍ ንጻሬ ነበረው።
አሌሃንድሮ ባልዴ 8.5🇪🇸ሁልጊዜም እንደስራው የማይወራለት የላማሲያ ምሩቁ አሌሃንድሮ ባልዴ ክለባችን እስካሁን ላሳካው ስኬት ወደፊትም ለሚያሳካው ስኬት ወሳኝ ሚና የሚጫወት ተጫዋች ነው። ትላንት 1 አሲስት ከማድረጉ በተጨማሪ ኳሷን እየገፋ የሄደበት መንገድ አስደናቂ ነበር። በጨዋታው 5 የተሳኩ ድሪብሎችን ማድረግ የቻለው አሌክስ ከጨዋታ ጨዋታ የድሪብሊንግ ችሎታውን እያሻሻለ ይገኛል።
ፍሬንኪ ዴ ዮንግ 7.7🇳🇱ፍሬንኪ ከፔድሪ ጋር በመሆን የመሃል ሜዳውን የሚቆጣጠሩበት መንገድ ድንቅ ነበር። ፍሬንኪ ትላንት 96% የማቀበል ስኬት የነበረው ሲሆን ጎልም ለማስቆጠር ተቃርቦ ነበር።
#ይቀጥላል
@BARCAFANSETHIOPIA@BARCAFANSETHIOPIA