Фильтр публикаций


📧 Resume ላይ ያለ email አድራሻችሁን ትርጉም የሚሰጥ አድርጉት። ለምሳሌ የኔ ስራ መፈለጊያ ኢሜይሌ hirebirhan@gmail.com ነበር።

የኔ ግን በቃ ብርሃንን ቅጠሩት የሚል ትዛዝ ይመስላል 😀 ። ከዚህ የተሻለ አድርጉት።


Репост из: Edemy
Get ready for an exciting session with Birhan Nega—a Full Stack Engineer at Exelia Technologies and the mind behind Skyhub Technology Solution! Many of you know him from his Telegram channel, where he shares valuable advice and support for developers.

Birhan has worked on global companies across Europe and the US, building innovative web applications using modern technologies. His experience in freelancing, remote work, and startup development has shaped his deep understanding of the industry's challenges and opportunities.

In this session, we’ll explore:

1.His journey into software engineering
2. His university experience and how it shaped his career
3. How he went from freelancing to remote work & launching a startup
4. Insights on his current projects & tech stack
5. Tips on becoming a highly competitive developer
6. Career advice

📅 Date: 02/06/2017 (Feb 9 2025)
⏰ Time: 8:00 PM ( Mata 2 Sehat)
📍 Live on: https://t.me/edemy251

Don't miss the chance to learn from an expert!

@edemy251


// Thanks for 6,000 followers!

print("You're all amazing!");

Seriously, let's keep learning and sharing and keep improving

Invite Friends, share your thoughts, boost the channel, ask your questions...

@birhan_nega


የስራ ማስታወቂያ ሲወጣ ሙሉውን ሳታነቡ ኮመንት ላይ "I am interested, here is my number please call me" ምናምን የምትሉ ሰዎች አስረግጨ ነው የምነግራችሁ ራሳችሁ ላይ አትቀልዱ 😊

This might offend you but I am sure you will Thank me later.


ቤት የሚሰራ ስራውን የሚጀምረው ከቤዝመንት አይደል? ፕሮግራሚንግ መማር የሚፈልግም ከ programming fundamentals መጀመር ይኖርበታል።
ለዚህ ደግሞ etcoders ላይ መንግሥት ያቀረበውን Programming fundamentals መውሰድ እመክራለሁ።

ባይሆን Next ብላችሁ እንዳታልፉት 😊


Paid Internship: Laravel & ReactJS (Next.js) Developer

-Company: PerfoNet Technology
-Location: On-site
-Duration: Internship Period
-Compensation: Paid

Requirements:
•Basic experience in Laravel & Next.js
•Knowledge of HTML, CSS, JavaScript & Git
•Eagerness to learn & work in a team

What We Offer:
•Hands-on project experience
•Mentorship from senior developers
•Potential for a full-time role
📩 Apply at internship@perfonet-technology.com


ይች ነገር እውነት ናት እንደ 👆


መድረስ የምንችልበትን ደረጃ መገመር ከባድ ሊሆን ይችላል። ያለንን ብቃትና ድክመት ማወቅ ግን አስፈላጊ ነው። በተለይ ያለንን inner capacity ማወቅ አለማወቅ አሁን ላለንበት ሁኔታ ወሳኙ ምክንያት ይሄ ነው።

እየቻልን እንደማንችል ቢሰማን፣ እንደምንችል አስበን ባንችልስ በሚል self doubt ውስጥ መቆየት ተገቢ አይደለም ። ምናልባት አንድ የምናውቀው ድክመት ኖሮብን ቀጣዩን step እንዳንደርስበት ይዞን ሊሆን ይችላል ። ሀሳቡ አለ ግን አልጠራም ለዛ ነው ኢንጅነር Bejai Nerash Naiker clarity of thought ያስፈልጋል የሚለን።

በግሌ ብዙ ጊዜ ራሴን ሲኒየር ሶፍትዌር ኢንጅነር ብሎ ለመጥራት ከብዶኝ ነበር። ስራ ላይ ግን Microsoft እና Google ከሰሩ ሰዎች ጋር አንድ ፕሮጀክት ላይ ሰርቻለሁ።

ሚድያዎች ላይ ኢንተርቪው ስጋበዝ am I the right person for this interview? Is my experience Worth sharing ብዬ ጊዜ ራሴ ጋር ክርከ ውስጥ ገብቻለሁ። ደስ የሚለው ነገር ዛሬ ላይ ራሴን መፈለጌ ልኬን ከትላንት በተሻለ እንዳውቅ አድርጎኛል ።

አንድ መስሪያ ቤትን በመልቀቅ የተሻለ ስራ ላለመፈለግ አንዱ መስናክል ሌላ ቦታ ስራ አላገኝም የሚል ፍርሃት ይመስለኛል ። ለዚህ መፍትሄው ወደ ሚቀጥለው ለመሄድ ምን attribute ልጨምር የሚለውን ማወቅ ይመስለኛል ። ቢነስም ቢሆንም የተለየ አይደለም።
ለህይወትህ ዋጋ ስጥ የሚለውን ማስታወቂያ ወደ ለራስህ ዋጋ ስጥ እናሳድገው።

@birhan_nega


#ለሰኞ
#backtowork

ሁሉም ቀን እንዳሰብነው ላይሆን ይችላል። ህይወት ትቀጥላለችና ነገን በማሰብ እንቀጥላለን ። ከአምስት አመታት በፊት ወደ custor computing PLC ተቀጥሬ ስገባ በዋናነት አለኝ የምለው ብቃት ቶሎ የመማር በፍጥነት deliver ማድረግ የመጀመር ብቃት ነው። የመጀመሪያ ልጃችን ተረግዞ ስለነበር የሚጠብቀኝ ነገር ብዙ እንደሆነ ስለተረዳሁ በአድሱ መስሪያ ቤት የምንገለገልባቸውን tech stacks ቀን ሌሊት ፣ ቅዳሜ እሁድ ሳልል መቀጥቀጥ ጀመርኩ። በተለ Maru Abebe ያኔ በ97$ የገዛልኝን አንድ መጽሀፍ ጨምሮ አንድ ሙሉ angular course ወስጀ በዛውም የተሰጡኝን ስራዎች ለመከወን እተጋለሁ።

እዛ መስሪያ ቤት ከመግባቴ በፊት freelancer ሆኘ fiveer ላይ ጥሩ rating ስለነበረኝ ስራዎችም ይመጡልኝ ነበር። (ስራ ላይ ስራ ሊደረብብኝ 😊)

በእሁዱ ቀን 65$ ዋጋ ያለው ስራ ድንገት ታዘዝኩና ይሄንማ አልመልሰውም ብዬ ባለቤቴን እናቷ ጋር ሸኝቸ ወደ ቢሮ መሄድ። ሙሉ ቀኔን ሰውቸ የመቶ ብር ኢንተርኔት ፓኬጅ ሞልቸ ሙሉ ቀን ታግዬ ሰርቸ ተረከበኝ ስለው ጣጣ አበዛብኝ፣ መጀመሪያ ያልተነጋገርነውን ሁሉ መጨመረ ጀመረ። እኔም ጨማምሬለት ምሽት አንድ ሰዓት ሲሆን ሌላም የቀረ ነገር አለ ብሎ ኮንትራቱን ሰረዘው 🤔

የሙሉ ቀን ልፋቴን ውሃ ቸልሶበት መቶ ብሬንና ጊዜየን አቃጥሎ ምንም አሳማኝ ባልሆነ ነገር ኮንትራቱንሰርዞብኝ ብናደድም አልሃምዱሊላህ ብዬ በምሽት ወደ ቤቴ ተመለስኩ።

Sometimes we earn, sometimes we learn
መልካም የስራ ሳምንት

2.5k 0 7 18 110

አትፍሩ 😂


6️⃣ ሺህ ሰብስክራይበሮች ልንገባ ነው። ቻናሉ እየጠቀማችሁ ይሆን?
Опрос
  •   ሶፍትዌር ኢንጀነሪንግ ተማሪ ነኝ
  •   ጀማሪ የሶፍትዌር ባለሙያ ነኝ
  •   ሙያዬ ከቻናሉ ይዘት ጋር አይገናኝም
  •   ሲኒየር ባለሙያ ነኝ (
182 голосов


Github roasted us guys 😂


Your direction is more important than your speed.


ማስታወሻ

ብዙዎች በውስጥ ከምትጠይቁ ግሩፕ ላይ ጠይቁ፣ አካውንቴን ፕረሚዬም ያደረግኩት በምክንያት ነው 😊

Followup question ከመጠየቅ ይልቅ መጀመሪያ ጥያቄያችሁን ሰብሰብ አድርጎ ማቅረብ ብትለምዱ

ሶስተኛ ብርሃን ቢመልስም ባይመልስም አትናደዱ ። ከቻልኩ እመልሳለሁ። ካልቻልኩ ተረዱኝ። 😃


"በቀላሉ ተሰርቶ ሀብታም የሚያደርግ ስራ" የሚል ማስታወቂያ ያመናችሁ ቀን በስጋም በመንፈሰም በከባዱ ትወድቃላችሁ።

Alex Abreham


150ሽ በወር ብትሰራ በቃኝ አይባልም። ባለፈው ፋና ላይ በነበረኝ ኢንተርቪው በወር አንድ ሽ ዶላር መስራት እንደምታስቡ ከባድ እንዳልሆነ ስናገር እውነት ይቻላል ያላችሁኝ የደወላችሁልኝም ብዙ ነበራችሁ ማለት ይቻላል ።

ግን እኔ የመጀመሪያ ስራዬ 10 ዶላር ነበረች። ትንሽ ናት አላልኩም ብዙ ብር እንዳገኘ ሰው ተደስቸ ሌላ 20 ዶላር ፍለጋ ከዛ ሀምሳና መቶ እያልኩ መቀጠል ....

ጀማሪ እያለሁ ከ15ሽ ብር በላይ የሚከፈለው ሳይ እኔም እገረም ነበር፣ ስደርስበት ቀላል እንደሆነና አኗኗራችንም በዛው ልክ ከፍ ስለሚል ወጭና ገቢው አብረው ያድጋሉ። ሰው የሚየየው ወደ ፊት ስለሆነ 30ሽ በላይ የሚከፈላቸውን ስናይ እዛ ብደርስ ችግሬ ሁሉ የሚቀረፍ ይመስለኝ ነበር ። ስደርስ ግን የተቀየረው ነገር በራስ መተማመኔ ብቻ ነው። ምክንያቱም 2 ሆነን በ30ሽ ብር መኖርና 4 ሆነን በ60ሽ መኖር እኩል እንደሆነ አላሰብነውም ነበር።

ቤተሰብም ሲጨምር ሀላፊነትም ሲጨምር የሚያስፈልገን ገንዘብ መጠን የሀላፊነት ስሜትና መሰል ነገሮች እያደጉ መጡ። ስለዚህ ስራዬ ላይ ይበልጥ aggressive እንድሆን ገፋፋኝ። 100ሽም ታለፈ 2 መቶም እንደዛው የተቀየረ ነገር ግን የለም።

መጨረሻ ላይ በማንኛውም ደመወዝ ይሁን መቀጠር ደበረኝ። በርግጥ አሁንም አውሮፓ እሰራለሁ ግን በእርግጠኝነት ድርጅቶቼ በደንብ መቆም ሲጀምሩ አቆማለሁ። እስከዛ ድረስ ተቀጥሬ እየሰራሁ ቤተሰብና startup ካምፓኒዎችን እደግፋለሁ።

If you keep the momentum, the process itself leads you.
እና 120ሽ is not a big deal ለማለት ነው 😊


Success comes from simplicity. The more straightforward your approach, the easier it is to make progress and achieve what you want.


Either you run the day or the day runs you.


Jim Rohn


Nvidia በቴክ ኢንዱስትሪው አስፈላጊ የሚባሉትን chips በማምረት ቀዳሚው ሲሆን በ AI ኢንዱስትሪው ውስጥም አስፈላጊ የሚባሉትን ነባርና አዳድስ ምርቶችን በማቅርብ የሚታወቅ ነው። ምርቶቹን ቻይናን ጨምሮ በሁሉም የአለም ሀገራት ያቀርባል ።

ቻይና አዳድሶቹን ምርቶቸን ካገኘች አሜሪካን ትቀድማለች በሚል ስጋት አድድሶቹን ለ Ai የተሰሩ ምርቶቹን ወደ ቻይና እንዳይገቡ ያደርጋል።

ቻይና ችግር የለውም አሮጌዎቹ ይበቁኛል ብላ ያለውን ተጠቅማ የአሜሪካ ትላልቅ companies በቢሊዮን ያወጡበትን chatgpt የሚገዳደር አፕ ስድስት ሚሊዮን ዶላር በአጭር ጊዜ ሰርተው በማምጣት በአንድ ቀን ብቻ 600B ዶላር አክስረውት አደሩ 😊


ግራፊክስ ድዛይነሮች የሚያምሩ ድዛይኖችን መስራት ከፈለጋችሁ

Freepik
Behance
Pinterest

ላይ ሀሪፍ ሳምፕሎችን ማግኘት ትችላላችሁ ።

Показано 20 последних публикаций.