የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምህላ ጊዜ ዐወጀች፤
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር አምላካችን በሽታውን ከአገራችን እንዲያርቅልን እስከ ትንሣኤ ድረስ የጸሎትና የምህላ ጊዜ ማወጇን ቅዱስ ፓትርያርኩ ገለጡ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ቅዱስ አቡነ ማትያስ ይህን፣ የተናገሩት በቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ 24 በሚባለው አካባቢ ሁለት ክርስቲያኖች ሰማዕትነትን በተቀበሉበት ቦታ ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት የመሠረት ድንጋይ ባስቀመጡበት ወቅት ነው።
ቅዱስ ፓትርያርኩ ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን በእምነት ጸንተው ፈጣሪያቸውን በጸሎት ከመጠየቅ በተጨማሪ፣ ተረጋግተው የጤና ባለሙያዎች የሚሰጧቸውን ምክር መተግበር እንጂ መፍራት እንደሌለባቸውም ተናግረዋል።
በዕለቱም የቦታው ባለይዞታ ለነበሩትና 'ያሳደግኳቸው ልጆች የሞቱበትን ቦታ ለሌላ አገልግሎት ማዋል ሐራም በመሆኑ፣ ትክ ካሰጣችሁኝ ቤተ ክርስቲያን ሥሩበት' በማለት ለተስማሙት የእስልምና እምነት ተከታይ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ተሠርቶ ሲያልቅ የቅዱስ ገብርኤል እና የቅድስት አርሴማ ጽላት እንደሚገባም ለማወቅ ተችሏል።
© ማኅበረ ቅዱሳን፤ ሕዝብ ግንኙነት