በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия

አቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፵፮
"ብቻውን ጥበብ ላለው ለእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘለዓለም ድረስ ክብር ይሁን አሜን" (ሮሜ ፲፮፣፳፯)።

እግዚአብሔር ብቻውን ጥበብ ያለው ነው። ፍጡራን ጥበብ ቢኖራቸው ፈጣሪ በጸጋ የሰጣቸው ነው። አምላክ ግን ብቻውን ጥበበኛ ነው። "ብቻውን" የሚለው አገላለጽ ከፍጡራን ሲለየው ነው እንጂ አብን ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ፣ ወልድን ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ፣ መንፈስቅዱስን ከአብና ከወልድ ሲለያቸው አይደለም። አብ ብቻውን ጥበብ ያለው ይባላል። ይህን ጊዜ "ብቻውን" የሚለው ቃል ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ ለማለት ሳይሆን ከፍጡራን ተለይቶ ለማለት ነው። ሦስቱ አካላት በጥበብ፣ በዕውቀት፣ በፈቃድ በጠቅላላው በአምላካዊ ሥራ አንድ ናቸውና።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf' rel='nofollow'>https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፵፯ ይቀጥላል

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፵፭
"የክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል" (ሮሜ ፲፮፣፲፮)።

ቤተ ክርስቲያን የሚለው ቃል ሦስት ትርጉም አለው። አንደኛው አምልኮ የምንፈጽምበት፣ የምንጠመቅበት፣ የምንቆርብበት ቤት ሕንፃው ቤተ ክርስቲያን ይባላል። ሁለተኛው እያንዳንዱ ምእመን ቤተ ክርስቲያን ይባላል። ይኽውም ቤተ ክርስቶስ (የክርስቶስ ወገን) ማለት ነው። ሰው በክርስቶስ ሲጠመቅ የክርስቶስ ወገን ይሆናል። ሦስተኛው የምእመናን አንድነት ቤተ ክርስቲያን ይባላል። የክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል የሚለው አገላለጽ በክርስቶስ አምነው፣ በክርስቶስ ስም ተጠምቀው የሚኖሩ ምእመናን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል ማለቱ ነው እንጂ ሕንፃው ሰላምታ ያቀርብላችኋል ማለቱ አይደለም።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf' rel='nofollow'>https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፵፮ ይቀጥላል

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፵፬
"በሕይወት ሆነን ብንኖር ለጌታ እንኖራለንና፥ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን። እንግዲህ በሕይወት ሆነን ብንኖር ወይም ብንሞት የጌታ ነን" (ሮሜ ፲፬፣፰)።

ጻድቃን በዚህች ምድር ሲኖሩም ለእግዚአብሔር ኖሩ። ለእግዚአብሔር መኖር ማለትም ሕግጋቱን በመጠበቅ ኖሩ ማለት ነው። ሲሞቱም ለእግዚአብሔር ሞቱ። ለእግዚአብሔር መሞት ማለትም ሕጉን ትእዛዙን እየፈጸሙና ለዓለም ሁሉ እየተናገሩ ሰማዕት ሆኑ ማለት ነው። የቅዱሳን የኑሮ መመሪያቸው ሕገ እግዚአብሔር ነው። ለማንኛውም ሰው ባለቤት አለው። ሰው የራሱ አይደለም። ከአባት ዘር ከእናት ደም ከፍሎ ወደዚህ ምድር እንዲመጣ ያደረገው እግዚአብሔር ነው። ሁላችንም የፈጣሪ ገንዘቦች በመሆናችን ቅዱስ ጳውሎስ "የጌታ ነን" ብሎ ተናገረ።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf' rel='nofollow'>https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፵፭ ይቀጥላል

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፵፫
"ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት" (ሮሜ ፲፫፣፲፬)።

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት ማለት በእርሱ አምናችሁ፣ ተጠምቃችሁ፣ ሥጋውን ደሙን ተቀበሉ ማለት ነው። በሌላ አገላለጽ ልበሱት ማለት በክርስቶስ ክርስቲያን ተባሉ ማለት ነው። እንዲሁም መልካም ሥራ ሠርታችሁ ክርስቶስ የጸጋ ተዋሕዶን ይዋሐዳችሁ ማለት ነው። ቅዱሳን ጻድቃን ክርስቶስን ስለለበሱት እውነትን በመመስከር ጸንተው ኖሩ፣ ታላላቅ ተአምራትን በእርሱ ስም አደረጉ። ቅዱስ አግናጤዎስ ለባሴ እግዚአብሔር ይባል ነበር። ይኽውም እግዚአብሔር በጸጋ የተዋሐደው የእግዚአብሔርን ሕግ በመዓልትም በሌሊትም የሚፈጽም ማለት ነው። ስለዚህ ክርስቶስን ልበሱት ማለትም በእርሱ አምናችሁ ተጠምቃችሁ ሕጉን ትእዛዙን ጠብቁ ማለት ነው።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf' rel='nofollow'>https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፵፬ ይቀጥላል

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፵፪
"ሁሉ ከርሱና በርሱ ለርሱም ነውና ለርሱ ለዘለዓለም ክብር ይሁን አሜን" (ሮሜ ፲፩፣፴፮)።

ራሱን በራሱ ያመጣ ፍጥረት የለም። ማንም ቢሆን ራሱን ካልካደ በቀር ራሴን በራሴ አመጣሁ አይልም። ፍጥረታትን ሁሉ በቸርነቱ ካለመኖር አምጥቶ የፈጠረ ልዑል እግዚአብሔር ነው። ሲፈጥርም በፈቃዱ ፈጥሯቸዋል እንጂ እነርሱን እንዲፈጥር ያስገደደው ሌላ አካል የለም። ከፍጥረታት በፊት ከእግዚአብሔር ውጭ የሆነ ሌላ አካል አልነበረምና። "ሁሉ ከእርሱ ነው" ማለት ፍጥረታት ሁሉ ከእርሱ የተገኙ መሆናቸውን ይገልጻል። "ሁሉ በእርሱ ነው" ማለትም ፍጥረታት ሁሉ የተፈጠሩት በእርሱ መሆኑን ያመለክታል። "ሁሉ ለእርሱ ነው" ማለትም የፍጥረታት ሁሉ ባለቤት እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን ያመለክታል። ለእግዚአብሔር መኖር ግን ሌላ ምክንያት የለውም። "እስመ አልቦ ውስተ ህላዌሁ አመክንዮ" እንዲል።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf' rel='nofollow'>https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፵፫ ይቀጥላል

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፵፩
"የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና" (ሮሜ ፲፣፲፫)።

የጌታን ስም ሰይጣናትም ይጠሩታል። ጠንቋዮችም ይጠሩታል። ሌቦች አመንዝራዎችም ይጠሩታል። በጠቅላላው ኢአማንያንም ይጠሩታል። ምግባረ ብልሹዎችም ይጠሩታል። ታዲያ የጠሩት ሁሉ ይድናሉ ያለው እነዚህን ሁሉ ይድናሉ ማለቱ ነውን? አይደለም። የጌታን ስም የሚጠራ ይድናል የተባለ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖና ተጠምቆ፣ ምግባር ትሩፋት ሠርቶ፣ ሥጋውን ደሙን ተቀብሎ የሚኖር ሰውን ያመለክታል። መልካም ሥራን እየሠሩ የጌታን ስም መጥራት ያድናል። ንሥሓ ገብተው ሥጋውን ደሙን ተቀብለው የጌታን ስም መጥራት ያድናል። እነዚህንና የመሳሰሉ መልካም ሥራዎችን ሳይሠሩ ስሙን መጥራት ብቻውን ግን አያድንም።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf' rel='nofollow'>https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፵፪ ይቀጥላል

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፵
"ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና፥ በአፉም መስክሮ ይድናልና" (ሮሜ ፲፣፲)።

አንድ ሰው ለመዳን ቢያንስ አራት ነገሮች ያስፈልጉታል። እነዚህም መጀመሪያ ለዚህች ዓለም ሠራዒ፣ አስተዳዳሪ፣ መጋቢ እንዳላት ማመን። የፈጠራት እግዚአብሔር መሆኑን፣ ይህ እግዚአብሔር ደግሞ በአካል ሦስት በባሕርይ አንድ መሆኑን ማመን ይገባል። ከሦስቱ አካላት አንዱ መዋረዳችንን አይቶ ከድንግል ማርያም ተወልዶ በመስቀል ተሰቅሎ እንዳዳነን ማመን ነው። ሁለተኛው አምነን መጠመቅ ነው። ሦስተኛው መልካም ሥራዎችን መሥራት ነው። አራተኛው ሥጋውን ደሙን መቀበል ነው። ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃል ማለቱ እነዚህን ነገሮች ሁሉ አድርጎ ሲያምን ነው። በአፉም መስክሮ ይድናል ያለው እውነትን ይዞ ከላይ ያሉትን ነገሮች ሠርቶ ሲመሰክር ነው። እንጂ እነዚህን ሳያደርግ በማመን ብቻ ይጸድቃል ማለት አይደለም።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf' rel='nofollow'>https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፵፩ ይቀጥላል

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፴፱
"ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍኽ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብኽ ብታምን ትድናለኽና" (ሮሜ ፲፣፱)።

ጌትነት የባሕርይ ጌትነትና የጸጋ ጌትነት ተብሎ በሁለት ይከፈላል። ጌትነት ምሥጢሩ ባለቤትነትን፣ ገዢነትን ያመለክታል። ለዓለም ጌታ አላት ማለት ባለቤት አላት ማለት ነው። ኢየሱስ ጌታ ነው ማለት የፍጥረታት ሁሉ ባለቤት እርሱ ነው ማለታችን ነው። ገዢነትን ሲያመለክት ደግሞ ኢየሱስ የፍጥረታት ሁሉ ገዢ ነው ማለታችን ነው። ፍጡራን ግን ጌታ ቢባሉ ከፈጣሪ ባገኙት ጸጋ ነው። ለሀብታቸው ባለቤት ቢሆኑ ሀብታቸውም ባለቤትነታቸውም ከፈጣሪ የተሰጠ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስን ጌታ ነው ስንለው ግን ለጌትነቱ፣ ለባለቤትነቱና ለገዢነቱ ሌላ ምክንያት የሌለው በባሕርይው ጌታ የሆነ ነው ማለታችን ነው።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf' rel='nofollow'>https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፵ ይቀጥላል

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፴፰
"ከእነርሱም (ከአባቶችም) ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ኾኖ ለዘለዓለም የተባረከ አምላክ ነው አሜን" (ሮሜ ፱፣፭)።

ቅዱስ ጳውሎስ የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት በግልጽ ከተናገረበት አንቀጽ አንዱ ይህ ነው። ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን የፈጠረ ወልደ እግዚአብሔር አዳምን ለማዳን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ። ከአባቶች ተወለደ ብሎ የተናገረው አያቶቹን ለመጥቀስ ነው። ይኽውም ከኢያቄም ጀምሮ እነ ዳዊትን እነአብርሃምን እና ሌሎችንም ታላላቅ ቅዱሳን ለመጥቀስ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ በባሕርይው አምላክ ነው። ቅዱሳን አምላክ ቢባሉ የጸጋ አምላክ ሆነው ነው። እርሱ ግን አምላክነቱ የባሕርይ አምላክ ነው። ለዘለዓለም የተባረከ አምላክ ተብሎ የተገለጸውም ለዚህ ነው።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf' rel='nofollow'>https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፴፱ ይቀጥላል

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፴፯
"የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚፈርደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው" (ሮሜ ፰፣፴፬)።

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፴፮ ላይ እንደተመለከትነው መንፈስ ቅዱስም ይማልድልናል (ይከራከርልናል) እንደተባለና አብም ይከራከርልናል (ይትዋቀስ በእንቲኣነ) እንደተባለ አይተናል። በዚህኛው ክፍል ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚፈርደው ተብሏል። ይህም በግእዙ "ወይትዋቀስ በእንቲኣነ" ይላል። ይኽውም ይከራከርልናል (ይማልድልናል) ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። ሁሉንም ቢል ትርጉሙ ተመሳሳይ ነው። ዋጋችንን ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሆኖ ይሰጠናል ማለት ነው። በሥጋው በደሙ አማካኝነት እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ ጸጋውን እያደለ ሰይጣንን እንድንቃወም ይረዳናልና ይማልድልናል አለ እንጂ ከትንሣኤ በኋላ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁልጊዜ እያማለደ ይኖራል ማለት አይደለም። ምድር ላይ በሠራልን የማዳን ሥራ አምነን ተጠምቀን ሥጋውን ደሙን ተቀብለን ብንኖር መንግሥተ ሰማያትን ሰጥቶ የሚፈርድልን እርሱ ነው።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf' rel='nofollow'>https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፴፰ ይቀጥላል

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፴፮
"እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገ፟ባ፟ን አናውቅምና፥ ነገር ግን፥ መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል" (ሮሜ ፰፣፳፮)።

መንፈስ ቅዱስን ይማልድልናል እያለ ነው። ዋጋ መስጠትን መማለድ ብሎ የሚገልጽበት ወቅት አለ። ይኽውም ውጤቱን በመቅድሙ መጥራት ነው። መንፈስ ቅዱስ የተለያዩ መከራዎችን ስንቀበል ዋጋችንን ይሰጠናል። ከአብ ከወልድ ጋር አንድ ሆኖ ለምዕመናን ዋጋቸውን ይሰጣቸዋል። እግዚአብሔር ምእመናን እንዳይወድቁ ይማልድላቸዋል ማለት ጸጋውን ያድላቸዋል። ከእነርሱ ጋር በረድኤት ሆኖ የሚድኑበትን መንገድ ይገልጽላቸዋል ማለት ነው። ይማልድልናል የሚለው ቃል በግእዝ "ይትዋቀስ-ይከራከርልናል" ተብሏል። ይህ ከሆነ ደግሞ አብም እንደሚከራከርልን (እንደሚማልድልን) ተጽፏል። "ስለእርሳቸው ይከራከርላቸዋልና በጠላታቸምም እጅ አይጥላቸውምና ከሚጠሏቸው ከጠላቶቻቸው እጅ ያድናቸዋል" እንዲል (፩ኛ መቃ. ፳፣፫)። ትርጉሙ ዋጋን ይሰጠናል ማለት ነው።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf' rel='nofollow'>https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፴፯ ይቀጥላል

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፴፭
"ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋራ አንድ እንኾን ዘንድ የተጠመቅን ዅላችን ከሞቱ ጋራ አንድ እንኾን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን። ሞቱንም በሚመስል ሞት ከርሱ ጋራ ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከርሱ ጋራ እንተባበራለን" (ሮሜ ፮፣፫_፭)።

በጥምቀት ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድ እንሆናለን። ስንጠመቅ ራሳችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይሆናል። እኛም ሕዋሳቶቹ እንሆናለን። ስንጠመቅ አካላችን የክርስቶስ ማደሪያ ይሆናል። ስለዚህ በእርሱ በክርስቶስ ክርስቲያን እንባላለን። ስንጠመቅ ሞቱን በሚመስል ሞት እንሞታለን። ሞቱን በሚመስል ሞት ስንሞት ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ እንተባበራለን። በጥምቀት ከእግዚአብሔር የጸጋ ልጅነትን እናገኛለን (ዮሐ. ፫፣፫)። በጥምቀት ሥርየተ ኃጢአትን እናገኛለን። ስንጠመቅ ከእርሱ ከጌታ ጋር አንድ እንሆናለን ማለት በጸጋ ተዋሕዶን ታላላቅ መንፈሳዊ ሥራዎችን እንድንሠራ ያደርገናል ማለታችን ነው።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf' rel='nofollow'>https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፴፮ ይቀጥላል

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፴፬
"ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋራ በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን" (ሮሜ ፭፣፲)።

ኢየሱስ ክርስቶስን ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ ነው ብለው የሚናገሩ ሰዎች በዚህ ኃይለ ቃል ይሸነፋሉ። "ወልደ እግዚአብሔር አይሞትም፣ አይራብም፣ አይጠማም፣ አይደክምም ወልደ ማርያም ይሞታል፣ ይራባል፣ ይጠማል፣ ይደክማል" እያሉ አንዱን ኢየሱስ ክርስቶስን ሁለት አድርገው የሚናገሩ ሰዎች አሉ። እኛ ግን አንዱን ኢየሱስ ክርስቶስን ወልደ አብም ወልደ ማርያምም እንለዋለን። ከተዋሕዶ በኋላ የሠራውን ሥራ በተዋሕዶ ሠራው እንላለን እንጂ እየነጣጠልን ይህ የሥጋ ሥራ ነው፣ ይህ የመለኮት ሥራ ነው እያልን አንናገርም።

ቅዱሳት መጻሕፍትም ኢየሱስ ክርስቶስን ወልድ ዋሕድ (አንድ ልጅ) ይሉታል እንጂ ሁለት አይሉትም። ይህንንም የሚያስረዳን ከላይ የጠቀስነው ኃይለ ቃል ነው። እግዚአብሔር በልጁ ሞት ታረቀን ብሎ ወልደ አብ በሥጋው እንደሞተ ነግሮናል። በምንታዌ (Dualism) የሚያምኑ ሰዎች የእግዚአብሔር ልጅ አይሞትም ካሉ እግዚአብሔር በልጁ ሞት ታረቀን ይልባቸዋልና ክሕደታቸው ከንቱ መሆኑን ይወቁ።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf' rel='nofollow'>https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፴፭ ይቀጥላል

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፴፫
"በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ" (ሮሜ ፫፣፳፬)።

ቤዛነት ማለት ምትክነት ማለት ነው። ይኽውም ለአዳም ስለአዳም እንደ አዳም ሆኖ የወደቀውን አዳምን ለማንሣት ያደረገው የቸርነት ሥራ ነው። ባጠፋው ጥፋት ምክንያት መሰቀል ይገባው የነበረ አዳም ነው። ነገር ግን በአዳም ምትክ (ህየንተ አዳም) ጌታ ተሰቅሎ አዳምን ነጻ አውጥቶታል። አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ ብሎ ማልቀስና ወደ እግዚአብሔር ማመልከት የሚገባው አዳም ነበር። ነገር ግን አዳም በበደል ስለተያዘ በፊቱ ቆሞ እንዲህ ብሎ ለመጮህ አልቻለም። ስለዚህ በአዳም ምትክ የአዳምን ጩኸት ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ጮኸለት። እንደ አምላክነቱም የአዳምን በደል በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ይቅር አለው። ምእመናን በክርስቶስ ቤዛነት እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ። ይህም ማለት ጌታ ያደረገውን የማዳን ሥራ አምነው፣ ተጠምቀው፣ ሥጋውን ደሙን ተቀብለው፣ መልካም ሥራን ሠርተው በእግዚአብሔር ቸርነት ይጸድቃሉ ማለት ነው። የእግዚአብሔር ቸርነት ካልተጨመረበት ሰው ምንም ያህል በጎ ሥራ ቢሠራ መጽድቅ እንደማይችል ለመግለጽ እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ ብሎ ተናገረ።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf' rel='nofollow'>https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፴፬ ይቀጥላል

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፴፪
"እምነታችኹ በዓለም ሁሉ ስለ ተሰማች አስቀድሜ ስለ ዅላችኹ አምላኬን በኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለኹ" (ሮሜ ፩፣፰)።

በምስጋና መጀመር ለሐዋርያት ልማዳቸው ነው። እግዚአብሔር አብን አስቀድሜ አመሰግናለሁ አለ። አምላኬ ያለው አብን ነው። ወልድን ቀጥሎ የሚያመጣው ነውና። በኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ አለ። ኢየሱስ ክርስቶስን ማመስገን አብን ማመስገን ነው። አብን ማመስገን ኢየሱስ ክርስቶስን ማመስገን ነውና። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በምስጋና አንድ ናቸው። እነርሱን የምናመሰግነው ምስጋና የባሕርይ ምስጋና ነው። ይኽውም ይህን ዓለም ካለመኖር አምጥተው ስለፈጠሩ፣ ብንወድቅ ከሦስቱ አካላት አንዱ ወልድ ሥጋችንን ተዋሕዶ በመስቀል ተሰቅሎ ስላዳነን፣ ብንራብና ብንጠማ ዘለዓለማዊነትን የሚያጎናጽፍ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ስለሰጠን እናመሰግነዋለን። እግዚአብሔር ምስጋና የባሕርይው ነው ማለታችን ባሕርይው ምስጉን ነው ማለታችን ነው። ይኽውም ቅዱሳን መላእክትና ሰዎች ቢያመሰግኑት የማይጨመርለት ባያመሰግኑት የሚቀነስበት አይደለም ማለታችን ነው።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf' rel='nofollow'>https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፴፫ ይቀጥላል

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፴፩
"ራሱን ያለምስክር አልተወም" (የሐዋ. ሥራ ፲፬፣፲፯)።

የዚህች ዓለም ፈጣሪ፣ አስተዳዳሪ እንዳላትና ይኽውም እግዚአብሔር እንደሆነ በብዙ መንገድ ራሱ አሳውቆናል። የፈጣሪን መኖር ከሚያረጋግጡልን ምስክሮች መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ።
፩) ሥነ ፍጥረት
፪) መጽሐፍ ቅዱስ
፫) ሥጋዌ
ቤት ያለባለቤት እንደማይገኝ ሁሉ ፍጡርም ያለ ፈጣሪ አልተገኘም። ሁሉንም ፍጥረት ካለመኖር ወደመኖር ያመጣና የፈጠረ ለእርሱ ምንም ምክንያት የሌለው ልዑል እግዚአብሔር ነው። ለእርሱ መኖር ሌላ ምክንያት እንደሌለውም "እስመ አልቦ ውስተ ህላዌሁ አመክንዮ" ተብሎ ተገልጿል። በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፉ የነቢያት ትንቢቶች ተፈጻሚ ሆነው በመታየታቸው ያጻፈው እግዚአብሔር እውነተኛ እንደሆነ ይመሰክራሉ። ስለዓለም አፈጣጠር በእርግጠኝነት የሚናገር መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። የእግዚአብሔርን መኖር በጎላ በተረዳ ነገር የሚያሳውቀን ደግሞ ከሦስቱ አካላት አንዱ ወልድ ከድንግል ማርያም ተወልዶ የአምላክነት ሥራን እየሠራ በማሣየቱ ነው።

© በትረ ማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf' rel='nofollow'>https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፴፪ ይቀጥላል

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፴
"በኢየሱስ ክርስቶስ ስምም ይጠመቁ ዘንድ አዘዛቸው" (የሐዋ. ሥራ ፲፣፵፰)።

በአብ ማመን በወልድ ማመን፣ በወልድ ማመን በአብ ማመን እንደሆነ ከዚህ ቀደም ተማምረናል። ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ ብሎ ያዘዛቸው በእርሱ ስም መጠመቅ በአብ ስም መጠመቅ ስለሆነ ነው። በእርሱ ስም መጠመቅ በመንፈስ ቅዱስ ስም መጠመቅ ስለሆነ ነው። በባሕርያዊ ግብር ሦስቱ አንድ ስለሆኑ የአንዱ ስም ቢጠቀስም ሁለቱንም የሚመለከት ጉዳይ እንደሆነ ደጋግመን ደጋግመን ተማምረናል። ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ ማለት በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ተጠመቁ ማለት ነው። በጥምቀት የእግዚአብሔር የጸጋ ልጆች እንሆናለን። ስንጠመቅ ከጥምቀት በፊት የሠራነው ኃጢአታችን ይሠረይልናል። በጥምቀት ድኅነትን እናገኛለን።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf' rel='nofollow'>https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፴፩ ይቀጥላል

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፳፱
"ጴጥሮስ ይህን ነገር ገና ሲናገር ቃሉን በሰሙት ሁሉ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደ" (የሐዋ. ሥራ ፲፣፵፬)።

"መንፈስ ቅዱስ ወረደ" ማለት ምን ማለት ነው? መንፈስ ቅዱስ የሌለበት ቦታ የለም። በሁሉ ቦታ ያለ ስለሆነ ወረደ ወጣ ሄደ የሚሉት ቃላት እንደ ቃላዊ ፍቻቸው አይተረጎሙም። አንድ ነገር ከሰማይ ወረደ ከተባለ ቀድሞ ከምድር አልነበረም ማለት ነው። ወደ ሰማይ ወጣ ከተባለ ደግሞ አስቀድሞ በምድር አልነበረም ማለት ነው። መንፈስ ቅዱስ ወረደ ማለት ግን ከሰማይ ታጣ ከምድር ተገኘ ማለት ሳይሆን ረድኤትን ሰጠ፣ ጸጋን አደለ ማለት ነው። የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ጸጋን ያሰጣል። ስለሆነም ጴጥሮስ ሲያስተምር በሰሙት ሰዎች ላይ ጸጋ እግዚአብሔር እንዳደረባቸው ለመግለጽ መንፈስ ቅዱስ ወረደ ተብሎ ተገልጿል። ቅዱሳት መጻሕፍት ጸጋ መንፈስ ቅዱስን መንፈስ ቅዱስ እያሉ እንደሚጠሩት ከዚህ ቀደም ተመልክተናል።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf' rel='nofollow'>https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፴ ይቀጥላል

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፳፰
"ከሙታንም ከተነሣ በኋላ ከርሱ ጋራ የበላን የጠጣንም እኛ ነን" (የሐዋ. ሥራ ፲፣፵፩)።

አንዳንዶች ኢየሱስ ክርስቶስን ከሙታን መካከል አልተነሣም እያሉ ይክዳሉ። በቅርብ በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተመሠረተው የእስልምና እምነትም ይህን ያስተምራል። ነገር ግን ከሙታን እንደተነሣ በዘመኑ ከእርሱ የተማሩ ሐዋርያት ከሙታን መካከል እንደተነሣ አይተውታል። ወንጌላዊው ሉቃስ "ከሙታን ከተነሣ በኋላ ከእርሱ ጋር የበላን የጠጣንም እኛ ነን" ብሎ የጻፈውም ለዚህ ነው። የክርስትና ሃይማኖትን ከሌሎች ቤተ እምነቶች ልዩ የሚያደርገው ይህ የትንሣኤ ጉዳይ ነው። ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቶ ትንሣኤ እንዳለ አረጋግጦልናል። ሌሎች ቤተ እምነቶች ትንሣኤ እንዳለ ቢያምኑ እንኳ ምስክር ግን የላቸውም። የእኛ ግን ራሱ ክርስቶስ ምስክር አለን። መነሣቱ እውነት እንደሆነም በዘመኑ የነበሩ ሰዎች ምስክር ናቸው።

© በትረ ማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf' rel='nofollow'>https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፳፱ ይቀጥላል

ነገረ ክርስቶስ ክፍል ፪፻፳፯
"እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኀይልም ቀባው፥ ርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከርሱ ጋራ ነበረና" (የሐዋ. ሥራ ፲፣፴፰)።

በመንፈስ ቅዱስ ቀባው የሚለው ትርጉሙ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ቀባው ማለት ነው። ይኽውም ከመታሰብ በላይ የሆኑ አምላካዊ ሥራዎችን ቅዱሳት መጻሕፍት ለመንፈስ ቅዱስ አድለው ቢናገሩም መቀባት የሦስቱም የአንድነት ሥራ ነው። ሥጋ ከቃል ጋር ተዋሕዶ አምላክ እንዲሆን ማድረግም የሦስቱም የአንድነት ሥራ ነው። በሃይማኖተ አበውም ዘአንገሦ ለሥጋ አዳም በመንፈስ ቅዱስ ወረሰዮ ቅዱሰ ወማሕየዌ ሲል ይገኛል። በመንፈስ ቅዱስ አዋሐጅነት ሥጋን አምላክ አድርጎ ማሕየዊና ቅዱስ ያደረገው ተብሎ ተገልጿል። ከዚህም ላይ መንፈስ ቅዱስ ይጠቀስ እንጂ ማዋሐድ የሦስቱም አካላት የአንድነት ሥራ ስለሆነ አብም ወልድም ያሉበት ሥራ ነው። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋራ ነበረ ተብሎ መነገሩ በህልውና አብና መንፈስ ቅዱስ በእርሱ ህልው ሆነው ስለሚኖሩ ነው።

© በትረማርያም አበባው

የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ
@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf' rel='nofollow'>https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።

ክፍል ፪፻፳፰ ይቀጥላል

Показано 20 последних публикаций.