✍ሰማይ ልብ✍
የት ገባሽ የት ወጣሽ ብዬ ሳልጠይቃት
ስትዞር እየዋለች ሳልጨቃጨቃት
ይኸው ስንት ዘመን...
በወጣችበት በር የማትገባን ፀሐይ
ሳፈቅራት የምኖር እኔ ነኝ ይህ ሰማይ።
.
አንተም ልክ እንደኔ...
ያፈቀርካትን ሴት
የት ገባሽ የት ወጣሽ ብለህ አትጠይቃት
.
ለፍቅር የሚሆን
ሰማይ ልብህን ያዝ
ፀሐይ ፍቅረኛህን እዛ ላይ ልቀቃት።
.
የትም ስትዞር ትዋል የትም ውላ ትደር
ስትመለስ ትግባ ባልወጣችበት በር
አንተ ሰማይ ከሆንክ...
ፀሐይ ባለችበት አንተም እዛዉ ነበርክ።
በላይ በቀለ
@blinkartss
@blinkartss 👈 ይቀላቀሉን
የት ገባሽ የት ወጣሽ ብዬ ሳልጠይቃት
ስትዞር እየዋለች ሳልጨቃጨቃት
ይኸው ስንት ዘመን...
በወጣችበት በር የማትገባን ፀሐይ
ሳፈቅራት የምኖር እኔ ነኝ ይህ ሰማይ።
.
አንተም ልክ እንደኔ...
ያፈቀርካትን ሴት
የት ገባሽ የት ወጣሽ ብለህ አትጠይቃት
.
ለፍቅር የሚሆን
ሰማይ ልብህን ያዝ
ፀሐይ ፍቅረኛህን እዛ ላይ ልቀቃት።
.
የትም ስትዞር ትዋል የትም ውላ ትደር
ስትመለስ ትግባ ባልወጣችበት በር
አንተ ሰማይ ከሆንክ...
ፀሐይ ባለችበት አንተም እዛዉ ነበርክ።
በላይ በቀለ
@blinkartss
@blinkartss 👈 ይቀላቀሉን